የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ክቡራን » Thu Apr 04, 2013 6:53 pm

ይቅርታ ትናንት ስጽፍ በችኮላ የተሳስትኩት ነገር እንዳለ የተገነዘበኩት አሁን ነው:: አቶ ምርጫው ዲያቆን አጥቶ በሰንበት የሚያስቀድሰው በሲዲ አስቀድቶ ነው ለማለት በዲሲ አልኩ መሰለኝ typo መሆኑን ለመጠቆም ያህል ነው:: መልካም ንባብ ይሁንልዎት የተከበሩ አንባቢ:: ይሄን ጽሁፍ እኮ እናም ጥሩ አድርገን እንድንጸፈው ድጋፍዎንና መዋጮ ( መዋጮ ስል የቃላት ሳይሆን የፍራንክ ቢያድርጉልን ጥሩ በሆነ ነበር:: በወጣ ይተካ:: ) :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat Apr 06, 2013 3:28 pm

ጠይና ይስጥልኝ...መቼም ግራሞቴን እዚህ መጥቼ ተንፈስ ካላደረኩ ምፈነዳ ይመስለኛል መሰለኝ...አማን ከሪም ነው..? ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወንድሞቼና እህቶቼ...ያቢይ ጾም እንዴት እያደረጋቹ ነው..?? እኔ አልዋሻችሁም አልጾምም:: ግን ባብዛኛው በሚጹም ሰዎች መኅል ስልተከበብኩኝ የጾም ምግብ እየበላሁ ነው:: ዲስፒሊንድ አይደለሁም እንጂ በመጾም አምናለሁ እንደዛ ስል ግን ስጋ የማሳድድ ካርኒቨርስ ነኝ ማለቴ አይደለም...እንደ ወንድሜ ዲጎኔ:: :lol: ወንድሜ ዲጎኔ እኮ አትክልት ባለበት ቦታ አይታይም:: ቅርጫ ባለበት ቦታ ግን ወንድሜ ዲጎኔ እነሆ እለ:: እነሆ እንግዲ ምን እንላለን..?? :D ታዲያላቹ ትናንት ማታ አንድ የቀይ ቪኖ ወዳጅ ጋር አንድ ክላሲክ ቦታ ተገናኝተን ገና ሳይጀመር ሞቅ ደመቅ ብሏል...ባራድኛው ፏ! ብሏል!! እንዴ ምነው ዛሬ ምን ተገኘ አልነው እኔና ጔደኛዬ...አባካቹ ዛሬ ማህበር ነበረኝ ተጠርቼ ማህበር ውዬ አሁን መምጣቴ ነው አለኝ...የምን ማህበር ብለን ጠየቅነው...እንዸ ዐትውቁም ዛሬ እኮ መድሀኒያለም ናቸው ያቢይ ጾም እኩሌታው ( ግማሹ ) እሁድ ይከበራል አለን... አጅሬ በቀይ ወይን ድክርት ያለው ለካ አቢይን ጾም ስላጋመሳት ነው:: "" እመቤቴ ላደረገችልኝ ነገር ምስጋና ለማድረስ አንድ ብርጭቆ ወይን ልጠጣ"" የሚል እንድ ሰበበ ቡዙ ልጅ አውቃለሁ:: ሌላው ደሞ የገረመኝ ነገር የኬኮች ፉክክር ነው ታዝባችኌል..?? ያበሻ ኬክ ቤት ስትሄዱ የጾም ኬክ እያሉ የሚሰሩትን ከቀመሳቹ ሁለተኛ የፍስክ እንዳትበሉ ነው የምትሆኑት..!! በጾም ኬክና በፍስክ ኬክ መማከል ፉክክር የተያዘ ይመስላል:: እውነተኛ ጾም ግን ያን አያስተመርም:: ጾም ራስን መግዛት ነው:: ጾም ማቅ ለበሶ ( ሊተራሊ ማቅ መልበስ ሳይሆን ) ራስንና ስጋን አያደከሙ መንፈስን ለዕጊዚአብሄር የማያስገዙቡት የመለየት ወይም የቅድስና ወቅት ነው:: ከስጋና ከቅቤ መለየት ብቻ በራሱ መንፈሳዊ ግብ አይደለም:: ከሁሉም ነገር በላይ ራስን መግራት ግድ ይላል:: ፍቅርን መዝራት ፍቅርን መስጠት በይቅርታና በንስሀ መኖርን ራስን ዝቅ ማድረግን ይጠይቃል:: አህያ ያማትችለውን ኅጢያት በትከሻ ላይ ተሸክሞ እጾማለሁ ማለት በራስ ላይ ፍርድ መጥራት ነው:: ለፈጻሜው በሰላም ያድርሳቹ:: እኔም መቼም ባልጾምም ያቢይ ጾምን ትክክለኛ መልክት ይሀው ባገኘሁት አጋጣሚ አስተላልፌአለሁ:: መቼም መጽሀፍ ቅዱስ እያሳዩ ኪስ ከሚያወልቁ ""ኢትዮ-ናይጄሪያውያን ፓስተሮች"" ወይም መስቀል እያሳዩ በሾኬ ከሚጥሉ ቄሶች ሳልሻል አልቀርም ብዬ እገምታለሁ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Wed May 01, 2013 1:20 am

አንድ ልጅ በቀደም የመምህር ግርማን ቪዲዮ እያየች ስልክ ደወለችልኝና እንዳየው እየመከረችኝ..
"" በጣም ይዘገንናል ..በጣም ያስፈራል እያለች ከቆየች ብኌላ ትንሽ ቆይታ ""ፈራሁኝ"" አለችኝ..
""ምነው??""
አልኴት
"" እኔንም ቪዲዮ ላይ እንዳሉት ሴቶች ጩሂ ጪሂ ያሰኝኘኛል "" አለችኝ....

ሳቅ ይዞኝ እንዴት ያረግሻል ስላት..

"" ከዱባይ ይዣት ነው የመጣሁት በይ በይ ይለኛል"" ስትለኝ
""ቆይ ጾም ይፈታ ታገሺው እኔ አስወጣልሻለሁ.. አልኴት::
እምቢ አላለችኝም:: :D :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat May 04, 2013 3:55 pm

ኦርቶዶክስ እምነት የታይታና የወግ እየሆነ ነው:: እምነቱን ወይም ቀኖናውን አይደለም እየኮነንኩ ያለሁት:: አማኞቹ ( በተለይ እኔን የሚያጋጥሙኝ ) ""በአል እንዴት ነው??""
ብዬ ስጠይቃቸው የሚነግሩኝ ስለ ትንሳኤው ስፕሪቹአል ሲጊኒፊካንስ ሳይሆን ጉልባን መብላታቸውንና ሄደው ቤት ክርስቲያን ስግደት ማድረጋቸውን ነው:: ይሄን በማድረጋቸውም አገር ቤት እንዳሉ ሆነው የተሰማቸው ስለ መሰላቸው ደስ እንዳላቸው ያወጉኛል....ዘመዴ ትናንት ማታ ስጋ እየከተፈች ምን አለችኝ መሰላቹ...
""ሁሉንም ቤተ ክርስቲያኖች እየዞርኩ ማየት የምነኘው ነገር ነው"" አለችኝ
""ለምን ?" ብዬ እንደዋዛ ጠየኴት::
""በቃ የሰው ብዛት ስታይ ደስ ይልሀል አገር ቤት ያለህ ነው የሚመስልህ....ሰው ከቤቱ የቀረ አይመስልህም..""
እኮ እያለች እያዳነቀች አወራችኝ:: ለነገሩ እቺ ዘመዴ ሰው ትወዳለች:: :D ነገሩ ግን ግራ አጋባኝና ጠጠር ያለ ጥያቄ ላነሳባት ፈለኩና ተውኩት::
""እውነት ሆይ መውጊያሽ የት አለ..?? "" ይላል ጸሀፊው:: ለነገሩ እኔም ዛሬ ማታ ቤተ ክርስቲያን ( ቅዱስ ሚካኤል ) ሄጂ ሌልቱን አሳልፋለሁ:: ግን ራሴን አየጠየኩት ነው የባህል ሰው ነኝ?? ወይስ የእምነት??"
መልሱን ከቤተ ክርስቲያን ስመለስ ይዥ እመጣለሁ:: Stay connected :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Thu May 09, 2013 2:20 am

በናታቹ በተለይ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ እንዳትቀየሙኝ ..ለማሾፍ አይደለም ግን ዛሬ አንድ ነገር አስቆኝ ነው ካልጻፍኩት እረሰዋለሁ:: አንዱ ነው እንግዲ (የኛው ልጅ ነው) አሁንማ ጺሙን ማሳደግ ጀምሯል:: እና ብቻ ከመሀል እጥፍ ብሎ ይሄድና ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ያ ው በቀን አምስት ጊዜ ስላት ማድረግ እንዳለበት አውቃለሁ:: አንድ ሌላ የማውቃት ውብ ልጅ እኔ ቢሮ ክላስ ሲኖራት እየመጣች ስላት ታደርጋለች:: ውሸቴን አይደለም እግዚአብሄር ምስክሬ ነው:: ስላት አድርጋ ከጨረሰች በኌላ ታመሰግነኝና ደስ ብሏት ትንሽ አውርታኝ ትሄዳለች:: ይሄ ልጅ ግን ከስላት ሲመለስ ፊቱ ፈጎ አይደለም የሚመጣው:: ተደብድቦ የመጣ ነው የሚመስለው:: :lol: ፊቱን ቅጭም አድርጎ ይመጣና የት ነበርክ ምናምን እያሉ ጔደኞቹ ሲጠይቁት ፊቱን እንደከሰከሰ ""ስላት ላይ ነበርኩ"" ይላል:: ሁሌም ዓላህ በጥፊ እያጠናገረው የሚመጣ ይመስለኛል:: እኔ ቢሮ ስላት የምታደርገው ልጅ ከስላት በኌላ ፊቷም ወዟም ያበራል:: ይሄ ልጅ ግን ቢቀርበት ይሻላል:: ምች ይምታው... መጋኛ ይምታው እኔ አላውቅም:: :D ምን እያደረገ ይሆን የሚመጣው..??
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Tue May 14, 2013 10:49 pm

እዚች ክፍል ውስጥ ፖሎቲካ እንዲደስኮር አልፈልግም ነበር:: እቺ ክፍል ስነ ጥበባዊ መድረኬ ናት:: :D ዋርካ ውስጥ እኮ ሁሉንም መሆን ይቻላል:: ይኅው አንጋፋው ወንድማችን ዲጎኔ ጋዜጠኞችን ሜንቶር አደርግ ነበር ብሎ የለ!! :D ዘንድሮ የማይሰማ ጉድ እኮ የለም:: ""ሰሳ የማያቁት አገር ሄዶ የሰሜን ድኩላ ነኝ አለ አሉ::"" :D :D እምቧ ዘቢደር ...እምቧ ዘቢደር...እምቧ ዘቢደር ዘቢደር...!! :lol: የኢህደግ ታጋዮች የትናንት የትግል ውሎ ና የዛሬን እነሱን እንድናስተያይ ፈለኩ:: በዚህ ጉዳይ ላይ የምለው ነገር ይኖረኛል ለዛሬ ግን ይህን ቪዲዮ ልጋብዝ:: እቺን ይጫኑ የተከበሩ አንባቢ ሆይ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby መራራ » Wed May 15, 2013 9:28 am

አንቺን እጅና እግርሽን የፊጢኝ አስሮ ለ አልሸባብ በ ስጦታ ማበርከት ነበር ሙች :lol: :lol: :lol: :lol: የባልትና ውጤቶች መሸጫ ሱቅሽንም ቢሮ አልሻት? :lol: :lol: :lol: ከ የሺ ማርት ወይስ ከ እናኑ እንጀራ ያቺ አንቺ ቢሮ የምትመጣው ልጅ? :lol: :lol: ምን ያህል ካርቶን እና ጋዜጣ ቢኖርሽ ነው ግን ሱቅሽ ለመስገጃ ምቹ የሆነው? :lol: :lol: :lol: አሁን ሶላት እና ሙስሊምን ለማጥላላት ካልሆነ የ ልጁ ፊት ማጥቆር አሊያም ሁሌም መኮሳተር አንቺ ምን ያገባሻል? ደንገጎ ግቢና :lol: :lol: :lol: ሲጀመርስ አንቺ ሆድሽ እና አሳዳሪሽ ኤፈርት እንጂ ስለ ሙስሊሙ ምን ጥልቅ አደረገሽ? ሆዳም:: :lol: :lol: :lol:


ክቡራን wrote:በናታቹ በተለይ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ እንዳትቀየሙኝ ..ለማሾፍ አይደለም ግን ዛሬ አንድ ነገር አስቆኝ ነው ካልጻፍኩት እረሰዋለሁ:: አንዱ ነው እንግዲ (የኛው ልጅ ነው) አሁንማ ጺሙን ማሳደግ ጀምሯል:: እና ብቻ ከመሀል እጥፍ ብሎ ይሄድና ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ያ ው በቀን አምስት ጊዜ ስላት ማድረግ እንዳለበት አውቃለሁ:: አንድ ሌላ የማውቃት ውብ ልጅ እኔ ቢሮ ክላስ ሲኖራት እየመጣች ስላት ታደርጋለች:: ውሸቴን አይደለም እግዚአብሄር ምስክሬ ነው:: ስላት አድርጋ ከጨረሰች በኌላ ታመሰግነኝና ደስ ብሏት ትንሽ አውርታኝ ትሄዳለች:: ይሄ ልጅ ግን ከስላት ሲመለስ ፊቱ ፈጎ አይደለም የሚመጣው:: ተደብድቦ የመጣ ነው የሚመስለው:: :lol: ፊቱን ቅጭም አድርጎ ይመጣና የት ነበርክ ምናምን እያሉ ጔደኞቹ ሲጠይቁት ፊቱን እንደከሰከሰ ""ስላት ላይ ነበርኩ"" ይላል:: ሁሌም ዓላህ በጥፊ እያጠናገረው የሚመጣ ይመስለኛል:: እኔ ቢሮ ስላት የምታደርገው ልጅ ከስላት በኌላ ፊቷም ወዟም ያበራል:: ይሄ ልጅ ግን ቢቀርበት ይሻላል:: ምች ይምታው... መጋኛ ይምታው እኔ አላውቅም:: :D ምን እያደረገ ይሆን የሚመጣው..??
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Thu May 16, 2013 1:29 am

ዝም በሉ እርሶ ሰላቶ!! እርሶን የመሰሉ ባንዶች ናቸው ያገራቸውን ልጆች እያሳለፉ የሚሰጡት !! ለካ ጌኛ ብቻ አይደሉም ባንዳ መሆንዎንም አስመሰከሩ:: እኔን እጅና እግሬን አስረው ላልሸባብ ወይ ለወሀቢስቶች ሊሰጡኝ ያስባሉ ማለት ነው..?? ቅንዳሻም ባንዳ!! :lol: እኔ ግን እንደ እርሶ አይደለሁም ...ምርጫ ቢሰጠኝ ለራበው የቀጨኔ ጅብ እጅና እግርዎን አስሬ ዳሌና ዳሌዎን ከፍቼ እስጠው ነበር:: እንዲነጭዎት!! :D ይሄን በጭራሽ አይጠራጠሩ:: በቅሎ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Thu May 23, 2013 1:42 am

አንዳንድ ነገሮችችን ሀደ - ኅደ እንበላቸው ...""ፈትለ- ነገር "" ይለዋል ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን እኮ ነው:: ነገር ሲፈትል:: እኔ ምን አይነት ሰዎች እንደደበሩኝ ታውቃላቹ ...በየሰከንዱ ሰውን የሚያመስግኑ.."" ወይ ያንተ ነገር እሷ እመቤቴ ትክፈለልኝ እንጂ... እኔማ እንዴት እችለዋለሁ??" ይሏችኌል::
""እሷ አለሁ ትበልህ..""ይሏችኌል::
የዚህ "ቫይብ" ምንድነው...ራሳቸውን ከጨዋታ ውጭ ሲያደርጉት ነው...ለምን በውስጣቸው ክፉዎች ናቸውና:: የነሱ ደግነት ባፋቸው ነው...ስለዚህ ውስጣቸው ደግ እንደማያስብ ደግ እንደማይሰራ ስለሚያውቁ እናንተ ላደረጋችሁላቸው ጥሩ ነገር ( ለነገሩ ሪተርን ፈልጋቹ አይደለም መልካም ነገር የምታደርጉት....የስ አንድ ኖ..! :wink: ) እነሱ ግን የቅዱሳትን ስም በየሰከንዱ ይደረድሩታል:: ይሄ ምርቃት አይደለም...ስዎቹ ምንም ጊዜ ደግ እንሰራለን ብለው ስለማያማኑ ሀላፊነታቸውን ከላያቸው ላይ እያወረዱ ነው:: ክቡራን ምን አለ በሉኝ:: እውነተኛ ሰው ምስጋናውን ጮክ እያለ አያወራም:: ግን እንዴት አድርጎ መመለስ እንዳለበት ከራሱ ጋር እየተሟገተ ዝምታን ይመርጣል:: የገባቹ እጃችሁን አውጡ:: ወንድሜ ዲጎኔ ቢሆንም እንኴን:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Fri Jun 14, 2013 2:01 pm

እኔ የምለው ሊማሊሙ ገደል ሊገባ አንድ ሀሙስ ቀርቶታል የተባለው ወያኔ መሄዱ ነው ብለን ስንጠብቅ እንዴት ሆኖ ነው ለግብጽ የውስጥ እግር እሳት የሆነባት ..?? እዝጎ... እዝጎ እዝጎ!! ስለገረመኝ ነው...ለሌላ አይደለም...
ተው ቻለው ሆዴ ተው ቻለው ሆዴ...
እንዲ ለሚቀረው ምነው መናደዴ... :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby መርፊው » Fri Jun 14, 2013 3:50 pm

ክቡ ክብነት አንተ የሰአት እላፊ ልጅ ፖለቲካው ላይ ስኬት ስታጣ ወደ ሀይማኖታዊ ጉንተላ ውስጥ ገባህ ምን ታ
ደርግ ቄስ ዘሙካን በዝረራ ከዋርካ ሲወጣ የእሱን ሚና ለመጫወት እብሪታዊ እየሱሳዊ ጥቃት ወይም ዘመቻ ከፍተሀልና የመልስ ምት ያስፈልገሀል ምን ይመስለሀል አንተ
የዋርካና የዘመኑ ደንቖሮ ? እየሱሳዊ ሽብርህን ከጀመርክ መንገዱንጨር ያድርግልህ ግን በዚህ ቤት ሳይሆን በሌላ ቤት ብናድርገው ይልሀል መርፊው ዘ_ነገደ የሁዳ ከነ ባርናባስ ሰፈር
ክቡራን wrote:በናታቹ በተለይ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ እንዳትቀየሙኝ ..ለማሾፍ አይደለም ግን ዛሬ አንድ ነገር አስቆኝ ነው ካልጻፍኩት እረሰዋለሁ:: አንዱ ነው እንግዲ (የኛው ልጅ ነው) አሁንማ ጺሙን ማሳደግ ጀምሯል:: እና ብቻ ከመሀል እጥፍ ብሎ ይሄድና ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ያ ው በቀን አምስት ጊዜ ስላት ማድረግ እንዳለበት አውቃለሁ:: አንድ ሌላ የማውቃት ውብ ልጅ እኔ ቢሮ ክላስ ሲኖራት እየመጣች ስላት ታደርጋለች:: ውሸቴን አይደለም እግዚአብሄር ምስክሬ ነው:: ስላት አድርጋ ከጨረሰች በኌላ ታመሰግነኝና ደስ ብሏት ትንሽ አውርታኝ ትሄዳለች:: ይሄ ልጅ ግን ከስላት ሲመለስ ፊቱ ፈጎ አይደለም የሚመጣው:: ተደብድቦ የመጣ ነው የሚመስለው:: :lol: ፊቱን ቅጭም አድርጎ ይመጣና የት ነበርክ ምናምን እያሉ ጔደኞቹ ሲጠይቁት ፊቱን እንደከሰከሰ ""ስላት ላይ ነበርኩ"" ይላል:: ሁሌም ዓላህ በጥፊ እያጠናገረው የሚመጣ ይመስለኛል:: እኔ ቢሮ ስላት የምታደርገው ልጅ ከስላት በኌላ ፊቷም ወዟም ያበራል:: ይሄ ልጅ ግን ቢቀርበት ይሻላል:: ምች ይምታው... መጋኛ ይምታው እኔ አላውቅም:: :D ምን እያደረገ ይሆን የሚመጣው..??
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby ክቡራን » Fri Jun 14, 2013 9:04 pm

ነፍሴው መርፌ አሰላማሌኩም በቅድሚያ እንደተለመደው ጭንቅላትህ በኔጌቲቭ ተሞልቶ ስለገባህ እንጂ ምንም አይነት ኢንሳልቲንግ እዚህ ውስጥ የለም:: እኔ ያየሁትን ነው የጻፍኩት.... ያ ልጅ ሌላ ጊዜ ሲስቅ አየዋለሁ ስላት አድርጎ ሲመለስ ግን ተከታትየዋለሁ..ሁሌም አኩርፎ ይመጣል:: ለምን እንደሆነ እኔም ባውቅ ደስ ይለኛል:: ካላህ ጋር መነጋገር ጸሎት (ሶላት) መሆኑ አልጠፋኝም እኔ ግራ የገባኝ ግን ልጁ ዳቦውን የተቀማ ይመስል አኩርፎ ነው የማየው ...ይሄ የሱ ነገር ብቻ ሊሆን ይችላል ሌላውን ሙስሊም ወንድሞቼንና እህቶቼን አይወክልም:: ለምሳሌ እኔ የማውቃት ትግስት (የአባቷ ስም የሙስሊም ነው አልጠቅስም...) ከሶላት በኌላ ዝም ብዬ ሳያት ዘምባባ ና ፊቷ እንደ ኦቾሊኒ ቅባት ያበራ ነው...ከዛ በኌላ ትንሽ ታወራኝና እንሰነባበታለን:: እኔም የሚቀጥለውን ጊዜ መምጣቷን በተስፋ እጠብቃለሁ:: ይሄ ልጅ ግን ሁሌም ከሶላት መልስ የማየው ምች የመታት አሮጊት ሆኖ ነው የሚታየኝ...እኔም ያየሁትን የልቤን በማወራበት ክፍል ውስጥ የታዘብኩትን እውነት ጻፍኩ:: እቤቴ መጥተህ ምን አድርግ ነው የምትለኝ...? ፉርኖ ዳቦ ይመስላል... ፊቱ እንደ ብርጭቆ ያበራል ብዬ ልጻፍልህ??? እንከባበር በዐላህ ይዥሀለሁ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Thu Nov 07, 2013 11:58 pm

ሰሞኑን ካንድ ልጅ ጋራ ስናወራ እገር ቤት ልሄድ አስቤአለሁ አለችኝ...ምነው በደህና አልኴት ..ጸበል ያስፈልገኛል ጸበል መጠመቅ እፈልጋለሁ በጣም ዲፕሬስ ሆኛለሁ አለችኝና ምክንያቱንም ጨምራ አስረዳችኝ:: ጸበል ያስፈለጋት ምክንያት ካገር ቤት ወደ ዚህ አገር ሊመጣ የነበረው ጔደኛዋ መምጫው አካባቢ ሲደርስ ስልኴን አለመመለሱና ይባስ ብሎም ከፌስ ቡክ ላይ የተጻጻፉትን የፍቅር ቃላቶች ና ውብ አበቦችን ማውረድ መጀመሩ መሆን በኅዘን አወጋችኝ:: እኔም የተሰማኝን ነገርኴት ...ጸበል መፍትሄ አይሆንም አልኴት...አዎን ልክ ነኝ እሱ ድሮፕ ካደረጋት ጸበል ሰው ሆኖ አያነሳትም...መፍትሄም አይሰጣትም:: መፍትሄው ያለው በጇ ነው..ይሄን ለማስረዳት ሞከርኩ:: እጊዚአብሄር አምላክ ሲፈጥረን ከጭንቅላትና ካስተሳሰብ ጋር እንደሆነና ይሄ ልጅ አንቺን ኢግኖር ቢያደርግሽ ሌሎች ፍቅር የራባቸው በዙሪያሽ አሉና መፈለግ እንጂ አጋንት እንዳለበት ሰው ጸበል ልጠመቅ ሱባኤ ልግባ ማለት በውነቱ ጸበልን ራሱን አቢዩዝ ማድረግና እንደውም በጸበል መቀለድ ይመስለኛል አልኴት :: ጸበል መጫወቻ ነው እንዴ..?? :D የእጊዝብሄር ሀላፊነት አለ እንደ ሰው የሰውም ሀላፊነት አለ:: መጽሀፍ እንዲህ ይላል..""የቄሳርን ለቄሳር የእጊዚአብሄርን ለእጊዚብሄር "" ይላል..መንፈስ ላብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን እነሆ ጆሮ ያለው ይስማ!!
ይቀጥላል++++++++++++++++
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Fri Nov 08, 2013 12:12 am

Good …better …best. Never let it rest until your good is better and your better is best…
መልካሙ ተበጀ እኮ ነው:: የዋናው ደራሲ ስም ጠፋብኝ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat Nov 09, 2013 12:49 am

ተስፋይ ገብረ አብ የሚባል ጭልፊት ኤርትራዊ የእንቆቆ ፈረሶች የገለምሶ ጥንቸሎች እያለ በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ ላይ ሲቀልድና ሲጫወት ነበር:: ይሄን የተገነዘቡት ወየንቲዎች ትንሽም ቢሆን መንገድም አሳይቶቻው ነበርና አስራ አንደኛው ሰአት ላይ ሲደርስ በቦሌ በኩል ካባቱ ወገኖቹ ጋር እንዲቀላቀል ላኩት:: ይሄ ከሆነ እነሆ አንድ አሰርት ሆነው:: ዲፖ ደሞ የተስፋይ ነገር ያባነነው ትናንት ሆነ ....የተስፋይ ብእር ያላባነናቸው ኦነጎችን ብቻ ነው:: ጫልቱ ዚ- ሄለን የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ ለቅቆ ያስጨፍራቸዋል:: ሾ! ሾ! ሾ! ሾሌ ያ ነጭ ጠላ ...አረፈረረፋ ጢቁሩ ዘዌ ሜቃ...! ቼ ቼ ቼ...!! :lol: ኢሾሾሾሾሾ...... :D
እና ምን አሰበኩ መሰላችሁ.. ድርሰት ለምን አልጽፍም ብዬ አስበኩ...ተስፋዬ በእንቆቆ ፈረሶች ሲላጥ.. እኔ ደሞ እነሆ ""የአፋበት ተኩላዎች"" ብዬ አንድ መጣጥፍ ወ-መጽሀፍ ብጤ ብጽፍ ምን ይለኛል..ብዬ አሰበኩ...!!
ልቀጥለው ነው እንግዲ ታሪኩ የሚጀምረው ከደቡብ አንበሶች ነው ...የደቡብ አንበሶች ድኩላ እንደ ልባቸው በየጫካው ስላገኙ ጠገብ አሉና እስኪ ላደን እንውጣ ብለው ወደ ሰሜን ሄዱ አሉ...የት ይደርሳሉ...አፋ-በት ኤርትራ.......ድርሰቱ ከዚህ ይጀምራል... :D .የምታውቁ ጨርሱት ...ስነ ጸሁፋዊ አስማት ይኖረው ግን.... ደረቅ አይሁን ....በስነ ጽሁፍ ልሳን የሾረ ይሁን እንደ ገጣሚ ዲጎኔ ግጥሞች ያሉ እሳት የሚተፉ ቃላቶችና ሀረጎች የሚወረውሩ ያንባቢን ቀልብ ሰንገው የሚይዙ ይሁኑ... :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8280
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 4 guests