የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ክቡራን » Fri Jun 20, 2014 4:50 pm

ይሄ የማሌዥያ አይሮጵላን ጠፍቶ ቀረ ማለት ነው..?? ወይ ቴክኖሎጂ ..ቴክኖሎጂ አንደ አደይ ምጽላል የበቆሎ ጠላ እየቀረረ መጣ ማለት ነው...?? :D አደይ ምጽላል ገበያ ሞቅ ሲልላቸው የእንስራው ጋን መጉደል ሲጀምር አየት ያደርጉትና ጠላውን ወደ ቅራሪነት በብርሀን ፍጥነት ይለውጡት እንደነበር አስታውሳለሁ:: ጥዋት ጠላ ልንጠጣ ገብተን እንደ እርጎ ጉሯሯችን እያራሰ የየሚወርደው ጠላቸው ወደ ቀትር አካባቢ አስማት የዞረበት ይመስል እንደ ምንጭ ውሀ ይቀጥናል....ለነገሩ ውሀው ኮልል ካለ ምንጭ ነው የሚቀዳው :: የሰማይ አምላክ የተመሰገነ ይሁን ማን ለውኅ ይከፍላል !!??
:D

""ተክሌስ"" ይለዋል አንዱ እኮ ነው ለጔደኛው ..

ጠጅ ሰውነቱን ያሞቀው ጔደኛው ደግሞ ""የስ"" ሲል ይመልሳል:: ..

""ሳቲሀስ ሜስ ..?? "" ብሎ ይጠይቀዋል...

አጅሬ አሁንም በጠጅ ሞቅታ "" የስ "" ይላል

""እሞ ሰቲኅስ መሰስ ..."" (ጠጥተህ ሹልክ በል ) ብሎ ይመክረዋል:: :D


ጉዲ ሰዲ አለ!! ኴኴቴ ሲንኴኴ..!! :D

እናማ ይህውላቹ ከህይወት እየጨለፍን እንድንማማር እቺን ያዋዜ ቤት ከፍቻታለሁ ...( ""የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች"" ) አሁን አሁን ሳስበው ከምከፍታቸው ቤት ብዛት አንጻር ለምን ኢንተርፕረነር ወይም ስራ ፈጣሪ አልሆንም እያልኩ ሳስብ ነበር...ለካ ወይዘሮ ሙሉም ( የንግድ ምክር ቤት የክብር ፕሬዝዳንት ) ዋናዋ ስራዋ ኢንተርፕረነር ናት በጤናዋ የሀረር ጃፋ ብርቱካን አልመ ሰለችም:: ያ መናጢ ዶክተርና ኢንጂነርም የሷን ዱካ እየተከታተለ እንደውም ከሷ ጋር ነው የምሰራው እያለም ቡዙ ብር አግኝቷል አሉ:: ( ሳሙኤል ዘሚካኤልን ማለቴ ነው ) አንዷን እርጥብ ጵንጤ የጌታ ልጅ ነኝ ብሏት 120 ሺ ብር ድው ! እንዳደረጋት ሰማሁ:: አይደንቅም ( በወንድሜ ዲጎኔ አንጻር ከመዝነው ) :: :lol:


ወደ ዋና ጉዳዬ ልገባ ነው ተከተሉኝ:: መጽሀፍት ወይንም ትምህርት ቤት ከሚያስተምሩን በላይ ህይወት በራሷ የምታስተምረን ቡዙ ቁም ነገሮች አሏት:: እነዚህን ህይወት ያስተማረኝን ቁም ነገሮች አካፍላችኍለለሁ:: ካልጻፍኩት በሌላ ነገር እጠለፍና እረሳዋለሁ:: በዚህ ላይ ዛሬ አርብ ነው:: መጀመሪያ ለራሳቹ ክብር ስጡ:: ራሳችሁን ዝቅ አታድርጉ:: ህይወት ስትፋለማቹ እናንተም መልሳቹ ተፋለሟት:: በቴስታ ካለቻቹ እናንተም አቅምሷት:: እጅ አትስጡ:: ሰዎች በግልም ሆነ በጋራ በኮሚቲም ሆነ በሸንጎ በናንተ ላይ ሊያድምባችሁ ይችላሉ..የአምላካችሁን ስም ጠርታቹ አንተ መላ ፍጠርልኝ ማለት ብቻ በቂ አይደለም:: ( ግን በውነት መስመር ላይ ስለመሆናቹ እርግጠኛ ሁኑ:: ) በርግጥ እጊዚብሄር አምላክ የተጠቃችና ብቸና የሆነችን ነፍስ ያያል:: ከጎኗም ይቆማል:: ግን ፍልሚያ ውስጥ የሚገባለት ደፋር ይፈልጋል:: ሙሴ የቀይ ባህርን የከፈለው ከዳር ቆሞ አይደለም:: ውሸት ነው :: ውሀ ውስጥ ከነ ልብሱ ተንቦጫርቆ ከገባ በኍላ ነው እንደ ግርግዳ መከፈል የተጀመረው:: እዳር ቆመህ ብታንዣብብ ችግሩን አትፈታም:: ሶቶ መሪና.. ላቫስታ!! ሳንታ ማሪያ....!! ብሎ መግባት ያስፈልጋል:: አልጨረስኩም መጣሁ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Thu Jun 26, 2014 6:24 pm

አለ ነገር አለ ነገር ..
የሚዘከር የሚሰፈር ..
የሚወራ የሚበጠር..

የሚሰማ ..የሚቀወር

አለ ነገር በሚል ርእስ ሰር የምለቀው ነጠላ ግጥም በቅርብ ቀን ይለቀቃል:: :D
ሰላም ነው?? የዚህ ቤት ፍሬንዶች!! 8)

ወይ መቅበጥ ወይ ልክን አለማወቅ..!! ሲያቀብጠኝ መጽሀፍ ጽፌ አቅፌው ቁጭ አልኩ .. :cry: :D ( እየሳቁ ማልቀስ ..) .እንደምንም አንድ 300 ያህሉ በእንተ እግዚአትነ ማርያም እያልኩ በጔደኞች ህብረትና ትብብር ጥረት ና ልፋት እንዲሁም ዑዑታ ጭምር ሊሸጥሉኝ ችለዋል:: ሌሎችን ማን ይግዛኝ!!? የኔ ወንድም ዲጎኔ ወጣት ደራሲያንን እንደሚያበራታታና ለሞራላቸውም ሲል 30 ና 40 መጽሀፍ ገዝቶ ለቅዱሳን ማህበር አባላት እንደሚያከፋፍል በዚህም የደራሲያንን ሞራል እንደሚደግፍ ሰማሁ:: እጊዚአብሄር እንደዚህ አይነት ሰዎች አያሳጣን:: ወንድሜ ዲጎኔ የአንዱ መጽሀፍ ዋጋ በዚህ አገር $15.00 ( አስራ አምስት ዶላር ብቻ ነው ):: ወንድሜ እንደምትገነዘበው ...አንድ ሰው ሁለት ጊዜ ስታር ባክስ ቢሄድ የሚያጠፋት ናት!! አንድ መጽሀፍ ገዛህ ማለት ግን በኢትዮጵያ ስንመነዝረው ያልተሸጡትን 6 ና 7 መጽሀፍ ዋጋ ሸፈንክ ማለት ነው:: ትልቅ እርዳታ ነው:: እና ሁሌም በክፉም በደጉም በጊዜውም አለ ጊዜውም ከጎኔ የሚቆመው ወንድሜ ዛሬም አለሁልህ እኔ እያለሁ ምንም አትሆንም!! እንደሚለኝ ምንም ጥርጥር የለኝም:: ዲግሻ መልስህ ይጠበቃል:: :D :arrow:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Wed Jul 02, 2014 6:01 pm

ዲግሻ ዘጋኝ!! ወይ መዝጋት!! የሲውዲን መንግስት የኤርትራዊን መሪ በግፍና በሰባዊ መብት ህጸጽ ሄግ ላይ አቅርቦታል:: እኛም በጭቁን ህዝቦች ና ልጆች ስም የካናዳ ና የሲውዲን ስንዴ ሱማሌ ተራ ወስዶ በደላሎች የቸበቸበና ያስቸበቸበን አጭቤ ሄግ ባናቀርበውም ለዋርካዋ ፍርድ ብናቀርበው ሀጥያት ይሆን?? አይመስለኝም:: የቀን ጉዳይ እንጂ ይሄ የእሪቻ ዋና ቃልቻ ቆሌ ቁጥር 1 ዲጎኘ አሞኘ በቅርብ እንደ ጅብ አውውውውውው!! ብሎ እንደሚጮህ ምንጮች ይገልጻሉ:: የኛም ተስፋ ነው:: :lol: !! ወንጌል ለማስመስል ቢጨብጥም ቅሉ!!

ወደ እለቱ ትምህርታችን እንሂድ !!

ህይወት የማታቌርጥ ትግል ናት ..ታገላት!! ታገላት!! ታገላት!! ሌላ መፍትሄ የለህም:: እንዳትወድቅ ተፍጨርጨር:: ያለሰራ አይብላ ያለው ካርል ማርከስ አይደለም:: ይልቁኑ እግዚአብሄር ነው:: እግዚአብሄር ጥረህ ግረህ በግንባርህ ወዝ ብላ የሚለውን ቃል ላዳም የሰጠው ያለም ፍጥረት ሲጀመር ነበር:: ይሄን ቀድሞ የተረዳው ካርል ማርከስ የእጊዛብሄርን ቃል ካፒ ፔስት አድርጎ በራሱ የኮሚኒስት ማኒፌስቶ ቫልዩም ላይ ጻፈው:: ከዛም ያልሰራ አይብላ የሚል ማህተም ከበላዩ አደረገበት:: ካርል ማርከስ የቅደመ አንታይ ክራይስት ምሳሌ ነው:: ዳግማዊና ታህታይ አንታይ ክራይስቶች እነማን ናቸው?? በሚለው ላይ እመለሳለሁ:: መንፈስ ላብያተ ክርስቲያናትና ለቤተ እስላማት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ!! አልሰማም ካልሽ እያንዳንድሽ የራስሽ ጉዳይ ነው:: መጣሁ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ጌታ » Wed Jul 02, 2014 7:13 pm

ክቡራን wrote:ወይ መቅበጥ ወይ ልክን አለማወቅ..!! ሲያቀብጠኝ መጽሀፍ ጽፌ አቅፌው ቁጭ አልኩ .. :cry: :D ( እየሳቁ ማልቀስ ..) .እንደምንም አንድ 300 ያህሉ በእንተ እግዚአትነ ማርያም እያልኩ በጔደኞች ህብረትና ትብብር ጥረት ና ልፋት እንዲሁም ዑዑታ ጭምር ሊሸጥሉኝ ችለዋል:: ሌሎችን ማን ይግዛኝ!!?


ጥያቄው መጽሐፍህ ስለምድነው ነው:: ተራሮችን ስላንቀጠቀጠው ትውልድ ነው? ሰባተኛንና ውቤ በረሃን ስላንቀጠቀጠው ወይስ በስደት በርገርን አንቀጥቅጦ ስለሰባው ትውልድ?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ቱሉቦሎ » Thu Jul 03, 2014 2:39 am

ጌታ wrote:
ክቡራን wrote:ወይ መቅበጥ ወይ ልክን አለማወቅ..!! ሲያቀብጠኝ መጽሀፍ ጽፌ አቅፌው ቁጭ አልኩ .. :cry: :D ( እየሳቁ ማልቀስ ..) .እንደምንም አንድ 300 ያህሉ በእንተ እግዚአትነ ማርያም እያልኩ በጔደኞች ህብረትና ትብብር ጥረት ና ልፋት እንዲሁም ዑዑታ ጭምር ሊሸጥሉኝ ችለዋል:: ሌሎችን ማን ይግዛኝ!!?


ጥያቄው መጽሐፍህ ስለምድነው ነው:: ተራሮችን ስላንቀጠቀጠው ትውልድ ነው? ሰባተኛንና ውቤ በረሃን ስላንቀጠቀጠው ወይስ በስደት በርገርን አንቀጥቅጦ ስለሰባው ትውልድ?


ይሄ የእፉኝት ልጅ ሾካካ የወያኔ ጋዜጠኛ outsider መስሎ ያው የቀጣሪውን የወያኔን ውዳሴ የሌላውን ወቀሳ እንጂ ሌላ ምን ይጽፋል ብለህ ትጠብቃለህ ?

እዛኛው ቤት የወያኔን የዘቀጠ የትምህርት ተቋም አዛኝ መስሎ ያው በሾካካ አመሉ በደርግ ላይ አላኮት እርፍ አለ :: ለምሻ እቅጩን ሲነግረው ያልገባው መስሎ ባማርኛ ጻፍልኝ ብሎ ሊያጭበረብር ሞከረ

እንደዚህ አይነት እስስት ሾካካ ሰው አይቼ አላውቅም
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Postby ክቡራን » Fri Jul 04, 2014 5:50 am

ወንድሜ ቱሉ ፈርሶ::
መሳደብ ፈልገህ እንጂ ጋዜጠኛው ( ጠያቂው ) ያለው አሁን ያ ችግር መፈታት ያለበት በዚህ መንግስት እንጂ በደርግ ስራት አየደለም እንደውም ""ያለፈውን ስራት ብናማርርና እዬዬ እያልን ብንክሰ ወይም ብንኮንን አሁን ፊታችን ላይ ያገጠጠውን የትምህርት ጥራት ድክመት አይፈታልንም!" የሚል አቌም አንዳለው ተረድቻለሁ:: ውይይቱን እንደገና በጽሞናና በረጋ መነፈስ ሆነህ እንዳታዳምጥ እጋብዝኅለሁ::
ቱሉ አተላ wrote:
ጌታ wrote:
ክቡራን wrote:ወይ መቅበጥ ወይ ልክን አለማወቅ..!! ሲያቀብጠኝ መጽሀፍ ጽፌ አቅፌው ቁጭ አልኩ .. :cry: :D ( እየሳቁ ማልቀስ ..) .እንደምንም አንድ 300 ያህሉ በእንተ እግዚአትነ ማርያም እያልኩ በጔደኞች ህብረትና ትብብር ጥረት ና ልፋት እንዲሁም ዑዑታ ጭምር ሊሸጥሉኝ ችለዋል:: ሌሎችን ማን ይግዛኝ!!?


ጥያቄው መጽሐፍህ ስለምድነው ነው:: ተራሮችን ስላንቀጠቀጠው ትውልድ ነው? ሰባተኛንና ውቤ በረሃን ስላንቀጠቀጠው ወይስ በስደት በርገርን አንቀጥቅጦ ስለሰባው ትውልድ?


ይሄ የእፉኝት ልጅ ሾካካ የወያኔ ጋዜጠኛ outsider መስሎ ያው የቀጣሪውን የወያኔን ውዳሴ የሌላውን ወቀሳ እንጂ ሌላ ምን ይጽፋል ብለህ ትጠብቃለህ ?

እዛኛው ቤት የወያኔን የዘቀጠ የትምህርት ተቋም አዛኝ መስሎ ያው በሾካካ አመሉ በደርግ ላይ አላኮት እርፍ አለ :: ለምሻ እቅጩን ሲነግረው ያልገባው መስሎ ባማርኛ ጻፍልኝ ብሎ ሊያጭበረብር ሞከረ

እንደዚህ አይነት እስስት ሾካካ ሰው አይቼ አላውቅም
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Fri Jul 04, 2014 3:54 pm

እሺ እንዴት ናችሁ አድባሩ.... ፓኔሪያ ካፌ ቤት ውስጥ እገኛለሁ.....ዛሬ ጁላይ 4 2014 ነው ስራ የለኝም:: ካንዲት የድሮ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን አንከር ጋዜጠኛ ጋር ቀጠሮ አለኝ ወደፊት አንዳንድ ፕሮጄክቶች አብረን የመስራቱ ሀሳብ አለን:: ከተሳካ!! ወደ ፓኔሪያ ስገባ ለረጅም ጊዜ አይቼው የማላውቀው አንድ ኤርትራዊ ወዳጄን አገኘሁ:: ያልተበረዘ ያልተከለሰ ኤርትራዊ ነው:: 11 ቁጥር 12 ቁጥር ከዛ ደሞ መስቀል በግንባሩ ላይ ብቻ ምን አለፋቹ ታቱ በታቱ !! ነው:: :D በዛ ላይ ፊቱ ቅጭም እንዳለ ነው:: የደረሱ ልጆችና እንደ ጦር የምትፈራው ወይም የምታከብረው ሚስት አለችው:: እሱ ግን ደስተኛ አይመስልም ጸሀይ ብትወጣና ብትጠልቅም አበቦች ቢፈነዱና ቢፈኩ የሰማይ ወፎች የፍቅር ዜማ ቢያዜሙ የዚህ ኤርትራዊ ወንድሜ ፊት ግን ተፈቶ አያውቅም:: ቅቅቅቅ:: ግን ወዳጆች ነን:; ለምን እንደሆነ ባላውቅም ለኔ አክብሮት ያለው ይመስለኛል:: በርጋታና በጽሞና ያወራኛል:: ከዛሬ አምስት ስድስት አመት በፊትም ሳገኘው አሁንም ሳገኘው ያው ነው:: ፊቱ ነው እንጂ ኮስትራ አንደበቱ ልስስልስ ነው:: መጣሁ... ከዱባይ ስልክ ስለደወለችልኝ ልጅ ላወራቹ አስቤያለሁ:: አንዳንድ ነገሮችን ቶሎ በማስታወሻ ካልያዝኴቸው በነው እንደ ጉም ይጠፋሉ....ህይወት የተለያዩ አዳዲስ ነገሮች ድምር ውጤት ናት:: ዖ ዖ የቀጠሮው ቦታ መቀየሩን ቴክስት አገኘሁ :: ተንቀሳቃሽ ቢሮዬን ( ላፕ ታፔን መስበብሰብ ጀምሬአለሁ)... ...stay tuned.... :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat Jul 26, 2014 12:54 am

እናንተዬ በፌስ ቡክ ..ቡቡቡ...ቡቡ..!! :lol: ( ጥቁር ሴቶች ደህና አድርጎ የሚያነጥራቸውን ጥቁር ወንድ ሲያቆማጥሉት ቡቡ..ቡ ..ቡ..ቡቡ !! ይሉታል:: ) :D ግን ቀልዱ ይቅርና በፌስ ቡክ ውስጥ ከወንድና ከሴት ታማኝ ማነው..?? እኛም እድሜአችንን እየቀንስን ገቢያችንን እያወፈረን እነሱም ውበታቸውን እያገዘፉልን እርስ በርስ እንፎጋገራለን:: ሁለታችንም ግን የምንዋሽ ይመስለኛል:: በቀደም ያገኘኌት ልጅ መነጽር አድርጋ የትነሳችውን ፎቶ አይቼ አላስቸለኝም :: ብትቆጪም ብትስቂም በፎቶሽ ወደጄሻለሁ እልኴት:: እባክሽ ፍቃድሽ ይሁንና ግሩፔ ውስጥ ልለጥፈው ብዬም ጠየኴት:: ሚስትህ ወይም ገርልህ ካልተቆጣችህ ጎ አሄድ!! አለችኝ:: ግድ የለም ፓንቹን እችለዋለሁ ብዬ መለስኩ:: :D ለሷ በሚገባ የሚሆን ማስታወቂያ አድርጌ ለጠፍኩት:: ሞዴል መሆን ትችላለች:: እዚህ አሜሪካ ባለፈው ያንድ ሞዴል ዝግጅት ላይ ተጋብዤ ነበር:: ከመቅጠናቸውና በታኮ ጫማ ቁመታቸውን ከማስመዝዛቸው በቀር ያንዳንዶቹ መልክ የጠላ ጣሳ ይመስላል:: ግን እዚህ አገር ውበት ማለት ፖስቸር ስትራክቸር ቴምፕሬቸር አግሪካልቸር ነው ተብሏል:: የፊት ውበት ሁለተኛ ነው:: :D እቺን ልጅ ሞዴል ትሆኛለች ስላት እረ አባክህ አትቀልድብኝ አለችኝ ..እኔ መንፈስ እየነገረኝ እንደማወራ እነሆ አልገባትም:: :D

እኔ የምለው ግን ትላልቅ የፕሮቴስታንትና ያፍሪካውያን በተለየ የናይጄሪያውያን ቸርች ባሉበት ቦታ አጠገብ ትላልቅ ቡፌ ቤቶች ከጎናቸው የሚከፈተቡት ምክንያት ምንድነው..?? ምን እየተካሄደ ነው?? ..ቸርች መሄድ ያስርባል..እንዴ ??

ወንድሜን አቶ እከሌን ልጠይቅ ፈልጌ ተውኩት:: ሰደበኝ እያለ መሰሎቹን ያሳድምብኛል...በክርስትናው ብቻ ሳይሆን ከዋናው እምነቴ ከእስልምናም ሊያስገልልኝ ይፈልጋል:: ይቅርብኝ:: ብሶቴንና ትዝብቴን እዚሁ ጽፌው ልውረድ::
ሰናይ ምሽት!! አርብ ነው ዛሬ ፏ ! እንላለን... የታባቱ! ድህነት እንደሆነ ድሮም እብራን ናት:: እሷም አትርቀን እኛም አንርቃት:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Tue Jul 29, 2014 8:43 pm

እሺ እንዴት ነው አድባሩ..አገሩ አፈሩ ቅቤው ..?? በነገራችን ላይ ቢዘገይም ኢድ ሙባረክ ብያለሁ:: ሁለት ወር ይሀው ከሀጥያት ሁሉ ተወግድነ ካልጋ ሳንወድቅ ጾምናት:: :lol: በነገራችን ላይ ወኅቢዝምን እንዳለ መፍራት ትክክል አይመስለኝም:: ትናንት አንድ ሙስሊም ቤተሰብ ኢድ ሙባረክ ለማለት ሄጄ ነበር:: ቡና ተፈልቶ ክትፎ ዱለት ሁሉ አቅርበውልኝ ደስ አሰኝተውኛል:: :D አላህ ይሙላላቸው:: ሁሉም ወሀቢስት አሸባሪ አይደለም:: ከሙስሊም ወዳጆቼ ጋር ስናወራ ወሀቢዝም በሳውዲ ውስጥ በሮያል ፋሚሊ የተጀመረውን የሀይማኖት አናርኪነት (ስራተ አልበኝነት) ለማስወገድ ወሀቢ የሚባል ሳውዲ አረቢያዊ ( ሪፎመርመር ) በመላኩ ቅዱስ ገብርዔል ( እንደተነገረኝ ) የወረደውን ቁራኑን ተከተሉ !! ብሎ የጀመረው እንቅስቃሴ እንጂ የግድ ወሀቢስት የሆነ ሁሉ አሸባሪ ነው ብሎ መናገር ወይም መገለጽ ናይቭ ነው:: አህባሽን አበሻው ኢትዮጵያዊ ሸካችን አብዱል ዝሀረሪ መስርተወታል:: ወበኢዝንም ደግሞ ወሀቢ ሪፎርም አድርገውታል:: ትክክለኛ አህባሽ ትክክለኛ ወሀቢስት ወደ ቁራኑ ይጔዛል እንጂ ፋናቲክ ሆኖ ሌላውን አይገድልም:: ፋናቲክ የሆነ ወሀቢስት ወይም አህባሽ ሌላውን እምነት ሊያጠፋ ከመጣ ትክክለኛ እስልምና አይደለም:: ቁራኑንም አይከተልም:: ሰው እምነቱን እንዲቀይር አታስገድዱ ይላልና :: ብቻ እኔ ያልገባኝ ነገር የመንግስተ ሰማያት ጉዳይ ነው:: መቼ ሞቼ መንግስተ ሰማይን እንደማይ ናፍቆኛል:: ሙስሊሞቹ ወገኖቼ መንግስተ ሰማያት እንደሚገቡ ፍጹም እርግጠኛ ናቻው:: እንደ ክርስቲያን እኔም መንግስተ ሰማይ እንደምገባ እኔም እርግጠኛ ነኝ:: እነዚህ ሙስሊሞቹ ወንድሞቼ ግን በግልጽ አይንገሩኝ እንጂ የኔን መንገስተ ሰማያት መግባት ይጠራጠራሉ.... ለምን..? ክርስቲያን በመሆኔ...":: እኔም አልነገርኴችውም እንጄ በልቤ አይገቧትም! እያልኩ አማቸዋለሁ:: ግን ማናችን እንገባ ይሆን..?? :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Thu Sep 22, 2016 11:23 pm

ይቺ መርቅ የሆነች ቤቴን ፈልጌ እገኘሁዋት እንዱ ባለስልጣናችን ባለፈው ጊዜ ሙሉ ኮንደምንየም እንዳለ ጠፋብኝ ሲሉ እቺም የድሃ ጎጆዬ ነበድ ገልዮ ያለች መስሎኝ ነበረ ሰውየው በዚህ ይሁን በሌላ እይታወቅም ከሚኒስትር ማእረጋቸው ተነስተዋል እንድ ወዳ ጄ ሲያጫውተኝ የመምሪያ እለቆችን ሰብስበው "ከሌላ ሰው ከምትሰሙት እኔ ልንገራችሁ ከንግዲህ የከተማ ልማት ሚኒስትር እይደለሁም እናንተ ግን በርታትታችሁ ስሩ" ብለው መመሪያ ሰጡን እለኝ፡፡ ሁሌም ሚኒስትሮች ሲባረሩ የሚያጋጥማቸው ክፍት ቦታ ግን የት እንደሆነ ታውቃላችሁ?? የጠቅላይ ሚኒስትሩ እማካሪ መሆን..ቅቅቅ የራሱን የሚኒስትር መስሪያ ቤት በደንብ አልመራም ተብሎ በብቃት የተነሳ ሚ/ር እንዴት ነው ለጠ/ ሚ./ር አማካሪነት ብቃት የሚያገኘው ? እመቤቴ ትፍታው!! እቺ አገር ቡዙ ጥሩ ነገሮችም ባለፉት አመታት ብናይባትም የዛኑ ያህል ቡዙ የሚገርሙ ነገሮች እሉባት ፡፡ ተጫወቱ መእምናን መጥተናል ክቡራን ነን፡፡ ከእዲሱ ሲ ኤ ም ሲ ሚክኤል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Fri Sep 23, 2016 5:23 pm

መላኩ ተፈራ የግዜር ታናሽ ወንድም የዛሬን ማርልኝ የነገን ኣልወልድም ብላ ነበረ የትናንት የጎንደር እናት ታዲያ ጡቶችዋን ወደ ሰማይ ኣድርጋ ኤሎሄ ስትል ለነበርች ለዚች ምስኪን እናት የደረሰላት ታማኝ በየነ ኣልነበረም ኣበበ በለው ኣልነበረም ፋሲል ደሞዝ ኣልነበሩም ወይም ፋርጣው ኣባ መልኬ ኣልነበሩም ወይንም ኣክሎግ ቢራራ የሚባለው ኣክትቢስት (Activist በጎንደርኛ አክትቢስት ነው የሚባለው ሎል ) ኣልነበሩም እነሱ እንደውም መላኩን ሲያመልኩ ኣንዳንዶቹም (ረ ቡዙዎች ማለት ይቻላል) በመተማ ኣድርገው ወደ ሱዳን ኣግሬ ኣውጭኝ ነበረ ያሉት፡፡ ይሄ በኛ እድሜ ያለ የትናንት ታሪክ ነው ፡፡ የጎንደርን እናት ለቅሶ ሰምተው እምባዎችዋን ያበሱላት ከተራራ እየተንደደረደሩ የወረዱ የትግራይ ኣናብስትና በቁጥር በወቅቱ ጥቂት የነበሩ የኣማራ ልጆች ናቸው፡፡ ዛሬ ጎንደር ናፈቅሽኝ... ጀግናው ጎንደሬ...መሬው... ሳንጃ.. ጃናሞራ.. የሚል ኣዝማሪ ሁላ ትናንት በመተማ ና በቦሌ በሩጫ ጥሎኣት የበረረ ጥልፍ ለባሽ የነበረ ነው፡፡ ከሚገርሙኝ ኣንዳንድ ነገሮች ፦፦
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Fri Oct 07, 2016 1:22 pm

ዘንድሮ ቡዙ ሰዎች ሞቱ ነፍስ ይማር!!

**ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል በ 80 የ እድሜ ዘመናቸው ባንኮክ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በህዋላ አርፈዋል፡፡

** በተባበሩት መንግስታት የ ኤ ርትራ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የነበሩት እምባሳደር ግርማ አስመሮም እንዲሁ አርፈዋል፡፡ ሰውየው ላለፉት 9 ወራት ጤንነት እንዳልነበራቸው የሚቀርባቸው ይናገራሉ ፡፡ አምባሳደር ግርማ ኤርትሬ ከመሆናቸው በፊት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ 7 ቁጥር ( የክንፍ ቦታ ) የኢትዮጵያን ማሊያ ለብሰው የሚጫወቱ ጎበዝ አጥቂ እንደነበሩ ወዳጆቻቸው ያስረዳሉ፡፡

** በኢትዮ ሱማሌ ጦርነት በ ዘመኑ ድንቅ የተባለትን ያየር ላየር ውጊያ ያደረጉት ና በህዋላም አይሮጵላናቸው ሲመታ በፓራሹት ሲወርዱ በሱማሌዎች ለ 11 አመት የታሰሩት በዋላም በ እስረኛ ልውውጥ ተፈተው የብርጋዴር ጄኔራልነት ማ እረግ የተሰጣቸው ጄኔራል ለገሰ ተፈራ በሀገረ አሜሪካ በህመም ሲሰቃዩ ከቆዩ በህዋላ እንዲሁ አርፈዋል፡፡ የህዝብ ድምጽ ነኝ የሚለው ኢሳት ስለ ጄኔራሉ የጤንነት ሁኔታም ሆነ ስለ ህመማቸው አንድም ቀን ትንፍሽ ብሎ አያውቅም፡፡

** ሻሮን ግሬይ የተባለች የ 30 አመት የፖስት ዶክትሪያል የእጽ ዋት ሳይንሰ ተመራማሪ ኦሮሚያ ውስጥ በመኪናዋ እንዳለች በድንጋይ ተደብድባ ሞታለች፡፡ የሁላችሁንም ነፍስ እጊዚእብሄር ይማር፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Fri Oct 07, 2016 5:39 pm

አንድ ጥናት ላይ ላይ የመላው አፍሪካ ጅዲፒ አንድ ላይ ቢደመር የፈረንሳይን አያክልም የሚል ነገር የሰማሁ መሰለኝ ( ጆሮየ ነው ወይስ ይሄ ነገር እውነት ነው)?? ሎል፡፡ ወይ እኛ በራሳችን ላይ እየቀለድን ነው ወይንም የነጭ ኢኮኖሚስቶች በኛ ላይ ሙድ ይዘውብን ( እያሾፉብን ) ነው?? የገባው ይናገር ..ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Fri Oct 14, 2016 7:45 am

አብዮት ልጅዋንም አንዳንዴም የልጅ ልጅዋንም ሳይቀር እንደምትበላ በደንብ ያወኩት በለማ 12 ነው ፡፡ ለማ 12 ማለት እዚህ ዋርካ ውስጥ ይሄ መንግስት እንዲወድቅ ዣንጥላ ለቤተ ክርስቲያን ከማስገባት አልፎ አለ የተባለ እዋቂ ጋ በመሄድ ጥሪቱን ያጠናቀቀ ሰው ነው፡፡ ለማ 12 ገር የጎጃ ም ሰው ስለሆነ እንዲጋበዙ የሚፈልጉ ያራዳ ልጆች ጠጋ ይሉና ስለዚህ መንግስት ክፉ ነገር አውቀው ያወሩና ቅጂለት ለዚህ አሽከር እያለ ከበር መልስ ካቲካላ ያጠጣቸው እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ይመስክራሉ ፡፡ ታዲያ እግረ መንገዱን እሱም ይጠጣ ነበር፡፡ ከ ዛ አረቄ ሲጠግብ እዚህ ዋርካ ላይ ይመጣና ካያሌው ጎበዜ በፊት ያማራ ክልል ርእሰ ብሄር እንድሆን ተጠይቄ ነበር ይለናል፡፡ ቅቅቅቅ፡፡ አይ ለሚቶ ዋርካ ውስጥ ያሉ ተሳታፊዎች ደስታ ከረሜላ እየሰጠ የሚታልላቸው የሰፈሩ ህጻናት ይመስሉታል መሰለኝ ቅቅቅቅ፡፡ አሁን ይባስ ተባለና እሱና መሰሎቹ ባስቀሰቀሱት አመጽ መንግስት ሁኔታው እስኪረጋጋ ቫይበርና ኢንተርኔትን ለጊዜው ስላገደ ለማ 12 ዋርካን ልትጽፍ አይደለም ልታየውም አልታደለችም፡፡ ባልዋን የጎዳች መስሎአት እንትንዋን በእንትን እንትን አደረገችው አለ አንዱ እኮ ነው ፡፡ ሎል..
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8251
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests