የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Wed Dec 07, 2016 2:31 am

በዋርካ ቆይታዬ ከምስቅባቸውና ከምዝናናባቸው ነገሮች አንዱ ሰዎች ያልሆኑትን ለመሆን ወይም በትክክለኛው ህይወታቸው ሞክረው ሞካክረው ያልተሳካላቸውን ነገሮች በምናብ ( ኢማጄኔሽን ) ማሳካት መቻላቸው ነው፡፡ ምሳሌ ልስጥ እዚህ ዋርካ ውስጥ በብቃት ቢመዘን የእድር ቤት ዘበኛ የመሆን ብቃት ሊኖረው የሚችል አንድ ሰው አለ፡፡ ይሄ ሰው ግን ( እኔ መጀመሪያ የሚቀልድ ይመስለኝ ነበር..ሎል) ኮስተር ብሎ ፈላስፋ ነኝ ይላል፡፡አይደለም ፍልስፍና አረፍተ ነገር አሰካክቶ ስሜቱን መግለጥ የማይችል የመንዝ በግ አይነት ነገር ነው፡፡ እረ ተው እንደ መንዝ በግ እትሁን ስትለው የሲውዘርላንድ በግ ብሆን እንዴት ነው ያዋጣኛል? አይነት ጥያቄ ይዞልህ ይቀርባል..ቅቅቅ ርሰርች ብለህ ስትጽፍ ስንት አይነት ሪሰርች አለ አስረዳኝ ብሎ የሞኝ ባገኝ ለቅሶ አይነት ጥያቄ ይጠይቅሃል፡፡ ስለ ፍራሽ የሆነ ነገር ለመግለጽ ጽፈህ ከሆነ የፍራሽ አይነቶችን አብራራልኝ ብሎ ይሞዘዛል፡፡ ሎል፡፡ አንዳንዴ ሳስበው ወፈፌ ነገር ይመስለኛል፡፡ እሱ ግን እኔ ፈላስፋው ይልሃል ኮስተር በማለት ቅቅቅ፡፡
Last edited by ክቡራን on Fri Dec 23, 2016 3:28 pm, edited 1 time in total.
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Fri Dec 23, 2016 2:46 pm

***እኔ ና ወንደላጤዎቼ***)
ምዕራፍ-1
(በዘሪሁን ገመቹ)
የ6 ኪሎ ልጅ ነኝ፡፡ 6 ኪሎ ስላችሁ ደግሞ የአዲስአባው እንዳይመስላችሁ፡፡እሱን በስምና በህልም ነው ማውቀው፡፡የጐባውን ማለቴ ነው ፡፡አኸ ለካ ጐባንም የማታውቁ አላችሁ፡፡ጐባ በደርግ ጊዜ የባሌ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ የነበረች በዘመነ ኢህአዲግ ከደረጃዋ ዝቅ ብላ ወደ ወረዳነት ያሽቆለቆለች ፤በደቡብ ኢትዬጵያ ከዋና ከተማችን አዲስአባ 446 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በ2743ሜ ከባህር ጠለል ከፍታ ላይ ጉብ ብላ የምትገኝ ከባሌ ብሄራዊ ፓርክ በ10 ኪ.ሜ ብቻ ምትርቅ ፡፡ ቀዝቃዛ የአየር ፀባይ ያላት..በእንቅስቃሴዋም ቀዘቀዘ ዕድሜ ጠገብ ከተማ ነች፡፡
ስለምኖርበት ከተማዬ ይሄን ያህል ካልኩ ስለራሴ ደግሞ ላውራችሁ፤ሳራ እባላለው፡፡የ19 ዓመት ወጣት ነኝ፡፤ፀጉሬ ወርቃማ ሆኖ በትኜ ስለቀው ወርዶ ወገቤ መሀከል የሚቆም ነው፡፡ጠይም አይነከብላላ..ክብደቴ 49 ኪ.ግ ቀመቴ 1.64 ነው፡፡አቤት እንዲህ ስል ይሄኔ ስንት ወንዶች ጐምዥታችሁብኛል? ለአቅመ ሄዋን እንደደረሰች አንድ አማላይ ወጣት የአዳምን ዘር የማማልልበት አፍላ የወጣትነት ስሜት በውስጤ የሚንፎለፎልብኝ አድርጋችሁ ገምታችሁኝ ሊሆን ይችላል? ግምታችሁ ስህተት ነው… አንድ 30 ዓመት የሚሆናት በችግር የታጠረች ኢትዬጵያዊ ወይዘሪት በቃ እኔ ማለት እሷ ነኝ ፡፡በዚህ ዕድሜዬ በየካፌ ቤቱ ከአፍቃሪዎቼ እና ከአድናቂዎቼ ጋር በመቀጣጠር ማኪያቶ በምልፍበት አይስክሬም በምልስበት በወር አንድ ቀን ሶደሬ ፤ላንጋኖ፤ሀዋሳ እያልኩ አለሜን በምቀጭበት ወቅት እናቴን እና ሁለት ወንድሞቼን አስተዳድራለው፤በክፍያ ኮሌጅ ከፍዬ እማራለው…(በነገራችን ላይ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ከበቂ ባላይ የሚሆን ነጥብ አስመዝግቤ ነበር ግን የተመደብኩበት ቦታ እናቴ እና ቤተሰቤን ጥዬ መሄድ ስላልቻልኩ ነው የተውኩት…)፡፡ አምስት ወንደላጤዎቼን ልብሳቸውን በማጠብ ፅዱ እያደረግኮቸው እና እያበስልኩ ሆዳቸውን በመሙላት ከእነሱ በምቀበለው ገንዘብ እራሴን ኖሬ ቤተሰቦቼን አኖራለው፡፡
እስከ አሁን የነገርኮችሁ በጠቅላላ ለእኔ ጫንቃ ከባድ አልነበረም፡፡ያልነገርኮችሁ ነው ምሬቴ፤እናቴ በሽተኛ ነች …ቀላል አደረግኩት አይደል?፡፡አልጋ ላይ ከቀረች አንድ አመት ከስድስት ወር አልፎታል..እንግዲህ እሷን መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ማሳከምም የእኔ ኃላፊነት ነው፡፡የ30 ዓመት አንድ ኢትዬጵያዊት ጠንካራ ሴት አድርጋችሁ ሳሉኝ ያልኮችሁ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡
ሸክሜን ያበዛብኝ ደግሞ አባቴ ነው፡፡ስለእሱ ሳስብ በጣም ነው የምበሳጨበት፡፡አመት ሆነው ጥሎን እብስ ካለ፡፡እሱ እስከሚሄድ ነገሮች መልካም ነበሩ፤ማለቴ ቢያንስ ከአምስቱ ወንደላጤዎቼ ጋር አልተዋወቅም ነበር፡፡የሰራውን ሰርቶ ለቤታችን ውጭ ሚበቃውን ብር ይዞ ይመጣ ነበር፤ እኔ እቤት ውስጥ ያለውን ጣጣ እወጣለው ፤እየተረዳዳን እናቴን እናስታምም..ሁለት ወንድሞቼን እናስተምር ነበር ፡፡ነበር ሆኖ ቀረ እንጂ፡፡
አይገርማችሁም ግን የወንድ አንጀት !!፤ እናቴ በእሱ ቦታ ብትሆን እንዲህ አታደርግም ነበር..በፍፁም፡፡ ጭካኔውን ከየት አምጥታ ?ማንም እንደሌለን እያወቀ? እናቴ በእግዜር እጅ እንደሆነች እያወቀ? አለውላችሁ የሚልን ምንም ዘመድ ከጐናችን እንደሌለን እያወቀ? መንግስትም እግዜርም ወደእኛ ቤት ፊታችን ማዞር ከተዉ በጣም እንደቆዩ እያወቀ ? ጥሎን እብስ ይላል፡፡ሳስበው የቤታችን መከራ ሳይሰለቸው ፤ የእናቴን ስቃይ በየቀኑ ማየትም ሳይመረው አልቀረም፡፡ ያለምንም ብጣቂ ተስፋ ያለምንም ቁራሽ ስንቅ ባዶችንን ጥሎን እብስ፡፡
‹‹አይዞሽ ስራ ፈለጋ ነው የሄደው.. የተሸለ ስራ ፈላልጐ ሰራ ሰራ በማድረግ ብር ጠርቀምቀም አድርጐ በቅርብ ይመጣልሻል..የጫንቃሽን ሸክምም ያቃልልሻል››እያላችሁ ልታፅናኑኝ እንዳትሞክሩ፡፡ እንደዛማ ቢሆን ትንሽ ፍንጥቅጣቂ ብርሀን…. ብጣቂ ቁራጭ ተስፋ ይኖረኝ ነበር..ግን እሱ እኮ ሙሉ በሙሉ ነው የተሸነፈው ከአመት በፊት ማታ ራቱን በልቶ ተኛ ጥዋት ለቁርስ መነሳት አሻፈረኝ አለ፡፡
‹‹ኑግ ወቃጮ እያለች ጐመን ቀንጣሾን ምች መታት›› አይደል የሚባለው፡፡ከዛሬ ነገ ትሞታለች እየተባለች የምትጠበቀው እናቴ ሳለች እሱ ቀድሞት ሞተ፡፡ ብሽቅ የሆነ አባት..በቀላሉ እጅ የሚሰጥ..መታገል የማይወድ ተሸናፊ የሆነ አባት…..
እናላችሁ ከዛ ቡኃላ ነው የእኔ እና የወንዳሌጤዎቼ ታሪክ የጀመረው..በተለይ ለእንደ እኔ አይነት ወጣት እና ቆንጆ ሴት የቤት ሰራተኝነት በቀላሉ የሚገኝ ስራ ስለሆነ ነው የተሰማራውበት፡፡
..እስቲ ወንደላጤዎቼን በዝርዝር ላስተወውቃችሁ…በቁጥር አምስት ናቸው ፡፡ሁሉም አንድ ጊቢ ውስጥ ነው ሚኖሩት ግቢው ሰፊ ሆኖ ሁለት ቦታ የተከፈለ ነው፡፡ አንደኛው የቤቱ ባለቤት አቶ ክንዴ የተባሉ አዛውንት ወንደላጤ ይኖሩበታል፤አቶ ክንዴን አንቱ ብሎ ማክበር እንኮን ይከብዳል..፡፡ሰውን አንቱ እና አንተ የሚያሰኘው ዕድሜው ሳይሆን ስብዕናው ነው፡፡ዕድሜው ከ60 በላይ እንደሚሆን መገመት ለማንም ከባድ ባይሆንም ቁመቱ ግን እንደስሙ ከአንድ ክንድ የማይረዝም መልኩ ቆንጆም አስጠሊታም የማይባል..ፀጉሩ ብዙም ያልሸበተ የተቁላላ የሽማጊሌ ፍንዳታ ነው ፡፡በዚህ ዕድሜያቸው ወንደላጤ ናቸው..ሚስት ድሮ ነበራቸው አሉ ግን ፈተው ብቻቸውን መኖር ከጀመሩ 1 ዓመት አልፎቸዋል፡፡የሚተዳደሩት በጡረታ፤ከሚያከራዩ ቤት በሚሰበስቡት የኪራይ ብር እና ከአራጣ ብድር ከሚሰበስቡት ትርፍ ነው››.አንደኛው ወንደላጤዬ እሷቸው ናቸው፡፡እይ የእኔ ነገር አንዴ እሳቸው አንዴ እሱ በማለት እያምታታው ነው አይደል ያወራዋችሁ..?ምን ላድርግ ሽማጊሌው እኮ ግራአጋቢ ነገር ነው፡፡ባይገርመችው በሳምንት ቢያንስ አንዴ ይጠይቀኛል:: ምንድነው ሚጠይቅሽ እንዳትሉኝ? እንኮን ለእናንተ ልነግራችሁ ለራሴም መልሼ ማሰብ እንኮን ያሳፍረኛል፡፡
ሁለተኛው ወንደላጤዬ ኩማንደር አልይ ይባላል፡፡የፖሊስ አዛዥ ነው፡፡ አልይ ልቅም ያለ ቆንጆ ነው….በቃ የወንድ መለሎ ነው.. በዛ ላይ ዘናጭ፡፡በተለይ የፖሊስ ዩኒፎርም ከመአረጉ ጋር ሲያደርግ ሲያምርበት ለብቻው ነው፡፡ በጣም ፅዱ ..በቅባት ወዝቶ በሽቶ ታጥቦ የሚወጣ፡፡ክፋቱ ጉረኛ ነው፡፡ጉረኝነቱ እንዲሁ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡በውበቱ ይመካል..በአለባበሱ ይንቀባረራል..በስራውም ባለው ማዕረግም ይመፃደቃል፡፡የከተማዋ ሴት ሁሉ በህልማቸው እሱን ለማግኘት ሲያልሙ የሚያድሩ አድርጐ የሚያስብ ነው ኩማንደር አልይ፡፡ አልይ ምንም ሱስ የለበትም፡፡ አይቅምም፤ አያጨስም አልፎ አልፎ ካልሆነም አይጠጣም..፡፡ግን በጣም ሙሰኛና በጣም ሴት አሳዳጅ ነው.. አረ አሳዳጅ ከሚለው ይልቅ ሴት ቀማሽ ነው ብላችሁ ይበልጥ ይገልፀዋል፡፡
ሶስተኛዋ ወንደላጤዬ ሙና ትባላለች፡፡ሙና ብቸኛዋ የሴት አሰሪዬ ነች፡፡ሴት ወንደላጤ ሳይሆን ሴተላጤ ነው አይደል መባል ያለባት? ሙናን እንደሴት አትቁጠሮት.. ፆታዋ ብቻ ነው ሴት ፤ጠቅላላ ስራው የወንድ ነው ፡፡ጠጪ ነች፤ ቃሚ ነች..ሁሉንም ነች፡፡እርግጥ ይሄም ብቻውን የወንደላጤነት ማዕረግ አያሰጣትም፡፡ሙና ውሃ ከባልዲ ቀድታ መጠጣት አትችልም፡፡ፓንቶን እራሱ በመከራ በሁለት ወር አንዴ ነው የምታጥበው፤ ተጠራቅሞ አንድ ኩርቱ ከሞላ ቡኃላ፡፡ እርግጥ ቢያንስ በሳምንት አንድ ፓንት ስለምትገዛ የፓንቶ ቁጥር ከቀበሌያችን ህዝብ ቁጥር እኩል የሚሆን ይመስለኛል፡፡ሙና ነርስ ነች፤ ደሞዞ 5ሺ አካባቢ ነው የወር ወጪዋ ግን ከ10 ሺ ብር በላይ ነው፡፡ከደሞዞ በላይ ያለውን ብር ቱጃር አባቶ ነው በየወሩ የሚልክላት ፡፡አይ ይህቺ አለም!!! የአንዳለንዱ አባት እንዲህ ለመጠጫ እና ለማበጃ ብር እየቆጠረ ለልጁ ይልካል..የእኔ አባት ግን!!!! ተውት ብቻ…
አራተኛውና አማስተኛው ወንደላጤዎቼ ዶክተር ሰምኦን እና ካሊድ ይባላሉ፡፡እዛው ጊቢ ውስጥ አንድ የጋራ ሳሎን ያለው ባለ ሁለት መኝታ ቤት አንድ ላይ ተከራይተው ነው የሚኖሩት ፡፡
ስለእነዚህ ሁለት ወንደላጤዎች በዝርዝር ላጫውታችሁ
አንደኛው ሰምኦን ነው..ስለ እሱ ሳስብ በመጀመሪያ በአእምሮዬ የሚመጣብኝ ጨበሬነቱ ነው፡፡ፀጉሩ ሁሌ ጫካ ውስጥ የከረመ ሽፍታ ያስመስለዋል፡፡ ሰምኦን ዘምተኛ ነው፤.ትንሽ ጠጪ ነው ፤ ቀሚም ነው፡፡ከሁሉም በላይ ግን በጣም ያጬሳል፡፡ሴትን በተመለከተ ግን መለኩሴ ነገር ነው፡፡ወይንም አላውቅም ሽምቅ ተዋጊ ነገር ሆኖ ሊሆንም ይችላል፡፡የህክምና ዶክተር ሲሆን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያስተማረ ሆስፒታል ውስጥም ይሰራል..ዶክተር ሰምኦን
የመጨረሻው ካሊድ ይባላል፡፡ነፍስ የሆነ ልጅ ነው፡፡ግን ምን ማለቴ ነው እሱጋር ስደርስ የሆነ የመቁላላት ሁኔታ ታየብኝ አይደል…?ብቻ ካሊድ ብዙም ያልፈካ..ብዙም ያልደበዘዘ ትንሽ ሚቅም፤ትንሽ ሚጠጣ፤አልፎ አልፎ ያጨሳል መሰለኝ..ጫወታው ቁጥብ..ፈገግታው ቁጥብ የሆነ ልጅ ነው፡፡የካሊድ ብቸኛው ችግር.. ችግር ማለት እንኮን ይከብዳል እኔ ማልወድለት ፀባዩ ሴት ማብዛቱ ነው፡፡ያበዛአ አንቺ ምንሽ ተነካ? እሱ ላይ ሲሆን ምነው ተንጨረጨርሽ ?ሴት ቀማሽ ነው ያልሽው ኮማንደር አልይ ላይ ለምን የዚህን ያህል አልተናደድሽም? ካላችሁኝ እውነታችሁን ነው እኔንም ገርሞኛል..ካሊድ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነው፡፡
ለማኛውም የእኔ 5 ወንደላጤዎች እነዚህ ሲሆኑ ፀባያቸውም እና ታሪካቸውን እኔ እስከደረስኩበት ጥልቀት ድረስ ይህንን ይመስላል፡፡ሌላውን ደግሞ በቀጣይነት አብረን እናየዋለን፡፡
ጸባይ ካላችሁ ክፍል ሁለት ይቀጥላል….ሎል ፡፡ በነገራችን ላይ ደራሲው ዘሪሁን ገመቹ ይሰኛሉ፡፡ ምንጭ ፌስ ቡክ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Sat Dec 24, 2016 9:10 pm

እኔና ወንደላጤዎቼ****)
ምዕራፍ -2
(በዘሪሁን ገመቹ)
ዛሬ ልክ እንደ መንግስት ሰራተኞች 2፤30 ሲሆን ወደ ቆሚ ስራዬ እየገባው ነው፡፡የምን ቆሚ ስራ አላችሁኝ አይደል? ሶስት ወር ቢሆንስ ያው ‹‹ማምሻም ዕድሜ ነው›› አይደል የሚባለው፡፡ደግሞ አንዱ ወንደላጤ ዞር ባይ ቢለኝ ሌላው ወንደላጤ ጋር እገባለው፡፡ደግሞ ከቁናው ሞልቶ መሬት ጭምር ተዘርግፎ ለተትረፈረፈ ወንደላጤ….
የወንደላጤዎቼ ቤት የሚገኘው ቀበሌ03 ሮብ ገበያ አካባቢ ከኢትዬያ ንግድ ባንክ ጀርባ ነው፡፡ደርሼ ግቢ ውስጥ ስገባ ካሊድ በረንዳው ላይ ቆሞ ፊቱን ሲታጠብ ደረስኩ፡፡የሌሎቹ ቤት ዝግ ነው፡፡
‹‹ደህና አደርክ ካሊዶ?›› አልኩት ከኃላው ደርሼ
‹‹ሀይ ባርች ደህና ነሽ››መለሰልኝ መታጠቡን ገታ አድርጐ፡፡ካሊድ ባርች ነው የሚለኝ፡፡
‹‹አለው ምነው ስራ የለም እንዴ?››
‹‹አረ አለ አሁን ልሄድ ነው››
‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ ቁርስ ልስራልሀ?››አልኩት
‹‹ባክሽ በዚህ ሰዓት ምግብ አይዋጥልኝም››
‹‹ታዲያ ምንድነው ሚዋጥልህ?››አልኩት ከተናገርኩ በቡኃላ ንግግሬ ራሴኑ አሳፈረኝ..እስቲ በፈጣሪ ምን ማለቴ ነው?፡፡
ከሊድም በፈገግታ እየተቅለሰለሰ ‹‹ያው ሚስት ብትኖረኝ በዚህ ሰዓት አንድ ጉርሻ ከንፈር ብታሽረኝ እሱን ገመጥ አድርጌ እያጣጣምኩ እሄድ ነበር›› አለኝ፤
‹‹እኔ ልስጥሀ ›› አይዞችሁ እንደዛ አልልኩትም፡፡ ግን ለትንሽ አዳልጦኝ ነበር..አትፍረዱብኝ ፈገግታው እኮ ልብን ፍርክስክስ ነው የሚያደርገው፡፡ የሆነ አዚማም ነገር ነው›፡፡
‹‹ሚስትማ ሞልቶል ››
‹‹ ከሞላማ አሳዩና እኛም ያለበት ሄደን የድርሻችንን እንፈልግ››
‹‹አይ አንተማ መሀከላቸው አይደለ ምትውለው?››
‹‹መሀከላቸው ማለት?››
‹፣ዩኒቨርሲቲ ነዋ…እንኮን ለእናንተ ለከተማው ወንድስ ይተርፉ የለ››
ተንከትክቶ ሳቀ‹‹ምን ያስቅሀል ?ዋሸው ?››
‹‹አይ ትክክል ልትሆኚ ትችያለሽ.. እኔ ግን ከተማሪ ጋር መነካካት አልፈልግም››
‹‹ብዙዎቹ ጓደኛችህ ግን በማርክ ሁሉ እንደሚደራደሩ ሰምቼያለው››
‹‹እስቲ እንዴት ነው ሚደራደሩት ንገሪኝ?››
‹‹እንደሰማውት ከሆነ ከወንዶቹ ጋር በገንዘብም መደራደር አለ ግን ከሴቶች ከሆነች በብዛት ሲ ለማግኘት አንድ ቀን ከአስተማሪው ጋር አብራ ታድራለች..ቢ ለማግኘት ከፈለገች 3 ቀን አብራው ማደር አለባት… ኤ ለማግኘት ከሆነ ደግሞ አንድ ሳምንት ››
‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል?››አለኝ ኮስተር ብሎ
‹‹ካሊዶ ሙት የእኛ ኮሌጅ ልጆች ሰማን ብለው ሲያወሩ የሰማውትን ነው ምነግርህ››
‹‹ሳሪ እኔ ጨዋነኝ ልልሽ አይደለም.. እንደማንኛውም ሰው ከተማሪ ውጭ ከሆነች ፍቃደኛ ሴት ጋር እወጣለው.. ያልሽው እውነት ከሆነ ግን በጣም አሳዛኝ ነገር ነው..ግን ይመስለኛል የአንድ ወይም የሁለት መምህራን ምግባር ነው እንዲህ የሁላችንንም ስም የሚበክለው››
አይዞህ አትዘን ለማንኛውም ቋሚዋን ፈለግ ፈለግ አድርገህ ተገላገል›› አልኩት
‹‹አጣዋ ከየት ላምጣ… አንቺም ዝም አልሺኝ››አለኝ
‹እኔማ…››ብዬ ቀጣይ ምን እንደምናገር በማሰላሰል ላይ ሳለው ከዛኛው ጊቢ የጥሪ ድምፅ ሰማው
ሳራ..አንቺ ሳራ››ጋሽ ክንዴ ናቸው…እኚ የእርጐ ዝንብ የሆኑ ሽማግሌ፤ዝም አልኮቸው፡፡
‹‹ባርች ሼባው ይጠራሻል››አለኝ ካሊድ ያልሰማው መስሎት
‹‹ሳራ..አንቺ ሳራ››
‹‹አቤት››አልኩ ድምፅን ከፍ አድርጌ››
‹‹አንዴ ነይ እስቲ ትናንት ቤት ስታስተካክይ መፅሀፍ ቅዱሴን የት አስቀመጥሽው?››
‹‹መኝታ ቤት ኮመዲኖ ላይ የለም?››
‹‹አጣውት ነይ እስቲ አንዴ ፈልጊልኝ››
ከዚህ አደንዛዥ ልጅ መለየት ቅር እያለኝ ‹‹መጣው›› ብዬው ወደ ዛኛው ጊቢ ሄድኩ፡፡ጋሽ ክንዴ በረንዳቸው ላይ ጋቢያቸውን ለብሰው ወንበር ላይ ቁጭ ብለዋል፡፡በእጃቸው መፅሀፍ ይዘዋል ‹‹ደህና አደሩ ጋሼ››
‹‹ደህና›› አሉኝ ፊታቸውን አጨማደው፡፡
የጠየቁኝን መፅሀፍ ቅዱስ ልፈልግላቸው አልፊያቸው ወደ ቤት ገባው፡፡ መኝታ ቤት ገብቼ ብፈልግ ብፈልግ ከየት ላምጣው?..ግራ ገባኝ፡፡ተመልሼ ወደ በረንዳ ወጣውና
‹‹ትናንት ካስቀመጥኩበት ቦታ የለም››አልኮቸው
‹‹ምኑ?›› አሉኝ
‹‹የጠየቁኝ መፅሀፍ ቅዱስ››
‹‹መፅሀፍ ቅዱስ..የምን መፅሀፍ ቅዱስ?››ግራ ተጋቡ ….እሳቸው ግራ ሲጋቡ እኔም አብሬያቸው ግራ ተጋባው..
‹‹እንዴ መፅሀፍ ቅዱሱ እጃቸው ላይ ነው››
‹‹ይዘውታል እኮ መፅሀፍ ቅዱሱን ››
‹‹አዎ ይዤዋለው›› አሉኝ ምንም እንዳልተፈጠረ
‹‹አጣውተ ስላሉኝ እኮ ነው?››
‹‹ብዬሽ ነበር እንዴ..?ቆይ ግነን ምነው በጥዋት መጣሽ?››
‹‹3 ሰዓት ሊሆን እኮ ነው››አልኮቸው ምንም እንኮን የጥያቄያቸው አቅጠጣጫው ባይገባኝም መልስ መስጠት ስላለብኝ፡፡
‹‹ሶስት ሰዓት ድረስ ታዲያ ተወዝፎ ይተኛል እንዴ?››
‹‹ማን?››
‹‹ይሄ ጭባ አስተማሪ ነዋ››ሳቄን አፈነኝ
‹‹ካሊዴን ነው ሚሉት?›
‹‹አዎ… አንቺ ልጅ ግን እኔ ስለምታሳዝኚኝ ነው ..እነዚህን ውርጋጥ ወንደላጤዎች አትመኚያቸው ..ፊትም እንዳትሰጪያቸው..››
‹‹የምን ፊት መስጠት አመጡብኝ ስራዬን ሰራለው ብር ይከፍሉኛል በቃ ፤የእኔ እና የእነሱ ግንኙነት በእኔነ በእርሷ መካከል እንዳለው አይነት ግንኙነት ነው››
‹‹ምልሽ እኮ እሱን ነው እንደ እኔ አትያቸው..እነዚ ውርጋጦች ገና ሮጠው ያልጠገቡ…በዛ ላይ ከየት እንደመጡ ማይታወቁ መጠጤዎች ናቸው…እኔ እንደውም ሀሉም የሚከፍሉሸ ከፍዬሽ እነሱ ደጅ ባትደርሺ ደስ ይለኛል››
‹‹አይዞዎት እኔ ራሴ እራሴን ጠብቃለው፤አሁን እርሶ ወደ ንባቦት ይመለሱ ብዬቸው ተመልሼ ወጣው፡፡
ካሊድ በራፉን ቆልፎ ወጥቶል ስራዬን ከኩማንደሩ ቤት ለመጀመር ወደዛው አመራው፡፡ደርሼ ሁለት ክፍል ያላትን የኮማንደር አልይን ቤት ከፈትኩ፡፡
‹‹አይ ዛሬስ አንድ ሴት ብቻ አይደለችም ያደረችው›› ስል አሰብኩ ፡፡‹‹በምን አወቅሽ አትሉኝም?፡፡››ገና በራፉን ስከፍት የወሲብ ሽታ ወደኃላ አስፈንጥሮ ገፈተረኝ፡፡ ቅልሽልሽ የሚያደርግ የወሲብ ሽታ ፡፡‹‹ደግሞ የወሲብ ሽታ ምን አይነት ነው አንቺስ እንት አወቅሽ ? ››እንዳትሉኝ መልሴ እኔ እንጃ እኔ ፤ዕድል ቀንቶኝ ቀምሼው መች አውቅና ብላችሁ ነው፡፡ ለወሲብ የሚሆን ዕድልማ በየቦታው ተዝረክርኮ ሞልቶል ለዛውም ወንደላጤዎች ቤት እየሰራው ..ለዛውም ኮሌጅ እየተማርኩ… ለዛውም ማታ እየተማርኩ… ለዛውም ቆንጆ ሆኜ..ብቻ ዋናው ምክንያቴ ድህነት አንጀቴን ስልብ ያደረገኝ ስለሆንኩ ለዚህ አይነት ጉዳይ ወኔዬ ስልብ ብሎብኝ … እንጂማ የጊዜ እጥረት እና የዕድል ጉዳይ እንኮን ያን ያህል አሳማኝ ምክንያት አይመስለኝም፡፡
በራፉን በልቅጬ ከፍቼው ትንሽ እንዲናፈስ ካደረግኩት ቡኃላ ወደ ውስጥ ገባው፡፡ ሳሎኑን ትናንት እንዳስተካከልኩት ነው ብዙም የተዘበራረቀ ነገር አይታየኝም..ተመስገን ነው፡፡ ለስራ ይሁን ለወሬ ጐጉቼ አላውቅም ተንደርድሬ ወደ መኝታ ቤት ገባው፡፡ እብድ ሲሮሮጥበት ያደረ ነው የሚመስለው
አንሶላው ወደዚህና ወደዚያ ተበታትኖል ብርድልብሱም እንደዛው፡፡ ወለሉ በውሃ ረስርሶል.. …ዉይ!!! ውሃ አልኩ እንዴ? ይሄ ምን ውሃ ነው ከደስታቸው ቡኃላ በድካም ሰውነታቸው ዝሎ በመሰላቸት ለመተጣጠብ ሲሞክሩ ወዲህና ወዲያ የረጫጩት የሰውነታቸው እድፍ ልቅላቂ ነው እንጂ…
ማስተካከል ጀመርኩ አይ ዕዳዬ ደግሞ የተጠቀመበትን እንኮን ሰብስቦ ጥሎ ቢሄድ ምን አለበት..ደግሞ ብዛቱ መቁጠር ጀመርኩ 1..2..3..4……7 በተሰቀለው!!! ኮንደሙን በአንድ ዙር ሁለት እና ሶስት እየደራረበ በማጥለቅ ነው እንዴ ተጠቀመው…?ነው ወይስ በነጠላው ነው ይሄን ሁሉ የተጠቀመው…?ይህቺ የዛሬዋ ሴት የተገዛች መሆን አለባት ፤300 ብር ገዝቶት ከሆነ 3 ጊዜ ብቻ አድርጎ ከሸኛት የአንዱ ዙር ዋጋ 100 ብር ሊሆንበት ነው..ስድስቴ ከሄደ ግን 50 ብር ይሆንለታል፡፡ያ ማለት ደግሞ ርካሽ ነው.. እሱ እንደውም ጐበዝ ነው ሰባቴ ስለሄደ ከ50 ብር በታችም አስገብቶታል፡፡
አንድ ወቅት አንድ ጐደኛዬ የነገረችኝ እውነተኛ ታሪክ ትዝ አለኝ በቀላ ሞላ በህይወት እያሉ በአንዱ ሆቴላቸው ቁጭ ብለው እንደማንኛውም ሰው የጥዋት ፀሀይ ይሞቃሉ፡፡አንድ ተስተናጋጅ መጣና ፊት ለፊታቸው ቁጭ ብሎ ሻይ ያዛል፡፡ያዘዘው ሻይ ይመጣለታል፡፡ደንበኛው ፊቱ የተቀመጡትን በቀለ ሞላን እንደ እሱ የቤቱ ደንበኛ አድርጐ በመቁጠር ችላ ይላቸውን ገልመጥ ገልመጥ እያለ በማንኪያ ስኳሩን እየዛቀ ብርጭቆ ውስጥ መጨመር ይጀምራል፡፡እሳቸውም በቆረጣ እያዩት ይታዘቡታል፤3 ማንኪያ 4፣5፣6 ማንኪያ ላይ ሲደርስ ሻዩ ከብርጭቆ ሞልቶ መፍሰስ ይጀምራል..በዚህ ጊዜ ልጨምር ይብቃኝ እያለ ሲያምታታ አጅሬው ምን ቢሉት ጥሩ ነው
‹‹ወንድም በቀለ ሞላን አከስራለው ብለህ ልብህን እንዳታፈነዳት››በማለት ከራማውን ገፈፉት፡፡እውነታቸውን ነው ኩማንደሩም ዛሬ እንደዛ ደንበኛ ስግብግብ እና ስስታም ሆኖ ያደረ መሰለኝ ነው ወይስ ስለጣፈጠው ይሆን?፡፡አቤት የእኔ ነገር አሁን ይሄን ሁሉ ምን አስቀባጠረኝ?ዋናው ነገር አሁን ይሄንን ሁሉ የተዝረከረከ ቆሻሻ ለቃቅሜ ጥለዋለው ወይስ እንዲሁ እንደተዝረከረከ ባለቤቱን ይጠብቅው?፡፡እንባዬ በዓይኔ ግጥም አለ፡፡ እናቴ ፌቴ ላይ መጣች፤ ፍልሰታን እንፆማለን ብለውኝ ቁርስ ያልባሉትእና ስድስት ሰዓት ሲሆን ቤተክርስቲያን ቆጥረው የሚሄዱት ምግብ ከእኔ የሚጠብቁት ወንድሞቼ ትዝ አሉኝ..አዎ አልይ በየወሩ ሚከፍለኝ 300 ብር በጣም ያስፈልገኛ፡፡ፔተስታል ፈለግኩና እጄን በዛ ጠቅልዬ አንድ በአንድ እየለቃቀምኩ ሌላ ፔስታል ውስጥ በማጨቅ አንድ ላይ አሰርኩት ና ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ወስጄ ጣልኩት፡፡
ከዛ በእጄ እንዳልነካውት ባውቅም እስኪለበልበኝ ድረስ እጆቼን በአጃክስ ፈትጌ ደጋግሜ ታጠብኩት፡ካዛ ምግብ ለመስራት ሽንኩርት መክተፍ ጀመርኩ፡ፈጠን ፈጠን ማለት አለብኝ ፡፡ገና የሶስት ቤት ስራ ይቀረኛል፡፡ደግሞ እያንዳንዱ ቤት ገና እንደሚጠብቀኝ አላውቅም..ስድስት ሰዓት ከመሆኑ በፊት የሁሉንም ቤት ዝግጁ ማድረግ ግዴታዬ ነው፡፡እስቲ እናንተም አታዋሩኝ ትኩረቴን በመሰብሰብ ስራዬን በፍጥነት እና በትኩረት ልስራበት…ባይሆን ነገ እንገናኝ፡፡
ክፍል 3 ይቀጥላል…
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Mon Dec 26, 2016 8:46 am

የሙሴ ከዘራ፡፡
የባልዋን አዲስ መኪና ጌታ ተናግሮኛል ብላ በከዘራ ያነከተችው አንድ ወዳጄ በዚህ ጌታ በሆነ ባልሆነው ተናገረኝ በሚል እንኪያ ሰላምታ የተነሳ ትንሽ ቁሱቃሶ ውስጥ በመግባታችን ክርሲማስን ለማክበር ጠርታኝ እቤትዋ ስሄድ ያንን የባልዋን መኪና ያነከተችበትን ከዘራ ( እስዋ ጌታ የሰጠኝ የሙሴ ከዘራ ትለዋለች) ይዛ ጠበቀችኝ፡፡ ሁኔታው አላመረኝም፡፡ ሎል፡፡ ሰላም ካልክዋት በህዋላ አያያዝዋ ስላላመረኝ "ቆይ የምትወጂውን ስጦታ መኪናዬ ውስጥ ረስቼዋለሁ ላምጣው" አልኩ ፡፡

"ምንድነው እሱ ?" አይንዋን አፍጣ ጠየቀችኝ..

"ፓናቶኒ የጣሊያን ኬክ ይዥልሽ መጥቻለሁ" አልኩ..

የያዘችውን ከዘራ ሳይ ወባ እንደያዘው ማንቀጥቀጥ ሊጀምረኝ ያሰበ ይመስላል .
"ኦ ኬ ሄደህ አምጣው" አለችኝ ...
"እናቴ የጽዮን ማርያም የዛሬን አውጭኝ!!" ብዬ የመኪናዬን በር እንደከፈትኩ ከመቼው ሞተሩን እንዳስነሳሁት ሳላውቅ ከ30 ደቂቃ በህዋላ እቤቴ በር ላይ ደረስኩ፡፡ ባየር ላይ በርሬ ይሆን በሃይ-ወይ ነድቼ እንዴት እንደደረስኩ የምታውቀው የጽዮን ማርያም ብቻ ናት ፡፡ ለኔ አሁን ድረስ ግልጽ አይደለም፡፡ ሎል፡፡ ጌታ አሳየኝ.. ጌታ ሹክ አለኝ..ጌታ ገለጸልኝ፣ ጌታ ተናገረኝ " እያሉ መንፈስ ቅዱስን የኪሳቸው ማህረብ ካደረጉ የአእምሮ በሽተኞች ይሰውራችሁ!! እያልኩ ገጠመኜን እዚህ ላይ እቅዋጫለሁ፡፡ ሎል፡፡ ዲሴምበር 25/2016፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Sun Jan 08, 2017 12:19 am

እኔና ወንደላጤዎቼ****)
ክፍል -4
(በዘሪሁን ገመቹ)
ወዳጆቼ ዛሬ ጭንቅ ላይ ነኝ::ታዲያ ያንቺ ጭንቀት ውስጥ መሆን ምን ይገርማል? እንደምትሉኝ አውቃለው::ግን ግድ የለችሁም አትፍረዱብኝ፡፡እናቴን እኮ አሞብኝ ነው፡፡ ለሊቱን ሙሉ ስትስል ነው ያደረችው፡፡አሁን ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛ፡፡ሀኪም ቤት ይዤት ልሄድ ፈልጌያለው ደግሞም አምስቱ ወንደላጤዎቼን ምን ላድርግ…ጦም ላውላቸው እንዴ?ግን ለአንድ ቀን ምን ችግር አለው ሆቴልም መብላት ይችላሉ፡፡
ፍቃድ ልጠይቅ ካሊዶ ጋር ደወልኩለት ‹ለምን ሌሎች ጋር ሳትደውይ… ?›እንዳትሉኝ በቃ እሱ ስለሚቀለኝ ነው..እሺ ይሁንላችሁ ከእሱ ጋር ማውራት ደስ ስለሚለኝ ነው፡፡የእናቴን መታመም ነገርኩ
‹‹ሄሎ ካሊዶ››
‹‹ሄሎ ሳሪ››
ዝም አልኩ… ዝም ያልኩት የማወራው ነገር ጠፍቶኝ ሳይሆን ሳራ ነው ወይስ ሳሪ ብሎ የጠራኝ? ሚለውን ሳብሰለስል ነው፡፡ከዚህ በፊት እንዲህ ጠርቶኝ አያውቅም ‹ባርች› ነው ሚለኝ፡፡
‹‹ሄሎ ሳሪ አይሰማም››ብሎ ደገመው፤ ቀድሜ የሰማውት እውነት እንደሆነ አረጋገጠለኝ
‹‹ከሊዶ ይሰማል… ትንሽ ችግር አጋጥሞኝ ነው..ማዘርን አሞብኛል››
‹‹እና ምን ልርዳሽ?››
‹‹አይ ማለቴ ስራ መግባት አልቻልኩም ልልህ ነው››
‹‹አረ ጣጣ የለውም..ለሙናና ለአልይ ነግርልሻለው…ለሼባው ብቻ ደውለሽ ንገሪው››
‹‹አመሰግናለው ካሊድ››
‹‹ችግር የለውም ..አይዞሽ ምትፈልጊው ነገር ካለ ደውይልኝ›› አለኝ
‹‹እሺ ደውላለው ..ቸው››ብዬው ስልኩን ዘጋው..የሆነ ደስ ሚል ስሜት ውስጤን ውርር አደረገኝ፡፡ ግን ምኑ ነው ደስ ያሰኘኝ ?ፍቃድ ስለሰጠኝ ይሆን ? ስትጨነቅ ያደረች ነፍሴን በስልክ ድምጹን ስለሰማች ይሆን ?እኔ እንጃ
‹‹ወደ ሽማግሌዬ ጋር ደወልኩ››
‹‹ሄሎ››
‹‹ሳራ ነኝ ጋሼ ክንዴ››
‹‹እሺ ሳራ ደህና አደርሽ››
‹‹ደህና ነኝ..ፍቃድ ልጠይቅ ነበር አደዋወሌ››
‹‹እንዴ የምን ፍቃድ…?እኔ እንዲህ አይነት መቅበጥ አልፈልግም..ደግሞ ከማን ጋር የት ለመሄድ ነው ፍቃድ?››ሀሳቤን ሳያስጨርሱ ቀባጠሩ
‹‹እናቴ ታማ እኮ ነው…ሆስፒታል ይዤት ልሄድ ነው››
‹‹….ውይ የእኔ ነገር..ችግር የለም..እኔ እኮ ያው ከእዚህ ግቢ ጠረንሽ ሲርቅ ስለሚጨንቀኝ ነው›..ግድ የለም ይዘዣት ሂጂ››ብለው ፈቀዱልኝ
ሁለት ሰዓት ሲሆን እናቴን በጋሪ ደግፌ ወደ ሆስፒታል ይዤያት ሄድኩ፡፡ማረፊ ቦታ ከሚገኝ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ አስተኛዋት እና ካርድ ቤት በመሄድ የተወሰነ ወረፋ ጠብቄ ካርድ ቆረጥኩና ወደ እናቴ እየተመለስኩ ለሙና ደወልኩላት
‹‹ሁሎ ሙና››
‹‹ሄሎ ሳሪች…ካሊድ እኮ ነገረኝ››
‹‹አዎ ባክሽ ዛሬ ትንሽ ባስ አለባት››
‹‹ታዲያ ለምን ይዘሻት አትመጪም?››
‹‹መጥቼያለው እኮ ግቢ ውስጥ ነኝ ያለውት፡፡››ብዬ ያለውበትን ቦታ ነገርኮት..ከአምስት ደቂቃ ቡኃላ መጣችና እናቴን አገላብጣ አየቻት…
‹‹አይዞሽ አሁን ይታከማሉ››አለቺኝ
‹‹ዶ/ር ሰምኦን ይኖራል እንዴ?›› ስል ጠየቅኮት መቼስ ‹ከማያውቁት መላዕክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል› ይባል የለ…እሱ እናቴን ቢያይልኝ በደንብ ያክምልኛል ብዬ ስላሰብኩ ነበር ሙናን ያማከርኮት
‹‹ተይው ባክሽ እሱ ቢኖርም የለም…ይሄኔ ያን ጨበሬውን እየጠቀለለ ሲጋራውን እያቦነነልሽ ነው››
‹‹ቢሆንም እሱ ቢያይልኝ ጥሩ ነበር››
ጐትታ ከእናቴ ራቅ አድርጋ ወሰደቺኝና ‹‹ቆይ እንትን ስጪኝ እያለ ዙሪያን የሚሽከረከር አንድ ሀኪም አለ ላናግረውና በደንብ እንዲያክማቸው እናደርጋለን››
‹‹እንትን ምንድነው?››
‹‹አንቺ ልጅ ነሽ ገና ለአቅመ-እንትን አልደረስሽም››ብላ እየተንከተተች ጥላኝ ሄደችና ከ15 ደቂቃ ቡኃላ ተመልሳ መጣች፡፡እናቴን ከግራና ከቀኝ ደግፈን ወደ አለችው ዶክተር ይዘናት ሄድን ..ወደ ውስጥ ዘለቅን እናቴን ወንበር ላይ ስናስቀምጣት የሀኪሙ ዓይን የሙና መቀመጫ ላይ እንደተጣበቀ ነበር….
‹‹…ዶ/ር እንግዲህ ስጥ ይሰጥሀል ነው የሚባለው››አለችውና እየፈገገች ወጥታ ሄደች፡፡ልጅ እግሩ ሀኪም ድንግርግሩ ወጣ …በጥዋቱ ግንባሩ ላይ ላቡ ቸፍ አለበት
…..የጥዋቱን ግማሽ ክፍለ ጊዜ በእናቴ ላይ ነው ያጠፋው ፤ ሚያስፈልጋትን ምርመራ ሁሉ ከመረመራት ቡኃላ ያስፈልጋል ያለውን 3 መድሀኒት አዘዘላት እና ካልተሸለቸው ከስሶስት ቀን ቡኃላ እቤት ድረስ መጥቶ እንደሚያያት ነግሮኝ ሁኔታውን ተከታትዬ እንዳሳውቀው ሞባይል ቁጥሩን ሰጠኝ፡፡ እናቴን ይዤ ወጣውና አግዳሚው ወንበር ላይ መልሼ አስተኝቼ ወደ ሆስፒታሉ መድሀኒት ቤት አመራው፡፡ እየተሳቀቅኩ ነው የሄድኩት፤ በእጄ ያለው 180 ብር ብቻ ነው፡፡ መድሀኒት ቤት ደረስኩና ለድራጊስቱ የመድሀኒቱን ትዕዛዝ ወረቀት አቀበልኩት አነበበና አንዱ ብቻ እንደሚገኝ ሌላውን ከውጭ እንድገዛ ወረቀቱን መልሶ ሰጠኝ …ሃያ ሶስት ብር ከፈልኩና ያገኘውትን መድሀኒት ይዤ እናቴን ወደቤት አይዤት ገባው፡፡
ካዛ ያደረግኩት ከተማ በመዞር መድሀኒቱን መፈለግ ነው …ቀይ መስቀል መድሀኒት ቤት ጀምሬ አንድም የቀረኝ ቦታ የለም አንዱን በ17 ብር አግኝቼ ገዛው፤ አንደኛው ጭራሽ ጠፋ ፤መነኸሪያው ጋር ከይልም ሆቴል ፊት ለፊት ያለ አንድ ፣ድሀኒት ቤት የሚሰራ ቀዥቃዣ ባለሞያ አዲስ አበባ ካልሆነ እዚ እንደማለጋኝ ዋጋው ከ2500-3000 ብር እንደሆነ ቀለል አድርጐ ነገረኝ ..ምን ነገረኝ አረዳኝ ልበላችሁ እንጂ፡፡ወደታች ፊቴን አዙሬ ወደ ሰፈር መመለስ ትቼ ወደላይ መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ይሄንን መድሀኒት አዲስአበባ አስልኬ ለማስገዛት እኮ ከሁሉም ወንደላጤዎቼ የሚቀጥለውን የሁለት ወር ደሞዜን ቅድሚያ መቀበል ሊኖርብኝ ነው፡፡ወይ ፍርጃዬ!!!፡፡በመዛጋጃ አጥር እና በጡረተኞች ጠጅ ቤት መካከል ወደ እናት ሜዲካ ኮሌጅ(እኔ የምማርበት ኮሌጅ ነው)የሚወስደውን መንገድ ተያያዝኩት.. ወደ ግራዬ ታጠፍኩና በቴሌ እና በፖሊስ ጣቢያው መካከል የሚወስደውን መንገድ ተያዝኩና መልሼ ወደ ቀኜ ታጣጠፍኩ መድሀንያለም ቤተክርስቲያን ስደርስ ተሳለምኩና ወደ ውስጥ ገባው ሰአቱ አምስት ሰአት አካባቢ ሆኖል ወቅቱ ፍልሰታ በማሆኑ ህጻናት በብዛት በጊቢው ይታያሉ፤ ዞሬ ተሳለምኩና አንዱ ጥግ ሄጄ ተሸጐጥኩ፡፡እዚህ ቤ.ክርስቲያን የመጣውት ለእግዚያብሄር ምንም ልነግረው አይደለም…ለምን ብዬ ምንስ እነግረዋለው? እሱ ስለ እኔም ሆነ ስለቤተሰቦቼ ምን የማያውቀው ነገር አለ?በቃ እንደፈለገ ያድርገኝ፡፡በእኔም ሆነ በቤተሰቦቼ ላይ እየደረሰብን ያለው መከራና መሳቀቅ በቂያችሁ አይደለም ካለ ሌላ ተጨማሪ ይመርቅልን..በቃ ምንም አልለውም፡፡እኔ የመጣውት በአካባቢው የሚበተነውን ቅዱስ ቀዝቃዛ አየር መንፈሴን ቢያቀዘቅዝልኝ ብዬ ነው..ጭንቅላቴ ውስጥ የሚንጫጫብኝን ነገር ፀጥ እንዲልልኝ ተመኝቼ ብቻ ነው መጣውት ቅዳሴው ስድስት ሰዓት ተጀምሮ ለ9 ሰዓት እስኪጠናቀቅ ከተጐለትኩበት ቦታ አልተነቃነቅኩም ነበር ቡኃላ ፆሚዎቹ ከቅዳሴው መልስ ሁሉም ከየቤቱ ቆጥሮ መጣውን ምግብ በመያዝ በአንድነት ምግቡን አስባርኮ ለመቆደስ ወደአንድ ቦታ ሲሰባሰብ እኔ ሹልክ ብዬ ከግቢው ወጣው…ስለማይመለከተኝ፡፡ከእቤት ስደርስ እናቴ በስጋት በር በሩን ስታይ ነበር የደረስኩት
‹‹ወይ ልጄ !!ምን ነካሽ ?የት ጠፋሽብኝ?››
‹‹አለው ባክሽ..አልኮት..››ብስጭት ብዬ
‹‹በአፍሽ እንኮን ምግብ ሳትቀምሺ እንደወጣሽ ትቀሪያለሽ?››አለቺኝ በሽታ ባደቀቀው አንጀቶ ለእኔ በሀዘኔታ እየተንሰፈሰፈች
ቀኑን ሙሉ ምግብ እንዳልቀመስኩ አሁን እናቴ ስታወራ ነው ትዝ ያለኝ፡፡
‹‹እነ እዬብስ?››
‹‹ከተማ ዞር ዞር ብለው እንዲፈልጉሽ ላክኮቸው››
‹‹አይ እማ!! እስቲ የት ብለው ይፈልጉኛል?››
‹‹ግራ ገባኛ መድሀኒቱን ገዛለው ብለሺኝ ነው የወጣሽ …በዛ ላይ ስልክሽ አይሰራም››
‹‹ባትሪ ጨርሶብኝ ነው….ሞክራችሁ ነበር እንዴ?››
‹‹እኛማ በምን እንሞክርልሻለን ሙና ነበረች የሞከረችልሽ ››
‹‹መጥታ ነበር?››አልኮት ብዙም ግድ በሌለው ስሜት
‹‹አዎ ይሄንን ፖስታ ስጪያት ብላኛለች›› ብለ ከራስጌዋ አንድ ካኪ ፖስታ አቀበለቺኝ፤ተቀብዬት ከፈትኩትና በውስጡ የያዘውን ስሬ ያለው ጠረጴዛ ላይ ዘረገፍኩት፡፡ አንድ አይነት የሆነ ብዙ ኪኒኒ ፤ አምስት የመቶ ብር ኖት እና አንድ ወረቀት ነው፤ወረቀቱን አነሳውና አነበብኩት
….ሳሪ የታባሽ ሄድሽ ነው ስልክሽን ብቀጠቅጥ ላገኝሽ አልቻልኩም፤ እናንተ ከሆስፒታል ከተመለሳችሁ ቡኃላ ዶክተሩን ሳናግረው ለማዘር ያዘዘላቸውን መድሀኒት ነገረኝ፤ መድሀኒቱ ውድ ከመሆኑም በላይ እዚህ በቀላሉ ማግኘት እንደማትቺይ ስላወቅኩ ጀለሶቼን አስቸግሬ አገኘውልሽ..በየ6 ሰዓት ልዩነት አንድ አንድ ፍሬ ይዋጡ..ደግሞ እንዳያቆርጡ፡፡ ብሩ ደግሞ ደሞዝሽ ነው አስር ቀን ቢቀረውም ይቸግርሻል ብዬ ነው…ቸው ይላል፡፡
እያነበብኩ ሳለ እንባዬ እርግፍ እርግፍ ይል ነበር፡፡ተነሳውና ከእማዬ መኝታ በራስጌ በኩል ግድግዳ ላይ የተለጠፈውን የመድሀኒያለም ስዕልን ተንጠራርቼ ሳምኩት
‹‹ምን አገኘሽ ልጄ?››ጠየቀቺኝ እማዬ
ሀዘኔንም ብስጭቴንም በአንዴ እርግፍ አድርጌ እየተፍለቀለቅኩ‹‹እማ መድሀኒያለም ቤተክርስቲያን ነበር የቆየውት ትንሽ ከፍቶኝ ነበር›.
‹‹ሆዴ እኮ ጠርጥሮል..ግን ምን ሆንሺብኝ?››
‹‹ይሄን መድሀኒት አጥቼ ነበር ..አድስአበባ ካልሆነ አይገኝም ብለውኝ››
‹‹አይ ልጄ አትዋሺኝ ..መግዣውን ፍራንክ አጥተሸ ነው አይደል?››
‹‹እንደዛም ማለት ትቺያለሽ..ትንሽ ውድ ነበር››
‹‹አንቺን የሰማሽ መድሀኒያለም እኔንም ቢሰማኝ ምን አለበት››
‹‹ምንድነው የሚሰማሽ?››
‹‹አንቺን ልጄን እያሳቀቅኩ ከምኖር ቢገላግለኝ ጥሩ ነበር››
‹‹እማ..እንዲህ ስትይ እኮ ነው ወኔዬን ሁሉ ውድምድም የምታደርጊው…ልፋቴን ሁሉ አየር ላይ የምትበትኚው ….ይልቅ አሁን ደስ ብሎኛል ቆንጆ ብና አፈላና እንተጣለን››
‹‹እሺ ግን መጀመሪያ አፍሽ ላይ ምግብ ጣል አድርጊ››
‹‹እሺ አብረን እንብላ››አልኩና ሚበላ ነገር ለማቅረራረብ አሮጌ ብረድስቶችን መከፋፈት ጀመርኩ……
ይቀጥላል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Sun Jan 15, 2017 1:53 am

(***እኔና ወንደላጤዎቼ***)
ምዕራፍ-5
(በዘሪሁን ገመቹ)
ከምሽቱ 3 ሰዓት ሲሆን ለቤተሰቡ እራት ሰርቼ አጠናቀኩና ለእኔ እና ሁለት ወንድሞቼ የጤፍ ቂጣ በጐመኝ፡፡ለእናቴ እሩብ ኪሎ ስጋ ገዝቼ ስለነበር ከዛሬም ተርፎ ለነገም እንዲበቃት አድርጌ በርበሬ ሳልጨምር ወአልጫ ወጥ ሰርቼላታለው፡፡በርበሬ ያልጨመርኩት ለበሽተኛዋ እናቴ ስለሚከብዳት ብቻ ሳይሆን በቤቱም ርጋፊ በርበሬ ስለሌለ ነው፡፡በነገራችን ላይ ስጋ የገዛውበትን ብር እንዴት እንዳገኘውት ልንገራችሁ…….
አስር ሰዓት አካባቢ ለካሊድ ሚስ ኮል አደረግኩለት..ከሁለት ደቂቃ ቡኃላ መልሶ ደወለልኝ፡፡
‹‹ይቅርታ ካሊዶ ስልኬ ሳንቲም ሰለሌለው ነው ሚስኮል ያደረግኩልህ››አልኩት
‹‹አረ ችግር የለውም..ሰላም ነሽ ግን?››
ሰላም ነኝ ነገ ስራ ከመግባቴ በፊት ከወጣችሁ አስቤዛ መግዣ ብር አስቀምጠህልኝ እንድትሄድ ልነግርህ ነው››
‹‹እሺ ስንት ላስቀምጥልሽ?››
‹‹ሁለት መቶ ብር››
‹‹እሺ አስቀምጣለው..ቸው›› ብሎኝ ተሰናበተኝ
ከአምስት ደቂቃ ቡኃላ የ50 ብር ካርድ በስልኬ ተላከልኝ..ከማን ይመስላችኃል? ከካሊድ..፡፡እንደው ምን ላርገው ?የእኔ ሀሳቢ..ታዲያ ሃምሳ ብር ሙሉ ምን አደርገዋለው እንዳልጀናጀንበት ፍቅረኛ የለኝ..፡፡ለአንድ ጓደኛዬ 30 ብሩን አስተላለፍኩላትና 25 ብር ሰጠቺኝ…በላዩ ላይ 10 ብር ጨምሬበት በ35 ብር ሩብ ኪሎውን ስጋ ለእናቴ ገዛውላት..ጠቅላላ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
በመጀመሪያ ለሁለቱ ወንድሞቹ በየግላቸው ራታቸውን ከቀረብኩላቸው ቡኃላ ለእናቴ ደግሞ ከሱቅ ከገዛውት አንደ እንጀራ ላይ ግማሹን ቆርሼ ከወጡ ፈሰስ አደረግኩበትና ሰጠዋት..የምግብ አቅሞ በሩብ እና በግማሽ እንጀራ መሀከል ነው፡፡
‹‹አንቺም ቁጭ በይና ብይ እንጂ››አለቺኝ እናቴ
‹‹ቆይ ብና ላፍላልሽና እበላለው››
‹‹ኸረ ተይ ደክሞሻል››
‹‹አይ አልደከመኝም ››አልኮት ና ፊኛን እየጠዘጠዘኝ ስለነበረ ወደውጭ ወጣው ሽንት ቤት
ስመለስ እናቴ እንድትበላ የሰጠዋትን ምግብ ፈጠን ፈጠን እያለች ልጆቾን ስታጐርስ ደረስኩ…..ድንገት ዘው ስል እሷም ልጆቹም ደነገጡ
‹‹እማ ምን መሆንሽ ነው?››
‹‹ልጆች እኮ ናቸው ይጐጐሉ››
‹‹አውቃለው ግን እኮ ታውቂ የለ የዚህ ያህል ብቻ ነው አቅሜ ሚፈቅደው››
‹‹ልጄ ላሳቅቅሽ ፈልጌ እኮ አይደለም….እኔ እንደሆነ ካቀረብሽልኝ ግማሹንም አልበላው..መትረፉ እኮ አይቀርም ብዬ ነው››
‹‹እንደፈለግሽ…››ብያት ለንቦጬን እንደጣልኩ ሲኒውን አቀራርቤ ብረት ምጣዱን ካለበት አምጥቼ የተቀጣተለው የከሰለ ማንደጃ ላይ ጥጄ መቁላት ስጀምር የእናቴን እጅ አፌ አካባቢ አየውት..ቀና ስል በአይኖቾም ጭምር እየተለማመጠቺኝ ነው
‹‹ምንድነው?››
‹‹ይህቺን ጉረሺ ልጄ››
‹‹ጭራሽ እኔም?››
‹‹አንቺስ ምን አለሽ..?እባክሽ ብቻዬን የበላውት እኮ አይጠጋኝም››
የሆነ ስሜት ውስጤን እርባሽብሽ አደረገኝ…በዓለም ላይ በጣም ከባዱ ነገር የሀገር መሪ ሆኖ ህዝብን ማስተዳደር አይደለም ሚከብደው እናት ሆኖ ቤተሰብ መምራት እንጂ.. እንጃ እኔ ግን መቼም የምወልድ አይመስለኝም..ለማኛውም እየሳቅኩ ጐረስኩላት እና ከመቀመጫዬ በመነሳት ለእናቴ ለነገዋ ብዬ ያስቀረውትን የስጋ ወጥ ያያዘ ብረድስት አንስቼ ለወንድሞቼ ገልብጬ አከፋፈልቸው..በዛን ጊዜ ወንድሞቼ ፊት ላይ ከታየው ደስታ ይልቅ እናቴ መላ ሰውነት ላይ የታየው የደስታ መፍለቅለቅ በብዙ እጥፍ ይበልጥ ነበር
‹‹ጐሽ ልጄ ክፉ አያግኝሽ…. እግዚያብሄር ይባርክሽ…. አጥተሸ የሰው እጅ አትይ..››እስኪሰለቸኝ መረቀችኝ፡፡እኔም ብናውን አፈላውና አቦሉን ካጠጣዋት ቡኃላ ሁለተኛው እስኪፈላ ለጥዋቶ ሚስኪን ሴት ልደውልላት ስልኬን ይዤ እቤቱን በመልቀቅ ወደ ውጭ ወጣው
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ሳሪ ሰላም ነሽ?››ቅዝቅዝ ብሎ ድክምክም ያለ በውስጡ ሕይወት የሌለው በድን ድምፅ ነበር የሰማውት
‹‹አላገኘሽውም እንዴ?››
‹‹አግኝቼዋለው››
‹‹እና ተስፋ የለውም?››
‹‹ያለው ይመስለኛል …ነገ እለቅልሻለው ብሎኛል››
‹‹ጐሽ እግዜር ይስጠው››
‹‹አዎ›› ከንግግሮ ውስጥ ምንም ዓይነት ደስታ አይመነጭም
‹‹ታዲያ ምነው ችግር አለ እንዴ?››
‹‹እህ.ህ..ህ››ሳግ የሞላበት ልቅሶዋን ለቀቀችው ደነገጥኩ
‹‹ምነው ምን ሆነሻል?››
‹‹ረከስኩልሽ….››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ለልጆቼ ስል ተበለጥኩ››
‹‹ማንነበር ስምሽ..?አዎ መሰረት ምንድነው የተፈጠረው?››
‹‹አሁን ከ30 ደቂቃ በፊት ነው ወደቤቴ የገባውት››
‹‹ከየት?››
‹‹ከሰውዬው ቤት?››
‹‹የቱ ሰውዬ›?›
‹‹ኩማንደሩ››
‹‹እንዴ!!! ቤቱ ምን ትሰሪያለሽ?››
‹‹ባሌን ለማስፈታት አንድ ያለኝ ምርጫ እቤቱ ሄጄ ቀሚሴን ለእሱ ማውለቅ ብቻ ነበር .እንደዛም አደረግኩት›››
‹‹ምን..?እሱነው እንደዛ አይነት ምርጫ ያቀረበልሽ?››
‹‹አዎ ወይ አልጋው ላይ እንድወድቅለት ከልሆነም 10ሺ ብር እንድከፍል ካለበለዚያ ፍቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ብቻ ሳይሆን በሽበርተኝነትም ሊከሰስ እንደሚችል አስፈራራኝ..እኔ ደግሞ በእጄ እንኮን 10 ሺ ብር 1 ሺ ብርም የለም››
‹‹ወይኔ በወላዳቲአምላክ እኔ ነኝ ጉድ የሰራውሽ››
‹‹አንቺም ምን አደረግሽ ?የ40 ቀን እድሌ ነው እንጂ እንዲ ያወረደኝ››
‹‹በበቃ አይዞሽ ጠንከር በይ..ደህና እደሪ ነገ አገኝሻለወ››
‹‹እሺ ደህና እደሪ››ብላ በለቅሶ እንደታጀበች ስልኩን ዘጋችው፡፡
ሴት መሆኔን ጠላው አረ ሴት መሆኔንም ብቻ ሰይሆን በአጠቃላይ ሰው መሆኔም አስጠላኝ፡፡የአቤ ጐበኛው ‹አልወለድም › መፅሀፍ አሁን በዚህ ጊዜ ነበር መፅፍ ያነበረበት..እስቲ በየቀኑ እንደፈለገ ለሚያገላብጠው እንትን እንዲህ የሰው ሰው ቅስም ስብርብር ማድረጉ ……አሊ የሚባል ሰውዬ በጣም አስጠላኝ፡፡ ( ግን ለመሆኑ ግምገማውና ጥልቅ ተሃድሶው አሊዎችን ይጨምራል?? የኔ አስተያየት ነው .. )
እናቴ በወንድሜ እስክታስጠራኝ ድረስ ወጭ እንደሀውልት ተገትሬ አዕምሮዬን በሀሳብ ሰውነቴን በብርድ እየተንዘፈዘፈ ነበር፡፡ሚስኪን እንደእኔ ቀን የጣላት ሴት እያልኩ ወደቤቴ ገባው…
ይቀጥላል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Thu Jun 08, 2017 8:27 am

ጊዜ ጠፍቶ ውሎአችን ከባንዶችና ከኢትዮጵያ ነቀርሶች ጋር ሆነ እንጂ እኮ እኛ ክቡራን እኮ ቦታችን ከነ ሄምንጌዊይ፣ ከነ ማክሲም ጎርኪይ፣ ከነ አጋታ ክርስቲል፣ ከነ በአሉ ግርማ፣ከ ነ ዮሃንስ አፍወርቅ ጋር ነበር፡፡ ወይ ነዶ!! ሎል፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Thu Jun 15, 2017 9:03 pm

እኔ የምለው አንድ ሰው የሚማረው ምን ለማድረግ ነው? ዶክተር ወይንም ኢኒጂነር የሚባለውን ታይትል ለማግኘት ነው ? የስም ቅጥያ ለማስፋት ነው ? ፍየል ለማገድ ነው ? ሎል፡፡ ሃገርን ለመርዳት ወይንም ደሞ ህዝብን ለማገልገል ነው ? የሃሳብ ፍሰት ያለው ይናገር!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Thu Jun 22, 2017 2:47 pm

በፌስ ቡክ ውስጥ አንድ ሴት የልጄን አባት ፈልጉልኝ ብላ የጻፈችውን ማስታወቂያ አነበብኩ፡፡ እኔም ያቅሜን ያህል እንኳን ብረዳት ብዬ እስኪ ሰው ሁሉ ከጥንት ጀምሮ የሚያቀው አንድ የቆየ አለሌ ዋርካ ውስጥ አለ... ጌታ አሳይቶኛል እያለ ያልሞከራት ሴት የለችም... የልጆቹን ቁጥር እሱም በትክክል የሚያውቃቸው አይመስለኝም ብዬ እዚህ ፎርም ውስጥ መጥታ እንድትሳተፍና በዛውም የልጅዋን አባት እንድታጣራ መከርኩዋክት፡፡ መቼም መረዳዳት ባህላችን አይደል ወገኖቼ፡፡ አጠፋህ እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሎል፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Fri Sep 28, 2018 1:56 am

እቺን ጽሁፍ ከጻፍክዋት ዘንድሮ ሁለት አመት ሆነ፡፡ የያዘችው እውነትም ሆነ የጽሁፉዋ ትርክት በዋናነት የሚያጠንጥበት የዋርካ ጥሬ እቃ አሁንም ድረስ ይዘቱን ሳይቀይር አለ፡፡ አይገርምም?? ሎል፡፡
በዋርካ ቆይታዬ ከምስቅባቸውና ከምዝናናባቸው ነገሮች አንዱ ሰዎች ያልሆኑትን ለመሆን ወይም በትክክለኛው ህይወታቸው ሞክረው ሞካክረው ያልተሳካላቸውን ነገሮች በምናብ ( ኢማጄኔሽን ) ማሳካት መቻላቸው ነው፡፡ ምሳሌ ልስጥ እዚህ ዋርካ ውስጥ በብቃት ቢመዘን የእድር ቤት ዘበኛ የመሆን ብቃት ሊኖረው የሚችል አንድ ሰው አለ፡፡ ይሄ ሰው ግን ( እኔ መጀመሪያ የሚቀልድ ይመስለኝ ነበር..ሎል) ኮስተር ብሎ ፈላስፋ ነኝ ይላል፡፡አይደለም ፍልስፍና አረፍተ ነገር አሰካክቶ ስሜቱን መግለጥ የማይችል የመንዝ በግ አይነት ነገር ነው፡፡ እረ ተው እንደ መንዝ በግ እትሁን ስትለው የሲውዘርላንድ በግ ብሆን እንዴት ነው ያዋጣኛል? አይነት ጥያቄ ይዞልህ ይቀርባል..ቅቅቅ ርሰርች ብለህ ስትጽፍ ስንት አይነት ሪሰርች አለ አስረዳኝ ብሎ የሞኝ ባገኝ ለቅሶ አይነት ጥያቄ ይጠይቅሃል፡፡ ስለ ፍራሽ የሆነ ነገር ለመግለጽ ጽፈህ ከሆነ የፍራሽ አይነቶችን አብራራልኝ ብሎ ይሞዘዛል፡፡ ሎል፡፡ አንዳንዴ ሳስበው ወፈፌ ነገር ይመስለኛል፡፡ እሱ ግን እኔ "ፈላስፋው" ይልሃል ኮስተር በማለት ቅቅቅ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Sat Sep 29, 2018 1:46 pm

የባሰው መጣ ሰውዬው ለይቶለታል ሎል.. ዛሬ ደሞ ያርሲቶትል ወንድም ነኝ ብሎ አረፈው..ሎል ይሄኔ ነው መሸሽ....
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Wed Oct 03, 2018 1:18 pm

ሌላው የሚገርመኝ ነገር ዋርካ ሲቆረቆር አብሮ እራሱን የቆረቆረ አንድ በግ አለ፡፡ የበጉን ፕሮፋይል ስታየው 2003 ጀምሮ የዋርካ እድምተኛ እንደሆነ ይነግርሃል፡፡ በነዚህ ረጅም አመታት ለዚህ የመወያያ መድረክ ክብር፣ ሞገስ ፣ ቅርስ መሆን የሚገባው ይሀ በግ የዋርካ አንባቢያን ሸክምና የመጥፎ ምሳሌ መገለጫ መሆኑን ስታየው ታዝናለህ፡፡ ባትማርም ፊደል ባትቆጥርም እኮ እድሜ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው፣ ህይወት በራስዋም ታላቅ ዩኒቨርሲቲህ ናት፡፡ ያለመታደል ሆኖ በ 2003 ጅማሪ ጸሃፊ ሆኖ የሚነግርህን ነገር ዛሬም ይደግልምሃል፡፡ ታላቁ የሳይንስ ሰው አልበርት አንስታይን ይመስለኛል ባንድ ወቅት ተጠይቆ ስለራስህ ምን ታስባለህ ሲባል ስለራሴ ሳስብ በመጀመሪያ የሚታየኝ አለማወቄን ማወቄ ነው ያለውን ቢረዳ ባራት እግር ከሚሄድ የመንዝ በግ እስካሁን በሁለት እግር የሚሄድ ሰው በሆነ ነበር...ዘገምተኛ ለውጥ ቢሆንም ..፡፡ ሎል፡፡
ኒህ ሃው ማ ..
ዋ ሄ ሃን ሽ ሽ ፣፣፣ትርጉሙን ከነ ነጠብጣቡ ጎልጉልልኝ እንትና ...ቅቅቅቅቅ
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ቆቁ » Wed Oct 03, 2018 2:15 pm

ስማ ነፍሱ ወደኛ አትምጣ
አንስታይንን ተነካ ማለት ፈላስፋው ተነካ ማለት ነው፣ ይግባህ.
አንስታይን እለማወቄን ማወቄ ነው ሲልህ የሰው ልጅ መሆኑን ሲነግርህ ነው
ነገር ግን አንተ ላት የሌለው በግ መሆንህ የሚገ'ለጸው አለማወቅህን ማወቅህ ብቻ ሳይሆን ማወቅህን አለማወቅህ ነው
ያ ነው የአንተ ችግር ይልሃል ፈላስፋው
ማወቃቸውን የማያውቁ ናቸው በርዓይ የሚባሉት ምክንያቱም በማያውቁ ሰዎች እንደ ከብት ስለሚነዱ
እየነዱህ ነው ወይም እየተነዳህ ነው !!!

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4236
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ቆቁ » Wed Oct 03, 2018 8:02 pm

አንስታይን " አለማወቄን ማወቄ ነው "
ይህ የወንድሜ የአንስታይን አባባል የሰውን ሰውነት የሚገልጽ አባባል ነው ነፍሱ
ይህንን አላውቅም ብለህ ለማወቅ ትጥራለህ ሰው ትጠይቃለህ ትመራመራለህ
አልበርት አንስታይን ይህንን ተጠቅሞ ነው የሬላቲቪቲን ቲዎሪ የቀመረው


ማወቅን አለማወቅ ግን ለየት ያለ ባህርይ ነው የሰው ልጅ ባህርይም አይደለም ፡ የእንስሳትም ባህርይ አይደለም
እንስሳት አንድ ጊዜ ያወቁትን ያውቃሉ
የሰው ልጅ ግን ያወቀውን ነገር ከረሳ ለማስታወስ ይሞክራል
ነገር ግን ያወቀውን ነገር እስታውሶ ካላወቀ ግን የዞረ ድምር አለበት ማለት ነው፡፡
እስቲ ተመልከቱት ወደ ውስጥ ገብቼ መዘርዘር አልፈልግም
አንድ ግለሰብ የሚያውቀውን ነገር ካላወቀ ምንድነው ?
ለምሳሌ ክቡዬ ዋርካ ላይ መለጠፉን ካላወቀው ኢሳት ላይ ለጠፈው ማለት ነው ? ፡ በምናቡ ፡ በህልሙ ግን ኒዮርክ ታይምስ ላይ ለጠፈው ሊባል ይቻላል፡፡

በነገራችን ላይ የሚገርሙኝ እንዳንድ ነገሮች የሚለው አርዕስት ለራስህ ተስማሚ ነው
ስለዚህም ነው የምትለጥፈውና የምትጽፈው ሲገርምህ የሚኖረውም የምታውቀውን እታውቅምና ፡
የማያውቁ ሰዎችን እያወቅህ አታውቃቸውምና ፡
ወንድሜ እጅህን ብቻ ሳይሆን ጭንቅላትህን ከሰጠህ ሰነበትክ እኮ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4236
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Postby ክቡራን » Wed Oct 03, 2018 9:29 pm

አዬ የበጎች ነገር ሎል.. ሰው ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ አሉ...ቡሬ፣ ሻሾ፣ ሰላም ነው?? ሎል፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests