የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby menzewu » Mon Feb 20, 2012 11:59 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:
ዘርዐይ ደረስ wrote:ይህን ታሪካዊ የሰማዕታት ቀን ለመዘከር ርእሱን ለከፈተው AddisMeraf እና ሌሎቻችሁም ሰላምታዬን እያቀረብኩ:-

AddisMeraf:-የዕለቱ 75ኛ ዓመት ታስቦ የሚውለው አንተ እንዳልከው ባለፈው ዓርብ ሳይሆን ዛሬ ነው::በተረፈ ያቀረብካቸው መረጃዎች ጠቃሚ ናቸው:: በቂ ጊዜ ሳገኝ
አንብቤአቸው እመለስበት ይሆናል ::


ተድላ ሀይሉ:-እንዳልከው ይህ ዕለት ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ በየካቲት 11 የህወሃት ምሥረታ አከባበር በዓል ተውጧል::ስለ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሰጠኸው አስተያየት ላይ ግን ቅሬታ አለኝ::ሁለቱና ሥሙ ብዙም የማይጠራው ስምዖን አደፍርሰው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፋሽስት ግፍ አንገፍግፏቸው በወቅቱ በነበራቸው አቅም የግፍ አገዛዙን ዕድሜ ለማሳጠር እንጂ አንተ እንደምትለው የሙከራውን መክሸፍ ተከትሎ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ፈልገው ያደረጉት አይደለም::እኔ በበኩሌ አንድም ታሪክ ጸሐፊ በዚህ ድርጊት ሲወነጅላቸው አልሰማሁም አላነበብኩምም::አንተ እንዳልከው ቢሆን ኖሮ ዕለቱ በየዓመቱ ታስቦ ሲውል ሥማቸው በጀግንነት አይጠራም ነበር::ያንተን አመለካከት የሚጋራ አንድ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ጸሐፊ ወይም አርበኛ ልትጠቅስልኝ ትችላለህ?

ሰላም ዘርዐይ ደረስ:-

የአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ታሪክ በአርበኝነት ሥም ሲጻፍላቸው የኖረው ጣሊያንን አርበድብደው ያባረሩት:-
1 ..... እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ከወንድማቸው እጅጉ ዘለቀ ጋር ተክለኃይማኖት አደባባይ በሥቅላት በሚቀጡበት:

2 ..... እነ ፊታውራሪ ታከለ ወልደሐዋርያት እንደ ተራ ሌባ ታድነው በገዛ ቤታቸው በእሩምታ ተኩስ ተደብድበው ለሞት በተዳረጉበት ዘመን ነበር::

በተቃራኒው ደግሞ እንደ እነ ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖት : ራስ ስዩም መንገሻ : ቢትወደድ አስፍሃ ወልደሚካኤልን የመሣሠሉ ቀንደኛ የጣሊያን ባንዶች በሹመት በሚንበሸበሹበት ዘመን ነበር ::

ታሪክን በትክክል መርምረን አጥፊውን ከእነ ጥፋቱ ካላቀረብን እውነቱ ሃሰት : ሃሰቱ ደግሞ እውነት መስሎ ይቀርባል ::

ስለዚህ ለእኔ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ጀብደኞችና የጣሊያን ፋሽስቶች ጥፋት አቀጣጣዮች እንጂ ጀግኖች አይደሉም ::
ተድላ


<ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች> አለች የአራት ኪሎ ሸሌ!! ደሞ ከመቸ ወዲህ ነው ተድላ ሀጎስ...ይቅርርታ ..ተድላ ሀይሉ ..የአርበኝነት ምስክር የሆነው? ይልቁንስ ያማረብህን የሳይበር ስም አጥፊነቱና አቃጣሪነቱን በርታበት. አርበኝነቱን በምግባርና በደም ዉርስ ለተላበሱት ተወው. ወንድነቱና አርበኝነቱ በስሜትህም በደምህም የለም.

አስታዋሽህ ሻቢያው መንዜ!!!
menzewu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Fri Dec 25, 2009 4:40 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Feb 21, 2012 12:14 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የሚከተሉት ታሪካዊ ፊልሞች ፋሽስት ጣሊያኖች በ5 ዓመቱ የጥፋት አገዛዛቸው ወቅት ምን ያህል ጭካኔ የተሞላባቸው ድርጊቶች ይፈጽሙ እንደነበረ ያሣያሉ :: የዛሬዎቹ ገዢዎችና የፋሽስት ጣሊያኖች የመንፈስ ልጆች የሆኑት ወያኔዎችና ሻቢያዎችም እንደፋሽስቶች ሁሉ የንፁሃንን ሕይወት በመቅጠፍ ከ40 ዓመታት በላይ ዘልቀዋል ::

ምንጮች:-
የሚከተለው ፊልም የፋሽስት ጣሊያን ወታደሮች በሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ተባርከው በኢትዮጵያውያን ሕፃናት ላይ ያዘንቡ የነበረውን የመርዝ ጋዝና የነርቭ ጋዝ የሚያሣይ ነው ::
1 ..... Italians bombing Ethiopian civilians with Vatican blessing.

በዚህኛው ፊልም ደግሞ "ጃፓኖች በቻይናውያን ላይ እንዳደረጉት ሁሉ እነርሱም ፋሽስት ጣሊያኖች በኢትዮጵያውያን ላይ የመርዝ ጋዝ እንዳይጠቀሙ ለምን እንደሚከለከሉ' ሲያማርር ታዳምጣላችሁ::
2 ..... Italians using mustard gas on Ethiopian civilians (1935-1941).

ስለጣሊያኖች የጦር ወንጀል ታሪካዊ ዘገባ :: ጣሊያኖች በኬሚካል ቦምቦች ጦርነት ለማካሄድ ምን ያህል በጥልቀት ተዘጋጅተውበት ነበር? በተቃራኒው እኛ ኢትዮጵያውያን ከ70 ዓመታት በኋላ እንኳን ለደረሠብን ግፍ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሠማት እንኳን እናመነታለን ::

የየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. የአዲስ አበባውን ጭፍጨፋ ከ12ኛው ደቂቃ በኋላ ታገኙታላችሁ :: በዚያ ጭፍጨፋ ያለቁት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከ46,000 እንደማያንሱ አስተማማኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ ::

የየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ጭፍጨፋን ተከትሎ ፋሽስቶች በመላ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንን በአሠቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፉን ቀጠሉበት :: በአጠቃላይ በአምሥቱ ዓመት የፋሽስቶች የወረራ ዘመን ከ1 ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል ::

3 ..... Italian War Crimes.

4 ..... La guerra di conquista dell'Etiopia, crimini sulle popolazioni e l'uso dei gas.

5 ..... WAR IN ETHIOPIA-ITALIANS IN ACTION.


ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Wed Feb 22, 2012 5:48 am

ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት የሚታሰቡበትን የካቲት አስራ ሁለትን በሚመለከት ከትላት ወዲያ በቪኦኤ የአፍሪካ ነክ ርዕሶች መለስካቸው አምሀ ሁለት ሰዎችን አወያይቶ አዳምጨ እዚህ ሳላመጣው ረሳሁት

ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ---በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ አሉ ከሚባሉት የታርክ ተመራማሪዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ነው::

ጥላሁን ጣሰው ---ታሪካው ልቦለድ "trying times'


http://www.voanews.com/amharic/audio/


እንደምትወዱት እገምታለሁ!

ናፖሊዮን ዳኘ::
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ጥልቁ1 » Wed Feb 22, 2012 9:07 am

ይህ ወቅት ሲመጣ ፣ ከጥቁር አሜሪካውያን የታሪክ ወር ጋር እየተገጣጠመ ፣ ለአለፉት 7 አመታት በግለሰብ ደረጃ የምዘክርበት መድረክ ስላለኝ ፣ ለህሊናየ ታላቅ እረፍት ይሰጠኛል። ለሌሎች ኩሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የምመክረው ፣ ይህን ቀን በያላችሁበት ፣ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ትዘክሩት ዘንድ አስታውሳለሁ።

ለምን እንደሆነ አላቅም ፣ አሁን አሁን ግን ህሊናየን የሚያስጨንቀኝ እና መልስ የማላገኝለት ምስጢር ፣ እንዴት ያ ሁሉ መሰዋትነት የተከፈለባት አገር ፣ ተንገዋላ ተንገዋላ የኢጣሊያኖች አሸከር የነበሩት እና እነ አቡነጴጥሮስን በጥይት ደብድበው የገደሉት ባንዳዎች እጅ ላይ ልትወድቅ ቻለች? (ልብ በሉ ፣ እነአቡነ ጴጥሮስ እራሳቸውን ለመሰዋትነት ሲያቀርቡ ፣ ትግራይ ውስጥ ግን ለጣሊያኖች ታቦት ወጥቶ ያሬዳዊ ዜማ ይቀርባላቸው ነበር። ልክ በኛ ዘመን ፣ አባ ገብረምድህን ለቢዮንሴ እንዳደረጉት ማለት ነው።) እውነት እኛ ኢትዮጵያውያን እንዴት ከታሪክ ምንም ሳንማር ቀርተን ፣ ያችን አገር ለዘመናት ሲያደሟት የኖሯት ባንዳዎች እንዲፈነጩባት ፈቀድን? አዎን ፈቅደናል። (ያኔ ሲመጡስ ጊዜው አስገድዶን አረብ እና አሜሪካም ተመሳጥሮብን ይባል) ዛሬ ግን ብንፈቅድ አይደል በኢትዮጵያዊነት ስም ሁሉ ተደራጅተን ፣ ሁለመናው እኛን የመሰለ ኢትዮጵያዊ እስኪገኝ ድረስ ተከፋፍለን ወያኔ የሚቀልድብን?

ናፖሊዮን ያቀረብኸውን የቪኦኤ ዘገባ ከማድመጤ በፊት ፣ የአስምሮም ና አብርሃ ደቦጭ የግራዚያኒ ግድያ ሙከራ ለ30 ሽ ህዝብ ርሸና ምክንያት ከመሆን አልፎ ፣ ለአርበኞች ቁርጠኝኘት ስለፈጠረው አስተዋጽዖ ያን ያህል ግንዛቤው አልነበረኝም። የኛስ ቁርጠኝኘትና ሌላውን ልዩነት አረጋግፎ ጥሎ አይናችን ወያኔ ላይ ብቻ እንዲተከል ስንት ሰው ማለቅ ይኖርበት ይሆን?... :?:

:(
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby AddisMeraf » Wed Feb 22, 2012 6:00 pm

የቀድሞ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አንጋፋውና አገር ወደዱ እምሩ ዘለቀ እግዚአብሔር እድሜ ሰጥቷቸው በ12 አመታቸው በአይናቸው ያዩትን አካፍለውናል:: ይህንን በማድረጋቸው በግሌ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው::


My Recollections

Imru Zelleke

Heroes are not calculators and speculators, they are made of pure spirit, they are people who give their life for a good cause, fully conscious of their mortality. Abraham Debotch and Moges Asgedom are pure authentic Ethiopian heroes who gave impetus and dignity to Ethiopian patriotism at its most critical hour. Their heroism sets an eternal symbol and a noble inspiration for all Ethiopian patriots, especially when our people suffer under the yoke of violent and ruthless dictatorships, and the national survival is at stake.

My personal recollections of those tragic days are somehow confused, I hope to be excused if memory fails me, and for not mentioning thousands of deeds that should be told and a plethora of people that should be remembered. The horror that happened after the attempt on Graziani’s life is an unforgettable incident and probably the most distressing life experience that has marked many of my generation and myself. After the attempt made on his life, Graziani gave free rein to all Italians, military and civilian alike, to kill, beat and arrest any Ethiopian at their whim. There ensued a terrible period of massacre and violence on the whole population. This episode of absolute terror lasted three days. Thousands died and were maimed by the Italians who were using guns, bayonets, knives even picks and shovels to prey on people, indiscriminate of age and gender. The Camice Nere (Black Shirts Fascists cadre), the Legione di Lavoro (Workers Legion) and the Polizzia Coloniale (Colonial Police) had a field day. Our house overlooked Menelik Square, from the second floor I could see many Italian military, civilians, and policemen killing and beating people who in panic were trying to take refuge in the Municipality. In my young mind what shook me to the core was the extreme and indiscriminate violence inflicted on peaceful people, which even today after witnessing the unfolding of so many dramas, I find difficult to rationalize. The massacre occurred all over the country, it is impossible to estimate how many people were killed, some say thirty thousand, I am sure there were more victims than that.

At the time our compound, in Arada, was occupied and had become the Headquarters of the Carabinieri. A day after the attempt on Graziani, my mother, my two sisters and I were arrested. I was twelve years old, my sisters Ketsela and Zena were nine and two years old arrested. . We were kept prisoners in the basement of a villa by our property. We passed a horrible and terrifying first night because there were some Italian prisoners that were being interrogated and were screaming in agony, (these Italian nationals were probably anti-fascists or criminals). The next day they brought us upstairs on the veranda and from there we were transferred to Akaki (Nefas Silk) where they had setup a large concentration camp. My half-brother Mesfin Zelleke was 22 years old, a civil engineer graduate from Lausanne University and the Ponts et Chausses (Bridges & Roads Faculty) of Montpellier University was also arrested and we met him in the camp. Hundreds of prisoners were brought there from all over Ethiopia. Many of them were country people and simple farmers, they did not know what was going on and why they were there. The camp was a sort of distribution center from where the prisoners were sifted and sent to various prisons and concentration camps.

We were crammed in large military tents with no facilities and sleeping on the ground with no cover. This was our initiation to the horrid realities that were to follow. Nothing exceptional happened in this camp but for one incident: an Italian sentinel bayoneted and killed a pregnant woman. The woman and her husband were peasants who had never been out of their village and did not understand why they were detained. The woman who wanted to relieve herself, went to the camp gate to ask for direction. It was very dark at night, when the sentinel saw this big fat woman accost him, he was so scared that he simply impaled her with his bayonet. Her husband, a fellow named Wolde Gabriel, went stark mad on the spot, became very violent and was put in chains. He was sent to Danane, where still chained, raving and screaming around the camp, he died after a few months.

We were kept in the Akaki camp for about a week, in the beginning of March 1937, they began sending the detainees to the various destinations where they would be jailed. Some groups were taken to Italy, a small number of intellectuals were sent to Nokra in the Dahlak Islands, the worst prison of all. The bulk of prisoners in Akaki went to the Danane concentration camp in Somalia, forty kilometers south of Mogadiscio. We were amongst this last group.

If I remember correctly the journey to Danane took about four weeks. There were hardly any roads but for tracks made by the army during the invasion. The prisoners were crammed in covered trucks without sides, there were no benches. The trucks were so crowded that no other position but sitting or standing was possible. Prisoners were allowed down from the trucks for a couple of short spells a day, to relieve themselves. Otherwise they had to stay in the trucks all the time. A small amount of food and water was given every day, mostly galletta (a hard piece of bread) and some tomato paste. When we arrived in Dire-Dawa, we camped outside the city. By then many people had become sick with malaria, diarrea and other ailments.

At Dire-Dawa a few people who had money on them, were allowed to go shopping under guard. The worst part of the journey was crossing the Ogaden past Jijiga. It was raining heavily and the grounds had simply become a mud pool. Whenever the trucks sank in the mud and could not move, all prisoners had to climb down and push them. The convoy could travel only a few kilometers a day. Even more people became sick of exhaustion and hunger. Some people died - as there was not time to bury them, the bodies were left by the road. The Somali askaris (colonial troops) that were guarding us were irascible and very cruel; they did not give any help to the prisoners. They would beat a prisoner for any excuse.

The Danane prison (was completely erased by the Italians when in the 1950’s they were administering Somalia under UN trusteeship) consisted of a very big compound surrounded by eight meters high walls, with guard towers. The compound was divided in four sections of which one contained the administration offices and the infirmary. The other three sections were for prisoners. Inside there were tukuls to house the prisoners. However, because of the large number of prisoners open sheds were also built around the walls, where a straw mat and a space of about eighty centimeters was allocated to each person. The walled camp was only for men, the women’s camp was outside in a separate area adjacent to the prison walls. The women’s compound consisted of some large military tents surrounded with barbed wire. Later on, when the number of prisoners increased they had to build yet more camps with tents and fences. Inside the camps relatives, friends and acquaintances tried to stay together in order to support each other.

There was no communication between the compounds. After a while they allowed married men to visit their wives on Sundays. There was no physical contact; they simply talked over the fence for the short time that was allowed. Because I was young I was allowed to go and visit my mother and my sisters. At one time I was so sick with malaria, they let me stay with my mother until I recovered. Outside the camps an isolated tent, called Lazaretto that served as a last resting place for those who were moribund and could not take care of themselves, They were simply left there to die. A young nurse and I were the only ones that went there to give them some water and food. Few lasted more than two or three days before they passed away.

I am not sure of the number, but I think there were, according Italian documents found in later years, some 6200 prisoners in Danane form which only 3000 survived. (** M. Dominioni, Study Piacentini 2004 photos) The first few months were terrible. Food consisted of boiled vegetables and gallettas that were already rotten and full of worms. Drinking water was drawn from wells dug in the vicinity of the sea, which made it salty. In the beginning there was no medical treatment, although later they assigned a doctor to the camp. People got sick with malaria, dysentery, scurvy, typhus, tropical sores and all sorts of diseases, caused by malnutrition and extremely bad living conditions. Several hundred died during the first few months, On the whole I think that more than one third of prisoners that were taken to Danane died there. Conditions in the main prisons were terrible because of the high walls surrounding it, there was not enough air circulation. The hot climate of the area made it suffocating and very unhealthy. There were only eight or ten holes in the latrines, you can imagine what it was like with hundreds of people suffering from diarrhea.

Every morning the adult males were taken out of the camp to gather wood and do some arduous work that the camp commandant had ordered. In the evening people prayed and cried ‘Igziyooo!,’ a group prayer chant. As I couldn’t do any heavy manual work because of my age, I was assigned to the infirmary where I helped cleaning and doing odd jobs. There, I saw more death and human agony than for the rest of my whole life. Otherwise there was not much to do; a lot of time was spent in reading the Bible and some religious literature that was available. Some of the educated took to teaching the young. Actually I learned Italian and many other subjects from them, especially from my brother. Chess and gebeta, played with rudimentary boards, were very popular games. Or else our time was taken up in arguments and speculations about our fate, religions, politics and history that led to endless discussions. There was no attempt to escape because the people in the surrounding areas were hostile. I heard later, though, that two men had escaped and made it home.

On Sundays we were allowed to go to the beach where we could wash ourselves and launder our meager clothing. Thank God, the climate was hot and whatever tattered cloths we had were enough to cover ourselves. Some people become skilled even at sewing some garments out of any rags they could find. Occasionally people were allowed to write home, they also received letters from their families. Spirits were generally high, there was always something to laugh or cry about, people had not lost hope they believed firmly that they would be free and that the Italian would go away someday. People helped each other in whatever way they could. There were no ethnic divisions, poor or rich, high or rank, everyone helped everyone. Compassion and generosity are indeed ingrained in the Ethiopian character; they are particularly manifest in such dire situations. Some of the people I remember are: Fitawrari Haile Zelleqa, Major Asfaw Ali, Major Bahru Kabba who died in prison, Ato Tewodros Mengasha, Yassu Mengasha (Lt. Gen) Tigre Makonnen Hailemariam, Ato Wolde Endeshaw, Ato Bekele Tessema, Ato Yassu (?), W/ro Tsige Mengasha, W/ro Atzede Wolde Amanuel, W/ro Shitaye Wolde Amanuel, Ato Bayou Wolde Giorgis, Ato Mokria Makonnen, Fitawrari Ambaw Gulilate, Fitawrari Wossene Awrariss , Ato Tekle Tsadik Mokria, and many others.

There are countless anecdotes about the Ethiopian moral fiber during the Italian occupation; some are funny others are sad. Here are two samples: one tragic-comic the other heroic: This story is about a remarkable man, it happened in Addis Ababa Tyit-bet (that was converted into a prison), where he was detained. His name was Dr. Alemework, he was a veterinarian graduate from the UK. The prison authorities had put him in charge of the infirmary. Not only did he not know anything about human ailments, he had no medicine to treat even a headache. His only real function was to register the dead in the prison ledger. So, on the column that said ‘cause of death’ he wrote in Italian ‘Morto per la Patria’ (Died for the Country). When this was discovered and he was interrogated his reply was that, since he didn’t know what caused their death, he it thought appropriate to register the real reason for which they were jailed. The Italians authorities were not amused, and they sent him to Nocra prison, where he stayed for five years. The other story is about a hero: His name was Captain Bezuayehu (later Dejazmatch). He was a member of the Imperial Guard. In Danane he use to tell us that as soon as he was freed, he was going to kill a few of the enemy and then join the resistance. Which he did.

Sometime in the fall of 1938 some three hundred of us were returned to Addis Ababa and freed. By that time Graziani, because of his excessive brutality and the spreading Ethiopian resistance, was replaced by the Duke of Aosta as Viceroy. The Italians had reversed to their former pacification policy and wanted to show clemency, which I suspect was the reason for our release. My brother was not freed; he was transferred to Nocra prison, in the Dahlak islands, were he stayed for another year. The remaining political prisoners were released from time to time, and all those who survived, some seven hundred out of about three thousand, returned home. We returned to Addis Ababa after another grueling journey across the Ogaden back to the camp in Akaky where we had departed from. A few days later came Cerulli, who was then Vice-Governor General, accompanied by Ras Hailu Tekle-Haimanot and Professor (Negadras) Afework, and told us that thanks to the clemency of the King, the Duce and everybody in the Fascist firmament we were pardoned for our crimes and set free.
AddisMeraf
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1615
Joined: Sun Nov 01, 2009 5:49 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Wed Feb 22, 2012 7:43 pm

ውይይቱ ጠቃሚ ነበር:: ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥናት ማዕከል እንዲኖር የቀረበው ሀሳብ ትክክል ነው:: ምክንያቱን በውጭ ሰዎች የተስፃፈው ባብዝኛው የራሳቸውን ፕሮፓጋንዳ ለማራገብ የተጠቀሙበት ስለነበር--- የጽንፈኛ ፖለቲካ ድርጂቶችም ሪፈረንስ የነበረውም እሱው ነው:: የኦነግ ሶቅራጥስ---አሰፋ ጃላታ ሳይቀር እንደ መጽሀፍ ቅዱስ የሚጠቀመው የነዚህን መርዘኛ ሰዎች ስራ ነው::

Basil Davidson የሚባለው ጋዜጠኛ ለምሳሌ ---በአፍሪካ የአርነት እንቅስቃሴዎች ቡዙ ነገሮችን የፅፈ ሲሆን ---በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጥላቻ ግን ይህ ነው የሚባል አልነበረም:: ከእንግዚዝ የማትለይ ቅኝ ገዥ ናት ብሎ በኤርትራም ላሉት ለሌሎቹም ያሽቃበጠ መርዛም እንግሊዝ ነው:: የራሳችን ---ከዚህ በፊት ኢትዮሴንትሪክ ቪው ብየ ያልኩት----የሚዳብርበት የኢንተሌክችዋል እንቅስቃሴ መታሰቡ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው:: ብዙ የሚጻፍ አለን::


አንድነቱን በተመለከተ ---እኔ ጸረ ህወሀት የሆነ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ጋር ህብረት መፍጠሩን በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ እጂግ በጣም የምደግፈው ነገር ነው:: ኢትዮጵያን ለዚህ እንድትደርስ የራሳቸው አስተዋጽኦ የነበራቸው ቡድኖች እና ከኢትዮጵያ ይልቅ ከሌሎች ድርጂቶች እና ሌላ ኮዝ ጠንከር ያለ ትስስር ያላቸው ሰወች ግን በእርግጥ ኢትዮጵያን ለመርዳት ነው የተነሱት ብሎ ለማመን እቸገራለሁ:: ምን ተጨባጭ ነግር ኖሮ ነው:: የኮምፕሮማይዙም ነገር ሳይገባኝ የቀረው በዚሁ ምክንያት ነው:: ለኢትዮጵያ ችግር ዋነኛው መፍትሄ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው....ወጣቱ ፈላስፋ ነን በሚሉ ልሂቃን መደናቆሩን ትቶ በህይወት ላይ ኮለል ያለ እይታ የተፈጠረ ለት እና ህወሀት ከዚህ በኍላ እጄን አይዝም አይገለኝም እገለዋለሁ...ገድየው እሞታለሁ የሚል ቁርጠኝነት ሲነሳ---ህወሀት ባንድ ጀምበር እንደሚጠፋ አልጠራጠርም! ያንን አስተሳሰብ መፍተር ነው ለኢትዮጵያ አስተማማኙ ነገር ብየ ነው የማምነው::


ናፖሊዮን ዳኘ::

ጥልቁ1 wrote:ይህ ወቅት ሲመጣ ፣ ከጥቁር አሜሪካውያን የታሪክ ወር ጋር እየተገጣጠመ ፣ ለአለፉት 7 አመታት በግለሰብ ደረጃ የምዘክርበት መድረክ ስላለኝ ፣ ለህሊናየ ታላቅ እረፍት ይሰጠኛል። ለሌሎች ኩሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የምመክረው ፣ ይህን ቀን በያላችሁበት ፣ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ትዘክሩት ዘንድ አስታውሳለሁ።

ለምን እንደሆነ አላቅም ፣ አሁን አሁን ግን ህሊናየን የሚያስጨንቀኝ እና መልስ የማላገኝለት ምስጢር ፣ እንዴት ያ ሁሉ መሰዋትነት የተከፈለባት አገር ፣ ተንገዋላ ተንገዋላ የኢጣሊያኖች አሸከር የነበሩት እና እነ አቡነጴጥሮስን በጥይት ደብድበው የገደሉት ባንዳዎች እጅ ላይ ልትወድቅ ቻለች? (ልብ በሉ ፣ እነአቡነ ጴጥሮስ እራሳቸውን ለመሰዋትነት ሲያቀርቡ ፣ ትግራይ ውስጥ ግን ለጣሊያኖች ታቦት ወጥቶ ያሬዳዊ ዜማ ይቀርባላቸው ነበር። ልክ በኛ ዘመን ፣ አባ ገብረምድህን ለቢዮንሴ እንዳደረጉት ማለት ነው።) እውነት እኛ ኢትዮጵያውያን እንዴት ከታሪክ ምንም ሳንማር ቀርተን ፣ ያችን አገር ለዘመናት ሲያደሟት የኖሯት ባንዳዎች እንዲፈነጩባት ፈቀድን? አዎን ፈቅደናል። (ያኔ ሲመጡስ ጊዜው አስገድዶን አረብ እና አሜሪካም ተመሳጥሮብን ይባል) ዛሬ ግን ብንፈቅድ አይደል በኢትዮጵያዊነት ስም ሁሉ ተደራጅተን ፣ ሁለመናው እኛን የመሰለ ኢትዮጵያዊ እስኪገኝ ድረስ ተከፋፍለን ወያኔ የሚቀልድብን?

ናፖሊዮን ያቀረብኸውን የቪኦኤ ዘገባ ከማድመጤ በፊት ፣ የአስምሮም ና አብርሃ ደቦጭ የግራዚያኒ ግድያ ሙከራ ለ30 ሽ ህዝብ ርሸና ምክንያት ከመሆን አልፎ ፣ ለአርበኞች ቁርጠኝኘት ስለፈጠረው አስተዋጽዖ ያን ያህል ግንዛቤው አልነበረኝም። የኛስ ቁርጠኝኘትና ሌላውን ልዩነት አረጋግፎ ጥሎ አይናችን ወያኔ ላይ ብቻ እንዲተከል ስንት ሰው ማለቅ ይኖርበት ይሆን?... :?:

:(
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Feb 22, 2012 10:54 pm

ጥልቁ1 wrote:...

ለምን እንደሆነ አላቅም ፣ አሁን አሁን ግን ህሊናየን የሚያስጨንቀኝ እና መልስ የማላገኝለት ምስጢር ፣ እንዴት ያ ሁሉ መሰዋትነት የተከፈለባት አገር ፣ ተንገዋላ ተንገዋላ የኢጣሊያኖች አሸከር የነበሩት እና እነ አቡነጴጥሮስን በጥይት ደብድበው የገደሉት ባንዳዎች እጅ ላይ ልትወድቅ ቻለች? (ልብ በሉ ፣ እነአቡነ ጴጥሮስ እራሳቸውን ለመሰዋትነት ሲያቀርቡ ፣ ትግራይ ውስጥ ግን ለጣሊያኖች ታቦት ወጥቶ ያሬዳዊ ዜማ ይቀርባላቸው ነበር። ልክ በኛ ዘመን ፣ አባ ገብረምድህን ለቢዮንሴ እንዳደረጉት ማለት ነው።) እውነት እኛ ኢትዮጵያውያን እንዴት ከታሪክ ምንም ሳንማር ቀርተን ፣ ያችን አገር ለዘመናት ሲያደሟት የኖሯት ባንዳዎች እንዲፈነጩባት ፈቀድን? አዎን ፈቅደናል። (ያኔ ሲመጡስ ጊዜው አስገድዶን አረብ እና አሜሪካም ተመሳጥሮብን ይባል) ዛሬ ግን ብንፈቅድ አይደል በኢትዮጵያዊነት ስም ሁሉ ተደራጅተን ፣ ሁለመናው እኛን የመሰለ ኢትዮጵያዊ እስኪገኝ ድረስ ተከፋፍለን ወያኔ የሚቀልድብን?

ጥልቁ:- ያነሣኸው ጥያቄ የአገራችንን የሕልውና መሠረት ዳግም እንድናጤን የሚያነቃ ጥያቄ ነው :: በእኔ አተያይ እንዴት 'ችግሩ ሊፈታ ይችላል?' ከሚል አቅጣጫ አስተያዬት ይኖረኛል ::

'AddisMeraf' :- የአምባሣደር እምሩ ዘለቀን የዐይን እማኝነት ያዘለ ጽሑፍ አቅርበህልናል : እናመሠግናለን:: እኔም ሩቅ ሣንሄድ በዚያው ጽሑፍ ውስጥ ባቀረቧቸው ተጨባጭ የምሥክርነት ቃሎች ተመርኩዤ የማቀርበው አስተያዬት ይኖረኛል ::

እመለሣለሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Feb 23, 2012 4:35 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

'AddisMeraf' የለጠፈልንን የአምባሣደር እምሩ ዘለቀን ጽሑፍ መነሻ በማድረግ የበኩሌን አተያይ ለማቅረብ እሞክራለሁ :: የእርሣቸው ጽሑፍ በዛ ያለ ሐተታ ያዘለ ሥለሆነ እንደ አስፈላጊነቱ በክፍል-በክፍል እየከፋፈልሁ አስተያዬቴን አቀርባለሁ ::

ክፍል 1:- የመነሻ ኃሣብ

ምንጭ:- Imru Zelleke, Posted on EthioReview, Wed Feb 22, 2012 12:19 pm. My collection of Fascist Italy's occupation of Ethiopia.


Heroes are not calculators and speculators, they are made of pure spirit, they are people who give their life for a good cause, fully conscious of their mortality.Abraham Debotch and Moges Asgedom are pure authentic Ethiopian heroes who gave impetus and dignity to Ethiopian patriotism at its most critical hour. Their heroism sets an eternal symbol and a noble inspiration for all Ethiopian patriots, especially when our people suffer under the yoke of violent and ruthless dictatorships, and the national survival is at stake.

የአንድን የኃሣብ ሙግት መነሻ በማገናዘብ ብቻ የሙግቱ መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል መሠረታዊ የሥነ-አመክንዮ ሕግ ያስተምረናል :: መነሻ ኃሣቡ 'ሥህተት' ከሆነ ምን በረቀቀ መንገድ በኃሣቡ ላይ ድጋፍ አድርጎ ቢሟገቱ በመጨረሻ የዚያን ኃሣብ ልዕልና ሊያቀዳጀው አይችልም :: መነሻ ኃሣቡ ትክክል ሆኖ ነገር ግን ለመደገፍ የተፈለገው ክስተት የዚያን ኃሣብ የሚቃረን ከሆነም እንዲሁ ከመነሻ ኃሣቡ ጋር ቅራኔ ይፈጥርና ባለኃሣቡን ከራሱ ትንታኔ ጋር ያላትመዋል :: ስለዚህ የአንድ የሙግት ጽሑፍ አቅራቢ ከመነሻ ኃሣቡ ጀምሮ ተራ በተራ የሚቀርቡት የማብራሪያ ትንታኔዎች እርስ በእርስ ሣይቃረኑ መዝለቃቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ::

ለአምባሣደር እምሩ ጽሑፍ መነሻው ኃሣብ በዚህ አንቀጽ የመጀመሪያው አረፍተ-ነገር ነው :: እንደእኔ ትርጓሜ :-

'ጀግኖች የአራጣ አበዳሪ ኅሊና ያላቸው ቁማርተኞች አይደሉም : ንፁህ መንፈስ ያላቸው : ሕይወታቸውን ለበጎ ዓላማ አሣልፈው ለመሥጠት ዝግጁ የሆኑና ሟች መሆናቸውን አምነው የተቀበሉ ሰዎች እንጂ ::'

ጥሩ የመነሻ ኃሣብ ነው :: ከዚህ አረፍተ ነገር በኋላ በአምባሣደር እምሩ ዘለቀ የቀረበልን ሐተታ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶምን ይህንን የጀግኖች መለያ የሆነውን ልዕልና እንዴት ሊቀዳጁ እንደሚገባ የሚተነትን ነው :: መጠየቅ ያለበት ጥያቄ :-
Code: Select all
በእርግጥ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ጀግኖች ነበሩ? አምባሣደር እምሩ ለጀግኖች ሚዛን አድርገው ያቀረቡትን ጣሪያ ነክተዋል? ወይስ በተቃራኒው እነርሱ ባቀጣጠሉት አመፅ ምክንያት በፋሽስት ጣሊያኖች ይጨፈጨፍ የነበረውን ሕዝብ ጥለው ሸሽተዋል?

በሚከተሉት ክፍሎች አብራራለሁ ::

ይቀጥላል ...

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Feb 23, 2012 6:13 am

ከአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ድርጊት በኋላ ፋሽስት ጣሊያኖች ምን አደረጉ?

አምባሣደር እምሩ ዘለቀ በዚያን ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ፋሽስት ጣሊያኖች የፈጸሙትን ድርጊት በልጅ አዕምሯቸው የቀረፁትን እንዲህ ይተርኩልናል :-
My personal recollections of those tragic days are somehow confused, I hope to be excused if memory fails me, and for not mentioning thousands of deeds that should be told and a plethora of people that should be remembered. The horror that happened after the attempt on Graziani’s life is an unforgettable incident and probably the most distressing life experience that has marked many of my generation and myself. After the attempt made on his life, Graziani gave free rein to all Italians, military and civilian alike, to kill, beat and arrest any Ethiopian at their whim. There ensued a terrible period of massacre and violence on the whole population. This episode of absolute terror lasted three days. Thousands died and were maimed by the Italians who were using guns, bayonets, knives even picks and shovels to prey on people, indiscriminate of age and gender. The Camice Nere (Black Shirts Fascists cadre), the Legione di Lavoro (Workers Legion) and the Polizzia Coloniale (Colonial Police) had a field day. Our house overlooked Menelik Square, from the second floor I could see many Italian military, civilians, and policemen killing and beating people who in panic were trying to take refuge in the Municipality. In my young mind what shook me to the core was the extreme and indiscriminate violence inflicted on peaceful people, which even today after witnessing the unfolding of so many dramas, I find difficult to rationalize. The massacre occurred all over the country, it is impossible to estimate how many people were killed, some say thirty thousand, I am sure there were more victims than that.

በአጭር አገላለጽ 'ፍፁም አሠቃቂ የሠቆቃ ቀናት ተከተሉ' ይሉናል ::

የድርጊቱ ፈጻሚዎችስ ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ የት ነበሩ ? ከዚያ በኋላ ምን አደረጉ ? ፕሮፌሠር ሪቻርድ ፓንክረስት በአንድ ወቅት ያቀረቡት ጽሑፍ የሚከተለውን ይላል :-
ምንጭ:- By Richard Pankhurst, Posted on Ethiopian Politics. The story of Abraha Deboch, Moges Asgedom and Simeon Adefres.

Abraha and Moges, as we all know, duly hurled their grenades, it is said from the Palace balcony. They then seized the opportunity of the general excitement following the explosions - to rush out of the compound.

They found Simeyon Adefres waiting for them as arranged. He then drove them northwards to Selale. Abraha had chosen this destination as his wife had found asylum at the ancient monastery of Debra Libanos.

Simeyon Adefres, his mission accomplished, remained a week in Selale after which he drove back to Addis Ababa, where he returned to his home, and remained there as if nothing had happened. His temporary disappearance was, however, reported to the Fascist police; as a result of he was arrested. His Opel and bank account were seized, and he tortured to death, thus entering the Pantheon of Ethiopia's martyrs.

አዲስ አበባን ጥለው ወደ ደብረ ሊባኖች ገዳም (ሰላሌ) ሸሹ :roll: :roll: :roll:
ምንጭ:- 'Mockler, Anthony,(1984 & 2003). Haile Selassie's war.' ገፅ 180::

ከዚያስ መጨረሻቸው ምን ሆነ ? ከኢትዮጵያ ግዛት ወደ ሱዳን ለመሸሽ ሲሉ ወሰን አካባቢ እንደተገደሉ ይነገራል ::
Fikre Tolossa, Posted on: Ethiobserver, Feb 22, 2012. Remembering our Forgotten Heroes.

እነርሱስ እሣት ጭረው ሸሹ :: ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን አጋጠመው ? በሚከተለው ክፍል እመለስበታለሁ ::

ይቀጥላል ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Feb 23, 2012 7:39 am

ክፍል 3: ከአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ድርጊት በኋላ ፋሽስት ጣሊያኖች በኢትዮጵያውያን ላይ ምን ዓይነት ድርጊቶች ፈፀሙ?

የመጀመሪያው ድርጊት 'የፋሽስት አገዛዝን ይቃወማሉ ተብለው የሚጠረጠሩትን ኢትዮጵያውያን' ማሠርና ማጋዝ እንዲህም መረሸን ነበር :: አምባሣደር እምሩ በግዞት ወደ ሶማሊያ ከተጋዙት ኢትዮጵያውያን መካከል ነበሩ :: ኢጣሊያኖች በተለይ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን እያደኑ ገድለዋል :: በእነ የእነ አብርሃ ደቦጭ ድርጊት አቀጣጣይነት የርሸና እርምጃ የተወሠደባቸው የተማሩ ኢትዮጵያውያን በወቅቱ አገሪቱ ካሏት ግማሽ ያህሉን ቁጥር እንደሚሸፍኑ ታሪካዊ ጥናቶች ያመለክታሉ :: በተጨማሪም ዋና ዋና የአገሪቱ የጦር መሪዎች (ለፋሽስት ኢጣሊያ ያመኑም ቢሆኑ) ከመገደልና ከመታሠር አላመለጡም ::

ምንጭ:- ፕሮፌሠር ባህሩ ዘውዴ '(Bahru Zewde, (1993).The Ethiopian Intelligentsia and the Italo-Ethiopian War, 1935-1941. The International Journal of African Historical Studies, Vol. 26, No. 2 (1993), pp. 271-295.)' በተለይ ገፆች 282-283: ይመልከቱ :
All those intellectuals whom the Italians could lay their hands on were rounded up and most of them were shot after perfunctory interrogations. These included many of the leaders of the Black Lion, sucha as Faqada-Sellase Benyam, Yosef, Kefle, and Belay.

Singled out as the mastermind of the whole plot was Bahshahwerad HabtaWald, who had earlier accompanied the Emperor into exile but had then returned and settled in Addis Ababa. According to one informant, the very fact of his return from exile was apparently one of the circumstances that made him a prime suspect in the eyes of the Italians. Given his proximity to the exiled Emperor, Bashahwerad's return to Ethiopia could only signify that he must have been entrusted with special mission. Second the Italians had discovered that he had double-crossed them by inserting a coded phrase (lagizew, "for the time being"), in a leaflet urging the people of Marhabete to submit, which the Italians had persuaded him to draft. Thirdly, the Italians had prior information, courtesy of the Emperor's private secretary, Qagnazmach Tekla-Marqos, who later defected to their side, that Bashawerad had been getting copies of Italian legation papers through an Eritrean agent before the war. At any rate, Bashahwerad was interrogated with particular severity, and he might well have died under torture.

The Graziani Massacre marked the almost total liquidation of the intellectual component of the Resistance.


ከዚያ በኋላ ከእሥርና ከርሸና የተረፉት ምሁራን ምን አቋም ያዙ?
1 ..... ሥደት አንዱ አማራጭ ነበር (ዮፍታሔ ንጉሤ : መኮንን ሀብተወልድ : ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ : ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ : ዶክተር መላኩ በያንን ይጠቅሷል )::
2 ..... ቀላል የማይባል ቁጥር የነበራቸው ምሁራን የፋሽስት ኢጣሊያ አገልጋይ ባንዶች ሆኑ :: አሁንም ከፕሮፌሠር ባህሩ ዘውዴ የጥናት ጽሑፍ ከገፅ284-285 የሚከተለውን እናገኛለን ::

Whether the Graziani Massacre contributed to an increase in the number of collaborators from among the intelligentsia is something that requires further investigation. While it is true that collaboration antedates the Massacre, it might very well be argued that some of the intellectuals might have been induced to collaborate by the ferocity of the Fascist repression following the Massacre. What is not subject to dispute is the fact that, as in the rest of Ethiopian society, there were collaborators just as there were ardent patriots among the intelligentsia. The defectors to the Fascist cause included such persons who had worked very closely with the emperor as his private secretary Qagnazmach Takla-Marqos Walda-Gabrel (promoted Dajjazmach and appointed "Ya Salale Abagaz" by the Italians). A prominent group that went over to the Fascist side was what has sometimes been referred to as the Catholic party, led by their mentor Blatten Geta Walda-Maryam, who had succeeded Takla-Hawaryaat as Ethiopian minister in Paris and chief of the Ethiopian delegation at the League of Nations in Geneva. The group included Berhana Marqos, Ethiopian charge d'affaires at Ankara on the outbreak of the war and already judged by Italian intelligence to be not too averse to the idea of an Italian protectorate; Blatta Ayyala Gabre, one-time president of the Special Court; and Balachaw Jamanah, director-general of Posts and Telecommunications.

Two intellectuals who put their considerable literary endowments to the service of Fascism were Blatta Walda-Giyorgis Walda-Yohannes and Afawarq Gabra-Iyyasus. As we have already seen, on the eve of the war, Walda-Giyorgis was one of those writing exhortative songs calling for the defense of the motherland. During the first two years of the Occupation, he is said to have remained in hiding. He then gave himself up and started to work for Fascist propagandain the weekly Ya Qesar Mangest Malektagna. But therew as no one who could rival Afawarq Gabra-Iyyasus for the dedication with which he served the Fascist cause and the virulence withwhich he attacked the Resistance.

On the outbreak of the war in October 1935, Afawarq had returned to Ethiopia from his diplomatic post in Rome. His return, his admirers emphasized, was incontrovertible evidence of his love for his country and it was contrasted with the defection at about the same time of Dajjazmach Hayla-Sellase Gugsa of eastern Tegray. In February 1936, apparently on instructions from the emperor, Afawarq was engaged in futile negotiations with the Italians for a peaceful resolution of the conflict. The terms proposed by Afawarq included Italian control over parts of Tegray and of the Ogaden, Borana, and Arsi, and appointment of six Italian advisers to the Ethiopian government to facilitate the exploitation of the country's economic resources. In return, the Italians were to recognize the emperor's sovereignty over the rest of Ethiopia, to cede Asab as a free port, and to pay Ethiopia 1.5 milliard lire. The two countries were then to sign a convention of mutual assistance in the event of aggression by a third party. But Mussolini found the terms unattractive, and the negotiations became altogether irrelevant after the decisive Italian victory at Maychaw.

Once the Italians entered Addis Ababa and established their rule, it does not seem to have taken Afawarq too long to decide to serve them. He turned the full power of his literary venom to ridicule the exiled emperor and to disparage the Resistance. He christened 5 May 1936, the day Italian troops entered Addis Ababa, the beginning of an Era of Mercy (Amata Mehrat)-comparable to the beginning of the Christian era on 1 A.D. He abused the guerrilla fighters as wild worms (ya dur teloch) and had only contempt for their bid to upset the Fascist order

ይህ ሁኔታ የአርበኝነት ትግሉን ምን ያህል ሊያወሣስበው እንደቻለ መገንዘብ አያዳግትም :: ከዚያም አልፎ ፋሽስቶች በኢትዮጵያ አርበኞች ተጋድሎ ተሸንፈው ከተባረሩ በኋላ ማን የድል አጥቢያ አርበኛ ሆኖ የአርበኞችን ትግል እንደነጠቀ ማስታወስ ይገባል :: አገሪቱ ከዚያ በኋላም ልታፈራ የቻለቸው የተማረ ኃይል ውጭ-ውጭ የሚናፍቅ ጥገኛ : ብሔራዊ ስሜት የሌለው ወይም እንደ እነ አፈወርቅ ገብረየሱስ የለየለት ባንዳ ሆነ :: ለምሣሌ ያህል በአሁኑ የወያኔ አገዛዝ ያለውን ሁኔታ ከላይ ከቀረበው የፕሮፌሠር ባህሩ የፋሽስት ጣሊያን አገዛዝ ዘመን ታሪካዊ ትንታኔ ጋር ሥናነፃፅረው ምን እንገነዘባለን ?

ኃሣቦቼን አሠባስቤ በማጠቃለያው ክፍል እመለሣለሁ ::

ይቀጥላል ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እንድሪያስ » Thu Feb 23, 2012 3:47 pm

አለቃ ተድላ :- የታሪክ ምሁራንና ተመራማሪዎች ሰፊ ጥናትና ምርምር አድርገው ያልደረሱበት ምስጢር ለአንተ በቀላሉ ኢንተርኔት ውስጥ ተከሰተልህ ማለት ነው ቅቅቅቅቅቅቅቅ እድሜና ጤና ይስጥህ እንጂ አንተ ገና ብዙ ታዕምር ትሰራለህ ::ወይ መዳህኒዓለም !!
ተድላ ..... አንተ'ኮ ሌትም ቀንም ከኢንተርኔት የማትወጣና ከእሱ ሌላ አለምና ህይወት መኖሩን የዘነጋህ የማህበራዊ ድረገጽ ሱሰኛ ነህ :: ኢንተርኔት ውስጥ ተዘፍቆ የሚኖር ሰው ደግሞ የማመዛዘን ብቃቱ እንደሚቆረቁዝ የታወቀ ነው:: ለዚህም ነው እራስህን ከልክ በላይ ከፍ አድርገህና ለራስህ ትልቅ ግምት ሰጥተህ የምትኖር የኢንተርኔት ዜጋ የሆንከው :: በነገራችን ላይ እርግጠኛ ባልሆንም የምትኖርበት አገር ስዊድን እንደሚሆን መገመት እችላለሁ :: ስዊድን ማለት ጥሮ ግሮ እራስን የመለወጥ አላማ የሌላቸው.....ምቹና አስተማማኝ የሆነ የሶሻል ዌልፌር ፕሮግራሟን አልመው የሚመጡ ስደተኞች መኖርያ ነች :: ተምሬ ጥሩ ሙያ ላይ ከተሰማራሁ በኋላ ከራሴ አልፌ ለወገን መከታና አለኝታ እሆናለሁ የሚል ተስፋ ሰንቆ ወደ ስዊድን የሚገባ የትህርት እድልም ሆነ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ ሳያገኝ መንግስት ቀለብ እየሰፈረለት ብቻ የሚኖረውም ቀላል አይደለም :: ታድያ ሁሉም ማለት ይቻላል ኢንተርኔት ውስጥ ውሎ ኢንተኔት ውስጥ የሚያድርና በማህበራዊ ድረ ገጾች ሱስ የተለከፈ ነው ::
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1810
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Postby ኤዶም* » Thu Feb 23, 2012 5:28 pm

ሰላም ተድላ ሀይሉ

እኔ ካንተ ለየት ያለ ሀሳብ አለኝ:: አብርሀ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም በ የካቲት 12 ቀን በፋሽስቱ አውራ ግራዝያኒ ላይ የመግደል ሙከራ አደረጉ.................ያሰቡት ግድያ ለጥቂት ከሸፈባቸው............ምንም እንኳን ድርጊቱ 'አጥፍቶ መጥፋት' አይነት ቢሆንም ግድያው መክሸፉን ሲረዱ ባገኙት አጋጣሚ ተጠቅመው በትግል አጋራቸው በስምኦን አደፍርስ ተባባሪነት ከሞት ለማምለጥ መቻላቸው ፈሪዎች አያደርጋቸውም::

የመግደል ሙከራው ተደርጎ ከከሸፈ በህዋላ እጅ ከፍንጅ ተይዞ እንደ በግ ከመታረድ በተገኘው ቀዳዳ ተጠቅሞ ማምለጡ ማንም ራሽናል ማይንድ ያለው ሰው የሚያደርገው ነው:: ከዚህ በህዋላ ግራዝያኒ በወሰደው ፍፁም አረመኔያዊ በሆነ እርምጃ የብዙ ሺዎች ህይወት መቀጠፉ አይካድም:: አምባሳደር እምሩ ዘለቀን ጨምሮ ብዙዎችን ለእስርና ለግዞት ዳርጓቸዋል::

በተለያዩ የታሪክ መፃህፍት እንዳነበብኩት የየካቲት 12 እልቂት የአርበኞችን ትግል ከመቸውም ጊዜ ይበልጥ አፋፋመው እንጂ አላቀዘቀዘውም.......ቤት ንብረታቸው አይናቸው እያየ የተቃጠለባቸው ሚስቶቻቸው ና ልጆቻቸው ህፃናትና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ሲጨፈጨፉ ያዩ ያገራችን ሰዎች ዱር ቤቴ ብለው በገፍ አርበኞችን መቀላቀል የጀመሩት ከዚህ ቀን በህዋላ ነው::

አርበኞች በየካቲት 12 እልቂት ምክንያት አልተንበረከኩም...ትግሩ አልተዳፈነም...ይልቁንም እጅግ እየተፋፋመ ነው የሄደው......የአብርሀና የሞገስ ድርጊት ባስከተለው መዘዝ ብዙዎች ቢያልቁም........እልፍ አእላፍ አርበኞችንም ወልዷል........

አብርሀና ሞገስ የበኩላቸውን ሞክረዋል....መፅሀፉም እንደሚለው....ደም ሳይፈስ ስርየት የለም.........ያለምንም ደም ግራዝያኒን ማስወገድ እንዴት እንደሚቻል አላውቅም..........በነሱ መዘዝ ሰው ስላለቀ መሞከር አልነበረባቸውም የሚለው ሙግት የትም አያደርስም............ደም እንዳይፈስ ከተፈለገ ግራዝያኒን እሽሩሩ እያሉ መኖር ነበረባቸው........ኢትዮጵያውያን ግራዝያኒን ባንቀልባ አዝለው እሽሩሩ የሚሉ ቢሆኑና እንደ ነ አብርሀና ሞገስ አይነቶች ግራዝያኒን እንቅልፍ የሚነሱ አርበኞች ባይኖሩ ኖሮ የአርበኞች ትግል በእንቅጭጩ ተቀጭቶ የጣልያን እድሜ ረጅም በሆነ ነበር

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም እንዲሉ.....ገና ለገና ጣልያን ይበቀለኛል በሚል ስጋት አርበኛው ሁሉ ከቤቱ ዱር ቤቴ ብሎ መውጣቱን አልተውም..............አንድ አርበኛ ቤቱን ጥሎ ወደ ጫካ መግባቱ ሲታወቅኮ ጣልያኖች ያርበኛውን ዘመዶች በሙሉ አንዳንዴም መንደሩን ሁሉ ያቃጥሉና ይዘርፉ ነበር...........አርበኞችን ለመቅጣት ያርበኞቹን ዘመድ አዝማድ ሁሉ ያስሩና ይገድሉ ነበርኮ...ዘመዶቻችሁ ካርበኞች ጋ ተቀላቅለዋል እየተባሉ በየመንደሩ የተገደሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው ......እናም ባንተ አመለካከት በመሸፈቱ ምክንያት ዘመዱና ጎረቤቶቹ የተገደሉበት አርበኛ ሁሉ ለሞታቸው ምክንያት ሆኗልና ከነአብርሀና ሞገስ ጋር እኩል መወገዝ አለበት ማለት ነው

ለመሆኑ ንጉሱ በማይጨው ላይ እስካፍንጫው ድረስ በዘመናዊ መሳርያ ታጥቆና ተደራጅቶ የመጣውን ሊቋቋሙት ፈፅሞ የማይቻላቸውን ሀይል እንደ ድፍረት በሚቆጠር ፈፅሞ በማይመጣጠን መልኩ ባብዛኛው ጎራዴና አንካሴ በያዘ ወዶ ዘማች ሰራዊታቸው መዋጋታቸውን እንዴት ታየዋለህ........ጣልያን የመርዝ ጭስ ተጠቅሞ የካቲት 12 ቀን ካለቀው ሰው ይበልጥ በየገደላ ገደሉ ባውሮፕላን እየተከታተለ የፈጀው ሰው ቁጥርኮ የትየለሌ ነው.......................

እነ አብርሀና ሞገስ አቅማቸውን አውቀው አርፈው መቀመጥ ከነበረባቸው ንጉሱም ማይጨው ላይ ጣልያንን መሞከር አልነበረባቸውም ማለት ነው.........ሌላም በዘመናችን ባይናችን ያየነውን ምሳሌ ልስጥህ........በ 2005 ኢሀዴግ ባደረገው ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ግርግር የብዙዎች ህይወት ጠፍቷል.......ብዙዎች ለእስርና ለግዞት እንዲሁም ለስደት በቅተዋል.....የብዙዎች ቤት ፈርሷል.....የብዙዎች ህይወት እንዳይመለስ ለዘላለም ተቀይሯል..........ይህ ሁሉ የሆነው ቅንጅት የተባለው ድርጅት ኢህአዲግን አለአቅሙ ነካክቶ በማቁሰሉ ነው................ይህንን የብዙዎችን ህይወት የበላ ለውጥ የመሩ የቅንጅት መሪዎችም ተሰደው አሜሪካና አውሮፓ ተቀምጠዋል...........በናንተ ምክንያት የሰው ህይወት ስለጠፋ መወገዝ አለባችሁ ሊባሉ ቀርቶ እንደ ጀግና ተቀጥረው ስማቸው ሲወደስ እንሰማለን

እነ አብርሀና ሞገስ ግራዝያኒን አቁስለውለጊዜው ለመሰውር ቢችሉም ተይዘው አገራቸው ውስጥ በግራዝያኒ ተገደሉ......እነሱ የለኮሱት ችቦ ተቀጣጥሎ ከየካቲ 12 በህዋላ አርበኞች በሰው ሀይልና በሞራል ተጠናክረው በጣት በሚቆጠሩ አመታት ውስጥ ግራዝያኒን ካገራቸው አባረሩ............

የቅንጅት መሪዎች ኢህአዲግን አቁስለው የብዙዎችን ህይወት አስጨርሰው......ወደ አሜሪካ ፈረጠጡ...ከዚህ ሁሉ መስዋእትነት በህዋላ....ይከው ካመታት በህዋላ እንክዋን ኢትዮጵያን ነፃ ሊያወጡ ይቅርና......ራሳቸውም እንደ አሜባ አርባ ቦታ ተራብተው እርስ በርሳቸው ይባላሉ..........ከብዙ አመታት በፊት መስዋእትነት ከፍለው ያለፉትን እውነተኛ ጀግኖች ስም ከማጥፋት ለምን ያሁኖቹን ማፈርያዎች..በቃችሁ ልንላቸው እንደማንደፍር ግርም ይለኛል

ማንም የፈለገውን ቢል አብርሀ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም እውነተኛ ጀግኖች ናቸው
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Feb 23, 2012 5:55 pm

ሰላም ኤዶም*:-

ዋርካ መጽዳቷን አልሰማህ ይሆናል ብዬ ልጠራህ ሳመነታ ብቅ አልክ: :lol:

አብርሃንና ሞገስን በሚመለከት ተድላን በተቃወምክበት ጉዳይ ብስማማም ንፅፅሩ ግን ላይ ግን በጭራሽ አልስማማም::

ኤዶም* እንደጻፈው:-

.........ሌላም በዘመናችን ባይናችን ያየነውን ምሳሌ ልስጥህ ........በ 2005 ኢሀዴግ ባደረገው ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ግርግር የብዙዎች ህይወት ጠፍቷል .......ብዙዎች ለእስርና ለግዞት እንዲሁም ለስደት በቅተዋል .....የብዙዎች ቤት ፈርሷል .....የብዙዎች ህይወት እንዳይመለስ ለዘላለም ተቀይሯል ..........ይህ ሁሉ የሆነው ቅንጅት የተባለው ድርጅት ኢህአዲግን አለአቅሙ ነካክቶ በማቁሰሉ ነው ................ይህንን የብዙዎችን ህይወት የበላ ለውጥ የመሩ የቅንጅት መሪዎችም ተሰደው አሜሪካና አውሮፓ ተቀምጠዋል ...........በናንተ ምክንያት የሰው ህይወት ስለጠፋ መወገዝ አለባችሁ ሊባሉ ቀርቶ እንደ ጀግና ተቀጥረው ስማቸው ሲወደስ እንሰማለን
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1219
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዲጎኔ » Thu Feb 23, 2012 6:02 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ለዚያች ሀገር ህዝቦች ነጻነት የታገሉ ሁሉ ሊወደሱ ይገባል::የገባሩ ስርአት ከኢትዮጲያ እንዲወገድ እኒያ ድንቅ መምህራን ተክሲ ሾፈሮችና ተማሪዎች ትግሉን የጀመሩት የካቲት 11 ቀን 1966 ስለሆነ አብረው ይታሰቡ::
ፋሽስቱ ግራዚያኒን ለማስወገድ ትልቅ ርምጃ የፈጸሙ እኒያ ጀግኖች የካቲት 12 እልቂት በፋሽስት ጣልያን ስለተፈጸመ ሙከራቸው ሊናቅ አይገባም::
ሂትለርን ለማስወገድ የተሳተፈና በሂትለር የተሰቀለ ፓስተር ቦንሆፍን ድርጊት አልቀበል ያልኩትን ዶ/ር ተኮላ ጥናታዊ ጽሁፍ ወዲህ ተቀብያለሁ::ሚሊዮኖች ከሚያልቁ አንድን አምባገነን ፋሽስት ማስወገድ ይመረጣል::
በተረፈ ታሪኩን በኢንተርኔት በመግለጽ ብቻ ሳንወሰን በያለንበት የህዝቦች አርነት ስብሰባዎችን እንካፈል::ወገን ጥልቁ እንዳመላከተው እኔም ባለሁበት ከተማ በየአመቱ ፌብርዋሪ የጥቁሮች ትግል ታሪክ ተሳትፌያለሁ::ጣልያን ሀገራችንን በወረረ ጊዜ በጥቂት ቀናት ሺዎች ጥቁር አሜሪካኖች ሊዋጉልን ተመዝገብው በሎጅስቲክ ሰበብ ቢከለከሉም ጥረቱ የድንቁ አክቲቪስት ዶ/ር መላኩ በያን መሆኑ ይሰመርበት::የወያኔን ግፍ መቃወም ሰልፍ መውጣት ወገቤን የሚሉ ሀገር ቤት እንዳልገባ ወያኔ ይጠምደኛል እያሉ የሚሞዳሞዱ ሁሉ ዋርካ ላይ ምን ቢሉ እውነቱን ፈጣሪ ያውቃል::ዛሬም ኒኦኮሎኒያሊስቶችና KKK በክፉ ቢጽፉ ወያኔና ጀሌዎቹ በካሜራ ቢከታተሉን አንዳች ሳይገድበን ለህዝቦች መብት በትግሉ መሳተፉን መጮሁን መሰብሰቡን እንቀጥላለን::
ዲጎኔ ሞረቴ ለገባርቹ ከተሰዉት ጀግኖች ጥላሁን ግዛው ማርታ መብራቱና ዋለልኝ መኮንን ክበብ አፍንጮ በር

ኤዶም* wrote:ሰላም ተድላ ሀይሉ
እኔ ካንተ ለየት ያለ ሀሳብ አለኝ:: አብርሀ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም በ የካቲት 12 ቀን በፋሽስቱ አውራ ግራዝያኒ ላይ የመግደል ሙከራ አደረጉ.................ያሰቡት ግድያ ለጥቂት ከሸፈባቸው............ምንም እንኳን ድርጊቱ 'አጥፍቶ መጥፋት' አይነት ቢሆንም ግድያው መክሸፉን ሲረዱ ባገኙት አጋጣሚ ተጠቅመው በትግል አጋራቸው በስምኦን አደፍርስ ተባባሪነት ከሞት ለማምለጥ መቻላቸው ፈሪዎች አያደርጋቸውም::

የመግደል ሙከራው ተደርጎ ከከሸፈ በህዋላ እጅ ከፍንጅ ተይዞ እንደ በግ ከመታረድ በተገኘው ቀዳዳ ተጠቅሞ ማምለጡ ማንም ራሽናል ማይንድ ያለው ሰው የሚያደርገው ነው:: ከዚህ በህዋላ ግራዝያኒ በወሰደው ፍፁም አረመኔያዊ በሆነ እርምጃ የብዙ ሺዎች ህይወት መቀጠፉ አይካድም:: አምባሳደር እምሩ ዘለቀን ጨምሮ ብዙዎችን ለእስርና ለግዞት ዳርጓቸዋል::

በተለያዩ የታሪክ መፃህፍት እንዳነበብኩት የየካቲት 12 እልቂት የአርበኞችን ትግል ከመቸውም ጊዜ ይበልጥ አፋፋመው እንጂ አላቀዘቀዘውም.......ቤት ንብረታቸው አይናቸው እያየ የተቃጠለባቸው ሚስቶቻቸው ና ልጆቻቸው ህፃናትና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ሲጨፈጨፉ ያዩ ያገራችን ሰዎች ዱር ቤቴ ብለው በገፍ አርበኞችን መቀላቀል የጀመሩት ከዚህ ቀን በህዋላ ነው::

አርበኞች በየካቲት 12 እልቂት ምክንያት አልተንበረከኩም...ትግሩ አልተዳፈነም...ይልቁንም እጅግ እየተፋፋመ ነው የሄደው......የአብርሀና የሞገስ ድርጊት ባስከተለው መዘዝ ብዙዎች ቢያልቁም........እልፍ አእላፍ አርበኞችንም ወልዷል........

አብርሀና ሞገስ የበኩላቸውን ሞክረዋል....መፅሀፉም እንደሚለው....ደም ሳይፈስ ስርየት የለም.........ያለምንም ደም ግራዝያኒን ማስወገድ እንዴት እንደሚቻል አላውቅም..........በነሱ መዘዝ ሰው ስላለቀ መሞከር አልነበረባቸውም የሚለው ሙግት የትም አያደርስም............ደም እንዳይፈስ ከተፈለገ ግራዝያኒን እሽሩሩ እያሉ መኖር ነበረባቸው........ኢትዮጵያውያን ግራዝያኒን ባንቀልባ አዝለው እሽሩሩ የሚሉ ቢሆኑና እንደ ነ አብርሀና ሞገስ አይነቶች ግራዝያኒን እንቅልፍ የሚነሱ አርበኞች ባይኖሩ ኖሮ የአርበኞች ትግል በእንቅጭጩ ተቀጭቶ የጣልያን እድሜ ረጅም በሆነ ነበር

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም እንዲሉ.....ገና ለገና ጣልያን ይበቀለኛል በሚል ስጋት አርበኛው ሁሉ ከቤቱ ዱር ቤቴ ብሎ መውጣቱን አልተውም..............አንድ አርበኛ ቤቱን ጥሎ ወደ ጫካ መግባቱ ሲታወቅኮ ጣልያኖች ያርበኛውን ዘመዶች በሙሉ አንዳንዴም መንደሩን ሁሉ ያቃጥሉና ይዘርፉ ነበር...........አርበኞችን ለመቅጣት ያርበኞቹን ዘመድ አዝማድ ሁሉ ያስሩና ይገድሉ ነበርኮ...ዘመዶቻችሁ ካርበኞች ጋ ተቀላቅለዋል እየተባሉ በየመንደሩ የተገደሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው ......እናም ባንተ አመለካከት በመሸፈቱ ምክንያት ዘመዱና ጎረቤቶቹ የተገደሉበት አርበኛ ሁሉ ለሞታቸው ምክንያት ሆኗልና ከነአብርሀና ሞገስ ጋር እኩል መወገዝ አለበት ማለት ነው

ለመሆኑ ንጉሱ በማይጨው ላይ እስካፍንጫው ድረስ በዘመናዊ መሳርያ ታጥቆና ተደራጅቶ የመጣውን ሊቋቋሙት ፈፅሞ የማይቻላቸውን ሀይል እንደ ድፍረት በሚቆጠር ፈፅሞ በማይመጣጠን መልኩ ባብዛኛው ጎራዴና አንካሴ በያዘ ወዶ ዘማች ሰራዊታቸው መዋጋታቸውን እንዴት ታየዋለህ........ጣልያን የመርዝ ጭስ ተጠቅሞ የካቲት 12 ቀን ካለቀው ሰው ይበልጥ በየገደላ ገደሉ ባውሮፕላን እየተከታተለ የፈጀው ሰው ቁጥርኮ የትየለሌ ነው.......................

እነ አብርሀና ሞገስ አቅማቸውን አውቀው አርፈው መቀመጥ ከነበረባቸው ንጉሱም ማይጨው ላይ ጣልያንን መሞከር አልነበረባቸውም ማለት ነው.........ሌላም በዘመናችን ባይናችን ያየነውን ምሳሌ ልስጥህ........በ 2005 ኢሀዴግ ባደረገው ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ግርግር የብዙዎች ህይወት ጠፍቷል.......ብዙዎች ለእስርና ለግዞት እንዲሁም ለስደት በቅተዋል.....የብዙዎች ቤት ፈርሷል.....የብዙዎች ህይወት እንዳይመለስ ለዘላለም ተቀይሯል..........ይህ ሁሉ የሆነው ቅንጅት የተባለው ድርጅት ኢህአዲግን አለአቅሙ ነካክቶ በማቁሰሉ ነው................ይህንን የብዙዎችን ህይወት የበላ ለውጥ የመሩ የቅንጅት መሪዎችም ተሰደው አሜሪካና አውሮፓ ተቀምጠዋል...........በናንተ ምክንያት የሰው ህይወት ስለጠፋ መወገዝ አለባችሁ ሊባሉ ቀርቶ እንደ ጀግና ተቀጥረው ስማቸው ሲወደስ እንሰማለን

እነ አብርሀና ሞገስ ግራዝያኒን አቁስለውለጊዜው ለመሰውር ቢችሉም ተይዘው አገራቸው ውስጥ በግራዝያኒ ተገደሉ......እነሱ የለኮሱት ችቦ ተቀጣጥሎ ከየካቲ 12 በህዋላ አርበኞች በሰው ሀይልና በሞራል ተጠናክረው በጣት በሚቆጠሩ አመታት ውስጥ ግራዝያኒን ካገራቸው አባረሩ............

የቅንጅት መሪዎች ኢህአዲግን አቁስለው የብዙዎችን ህይወት አስጨርሰው......ወደ አሜሪካ ፈረጠጡ...ከዚህ ሁሉ መስዋእትነት በህዋላ....ይከው ካመታት በህዋላ እንክዋን ኢትዮጵያን ነፃ ሊያወጡ ይቅርና......ራሳቸውም እንደ አሜባ አርባ ቦታ ተራብተው እርስ በርሳቸው ይባላሉ..........ከብዙ አመታት በፊት መስዋእትነት ከፍለው ያለፉትን እውነተኛ ጀግኖች ስም ከማጥፋት ለምን ያሁኖቹን ማፈርያዎች..በቃችሁ ልንላቸው እንደማንደፍር ግርም ይለኛል

ማንም የፈለገውን ቢል አብርሀ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም እውነተኛ ጀግኖች ናቸው
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ሓየት11 » Thu Feb 23, 2012 6:41 pm

ተድላ ሀይሉና "ቦቢዎቹ" በነ መለስ መንገድ እየተከተሉ ታሪክን ለራሳቸው በሚጥም መልኩ በራሳቸው መንገድ መጻፍን ነው የተያያዙት:: በእነ መለስ መንገድ ቢከተሉም, ፍላጎታችው ቢመሳሰልም መድረሻቸው የሚቃኘው ግን በዘራቸው ነው:: በሌላ ግልጽና አጭር አነጋገር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድም ትግርኛ ተናጋሪ በበጎ እንዳይነሳ ነው ጥረታቸው :idea: በቀል የወለደው እንጭጭ ጭንቅላት ማለት ይህ ነው:: አንዱ ወያኔ ተነስቶ የምኒሊክን ስም ካጎደፈ አማራ ነኝ ባዩ ይነሳና የካሳ ምርጫን ስም ያከስለዋል :lol: ስብሓትን ስናደንቅ ማድነቅስ ሎሬት ጸጋዬን ይሉናል :lol: አሁን ደግሞ የአርበኝነት ጥንስስ ጣዮችን እያጎደፉ ይገኛሉ:: አንድ ሀቅ ልንገራችሁ:: የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታ ለኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች የሚመጥን አይደለም:: ጊዜውና ሁኔታው ቀድሞን ሄዷል:: እኛ ያለነው በ19ኛው ክፍለዘመን ቼርኬ እየተነዳን ነው (እኛ ስል በኢትዮጵያዊነቴ አይቼው እንጂ በግሌ ገና ካልተወለዱት ከቆንጆዎቹ እንደሆንኩ ነው የማምነው :lol: ) :: መፍትሄው ሽማግሎችን ጥግ በማስያዝ ይጀምራል:: በበቀል እየተነዱ ያውም እንደ ሰገራቸው በሚጸየፉት ድርጅት መንገድ እየተከተሉ ታሪክን የሚያቆሸሹ አተላዎች ወግዱ ሊባሉ ይገባል:: ወይም ደግሞ ለማበላሸቱም የራሳችሁ የሆነ ኖቤል መንገድ ፍጠሩና የፈጠራ ብቃታችሁን መዝነን ተስፋ እንጣልባችሁ :lol: አንድ ቀን የፈጠራ ችሎታችሁን ለበጎ ነገር ታውሉት ይሆናል የሚል ተስፋ :roll:

@ ለዘርዐይ
ለምን እንደማትስማማ ጭምር ጫር ብታደርግልን?

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ኤዶም*:-

ዋርካ መጽዳቷን አልሰማህ ይሆናል ብዬ ልጠራህ ሳመነታ ብቅ አልክ: :lol:

አብርሃንና ሞገስን በሚመለከት ተድላን በተቃወምክበት ጉዳይ ብስማማም ንፅፅሩ ግን ላይ ግን በጭራሽ አልስማማም::

ኤዶም* እንደጻፈው:-

.........ሌላም በዘመናችን ባይናችን ያየነውን ምሳሌ ልስጥህ ........በ 2005 ኢሀዴግ ባደረገው ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ግርግር የብዙዎች ህይወት ጠፍቷል .......ብዙዎች ለእስርና ለግዞት እንዲሁም ለስደት በቅተዋል .....የብዙዎች ቤት ፈርሷል .....የብዙዎች ህይወት እንዳይመለስ ለዘላለም ተቀይሯል ..........ይህ ሁሉ የሆነው ቅንጅት የተባለው ድርጅት ኢህአዲግን አለአቅሙ ነካክቶ በማቁሰሉ ነው ................ይህንን የብዙዎችን ህይወት የበላ ለውጥ የመሩ የቅንጅት መሪዎችም ተሰደው አሜሪካና አውሮፓ ተቀምጠዋል ...........በናንተ ምክንያት የሰው ህይወት ስለጠፋ መወገዝ አለባችሁ ሊባሉ ቀርቶ እንደ ጀግና ተቀጥረው ስማቸው ሲወደስ እንሰማለን
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests