የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ኤዶም* » Thu Feb 23, 2012 7:03 pm

ሰላም ዘርዐይ ደረስ

ዋርካ መፅዳቷን አለመፅዳቷን በቅርብ እየተከታተልኩ ነበር ..ርቄ አልሄድኩም ነበር :lol: .....የቅንጅት መሪዎችን በ2005 ለሆነው ነገር ሙሉ በሙሉ አልከሳቸውም.........ህዝቡን በመቀስቀስ የነበራቸው ሚና ግን አይካድም......ይህ ሚና እንግዲህ ....."በጎም" "መጥፎም" ሊሆን ይችላል.......ነገሮችን የምናይባቸው መንገዶች እንደአመለካከታችን ሊለያይ ይችላል

ከትሬዱ አላማ ውጭ በንፅፅር ያስቀመጥኩት ወድጄ አደለም........አብርሀና ሞገስ በግራዝያኒ ላይ የመግደል እርምጃ ባያደርጉ ኖሮ ህዝብ አያልቅም ነበር .....እነሱ የለኮሱት እሳት እንዳይሞቃቸው ሲፈረጥጡ

1. የ አዲስ አበባ ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፈጨፈ
2. ምሁራን ከአገር ወጥተው ተሰደዱ
3. አንዳንዶችም ባንዶች ሆኑ

የሚል ድምዳሜ ተድላ ሀይሉ ፅፎ ሳነብ....ምንም እንክዋን ከየካቲት 12 በህዋላ በነ አብርሀም ና ሞገስ የተለኮሰው እሳት ተቀጣጥሎ የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ቢበላም የነግራዝያኒን እድሜ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀጥፎታል


ወደ ንፅፅሩ ስመጣ በ2005 ምርጫ ግርግር ኢህአዲግን ባልጠበቀው መልኩ ያቆሰሉት የቅንጅት መሪዎች.......ነገሩ በጠበቁት መልኩ ሳይጠናቀቅ ሲቀር......ለሁለት አመታት ቃሊቲ ከከረሙ በህዋላ...እስካሁን ድረስ የሚያነጋግረውን አሳፋሪ 'የይቅርታ ደብዳቤ' ፅፈው ካገር ተሸበለሉ...በዚሁ ጦስ ደግሞ

1. የብዙ ሰዎች ህይወት ጠፋ
2. ብዙዎች ለእስርና ስደት ተዳረጉ
3. እነ ልደቱ እና ሰለሞን ተካልኝ አይነቶች ደግሞ ለኢሀዲግ አደሩ

የህዝቡ የትግል ስሜት ተዳፈነ....... ይከው አሁን ከ 7 አመታት በህዋላ ኢሀዴግ ሊወድቅ ቀርቶ ጭራሽ ተጠናክሮ ወጣ.......

ከየካቲት 12 በህዋላ የአርበኞች ስሜት ተቀጣጥሎ በአምስት አመት ውስጥ ነጻነትን ሲወልድ .......ከ2005 ቱ የለውጥ ማዕበል ...ከ 7 በህዋላ የተቃዋሚዎች መዳከምና መከፋፈል በቀር ...የነዚህ ሁለት የታሪክ ክስተቶች እውነት እንዴት አይመሳሰልም ትላለህ?
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby የተሞናሞነው » Thu Feb 23, 2012 7:20 pm

ሰላም ጋሽ ተድላና ሌሎች ወገኖች

ከላይ በተነሳው ጉዳይ ከሞላ ጎደል እኔም ከኤዶም ጋር እስማማለሁ:: አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በምን ስሌት እንደሚወነጀሉ አልገባኝም...እስካሁንም ሆን ብለው ጠብ ጭረው የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስፈጀት ያደረጉት ነው የሚል አንድምታ ያለው ጽሁፍ አላነበብሁም:: እንዴውም እንደ እኔ እይታ እዚህ ጋር ሁለቱ ግለሰቦች ከፋሽስቶቹ መርጠው ያነጣጠሩት ዋናውን አለቃ ግራዚያንን ነውና ድፍረታቸውንና ጀግንነታቸውን የበለጠ ያደርገዋል:: አቁስለውት ከዚያ በኋላ የደረሰውን የብቀላ እልቂት ስናስብም ግራዚያንን ገድለውት ቢሆንስ ብለን ማሰብም አለብን...አካሄዳቸውም ሊገድሉት ነውና:: አላማቸው ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ በጣሊያኖች ላይ ሊደርስ የሚችለው የፋሽስታዊ የበላይነት ስሜት ኪሳራ እንዲሁም በተቃራኒው በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈጥረው የአሸናፊነት ስሜትና ሃገራዊ መነቃቃት ቀላል ሊሆን እንደማይችል መገመት አያዳግትም::

ፋሽስት እነ ሞገስ አስገዶምና አብርሃም ደቦጭ ያንን ሙከራ ካደረጉ በኍላ የደረሰውን እልቂት አስበን ከሆነም በፊትም ቢሆን ይሄው ፋሽስት ኢትዮጵያዊያንን ቅቤ ሲቀባቸው ብሩንዶ ሲያበላቸው አይደለም የነበረው:: በመርዝ ጋዝ ረፍርፎ ቤተ ክርስቲያናቸውን አቃጥሎ ንጉሳቸውን ለስደት ዳርጎባቸው በፋሽስታዊ መንገድ ነው ይዟቸው የነበረው:: ታዲያ በዚህ ፋሽስት አለቃቸው ላይ የተደረገው ሙከራ በምን ስሌት ያንን ደፋር ድርጊታቸውን ልናሳንሰው እንችላለን? ምናልባት እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ ግራዚያንን ከማቁሰል አልፈው ይገድሉት ነበር ብሎ እንደ አስተያየት መስጠት ይቻል ይሆናል እንጂ ድርጊታቸው ለዚያ ሁሉ እልቂት ዳርጎናል ማለቱማ ፋሽስትን እሽሩሩ ብሎ መያዝ ይሻል ነበር የሚል አስተያየት ከመስጠት ጋር ይቀራረባል::


ልጅ ሞንሟናው
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Feb 24, 2012 7:51 am

ማጠቃለያ

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በዚህ ክፍል ቀደም ባሉት ሦሥት ክፍሎች ያቀረብኳቸውን ትንታኔዎች ወደአንድ ማጠቃለያ ለማምጣት እሞክራለሁ ::

ለትንታኔየ መነሻ ያደረግሁት የአምባሣደር እምሩ ዘለቀን ጽሑፍ ነበር ::

ተድላ ሀይሉ wrote:ክፍል 1:- የመነሻ ኃሣብ

ምንጭ:- Imru Zelleke, Posted on EthioReview, Wed Feb 22, 2012 12:19 pm. My collection of Fascist Italy's occupation of Ethiopia.


Heroes are not calculators and speculators, they are made of pure spirit, they are people who give their life for a good cause, fully conscious of their mortality.Abraham Debotch and Moges Asgedom are pure authentic Ethiopian heroes who gave impetus and dignity to Ethiopian patriotism at its most critical hour. Their heroism sets an eternal symbol and a noble inspiration for all Ethiopian patriots, especially when our people suffer under the yoke of violent and ruthless dictatorships, and the national survival is at stake.


... ለአምባሣደር እምሩ ጽሑፍ መነሻው ኃሣብ በዚህ አንቀጽ የመጀመሪያው አረፍተ-ነገር ነው :: እንደእኔ ትርጓሜ :-

'ጀግኖች የአራጣ አበዳሪ ኅሊና ያላቸው ቁማርተኞች አይደሉም : ንፁህ መንፈስ ያላቸው : ሕይወታቸውን ለበጎ ዓላማ አሣልፈው ለመሥጠት ዝግጁ የሆኑና ሟች መሆናቸውን አምነው የተቀበሉ ሰዎች እንጂ ::'

መነሻ ኃሣቡን የሞገትኩባቸው ጥያቄዎች :-
Code: Select all
1 ..... በእርግጥ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ጀግኖች ነበሩ?

2 ..... አምባሣደር እምሩ ለጀግኖች ሚዛን አድርገው ያቀረቡትን ጣሪያ ነክተዋል? ወይስ በተቃራኒው እነርሱ ባቀጣጠሉት አመፅ ምክንያት በፋሽስት ጣሊያኖች ይጨፈጨፍ የነበረውን ሕዝብ ጥለው ሸሽተዋል?


የመጀመሪያውን ጥያቄ ለመመለስ :-
@ ..... ጀግና ለሕይወቱ እንደማይሣሣ አምባሣደር እምሩ አስገንዝበውናል :: አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም እኒያን 7 ወይም 10 (ታሪኩን እንደዘገቡት ጸሐፊዎች አቀራረብ ቁጥራቸው ስለሚለያይ) ቦምቦች በፋሽስት ጣሊያኑ ጄኔራል ግራዚያኒ እና አጀቦቹ ላይ ከወረወሩ በኋላ ያደረጉት ነገር ቢኖር የራሣቸውን ሕይወት ለማዳን መሸሽ ነበር :: ሽሽታቸው የተደመደመው ከኢትዮጵያ ግዛት ሊወጡ ሲሉ ጠረፍ ላይ እንደሆነ ተጠቁመናል :: በተቃራኒው እነርሱን እንዲያመልጡ የረዳቸው አጋራቸው ስሞዖን አደፍርስ እስከመጨረሻው ድረስ በዓላማው ጸንቶ በፋሽስት ጣሊያኖች የሚደርስበትን ሥቃይ ሁሉ ተቀብሎ ሞትን ፊት ለፊት ተጋፍጧል :: ከሕፃንነቴ ጀምሮ ሥሰማው የኖርኩት 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሚባሉ ጀግኖች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው አቆሠሉት ...' ሲባል እንጂ ስምዖን አደፍርስ የሚባል ጀግና ያን ያህል መስዋዕትነት መክፈሉን ሠምቼ አላውቅም :: 'ሠምቼ አውቃለሁ' የሚል ሰው ካለ ማስረጃውን አቅርቦ ይሞግተኝ :: እንዲያውም የአሁን ዘመን ታሪክ ጸሐፊዎች ባያስታውሱት ኖሮ ከእነጭራሹም እንደዚያ ያለ ሰው መፈጠሩንም የሚያስታውስ ሰው አይኖርም ነበር :: ታዲያ የእነ 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም' ተግባር 'የጀግንነት ተግባር ነው' ካልን ለምን የስምዖን አደፍርስ ሥም አብሮ ሲወደስ አልኖረም ? እርሱ ቲፎዞ ስለሌለው ይሆን? ወይስ ከዚህ ፕሮፓጋንዳ ጀርባ ሌላ የተወሣሠበ ፖለቲካ ይኖር ይሆን?

ለሁለተኛው ጥያቄ የሚቀርበው መልስ ለጀግና ተግባር ትክክለኛው መመዘኛ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ :: አንድ ሰው በግል ዕምነቱ አንድ ትልቅ ተግባር ሊፈፅም ይነሣል :: ያንን ተግባር በመፈፀሙ ተጠቃሚም ይኖራል : ተጎጂም ይኖራል :: ተጠቃሚዎቹ 'ጀግና' ሲሉት ተጎጂዎቹ 'ጨካኝ' ይሉታል :: የሰውዬው ተግባር ከሁለቱም ውጪ የሆነ ያልተፈለገውን ውጤት ያመጣ ከሆነ ደግሞ የቀቢፀ-ተስፋ ድርጊት እንጂ ጀግንነት አይሆንም :: ሰውዬው ያሠበውን ተቃራኒውን ውጤት ካመጣ እንዲያውም ከንቱ ጀብደኝነት እንጂ የጀግንነት ተግባርም ሆኖ መቆጠር አይኖርበትም ::

ከላይ ብዙዎቻችሁ በስሜት የእኔን ኃሣብ ልጣጣጥሉት ስትዳዱ አስተውያለሁ : ቁስላቸው የተነካ የሹምባሽ ልጆችም ተንጨርጭረዋል :: መሠረታዊ ነጥቡ ግን እናንተ ጀግኖች የምትሏቸው 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም' ለእኔ ጀግኖች አይደሉም :: እጅግ ሲበዛ በቀቢፀ-ተስፋ የተፍጨረጨሩ ሰዎች ነበሩ : ጀብደኞችም ጭምር ::

እስኪ አስቡት በእነ አብርሃ ደቦጭ ድርጊት አሣብቦና አስታክኮ ፋሽስት ጣሊያን በፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ምክንያት
@ ..... በሥንት ድካም ኢትዮጵያ ካስተማረቻቸው ወጣቶች መካከል በዚያ አጭር ጊዜ ግማሽ ቁጥር ያላቸውን ማጣት ቀላል ነበር?

@ ..... በአርበኞችስ ትግል ላይ የፈጠረው የአመራር ክፍተትስ?

@ ..... በዚያ ድርጊት ምክንያት በተፈጠረው የተማረ ኃይልና የሠለጠነ የጦር አመራር እጅጉን መመናመን ሣቢያ የተከሠቱት ችግሮች እኮ አገሪቱ ከፋሽስቶች በአርበኞቿ ትግል ነፃ ከወጣች በኋላ ያፈጠጡ ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል :!:

@ ..... ከ1933 ዓ.ም. በኋላ የተማረ ኃይል ለማዘጋጀት ምን ያህል ድካም ጠየቀ ?

@ ..... በአስተዳደርስ ረገድ የአፄ ኃይለሥላሤ አገዛዝ በአመዛኙ በባንዶችና በሥደተኞች እየታገዘ አርበኞችን በማግለል ይበልጥ ፈላጭ ቆራጭ ፍጹማዊ የዘውድ አገዛዝ ሆኖ ለመቀጠል ተመቸው ::

@ ..... በባህልም ረገድ 'ባንዳነት' የሚመረጥ እንጂ የሚነቀፍ ሣይሆን ይበልጥ እያጎመራ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ዘለቀ ::

ስለዚህ ወገኖቼ ከሕፃንነታችን ጀምሮ በማደንዘዣ የፕሮፓጋንዳ መርፌ ከተወጋነው የእንቅልፍ መድኃኒት ሠመመን እንድንነቃ እንዲህ ዓይነቶቹን 'የተለምዶ የጀግንነት ታሪኮች' እንደገና እንፈትሽ ::

አክባሪያችሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Feb 24, 2012 11:26 am

ሰላም ተድላ ሀይሉ:-

ከሕፃንነቴ ጀምሮ ሥሰማው የኖርኩት 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሚባሉ ጀግኖች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው አቆሠሉት ...' ሲባል እንጂ ስምዖን አደፍርስ የሚባል ጀግና ያን ያህል መስዋዕትነት መክፈሉን ሠምቼ አላውቅም :: 'ሠምቼ አውቃለሁ ' የሚል ሰው ካለ ማስረጃውን አቅርቦ ይሞግተኝ :: እንዲያውም የአሁን ዘመን ታሪክ ጸሐፊዎች ባያስታውሱት ኖሮ ከእነጭራሹም እንደዚያ ያለ ሰው መፈጠሩንም የሚያስታውስ ሰው አይኖርም ነበር :: ታዲያ የእነ 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ' ተግባር 'የጀግንነት ተግባር ነው ' ካልን ለምን የስምዖን አደፍርስ ሥም አብሮ ሲወደስ አልኖረም ? እርሱ ቲፎዞ ስለሌለው ይሆን ? ወይስ ከዚህ ፕሮፓጋንዳ ጀርባ ሌላ የተወሣሠበ ፖለቲካ ይኖር ይሆን ?


ይህ ዕለት በየዓመቱ ሲታሰብ አንተም እንዳልከው እኔም የአብርሃ ና የሞገስ ሥም እንጂ የስምኦን አደፍርሰው* ሥም ትኩረት አይሰጠውም::ከ 3 ዓመት በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ርእስ ከፍቼ ነበር::

http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... hp?t=32236

አንዳንዴ ቁም ነገር የማያጣው ሾተልም(እሱም እንዳንተ ያባቱን ሥም አደፍርስ ነው ያለው) ወዲያውኑ ይህን ርእስ ከፍቶ የሚከተለውን ትረካ አቅርቧል::

http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... hp?t=32247

ቆየት ያሉ ጋዜጦች ማግኘት የምትችል ከሆነም በደርግ ጊዜ 'ምን ሠርተው ታወቁ?' በመባል የሚታወቅ ሳምንታዊ(ሐሙስ) ዓምድ ላይ የስምኦን የህይወት ታሪክና ከነ አብርሃ ጋር ዝግጅቱ ላይ እንደተሳተፈ ተጠቅሷል(ፎቶውም አለ)::

ከአንተ ጋር የማልስማማበት ነገር ቢኖር የስምኦን ታሪክ ሆን ተብሎ ተድበስብሷል የሚል ጥርጣሬ ያለህ መሆኑ ነው::ሁኔታዎችን ማየት ያለብን ግን ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ነው::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1219
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Fri Feb 24, 2012 5:17 pm

ጋሽ ተድላ

በአብርሀም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ላይ ያለህን አስተያየት እንኳን አልጋራውም:: እስከ ገባኝ ድረስ ሞገስ አስገዶም እና አብርሀም ደቦጭ በራሳቸው ተነሳሽነት ብቻ ያደረጉትን አላደረጉም:: የፖለቲካም ወታደራዊ ምክክርም ነበር:: ለዚህ ሚሽን የተመረጡት ልጂ እንዳላቸው ከተረጋገጠ በኍላ ነው የሚል ነገር ሁሉ ሰምቻለሁ::

ርግጥ ነው ያስመለጣቸው (ሾፌር?) በጥሊያን በስቅላት ተገድሎአል:: ከከፈለው መስዋዕትነትም አንጻር መዘከር ያለበትን ያህል አልተዘከረም:: ያ ማለት ግን ተመክሮበት ተደረገ የሚባለውን የነ አብርሀምን ስራ መረሳት ያለበት አይመስለኝም:: በህወሀትም ላይ እንዲሁ አይነት አዳዲስ አብርሀም እና ሞገሶች ናቸው የሚያፈልጉት:: በተገኘበት ሁሉ የህወሀት የሆነን ነገር ላይ አደጋ መጣል::

ናፖሊዮን ዳኘ::


ተድላ ሀይሉ wrote:ማጠቃለያ

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በዚህ ክፍል ቀደም ባሉት ሦሥት ክፍሎች ያቀረብኳቸውን ትንታኔዎች ወደአንድ ማጠቃለያ ለማምጣት እሞክራለሁ ::

ለትንታኔየ መነሻ ያደረግሁት የአምባሣደር እምሩ ዘለቀን ጽሑፍ ነበር ::

ተድላ ሀይሉ wrote:ክፍል 1:- የመነሻ ኃሣብ

ምንጭ:- Imru Zelleke, Posted on EthioReview, Wed Feb 22, 2012 12:19 pm. My collection of Fascist Italy's occupation of Ethiopia.


Heroes are not calculators and speculators, they are made of pure spirit, they are people who give their life for a good cause, fully conscious of their mortality.Abraham Debotch and Moges Asgedom are pure authentic Ethiopian heroes who gave impetus and dignity to Ethiopian patriotism at its most critical hour. Their heroism sets an eternal symbol and a noble inspiration for all Ethiopian patriots, especially when our people suffer under the yoke of violent and ruthless dictatorships, and the national survival is at stake.


... ለአምባሣደር እምሩ ጽሑፍ መነሻው ኃሣብ በዚህ አንቀጽ የመጀመሪያው አረፍተ-ነገር ነው :: እንደእኔ ትርጓሜ :-

'ጀግኖች የአራጣ አበዳሪ ኅሊና ያላቸው ቁማርተኞች አይደሉም : ንፁህ መንፈስ ያላቸው : ሕይወታቸውን ለበጎ ዓላማ አሣልፈው ለመሥጠት ዝግጁ የሆኑና ሟች መሆናቸውን አምነው የተቀበሉ ሰዎች እንጂ ::'

መነሻ ኃሣቡን የሞገትኩባቸው ጥያቄዎች :-
Code: Select all
1 ..... በእርግጥ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ጀግኖች ነበሩ?

2 ..... አምባሣደር እምሩ ለጀግኖች ሚዛን አድርገው ያቀረቡትን ጣሪያ ነክተዋል? ወይስ በተቃራኒው እነርሱ ባቀጣጠሉት አመፅ ምክንያት በፋሽስት ጣሊያኖች ይጨፈጨፍ የነበረውን ሕዝብ ጥለው ሸሽተዋል?


የመጀመሪያውን ጥያቄ ለመመለስ :-
@ ..... ጀግና ለሕይወቱ እንደማይሣሣ አምባሣደር እምሩ አስገንዝበውናል :: አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም እኒያን 7 ወይም 10 (ታሪኩን እንደዘገቡት ጸሐፊዎች አቀራረብ ቁጥራቸው ስለሚለያይ) ቦምቦች በፋሽስት ጣሊያኑ ጄኔራል ግራዚያኒ እና አጀቦቹ ላይ ከወረወሩ በኋላ ያደረጉት ነገር ቢኖር የራሣቸውን ሕይወት ለማዳን መሸሽ ነበር :: ሽሽታቸው የተደመደመው ከኢትዮጵያ ግዛት ሊወጡ ሲሉ ጠረፍ ላይ እንደሆነ ተጠቁመናል :: በተቃራኒው እነርሱን እንዲያመልጡ የረዳቸው አጋራቸው ስሞዖን አደፍርስ እስከመጨረሻው ድረስ በዓላማው ጸንቶ በፋሽስት ጣሊያኖች የሚደርስበትን ሥቃይ ሁሉ ተቀብሎ ሞትን ፊት ለፊት ተጋፍጧል :: ከሕፃንነቴ ጀምሮ ሥሰማው የኖርኩት 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሚባሉ ጀግኖች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው አቆሠሉት ...' ሲባል እንጂ ስምዖን አደፍርስ የሚባል ጀግና ያን ያህል መስዋዕትነት መክፈሉን ሠምቼ አላውቅም :: 'ሠምቼ አውቃለሁ' የሚል ሰው ካለ ማስረጃውን አቅርቦ ይሞግተኝ :: እንዲያውም የአሁን ዘመን ታሪክ ጸሐፊዎች ባያስታውሱት ኖሮ ከእነጭራሹም እንደዚያ ያለ ሰው መፈጠሩንም የሚያስታውስ ሰው አይኖርም ነበር :: ታዲያ የእነ 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም' ተግባር 'የጀግንነት ተግባር ነው' ካልን ለምን የስምዖን አደፍርስ ሥም አብሮ ሲወደስ አልኖረም ? እርሱ ቲፎዞ ስለሌለው ይሆን? ወይስ ከዚህ ፕሮፓጋንዳ ጀርባ ሌላ የተወሣሠበ ፖለቲካ ይኖር ይሆን?

ለሁለተኛው ጥያቄ የሚቀርበው መልስ ለጀግና ተግባር ትክክለኛው መመዘኛ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ :: አንድ ሰው በግል ዕምነቱ አንድ ትልቅ ተግባር ሊፈፅም ይነሣል :: ያንን ተግባር በመፈፀሙ ተጠቃሚም ይኖራል : ተጎጂም ይኖራል :: ተጠቃሚዎቹ 'ጀግና' ሲሉት ተጎጂዎቹ 'ጨካኝ' ይሉታል :: የሰውዬው ተግባር ከሁለቱም ውጪ የሆነ ያልተፈለገውን ውጤት ያመጣ ከሆነ ደግሞ የቀቢፀ-ተስፋ ድርጊት እንጂ ጀግንነት አይሆንም :: ሰውዬው ያሠበውን ተቃራኒውን ውጤት ካመጣ እንዲያውም ከንቱ ጀብደኝነት እንጂ የጀግንነት ተግባርም ሆኖ መቆጠር አይኖርበትም ::

ከላይ ብዙዎቻችሁ በስሜት የእኔን ኃሣብ ልጣጣጥሉት ስትዳዱ አስተውያለሁ : ቁስላቸው የተነካ የሹምባሽ ልጆችም ተንጨርጭረዋል :: መሠረታዊ ነጥቡ ግን እናንተ ጀግኖች የምትሏቸው 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም' ለእኔ ጀግኖች አይደሉም :: እጅግ ሲበዛ በቀቢፀ-ተስፋ የተፍጨረጨሩ ሰዎች ነበሩ : ጀብደኞችም ጭምር ::

እስኪ አስቡት በእነ አብርሃ ደቦጭ ድርጊት አሣብቦና አስታክኮ ፋሽስት ጣሊያን በፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ምክንያት
@ ..... በሥንት ድካም ኢትዮጵያ ካስተማረቻቸው ወጣቶች መካከል በዚያ አጭር ጊዜ ግማሽ ቁጥር ያላቸውን ማጣት ቀላል ነበር?

@ ..... በአርበኞችስ ትግል ላይ የፈጠረው የአመራር ክፍተትስ?

@ ..... በዚያ ድርጊት ምክንያት በተፈጠረው የተማረ ኃይልና የሠለጠነ የጦር አመራር እጅጉን መመናመን ሣቢያ የተከሠቱት ችግሮች እኮ አገሪቱ ከፋሽስቶች በአርበኞቿ ትግል ነፃ ከወጣች በኋላ ያፈጠጡ ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል :!:

@ ..... ከ1933 ዓ.ም. በኋላ የተማረ ኃይል ለማዘጋጀት ምን ያህል ድካም ጠየቀ ?

@ ..... በአስተዳደርስ ረገድ የአፄ ኃይለሥላሤ አገዛዝ በአመዛኙ በባንዶችና በሥደተኞች እየታገዘ አርበኞችን በማግለል ይበልጥ ፈላጭ ቆራጭ ፍጹማዊ የዘውድ አገዛዝ ሆኖ ለመቀጠል ተመቸው ::

@ ..... በባህልም ረገድ 'ባንዳነት' የሚመረጥ እንጂ የሚነቀፍ ሣይሆን ይበልጥ እያጎመራ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ዘለቀ ::

ስለዚህ ወገኖቼ ከሕፃንነታችን ጀምሮ በማደንዘዣ የፕሮፓጋንዳ መርፌ ከተወጋነው የእንቅልፍ መድኃኒት ሠመመን እንድንነቃ እንዲህ ዓይነቶቹን 'የተለምዶ የጀግንነት ታሪኮች' እንደገና እንፈትሽ ::

አክባሪያችሁ ::

ተድላ
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ኤዶም* » Fri Feb 24, 2012 8:05 pm

@ ..... ጀግና ለሕይወቱ እንደማይሣሣ አምባሣደር እምሩ አስገንዝበውናል :: አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም እኒያን 7 ወይም 10 (ታሪኩን እንደዘገቡት ጸሐፊዎች አቀራረብ ቁጥራቸው ስለሚለያይ ) ቦምቦች በፋሽስት ጣሊያኑ ጄኔራል ግራዚያኒ እና አጀቦቹ ላይ ከወረወሩ በኋላ ያደረጉት ነገር ቢኖር የራሣቸውን ሕይወት ለማዳን መሸሽ ነበር :: ሽሽታቸው የተደመደመው ከኢትዮጵያ ግዛት ሊወጡ ሲሉ ጠረፍ ላይ እንደሆነ ተጠቁመናል


እነዚህ ሰዎች ለህይወታቸው ቢሳሱ ኖሮ ቀድሞውኑ አርፈው ይቀመጡ ነበር......አንተ አቅልለህ 7 ወይም 10 በማለት የጠቀስካቸውን ቦንቦች በፋሽስቱ አውራ ላይ በቅርብ ርቀት ሆነው ለመወርወር የቻሉ ሰዎች እንዴት ለህይወታቸው የሚሳሱ ፈሪዎች እንደተባሉ ሊገባኝ አይችልም...........አላማቸው ግራዝያኒ ነበር......የቻሉትን ያህል ሞከሩ........አልሆነላቸውም ቀድመው ባዘጋጁት መንገድ በስምኦን ርዳታ ለጊዜውም ቢሆን ማምለጥ ቻሉ.........እንደ በግ ተይዘው መታረድ ነበረባቸው የሚለው ጉዳይ ማንን በምን መልኩ ሊጠቅም እንደሚችልም አይገባኝም.......ጥይት ሲተኮስብህ ከለላ ፈልጎ ከጥይቱ መዳን ፈሪ የሚያስብል ከሆነ .....የፈሪን ትርጉም በጥልቀት ማጥናት ሊኖርብን ነው ማለት ነው....ለመሆኑ አያድርገውና ፊት ለፊትህ ጠላትህ ሊገድልህ በግላጭ አግኝቶህ አልሞ ቢተኩስብህ ደረትህን ገልብጠህ ትቀበለዋለህ ወይስ ባገኘከው አጋጣሚ ተጠቅመህ ከተጋረጠብህ አደጋ ለማምለጥ ትሞክራለህ?

በተለያየ ምክንያት ኢህአዴግ እንዳያስረን እንዳይገድለን ፈርተን ተሰደድን በማለት በሺዎች የሚቖጠሩ ራሳቸውን የፖለቲካ ስደተኞች ብለው የሚጠሩ ከአገራቸው በሚወጡበትና በስደት ምድር እንደ ጀግና በሚታዩበት ዘመን የፋሽስቱን አውራ ግራዝያኒን በቦንብ አቁስለው በመላ አገሪቱ እንደ አውሬ ቀን ከሌት የሚታደኑ ሁለት ሰዎች አገራቸው ጠረፍ ላይ ተይዘው መገደላቸው ፈሪ ተብለው መፈረጃቸው የሚገርም ነው :?

በተቃራኒው እነርሱን እንዲያመልጡ የረዳቸው አጋራቸው ስሞዖን አደፍርስ እስከመጨረሻው ድረስ በዓላማው ጸንቶ በፋሽስት ጣሊያኖች የሚደርስበትን ሥቃይ ሁሉ ተቀብሎ ሞትን ፊት ለፊት ተጋፍጧል :: ከሕፃንነቴ ጀምሮ ሥሰማው የኖርኩት 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሚባሉ ጀግኖች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው አቆሠሉት ...' ሲባል እንጂ ስምዖን አደፍርስ የሚባል ጀግና ያን ያህል መስዋዕትነት መክፈሉን ሠምቼ አላውቅም :: 'ሠምቼ አውቃለሁ ' የሚል ሰው ካለ ማስረጃውን አቅርቦ ይሞግተኝ :: እንዲያውም የአሁን ዘመን ታሪክ ጸሐፊዎች ባያስታውሱት ኖሮ ከእነጭራሹም እንደዚያ ያለ ሰው መፈጠሩንም የሚያስታውስ ሰው አይኖርም ነበር :: ታዲያ የእነ 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ' ተግባር 'የጀግንነት ተግባር ነው ' ካልን ለምን የስምዖን አደፍርስ ሥም አብሮ ሲወደስ አልኖረም ? እርሱ ቲፎዞ ስለሌለው ይሆን ? ወይስ ከዚህ ፕሮፓጋንዳ ጀርባ ሌላ የተወሣሠበ ፖለቲካ ይኖር ይሆን ?የስምኦን አደፍርስ ድርሻ የሚናቅ አልነበረም...ህይወቱን የሚያስከፍል ታላቅ ስራ ነው የሰራው.........ለምን ስሙ እንደማይጠቀስ አይገባኝም......ስሙ ከነሱ ጋር መነሳት ነበረበት........ሆኖም የሱ ስም ያለመጠቀሱ የነሱን ስራ አያሳንሰውም.........እዚህ ላይ ምንም አይነት ፖለቲካ የለም....የታሪክ ፀሀፊዎች ለአስመላጩ መስጠት የሚገባቸውን ትኩረት ሳይሰጡ በሁለቱ ሰዎች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጋቸው ስህተት ነው........ያ ማለት ግን በምንም ምክንያት የነአብርሀና ሞገስን ታሪክ ለውጦ ፈሪ ሊያገርጋቸው አይችልም

ለሁለተኛው ጥያቄ የሚቀርበው መልስ ለጀግና ተግባር ትክክለኛው መመዘኛ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ :: አንድ ሰው በግል ዕምነቱ አንድ ትልቅ ተግባር ሊፈፅም ይነሣል :: ያንን ተግባር በመፈፀሙ ተጠቃሚም ይኖራል : ተጎጂም ይኖራል :: ተጠቃሚዎቹ 'ጀግና ' ሲሉት ተጎጂዎቹ 'ጨካኝ ' ይሉታል :: የሰውዬው ተግባር ከሁለቱም ውጪ የሆነ ያልተፈለገውን ውጤት ያመጣ ከሆነ ደግሞ የቀቢፀ -ተስፋ ድርጊት እንጂ ጀግንነት አይሆንም :: ሰውዬው ያሠበውን ተቃራኒውን ውጤት ካመጣ እንዲያውም ከንቱ ጀብደኝነት እንጂ የጀግንነት ተግባርም ሆኖ መቆጠር አይኖርበትም ::


ይህ እንግዲህ ያንተ አስተያየት ነው.........ጀግኖች የተባሉትን በተለይም የጦር ሜዳ ጀግኖችን ብትጠይቅ ግን የምታገኘው መልስ የተለየ ነው.........ጀግና ምንም እንኳን የተለያየ አላማ ኖሯቸው ቢዋጉም ሌላውን ጀግና አይንቅም.....ይህ እውነት ነው....ጣልያኖች ሳይቀር ..የራስ አሉላን ጀግንነት መስክረዋል....የደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶን ወንድነት እሬት እሬት እያለ እየመረራቸውም ቢሆን አውርተውታል......የአንዳንድ የደርግ የጦር መሪዎችን ጀግንነት በአድናቆት የሚገልፁ የወያኔ ኮማንደሮች አጋጥመውኛል....በተቃራኒው ደግሞ ያንዳንድ የወያኔ ኮማንደሮችን ብቃትና ጀግንነት በአድናቆት የሚገልፁ የደርግ መኮንኖችም አሉ.......;...የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ የሚባለው አረቦቹ ቦንብ ታጥቀው በሰላማዊ ህዝብ መሀል ፈንድተው የሚሞቱት አይነትን ነው......ያ ጀግንነት አደለም.........በመርዝ ጭስ ሳይቀር ተጠቅሞ የአገሪቷን ህዝብ ለመጨረስ ግዳጅ ተሰጥቶት የመጣን አረመኔ መሪን ለመግደል የሞከሩ ሰዎች ከጀግኖችም በላይ ጀግኖች ናቸውከላይ ብዙዎቻችሁ በስሜት የእኔን ኃሣብ ልጣጣጥሉት ስትዳዱ አስተውያለሁ : ቁስላቸው የተነካ የሹምባሽ ልጆችም ተንጨርጭረዋል


ያንተ ሀሳብኮ የእግዚአብሄር ቃል አይደለም.......ብዙዎች ካንተ ጋ አለመስማማታቸው ራሱ ሀሳብህን እንድትመረምር ያደርግሀል እንጂ......ለምን እኔ ያልኩትን እንደ ገደል ማሚቶ አላጋባችሁም ማለትን ምን አመጣው?......ሌሎች ያላቸውን ሀሳብ መግለፅ መሞከራቸው ራሱ አስገርሞሀል.......ለመሆኑ "የኔን ሀሳብ ለማጣጣል የምትዳዱ" ብለህ ለማለት አንተ ማን ነህ?.........የሹም ባሽ ልጅ የሹም ባሾች አለቃን (ግራዝያኒን) ሊገድሉ የሞከሩትን የሚያወግዝ ይመስለኛል........ግራዝያኒ ላይ ግድያ ያደረጉትን ሰዎች በግልፅ እየወረፍክ ብቻ ሳይሆን እያወገዝክ ያለከው ደሞ አንተ ብቻ ነህ :cry:


እስኪ አስቡት በእነ አብርሃ ደቦጭ ድርጊት አሣብቦና አስታክኮ ፋሽስት ጣሊያን በፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ምክንያት

@ ..... በሥንት ድካም ኢትዮጵያ ካስተማረቻቸው ወጣቶች መካከል በዚያ አጭር ጊዜ ግማሽ ቁጥር ያላቸውን ማጣት ቀላል ነበር ?


እነ አብርሀ ና ሞገስ ያንን ባያረጉ ኖሮ ፋሽስቱ ጭፍጨፋ አያካሄድም ነበር ማለትህ ነው? ከየካቲት 12 በፊትበግራዝያኒ አመራር ሰጪነት ያለቁት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንስ ሰዎች አይደሉም......ጣልያንስ ያን ቀን ብቻ ለዛውም አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ነው ጭፍጨፋ ያደረገው?.......አንተን የሚያሳዝንህ ከተማሩት ወጣቶች አብዛኞቹ ማለቃቸው ብቻ ነው......በየ ክፍለ ሀገሩ እልፍ አእላፍ ሚስኪን ድሀ ያልተማሩ ገበሬዎችስ ከነ ደሳሳ ጎጆዎቻቸው በተኙበት በቦንብ እየተደበደቡ መጋየታቸውስ አያሳዝኑህም?.............ወደድንም ጠላንም ጣልያን የመጣው ሊያሰለጥነን ሳይሆን ባርያ አርጎ ሊገዛን ነበር.........ይህንን የሰለጠነ አረመኔ ሰራዊት ለመጋፈጥ ደግሞ ዋጋ መክፈል ነበረብን.......ዋጋ ከፈልን...አርበኞቻችን ባላቸው አቅምና እውቀት ተጠቅመው ተዋጉ.......የትግል ስልታቸው ኮላተራል ዳሜጅ አልነበረውም ማለት አይቻልም.......ይህን ኮላተራል ዳሜጅ መቀነስ ይችሉ ነበር ሌላ ጉዳይ ነው...ዋናው ጉዳይ ግን መታገል ካለባቸው ይህ ኮላተራል ዳሜጅ መከፈሉ አይቀሬ ነበር.......በጊዜው በነበራቸው እውቀት ደግሞ የተከተሉት ስልት ደግሞ በጦር ት. ቤት አካዳሚ ላልተማሩ ባገር ፍቅር እና አልገዛ ባይነት ስሜት ተነሳስተው ለተዋጉ ሰዎች ፈፅሞ መጥፎ አልነበረም

በአርበኞችስ ትግል ላይ የፈጠረው የአመራር ክፍተትስ ?ይህንን አንተ ገና ስታነሳ ሰማሁ....አርበኞችመሪዎቻቸው ሲወድቁ በየቀያቸው የጎበዝ አለቃ እየሾሙ ሲዋጉ እንደነበር ነው ሲነገር የሰማሁት.........ቀድሞውኑስ ማዕከላዊ የሆነ የተደራጀ አንድ ወጥ አመራር የት ነበራቸውና ነው........ልክ ትልቅ ክፍተት እንደተፈጠረ የሚነገረው?

..... በዚያ ድርጊት ምክንያት በተፈጠረው የተማረ ኃይልና የሠለጠነ የጦር አመራር እጅጉን መመናመን ሣቢያ የተከሠቱት ችግሮች እኮ አገሪቱ ከፋሽስቶች በአርበኞቿ ትግል ነፃ ከወጣች በኋላ ያፈጠጡ ችግሮች ሆነው ቀጥለዋልበዚህ ችግር እነ አብርሀ ና ሞገስ እንዴት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አይገባኝም......ከባዕድ አገዛዝ ነጻ ከሆንን በህዋላ ወታደራዊ መሪዎችንና ምሁራኖችን ለመፍጠር ከስክራች መጀመር ነበረብን....የነበሩንን በጣት የሚቆጠሩ ምሁራንና የጦር ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት አጥተናል........መላው አገሪቱን ጣልያን በነዚህ ሁለት ሰዎች ምክንያት የወረረ ይመስል እንዲሁም ሁሉንም ነገር በነሱ ምክንያት ነው የሆነው ብሎ ማሰብ እብደት ብቻ ነው


ከ 1933 ዓ .ም . በኋላ የተማረ ኃይል ለማዘጋጀት ምን ያህል ድካም ጠየቀ ?

@ ..... በአስተዳደርስ ረገድ የአፄ ኃይለሥላሤ አገዛዝ በአመዛኙ በባንዶችና በሥደተኞች እየታገዘ አርበኞችን በማግለል ይበልጥ ፈላጭ ቆራጭ ፍጹማዊ የዘውድ አገዛዝ ሆኖ ለመቀጠል ተመቸው ::አብርሀና ሞገስ ቦንብ ባይወረውሩ ኖሮ የተማረ የሰው ሀይል እጥረት አይኖርብንም ነበር.........የሚገርም አባባል ነው............ጣልያንን አርበኞች ባይነካኩት ኖሮኮ በሌሎች አፍሪካ አገሮች እንደታየው ለዘመናት ቅኝ ገዢ ሆኖ ይቀመጥ ነበር.......አርበኞችምኮ ጫካ ገብተው ባይዋጉ ኖሮ እነሱም ዘመዶቻቸውም አያልቁም ነበር....ቀጥሎ የምፅፍልህን ነገር በደንብ አስተውልና አንብበው

:!: :!: ..መርከብ በወደብ ላይ መልህቁን ጥሎ እስከቆመ ድረስ ምንም አይነት አደጋ አያጋጥመውም.......መርከብ የተሰራው ግን ወደብ ላይ እንዲገተር አደለም :!: :!:

ለነጻነት የሚከፈል መስዋዕትነት ትርፍ እንጂ ኪሳራ አይደለም.........
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ዞብል2 » Fri Feb 24, 2012 11:41 pm

ስማ ኤዶም የአብርሀና የሞገስን የገልፅክበትን አስተያየት እጋራሀለሁ ተድላም ሀሳቡን እንደ ሚያስተካክለው ተስፋ አለኝ::

አንድ ጥያቄ የቅንጅትና የወያኔን ፍልሚያ ለምንድነው ከዚህ የአርበኞች ትግል ጋር ያመሳሰልከው :?:
ቅኝ ገዝቼ ላስልጥናችሁ ካለ የውጭ ወራሪ ጋር የተደረገ የ5ዓመት ትግልና :!: ዲሞክራት ሳይሆን ዲሞክራት ነኝ ብሎ ነፃ ምርጫን አውጆ ሲሸነፍ እጅ ወደ ላይ ካለ አምባገነን ጋር የተደረገን ግብግብ :!: ወይስ አፍቃሪ ወያኔ ስለሆንክ በፎርም ወያኔዎች ቅኝ ገዢ መሆናቸውን እየነገርከነው :wink: :P :lol: :lol:


ዞብል ከአራዳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Feb 25, 2012 1:24 am

ሰላም ለሁሉም :-

ዘርዐይ ደረስ : ናፖሊዮን ዳኘና ዞብል :- እናንተ በዚህ ጉዳይ ላይ የተወጋችሁት ኃይለኛውን የሠመመን መርፌ ነው :: ቀስ በቀስ ጉዳዩ እየተገለጠ ይታያችኋል ብዬ አምናለሁ ::

ኤዶም* :- ለአንተ ሠፋ ያለ ማብራሪያ ስለሚያስፈልግህ ድጋሚ እመጣለሁ :: ከእነ-እንድርያስ ወገን እስካልሆንክ ድረስ አንተን 'ሹምባሽነት' አይመለከትህም ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Feb 26, 2012 5:11 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ኤዶም* :- የማጠቃለያ ኃሣቤን ማሠሪያ አረፍተ ነገር ምንም አስተያዬት አልሠጠህበትም :: ለምን ይሆን? :roll: :roll: :roll: ወጣም ወረደ ከመጨረሻ ጀምሬ ወደ መንደርደሪያ ኃሣቡ በወፍ-በረር አቋርጬ ለመድረስ እሞክራለሁ ::

ተድላ ሀይሉ wrote:@ ..... በባህልም ረገድ 'ባንዳነት ' የሚመረጥ እንጂ የሚነቀፍ ሣይሆን ይበልጥ እያጎመራ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ዘለቀ ::

ኃሣቤን ስተነትን መቋጫ ያደረግሁት ይህንን አረፍተ ነገር ነበር :: ወንድሜ 'ጥልቁ'ም እንዲህ ብሎ ሞግቶናል :-

ጥልቁ wrote:ለምን እንደሆነ አላቅም ፣ አሁን አሁን ግን ህሊናየን የሚያስጨንቀኝ እና መልስ የማላገኝለት ምስጢር ፣ እንዴት ያ ሁሉ መሰዋትነት የተከፈለባት አገር ፣ ተንገዋላ ተንገዋላ የኢጣሊያኖች አሸከር የነበሩት እና እነ አቡነጴጥሮስን በጥይት ደብድበው የገደሉት ባንዳዎች እጅ ላይ ልትወድቅ ቻለች ? (ልብ በሉ ፣ እነአቡነ ጴጥሮስ እራሳቸውን ለመሰዋትነት ሲያቀርቡ ፣ ትግራይ ውስጥ ግን ለጣሊያኖች ታቦት ወጥቶ ያሬዳዊ ዜማ ይቀርባላቸው ነበር። ልክ በኛ ዘመን ፣ አባ ገብረምድህን ለቢዮንሴ እንዳደረጉት ማለት ነው። ) እውነት እኛ ኢትዮጵያውያን እንዴት ከታሪክ ምንም ሳንማር ቀርተን ፣ ያችን አገር ለዘመናት ሲያደሟት የኖሯት ባንዳዎች እንዲፈነጩባት ፈቀድን ? አዎን ፈቅደናል። (ያኔ ሲመጡስ ጊዜው አስገድዶን አረብ እና አሜሪካም ተመሳጥሮብን ይባል ) ዛሬ ግን ብንፈቅድ አይደል በኢትዮጵያዊነት ስም ሁሉ ተደራጅተን ፣ ሁለመናው እኛን የመሰለ ኢትዮጵያዊ እስኪገኝ ድረስ ተከፋፍለን ወያኔ የሚቀልድብን ?

እኔ መልሴ:- 'የዛሬ 71 ዓመት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሤ በእንግሊዞች ዕርዳታ ዳግም ለዙፋን ሲበቁ "የውሾን ነገር ያነሣ ውሾ ይሁን -አንተ ባንዳ : አንተ አርበኛ : አንተ ሥደተኛ እየተባባላችሁ አትከፋፈሉ ብለው ባንዶችን የሥደተኞችና የአርበኞች የበላይ በማድረጋቸው : እንዲሁም እንደነዚያ ከ10 ያልበለጡ ቦምቦች እንደ ደንጊያ ወርውረው ነፍሴ አውጪኝ ብለው የሸሹ ጀብደኞችን ዓይነቶቹን ሰዎች ጀግና : ፋሽስት ጣሊያንን በጦርነት አርበድብደው አገራቸውን ያለእንግሊዝ ዕርዳታ ነፃ ያወጡትን የእነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪን : የእነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀን : የእነ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያትን የመሣሠሉትን ምርጥና ጀግና አርበኞችን በግፍ ስላስገደሉ ከዚያ ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ ጀግንነት የተነወረ : በተቃራኒው ደግሞ ባንዳነት የተከበረ የፖለቲካ ባህል ሆኖ ዘለቀ :" እላለሁ ::

ኤዶም* :- ልክ አንተ እንዳደረግኸው ረዥም የመልስ-መልስ መሥጠት ይቻል ነበር :: ነገር ግን "አውቆ የተደበቀን ቢጠሩት አይሠማም" ይባላልና እንዲያው የእኔ እና ያንተ የኃሣብ ሙግት ጉንጭ አልፋ እንዳይሆን ብዬ ነው :: ለማሣጠር የመዝጊያ ኃሣቤ ወዴት እንዳመራ ሥትገነዘብ ከመካከል አረፍተ-ነገሮችን እየመዘዝክ ብቻ መሞገት መሞከርህ ይግባኝ የሌለው ፍርድ እንደሠጠህ ያስቆጥርብሃል ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby መቅደላዊ » Sun Feb 26, 2012 10:20 am

ተድላ ሀይሉ wrote:
ዘርዐይ ደረስ wrote:ይህን ታሪካዊ የሰማዕታት ቀን ለመዘከር ርእሱን ለከፈተው AddisMeraf እና ሌሎቻችሁም ሰላምታዬን እያቀረብኩ:-

AddisMeraf:-የዕለቱ 75ኛ ዓመት ታስቦ የሚውለው አንተ እንዳልከው ባለፈው ዓርብ ሳይሆን ዛሬ ነው::በተረፈ ያቀረብካቸው መረጃዎች ጠቃሚ ናቸው:: በቂ ጊዜ ሳገኝ አንብቤአቸው እመለስበት ይሆናል ::


ተድላ ሀይሉ:-እንዳልከው ይህ ዕለት ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ በየካቲት 11 የህወሃት ምሥረታ አከባበር በዓል ተውጧል::ስለ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሰጠኸው አስተያየት ላይ ግን ቅሬታ አለኝ::ሁለቱና ሥሙ ብዙም የማይጠራው ስምዖን አደፍርሰው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፋሽስት ግፍ አንገፍግፏቸው በወቅቱ በነበራቸው አቅም የግፍ አገዛዙን ዕድሜ ለማሳጠር እንጂ አንተ እንደምትለው የሙከራውን መክሸፍ ተከትሎ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ፈልገው ያደረጉት አይደለም::እኔ በበኩሌ አንድም ታሪክ ጸሐፊ በዚህ ድርጊት ሲወነጅላቸው አልሰማሁም አላነበብኩምም::አንተ እንዳልከው ቢሆን ኖሮ ዕለቱ በየዓመቱ ታስቦ ሲውል ሥማቸው በጀግንነት አይጠራም ነበር::ያንተን አመለካከት የሚጋራ አንድ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ጸሐፊ ወይም አርበኛ ልትጠቅስልኝ ትችላለህ?

ሰላም ዘርዐይ ደረስ:-

የአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ታሪክ በአርበኝነት ሥም ሲጻፍላቸው የኖረው ጣሊያንን አርበድብደው ያባረሩት:-
1 ..... እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ከወንድማቸው እጅጉ ዘለቀ ጋር ተክለኃይማኖት አደባባይ በሥቅላት በሚቀጡበት:

2 ..... እነ ፊታውራሪ ታከለ ወልደሐዋርያት እንደ ተራ ሌባ ታድነው በገዛ ቤታቸው በእሩምታ ተኩስ ተደብድበው ለሞት በተዳረጉበት ዘመን ነበር::

በተቃራኒው ደግሞ እንደ እነ ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖት : ራስ ስዩም መንገሻ : ቢትወደድ አስፍሃ ወልደሚካኤልን የመሣሠሉ ቀንደኛ የጣሊያን ባንዶች በሹመት በሚንበሸበሹበት ዘመን ነበር ::

ታሪክን በትክክል መርምረን አጥፊውን ከእነ ጥፋቱ ካላቀረብን እውነቱ ሃሰት : ሃሰቱ ደግሞ እውነት መስሎ ይቀርባል ::

ስለዚህ ለእኔ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ጀብደኞችና የጣሊያን ፋሽስቶች ጥፋት አቀጣጣዮች እንጂ ጀግኖች አይደሉም ::

ተድላ


ለአተላው ተድላ ሀይሉ ! ሰማእቶቻችንን ማንቆሸሹ ወያኔዎችና ሻእብያዎች ከሚያደርሱት ፀረ-ኢትዮጵያ ወንጀል ያላነሰ ነው:; አንተ እራስህ ሻእብያ ሳትሆን አትቀርም:: ስለ ኢትዮጲያ የአዞ ልቅሶህን ማፈስስህንና መቀልድህን እንድታቆም ትጠየቃለህ:: ደንባራ ባንዳ!
United we stand, divided we fall!
መቅደላዊ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 614
Joined: Tue Dec 01, 2009 11:07 am
Location: Ethiopia

Postby AddisMeraf » Sun Feb 26, 2012 5:44 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ኤዶም* :- የማጠቃለያ ኃሣቤን ማሠሪያ አረፍተ ነገር ምንም አስተያዬት አልሠጠህበትም :: ለምን ይሆን? :roll: :roll: :roll: ወጣም ወረደ ከመጨረሻ ጀምሬ ወደ መንደርደሪያ ኃሣቡ በወፍ-በረር አቋርጬ ለመድረስ እሞክራለሁ ::

ተድላ ሀይሉ wrote:@ ..... በባህልም ረገድ 'ባንዳነት ' የሚመረጥ እንጂ የሚነቀፍ ሣይሆን ይበልጥ እያጎመራ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ዘለቀ ::

ኃሣቤን ስተነትን መቋጫ ያደረግሁት ይህንን አረፍተ ነገር ነበር :: ወንድሜ 'ጥልቁ'ም እንዲህ ብሎ ሞግቶናል :-

ጥልቁ wrote:ለምን እንደሆነ አላቅም ፣ አሁን አሁን ግን ህሊናየን የሚያስጨንቀኝ እና መልስ የማላገኝለት ምስጢር ፣ እንዴት ያ ሁሉ መሰዋትነት የተከፈለባት አገር ፣ ተንገዋላ ተንገዋላ የኢጣሊያኖች አሸከር የነበሩት እና እነ አቡነጴጥሮስን በጥይት ደብድበው የገደሉት ባንዳዎች እጅ ላይ ልትወድቅ ቻለች ? (ልብ በሉ ፣ እነአቡነ ጴጥሮስ እራሳቸውን ለመሰዋትነት ሲያቀርቡ ፣ ትግራይ ውስጥ ግን ለጣሊያኖች ታቦት ወጥቶ ያሬዳዊ ዜማ ይቀርባላቸው ነበር። ልክ በኛ ዘመን ፣ አባ ገብረምድህን ለቢዮንሴ እንዳደረጉት ማለት ነው። ) እውነት እኛ ኢትዮጵያውያን እንዴት ከታሪክ ምንም ሳንማር ቀርተን ፣ ያችን አገር ለዘመናት ሲያደሟት የኖሯት ባንዳዎች እንዲፈነጩባት ፈቀድን ? አዎን ፈቅደናል። (ያኔ ሲመጡስ ጊዜው አስገድዶን አረብ እና አሜሪካም ተመሳጥሮብን ይባል ) ዛሬ ግን ብንፈቅድ አይደል በኢትዮጵያዊነት ስም ሁሉ ተደራጅተን ፣ ሁለመናው እኛን የመሰለ ኢትዮጵያዊ እስኪገኝ ድረስ ተከፋፍለን ወያኔ የሚቀልድብን ?

እኔ መልሴ:- 'የዛሬ 71 ዓመት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሤ በእንግሊዞች ዕርዳታ ዳግም ለዙፋን ሲበቁ "የውሾን ነገር ያነሣ ውሾ ይሁን -አንተ ባንዳ : አንተ አርበኛ : አንተ ሥደተኛ እየተባባላችሁ አትከፋፈሉ ብለው ባንዶችን የሥደተኞችና የአርበኞች የበላይ በማድረጋቸው : ......ፋሽስት ጣሊያንን በጦርነት አርበድብደው አገራቸውን ያለእንግሊዝ ዕርዳታ ነፃ ያወጡትን የእነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪን : የእነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀን : የእነ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያትን የመሣሠሉትን ምርጥና ጀግና አርበኞችን በግፍ ስላስገደሉ ......."


ተድላ


ሰላም ተድላ

ከላይ ያቀላሁትን አባባልህን እጋራዋለሁ:: ኢትዮጵያ ዛሬ ለቅወደቀችበት መከራ አንዱ መንስኤ የሆነው ጉዳይ አጼ ሐይለ ሥላሴ ተመልሰው አገር ሲገቡ ባንዳዎችን በሚመለከት የተከተሉት መንገድ ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል:: በአገር በዱር በገደል ተንከራተው ለአገራቸው የተዋጉት አርበኞች የንጉሱ መሰደድ በወቅቱ ቅር ቢያስኛቸውም የሐገራቸውን አንድነት ጉዳይ በማስቀደም የንጉሱን መመልስ ተቀበሉ:: እስከ ዛሬ ድረስ መልሱን ባላገኘሁለት ሁኔታ ግን ንጉሱ ባንዳውንና የባንዳው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ከፍ አደረጉ:: በኤርትራ ውስጥ ከጣሊያን ጎን ቆመው በአስካሪነት ያገለገሉ ባንዳ ወታደሮች ንጉስ ከስልጣን እስከ ወረዱ ድረስ ከጣሊያን ኤምባሲ የጡረታ ደሞዝ ይቀበሉ ነበረ:: ELF የተመሰረተውም በነኚሁ የጣሊያን አገልጋዮች ነበረ:: ዞሮ ዞሮ እነኚያ ባንዶቹ መልሰው የአጼ ሐይለ ሥላሴን ውድቀትና የኢትዮጵያን መከራ ካመጡት ውስጥ ናቸው::
AddisMeraf
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1615
Joined: Sun Nov 01, 2009 5:49 pm

Postby ኤዶም* » Mon Feb 27, 2012 7:43 pm

ሰላም ተድላ ሀይሉ.........

@ ..... በባህልም ረገድ 'ባንዳነት ' የሚመረጥ እንጂ የሚነቀፍ ሣይሆን ይበልጥ እያጎመራ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ዘለቀ ::


የሚለውን የመደምደምያህን አንድ ክፍል ሆን ብዬ አልዘለልኩትም........የባንዳዎችን ጌታ ግራዝያኒን ለመግደል የሞከሩ ሰዎች በምን አይነት መልኩ ባንዳነት ባህል እስኪሆን ድረስ የሚመረጥ እስኪሆን ድረስ ለዚህ አስቀያሚ ነገር ታላቅ አስተዋፅዖ እንዳበረከቱ አልታይ ስላለኝ ብቻ ነው

በነገራችን ላይ አንተ ያነሳካቸው ታላላቅ ስመጥር አርበኞች
ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ : እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ : እነ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያት...ሌሎችም እነ ልጅ ሀይለ ማርያም ማሞ...ራስ አበበ አረጋይ....ወዘተ..........ዱር ቤቴ በማለት ጠላትን የእግር እሳት የሆኑበት ጀግኖችና ቀድሞ የማይታወቁ የነበሩ የጎበዝ አለቆች መታወቅ የጀመሩት ከየካቲት 12 በህዋላ ነበር

ንጉሱ ከስደት እንደተመለሱ ስልጣኔን ይቀናቀኑኛል ያሏቸውን ብዙ ተከታይ የነበራቸውን ገናና እና ታዋቂ ስመጥር አርበኞን የፊውዳል ዘር ያለባቸውን ጥቂቶቹን በጋብቻ ሌሎችንም በሹመት ደልለው ታማኝ አሽከር ሲያደርጓቸው..........እውነተኛ አርበኞች የሆኑትን እንደነ በላይ አይነቶቹን. ባደባባይ ሰቅለዋል.......በላይ ዘለቀን ምን አይነት ሹመት እንስጥህ ምን እንበልህ ብለው ሲጠይቁት......ቀድሞውኑ ለሹመት ያልታገለው ቆፍጣናው በላይ ዘለቀ.....'እናቴ በላይ ብላኛለች!!!! ከዚህ በላይ ሹመት አልፈልግም !!!!" በማለቱ....ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም እንዲሉ......ሰበብ ፈልገው ያን የወንድ ቁና ጀግና በእንቅጭጩ ቀጩት

ያርበኞችን ድንቅ ተጋድሎ ዋጋ ለማሳጣትም በዱር በገደል ላገራቸው የሞቱላትና የቆሰሉላትን ወደ ጎን በመተው.....ባንዶችን እና ከሀዲዎችን ሾሙ.........አርበኞች ጠላትን አሸንፈው መናገሻ ከተማውን የተቆጣጠሩበትን መጋቢት 28 ማክበር ትተው...እሳቸው ኦሜድላ የገቡበትን ሚያዝያ 27 የነፃነት ቀን ነው ብለው አወጁ

ይህን ሁሉ የምቸከችከው ባንዳነት የተጀመረውና ያበበው በነዚህ ሁለት ሰዎች ምክንያት ነው የሚለውን ሀሳቤን ሆን ብለህ ሳታነሳው አለፍክ ስላልከኝ........ባንተው አባባል ባንዳነት የሚመረጥ ሊሆን የቻለበትን ምክንያት ለማስረዳት ነው

ይህ ሁሉ የሆነው አብርሀ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በግራዝያኒ ላይ ባደረጉት የግድያ ሙከራ ነው ብለህ ካመንክ እንግዲህ ምንም ማረግ አልችልም.........በዚህ ጉዳይ ላይ መስማማት ስለማንችል.....ላለመስማማት ተስማምተን ነገሩን ብንቋጨው መልካም ነው

አውቆ የተኛ..........ቢቀሰቅሱትም አይሰማም ብለህ የተረትከው ያላግባብ የገባ ነገር ነው...እኔስ አውቄ ተኝቼ ነው ይባል.....ሌሎቹስ የአብርሀና ሞገስን ስራ ጀግንነት ነበር ብለው የሚያምኑት.....አንተው ራስክ በዚህ ትሬድ በሀይለኛ የሰመመን መድሀኒት ተወግተዋል ያልካቸውስ መች ይሆን ከዚህ እንቅልፍ የሚነቁት??????????
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Feb 27, 2012 9:50 pm

ኤዶም* wrote:ሰላም ተድላ ሀይሉ.........

@ ..... በባህልም ረገድ 'ባንዳነት ' የሚመረጥ እንጂ የሚነቀፍ ሣይሆን ይበልጥ እያጎመራ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ዘለቀ ::


የሚለውን የመደምደምያህን አንድ ክፍል ሆን ብዬ አልዘለልኩትም........የባንዳዎችን ጌታ ግራዝያኒን ለመግደል የሞከሩ ሰዎች በምን አይነት መልኩ ባንዳነት ባህል እስኪሆን ድረስ የሚመረጥ እስኪሆን ድረስ ለዚህ አስቀያሚ ነገር ታላቅ አስተዋፅዖ እንዳበረከቱ አልታይ ስላለኝ ብቻ ነው

ሁለቱም :- አብርሃ ደቦጫና ሞገስ አስገዶም ያንን የጀብደኛ ተግባር እስኪፈፅሙ ድረስ የጣሊያን ባንዶች ነበሩ :: በተለይ አብርሃ ደቦጭ በፋሽስት ጣሊያን የቅኝ ግዛት አስተዳደር የፖለቲካ ክፍል የሚሠራ ሠላይ ነበር :: ዋናው ጉዳይ እነርሱ ያንን ድርጊት እስኪፈጽሙ ድረስ የነበሩት ሁኔታ ብቻ ሣይሆን በመጨረሻ ላይ ተጸጽተውም ይሁን በሌላ ምክንያት ጌታቸውን ጄኔራል ግራዚያኒን ለመግደል ወስነው ቦንብ መጣላቸው ቢያንስ ለንስሃ ያበቃቸዋል : ጀግና አርበኛ ግን አያደርጋቸውም ::

ኤዶም* wrote:በነገራችን ላይ አንተ ያነሳካቸው ታላላቅ ስመጥር አርበኞች
ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ : እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ : እነ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያት...ሌሎችም እነ ልጅ ሀይለ ማርያም ማሞ...ራስ አበበ አረጋይ....ወዘተ..........ዱር ቤቴ በማለት ጠላትን የእግር እሳት የሆኑበት ጀግኖችና ቀድሞ የማይታወቁ የነበሩ የጎበዝ አለቆች መታወቅ የጀመሩት ከየካቲት 12 በህዋላ ነበር

ትልቅ ሥህተት :!: እነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ከዚያ በፊት ሣይታወቁ ከኖሩ ከዚያ በኋላ እንዴት እንደእንጉዳይ ፈሉ ? አየህ እኒህን ሁለት ጀብደኞች (አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም) ከአቅማቸው በላይ እንዴት እንደካብኻቸውና ዋናዎቹን ጀግኖች እንዴት እንዳኮሠስካቸው :!: ለመሆኑ እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ሽፍትነት የጀመሩት ጣሊያን ከገባ በኋላ ነበር? ራስ አበበ አረጋይ እና ሌሎች በሸዋ : በጎንደር : በወሎ (በተለይ በላስታ እና አማራ ሣይንት) የነበሩት አርበኞች ከዚያ በፊት በአርበኝነቱ ተግባራቸው ጭራሽ አይታወቁምም ነበር ማለትህ ነው ?

ኤዶም* wrote:ንጉሱ ከስደት እንደተመለሱ ስልጣኔን ይቀናቀኑኛል ያሏቸውን ብዙ ተከታይ የነበራቸውን ገናና እና ታዋቂ ስመጥር አርበኞን የፊውዳል ዘር ያለባቸውን ጥቂቶቹን በጋብቻ ሌሎችንም በሹመት ደልለው ታማኝ አሽከር ሲያደርጓቸው..........እውነተኛ አርበኞች የሆኑትን እንደነ በላይ አይነቶቹን. ባደባባይ ሰቅለዋል.......በላይ ዘለቀን ምን አይነት ሹመት እንስጥህ ምን እንበልህ ብለው ሲጠይቁት......ቀድሞውኑ ለሹመት ያልታገለው ቆፍጣናው በላይ ዘለቀ.....'እናቴ በላይ ብላኛለች!!!! ከዚህ በላይ ሹመት አልፈልግም !!!!" በማለቱ....ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም እንዲሉ......ሰበብ ፈልገው ያን የወንድ ቁና ጀግና በእንቅጭጩ ቀጩት

በዚህ እንስማማለን ::

ኤዶም* wrote:ያርበኞችን ድንቅ ተጋድሎ ዋጋ ለማሳጣትም በዱር በገደል ላገራቸው የሞቱላትና የቆሰሉላትን ወደ ጎን በመተው.....ባንዶችን እና ከሀዲዎችን ሾሙ.........አርበኞች ጠላትን አሸንፈው መናገሻ ከተማውን የተቆጣጠሩበትን መጋቢት 28 ማክበር ትተው...እሳቸው ኦሜድላ የገቡበትን ሚያዝያ 27 የነፃነት ቀን ነው ብለው አወጁ

ንጉሡ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከመናገሻው ከተማ የገቡበት ዕለት ነው :: መጋቢት 25 ቀን 1933 ዓ.ም. ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ በአምቦ መሥመር የነበረውን የጣሊያን መንጋ ድል አድርገው በአምቦ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ አውለብልበዋል :: መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም. ጀግናው በላይ ዘለቀ ከ20,000 የማያንስ ጦሩን አሠልፎ ንጉሠ ነገሥቱን ደብረማርቆስ ላይ የተቀበለበት ዕለት ነበር :: በዚያ ይስተካከል :: በእርግጥ መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም. የእንግሊዝ ጦር አዲስ አበባን እና መቀሌን ቀድሞ ተቆጣጥሯል ::

ኤዶም* wrote:ይህን ሁሉ የምቸከችከው ባንዳነት የተጀመረውና ያበበው በነዚህ ሁለት ሰዎች ምክንያት ነው የሚለውን ሀሳቤን ሆን ብለህ ሳታነሳው አለፍክ ስላልከኝ........ባንተው አባባል ባንዳነት የሚመረጥ ሊሆን የቻለበትን ምክንያት ለማስረዳት ነው

ባንዳነት በእነርሱ ምክንያት አልተጀመረም : እነርሱም የፋሽስት ጣሊያን የመጀመሪያዎቹም የመጨረሻዎቹም ባንዶች አልነበሩም :: እኒያን አሥር ቦምቦች በግራዚያኒ እና አጀቦቹ ላይ እስኪጥሉ ድረስ ግን በይፋ የፋሽስት ጣሊያን ባንዶች ነበሩ : ነገር ግን ጌታቸውን ጄኔራል ግራዚያኒን ለመግደል ከኢትዮጵያውያን አርበኞች ጋር አቅደው ሞከሩ : አልተሣካላቸውም :: ድርጊታቸው የቀቢፀ-ተስፋ የጀብደኝነት ተግባር ነበር :: እነርሱን ከሚገባው በላይ እያሞካሹ ዋናዎቹን ጀግኖች አርበኞችን ማኮሠስ ግን ለተተኪው ትውልድ የሚያስተላልፈው መጥፎ መልዕክት "ጀግና ማለት ከድሮ ጀምሮ ባንዳም ቢሆን በመጨረሻ ግን ለወገኖቹ እንደ እሣት-ራት አንዴ ታይቶ ራሱን ለጥፋት የሚያቀርብ እንጂ ሁልጊዜም አስቦና አመዛዝኖ ተገቢውን ተግባር በተገቢው ሥፍራ የሚፈጽም ሰው አይደለም :" የሚል ይሆናል :: ስለዚህ ነው ከጣሊያን ወረራ በኋላ በተነሣው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት የጀብደኛና ክልፍልፍ ማርክሲስቶች-ሌኒኒስቶች-ስታሊኒስቶች የቅዠት ተግባር እስከዛሬ ድረስ እንደ ጀግንነት ተግባር ተቆጥሮ ሲወደስ የምናየው - 'አንቀፅ 39:- የብሔር : ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል' የሚለው አቋማቸው:: ኢትዮጵያውያን ባለፈው ታሪካቸን ከተሠሩ ሥህተቶች በትክክል ለመማር ያለመቻላችን ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ ማቅረብ ይቻላል! - ጀብደኝነትን እንደ ጀግንነት የመቁጠር አባዜ 8)

ኤዶም wrote:ይህ ሁሉ የሆነው አብርሀ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በግራዝያኒ ላይ ባደረጉት የግድያ ሙከራ ነው ብለህ ካመንክ እንግዲህ ምንም ማረግ አልችልም.........በዚህ ጉዳይ ላይ መስማማት ስለማንችል.....ላለመስማማት ተስማምተን ነገሩን ብንቋጨው መልካም ነው

አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የፈፀሙት ድርጊት ለጄኔራል ግራዚያኒ የጭፍጨፋ ዘመቻ በሩን ወገግ አድርጎ የከፈተለት የማደናገሪያ ምክንያት ነበር :: 'እነርሱ ያንን ባያደርጉ ኖሮ' ተብሎ ታሪክን መቀልበስና ማስተካከል አይቻልም : አንዴ የተፈጸመ ድርጊት ነውና : ሆኗል ሆኗል በቃ :!: ነገር ግን የእነርሱን ድርጊት ተከትሎ የመጣውን ጥፋት ማደባበስ ተገቢ አይደለም ::

ኤዶም* wrote:አውቆ የተኛ..........ቢቀሰቅሱትም አይሰማም ብለህ የተረትከው ያላግባብ የገባ ነገር ነው...እኔስ አውቄ ተኝቼ ነው ይባል.....ሌሎቹስ የአብርሀና ሞገስን ስራ ጀግንነት ነበር ብለው የሚያምኑት.....አንተው ራስክ በዚህ ትሬድ በሀይለኛ የሰመመን መድሀኒት ተወግተዋል ያልካቸውስ መች ይሆን ከዚህ እንቅልፍ የሚነቁት??????????

በኃሣብ ያለመስማማት ይቻላል :: ውይይት ከተባለ ግን ሁላችንም በአንድ መሥመር መሄድ የለብንም :: ደግሞም 'ኢትዮጵያውያን እንዲህ የነገር ውሉ የጠፋብን ለምን ይሆን?' ተብሎ ሲጠየቅ በታሪክ የተከናወኑ ድርጊቶችን እና ፈጻሚዎቻቸውን አንድ በአንድ ማስተንተን ይጠብቅብናል - እንደ መና ከሠማይ የሚወርድልን መፍትሔ የለምና :: ቢመረንም እንደ ኮሦ መድኃኒት ሃቅን ለመቀበል መድፈር ይኖርብናል ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ኤዶም* » Tue Feb 28, 2012 8:53 pm

ሁለቱም :- አብርሃ ደቦጫና ሞገስ አስገዶም ያንን የጀብደኛ ተግባር እስኪፈፅሙ ድረስ የጣሊያን ባንዶች ነበሩ :: በተለይ አብርሃ ደቦጭ በፋሽስት ጣሊያን የቅኝ ግዛት አስተዳደር የፖለቲካ ክፍል የሚሠራ ሠላይ ነበር :: ዋናው ጉዳይ እነርሱ ያንን ድርጊት እስኪፈጽሙ ድረስ የነበሩት ሁኔታ ብቻ ሣይሆን በመጨረሻ ላይ ተጸጽተውም ይሁን በሌላ ምክንያት ጌታቸውን ጄኔራል ግራዚያኒን ለመግደል ወስነው ቦንብ መጣላቸው ቢያንስ ለንስሃ ያበቃቸዋል : ጀግና አርበኛ ግን አያደርጋቸውም


ያንድ ሰው ማንነት የሚለካው በትናንት ምንነቱ ሳይሆን በዛሬው ማንነቱ ነው.....በታሪክ መፃህፍት በአድዋ ጦርነት ብዙ ባንዶች ከጠላት ጋ ሆነን አገራችንን አንወጋም በማለት በገፍ ወደ ሚኒልክ ጎራ እንደፈለሱ ተጽፎ አንብቤያለሁ............ለአድዋ ድል እጅግ ወሳኝ ሚና የተጫወቱት ባሻ አውኣሎም የጣልያን የስለላ ክፍል ባልደረባ ነበሩ.............የቁርጥ ቀን ሲመጣ ግን ጣልያንን ጉድ አርገውት ከ አጼ ሚኒልክ ጋ ማበር ብቻ ሳይሆን ለድሉ መገኘት ታላቅ አስተዋፅኦ አበረከቱ...........ስለኚህ ታላቅ ሰው ሳስብ የሚታየኝ ድፍረታቸው ብልሀታቸውና ላገራቸው ያላቸው ፍፁም ፍቅር እንጂ የጣልያን አገልጋይነታቸው አደለም.... ያንተን አላውቅም ቢያንስ ለኔ ጀግና ናቸው


ትልቅ ሥህተት እነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ከዚያ በፊት ሣይታወቁ ከኖሩ ከዚያ በኋላ እንዴት እንደእንጉዳይ ፈሉ ? አየህ እኒህን ሁለት ጀብደኞች (አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ) ከአቅማቸው በላይ እንዴት እንደካብኻቸውና ዋናዎቹን ጀግኖች እንዴት እንዳኮሠስካቸው ለመሆኑ እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ሽፍትነት የጀመሩት ጣሊያን ከገባ በኋላ ነበር ? ራስ አበበ አረጋይ እና ሌሎች በሸዋ : በጎንደር : በወሎ (በተለይ በላስታ እና አማራ ሣይንት ) የነበሩት አርበኞች ከዚያ በፊት በአርበኝነቱ ተግባራቸው ጭራሽ አይታወቁምም ነበር ማለትህ ነው ?ከተሳሳትኩ እታረማለሁ..........ማለት የፈለግኩት የአርበኞች ዝና መግነን የጀመረው ከየካቲት 12 በህዋላ ነበር ነው እንጂ የተጠቀሱት ስመጥር አርበኞች ህልውና ፈፅሞ አይታወቅም አልወጣኝም.....እነ አብርሀን ለማሞገስ ሌሎችን ጥላሸት መቀባት የለብኝም.........አብርሀና ሞገስ ጀግኖች ነበሩ ማለት በምንም መልኩ የበላይን ወንድነት አይቀይረውም............በነገራችን ላይ በላይ ዘለቀን ጨምሮ ሌሎቹም ጀግኖች አርበኞቻችን ንጉሱ አገሪቷን ጥለው ወደ ስደት ከመሄዳቸው በፊት ስለነበራቸው ታሪክ የምታውቀውን ብታካፍለኝ ደስ ይለኛል..........ታሪካቸው ጎልቶ የወጣው በአምስቱ የጠላት አገዛዝ አመታት ስለመሰለኝ ነው......ከተሳሳትኩ አሁንም ለመታረም ዝግጁ ነኝ

ንጉሡ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ .ም . አዲስ አበባ ከመናገሻው ከተማ የገቡበት ዕለት ነው :: መጋቢት 25 ቀን 1933 ዓ .ም . ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ በአምቦ መሥመር የነበረውን የጣሊያን መንጋ ድል አድርገው በአምቦ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ አውለብልበዋል :: መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ .ም . ጀግናው በላይ ዘለቀ ከ 20,000 የማያንስ ጦሩን አሠልፎ ንጉሠ ነገሥቱን ደብረማርቆስ ላይ የተቀበለበት ዕለት ነበር :: በዚያ ይስተካከል :: በእርግጥ መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ .ም . የእንግሊዝ ጦር አዲስ አበባን እና መቀሌን ቀድሞ ተቆጣጥሯል ::ለእርማቱ አመሰግናለሁ......መጋቢት 28 እና ሚያዝያ 27 ሁሌም ግራ ያጋቡኛል......አራት ኪሎ ያለውን የነጻነት ሀውልት ንጉሱ ሚያዝያ 27 ብለው ሰየሙት...ደርግ ደግሞ መጋቢት 28 አለው...ኢህአዲግ ደግሞ መልሶ በጥንት ስሙ ሚያዝያ 27 ብሎታል....የታሪክ አዋቂዎች ትክክለኛውን የነፃነት ቀን ቢያረጋግጡልን መልካም ነበር


እኒያን አሥር ቦምቦች በግራዚያኒ እና አጀቦቹ ላይ እስኪጥሉ ድረስ ግን በይፋ የፋሽስት ጣሊያን ባንዶች ነበሩ : ነገር ግን ጌታቸውን ጄኔራል ግራዚያኒን ለመግደል ከኢትዮጵያውያን አርበኞች ጋር አቅደው ሞከሩ : አልተሣካላቸውም :: ድርጊታቸው የቀቢፀ -ተስፋ የጀብደኝነት ተግባር ነበር :: እነርሱን ከሚገባው በላይ እያሞካሹ ዋናዎቹን ጀግኖች አርበኞችን ማኮሠስ ግን ለተተኪው ትውልድ የሚያስተላልፈው መጥፎ መልዕክት "ጀግና ማለት ከድሮ ጀምሮ ባንዳም ቢሆን በመጨረሻ ግን ለወገኖቹ እንደ እሣት -ራት አንዴ ታይቶ ራሱን ለጥፋት የሚያቀርብ እንጂ ሁልጊዜም አስቦና አመዛዝኖ ተገቢውን ተግባር በተገቢው ሥፍራ የሚፈጽም ሰው አይደለም :" የሚል ይሆና


ማንም ሰው ቢሆን ትናንት ባረገው ነገር ተፀፅቶ ወገኑን ለመካስ ቢነሳሳ ሊመሰገን ይገባዋል እንጂ በድርጊቱ ሲወገዝ መኖር የለበትም...........በመፅሀፍ ቅዱስ...የክርስቶስ አሳዳጅ የነበረው ጳውሎስ የክርስቶስ ተከታዮቹን አሳዶ በመግደልና በማስገደል ቀንደኛ ገዳይ ነበር.....ሆኖም በመጨረሻ ከዚህ ክፉ ድርጊቱ ተቆጥቦ የክርስቶስን ትምህርት በማስፋፋት ቁጥር አንድ ሀዋርያ ሊሆን በቅቷል.......ጳውሎስን ሳስብ የሚታየኝ ታላቅ የእምነት አባት መሆኑ እንጂ ነፍሰ ገዳይ እንደነበር አይደለም........እነ አብርሀ እና ሞገስን ከጳውሎስ ጋ ማወዳደሬ አይደለም.......ያንድ ሰው ያለፈ ማንነት ባሁኑ እሱነቱ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ አንዳንዴ ምንም ላይሆን እንደሚችል ለማሳየት ያቀረብኩት ምሳሌ እንደሆነ ይታወቅልኝ ዘንድ አደራ እላለሁ

አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የፈፀሙት ድርጊት ለጄኔራል ግራዚያኒ የጭፍጨፋ ዘመቻ በሩን ወገግ አድርጎ የከፈተለት የማደናገሪያ ምክንያት ነበር


እኔ ደግሞ እንዲህ አስባለሁ........ጀነራሉ አገሩን ጣልያንን ለቆ በመርከብ ሲሳፈር ከፋሽስቱ አውራ ከመሶሎኒ ቡራኬ ተቀብሎ.....''ኢታልያ ሆይ ባህርን ተሻግረን አዲስ ድንግል መሬት እናወርስሻለን" የሚለውን መዝሙር እየዘመረ....በዚህ ምኞቱ ላይ የሚነሳበትን ማንኛውንም አይነት ተቃውሞ አፈር ለማስገባት ምሎና ተገዝቶ ይህንን ህልሙን እውን የሚያደርግበት በአለም የተከለከለውን የመርዝ ጭስ ሳይቀር አስጭኖ ሴት ህፃን አሮጊት ሽማግሌ ሳይል ጨፍጭፎ ሊያስገብር ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነው

አብርሀና ሞገስ ቦንብ ወረወሩ አልወረወሩ.....እልቂቱ አይቀሬ ነበር......የአዲስ አበባን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ምንም አይነት ምክንያት አያስፈልገውም ነበር.....ማንን ፈርቶ ነው ለጭፍጨፋው ምክንያት የሚፈልግለት.. :!: .......ያደረገውም ይህንኑ ነበር........

በኃሣብ ያለመስማማት ይቻላል :: ውይይት ከተባለ ግን ሁላችንም በአንድ መሥመር መሄድ የለብንም :: ደግሞም 'ኢትዮጵያውያን እንዲህ የነገር ውሉ የጠፋብን ለምን ይሆን ?' ተብሎ ሲጠየቅ በታሪክ የተከናወኑ ድርጊቶችን እና ፈጻሚዎቻቸውን አንድ በአንድ ማስተንተን ይጠብቅብናል - እንደ መና ከሠማይ የሚወርድልን መፍትሔ የለምና :: ቢመረንም እንደ ኮሦ መድኃኒት ሃቅን ለመቀበል መድፈር ይኖርብናል ::


እስማማለሁ.......እንደኮሶ መድሀኒት ልትመር የምትችለዋን ሀቅ ለመቀበል መድፈር እንዳለብን ባምንም......ሀቅ ምንድናት ? በሚለው ጥያቄ ላይ ግን አሁንም መግባባት ያለብን ይመስለኛል.........
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Feb 28, 2012 9:54 pm

ሰላም ኤዶም* :-

ለረዥሙ የመልስ-መልስ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ :: የሚከተለውን ጥያቄህን ለመመለስ ያህል ነው ::

ኤዶም wrote:ለእርማቱ አመሰግናለሁ ......መጋቢት 28 እና ሚያዝያ 27 ሁሌም ግራ ያጋቡኛል ......አራት ኪሎ ያለውን የነጻነት ሀውልት ንጉሱ ሚያዝያ 27 ብለው ሰየሙት ...ደርግ ደግሞ መጋቢት 28 አለው ...ኢህአዲግ ደግሞ መልሶ በጥንት ስሙ ሚያዝያ 27 ብሎታል ....የታሪክ አዋቂዎች ትክክለኛውን የነፃነት ቀን ቢያረጋግጡልን መልካም ነበር::

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በብዙ የታሪክ ጸሐፊዎች በስፋት ተዘግቧል :: ቀኖቹን ለማመሣከር እኔ ይበልጥ የምመርጠው በዚያን ወቅት በዘመቻ ላይ የነበሩ አገሮች በጻፏቸው የየዕለት ዝክሮች (War Chronicles) ላይ ነው :: አንዱ ቢሣሣት በሌላው ምንጭ ማመሣከር ይቻላልና:: ለዚህ ጥያቄህ የሚከተሉትን የእንግሊዝ አገር ምንጮች ማመሣከር ትችላለህ ::

ምንጮች:-
1 ..... Neil Orpen, East African and Abyssinian Campaigns.South African Force, World War II, Volume I.

2 ..... British Forces War Operations in East Africa: 1940-41.

3 ..... British Military History - East Africa 1940 - 47.


በጣሊያኖችም ወገን ተመሣሣይ ታሪካዊ ሠነዶች ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests