የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Apr 07, 2012 12:48 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የዛሬ 71 ዓመት ጀግኖች ኢትዮጵያውያን አርበኞች የፋሽስት ጣሊያን ወራሪዎችን ድል አድርገው በመናገሻ ከተማችን በአዲስ አበባና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች ሠንደቅ ዓላማችንን በታላቅ ክብርና ግርማ ሞገስ ያውለበለቡበት ዕለት ነበር :: ዛሬ እኛም ይህንን ቀን ማክበር ይገባናል ::

ታሪካዊ ምንጮች:-
1 ..... UNESCO Archives. Patriots Day.

2 ..... Uploaded by ethioNiGisT on Feb 20, 2009. the Arbegna Belay Zeleke (drama).


ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby AddisMeraf » Sat Apr 07, 2012 6:47 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የዛሬ 71 ዓመት ጀግኖች ኢትዮጵያውያን አርበኞች የፋሽስት ጣሊያን ወራሪዎችን ድል አድርገው በመናገሻ ከተማችን በአዲስ አበባና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች ሠንደቅ ዓላማችንን በታላቅ ክብርና ግርማ ሞገስ ያውለበለቡበት ዕለት ነበር :: ዛሬ እኛም ይህንን ቀን ማክበር ይገባናል ::

ታሪካዊ ምንጮች:-
1 ..... UNESCO Archives. Patriots Day.

2 ..... Uploaded by ethioNiGisT on Feb 20, 2009. the Arbegna Belay Zeleke (drama).


ተድላ


ሰላም ተድላ

ይሄንን ታላቅ ቀን እንድናስብ ስላስታወስከን በጣም አመስግናለሁ:: በአሉን በማስመልከት VOA ያቀረበውን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ተጭናችሁ አዳምጡ::
AddisMeraf
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1615
Joined: Sun Nov 01, 2009 5:49 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Apr 08, 2012 4:27 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ሰላም 'AddisMeraf' :-

እንግሊዞች ከ71 ዓመታት በፊት መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ ኤፕሪል 6, 1941) አዲስ አበባ ሲገቡ የነበረው ሁኔታ ይህንን ይመሥል ነበር ::

ምንጭ:- The Fall Of Addis Ababa - Pathe Gazette… 1941.

ኢትዮጵያውያን አርበኞች ተንኮለኞችን እንግሊዞችን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ምድር ለማስወጣት ከ10 ዓመታት ያለነሠ ጊዜ ወስዶባቸው ነበር ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Apr 26, 2012 11:07 pm

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ታላቁ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ "እንኳን ሕዝቡ መሬቲቱም ለአንተ እንዳትገዛ ገዝቻለሁ ::" ብለው የፋሽስቶችን የግፍ የሞት ፅዋ ያለምንም ፍርሃት የተቀበሉ አባት ነበሩ :: ዛሬ : ዛሬ ምን ዓይነት አባት ተብየዎች እንደ አሸን እንደፈሉ እያየን ነው :: ለማንኛውም ዶክተር ታዲዮስ ታንቱ በየሣምንቱ በፍትህ ጋዜጣ 'የአውደ-ታሪክ' አምድ በሚያቀርቡት ሐተታ ያለፈው አርብ ዕለት የእኒህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ አርበኛ እና የሐይማኖት አባት ዘክረዋልና ያንን እንድታነቡት አዚህ አምጥቼዋለሁ ::

ለታሪክ ግንዛቤ :- የወያኔን ሕገ-አራዊት ያዘጋጀው የሟቹ የክፍሌ ወዳጆ አባት ነጋድራስ ወዳጆ አሊ የፋሽስቱ ፍርድ ቤት የግራ ዳኛ ሆኖ አቡነ ጴጥሮስ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ከፈረዱት አንዱ ነበር :: ባንዳ : የባንዳ ልጅ መሠረተ ባንዳ ማለት እንዲህ ነው ::

ምንጭ:- ታዲዮስ ታንቱ (ዶክተር) : ቅፅ 5 : ቁጥር 184 : ገፅ 14 :: አርብ ሚያዝያ 12 2004 ዓ.ም :: አርበኞች መሞትን ማን አስተማራቸው? ታላቁ ጴጥሮስ ነው ባርኮ የሰጣቸው - ለአቡነ ጴጥሮስ ከተቀኘው የተወሰደ::


ትኩሱን ደማቸውን ውሾች ልሰዋል። አሁን ቀዝቅዟል። ከአፈር ተዋህዷል። ጉንዳኖች ደግሞ ሰፍረውበታል። በተራቸው የቅዱሱን ደም ይዋኙታል። መስቀላቸው ከቀኝ እጃቸው አጠገብ ወድቋል። ግራ እጃቸው ከአምባር መዋያ መልስ በጭቃ ተለውሷል። ጥፍሩ እንኳን አይታይም! ልብሳቸውም በጭቃ ተለውሷል። ራሳቸው በጥይት ተፈረካክሷል። አንድ አሞራ እየበረረ መጥቶ በሬሳቸው ላይ ሊያርፍ ሲል በሰዎች ተባርሯል። መላ አካላቸው ደቅቋል። ዓይኖቻቸው ወደ አረንጓዴነት ተቀይረዋል። አፋቸው በመጠኑ ተከፍቷል። ሕዝበ ክርስቲያን በውስጡ ለውስጡ ያለቅሳል። ማን ሬሳቸውን ደፍሮ ያንሳ? የፋሽስቶች ውሳኔ በቅፅበት ተፈፃሚ ይሆንበታል። ሬሳቸው ተዘርሮ ውሏል። ለብዙ ሰዓታት ተኝቷል። የጨው ተራ አፈር በሐምሌ ዝናብ ቦክቷል። ሰዎች የጀግናውን ሐዋርያ ሬሳ ላለመርገጥ ሲጠነቀቁ ይስተዋላል። አንዳንዶች ግን በጉዳያቸው የህሊና ስሌት ተመስጠው ሲገሰግሱ ጭቃ በእጅጉ ያፈናጥሩበታል። ከመንገድ ዞር ለማድረግ እንኳን የፋሽስቶች ፈቃድ ሊወርድ ይገባል። ይህ ሳይደረግ ማን ይደፍራል? በገዛ ስሜቱ ስሜቱን ያስተናገደ ይገደላል! ሬሳው ውሎ ቢያድርም በዚያው ይቀጥላል!

በድንገት ግን ለውጥ ተስተውሏል። የጀግናው ሐዋርያ ሬሳ ተነስቷል። በቦታው አልነበረም። ማን ወሰደው? ሲያልፉ ያዩት ሲመለሱ አጥተውታል። ወስዶ የደበቀው ይታወቅ። የሁሉም ጥያቄ ሆኗል። የፍርድ ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ ደግሞ በጣም ተናድዷል። የሚቀበርበትን ቦታ መወሰን ፈልጓል። ምን ጉድ ነው እናንተዬ? ዳኛው ከመኻል ወንበር ተቀምጦ ቅጣቱን አፅድቋል። አገዳደሉም በትእዛዙ ተፈፅሟል። አሁን ደግሞ የቀብር ቦታ ምርጫ እንዴት የዳኛ ኃላፊነት ሊሆን ይችላል? የእኚህ ሐዋርያ ግፍ አልበዛም ትላላችሁ? ሬሳቸው ከተቀበረበት ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተቆፍሮ እንዲወጣ ተደርጓል። የዳኛውን ትእዛዝ ዳኛው ራሱ ካልቀለበሰው ማን ይቀለብሰዋል? ከከተማ ዳር ተወስዶ በምስጢር ስፍራ እንዲቀበር ለለማዳ አገልጋይ ባንዳዎች ትእዛዝ ወርዷል። በምክንያቱ ምክንያት በምስጢር ተወስዶ በድብቅ ከአፈር ውስጥ ገብቷል። አቡኑ በአደባባይ ተገድለዋል። ነፍስ አልባ ተክለ አካላቸው ግን በበድን ይዘቱ ተሰውሯል።

አርበኛውና ሐዋርያው ብፁዕ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል መገደላቸው በታሪክ ዓይን በቦግታ ይስተዋላል። ጥያቄ አይታሰብም! የባንዳዎች ሎሌያዊ ሚና ግን በደረጃው ዘወትር አለመታሰቡ ለምንድን ነው? ተገቢም አላስፈላጊም ጥያቄ መሆኑን አንጣ! በታሪክ ሐቅ ላይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ወግ የለም። እውነት እንደ ወረደ ለትውልድ ይውረድ! ባንዳ ከባዕዳን ወራሪ ባላነሰ ደረጃ ኢትዮጵያን ጎድቷታል። ታሪካችን ደግሞ ከባንዳና ከከሐዲ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ይህ ትውልድ የታሪካችንን ታሪካዊ ፍሰት አይጣ! ጀግኖች ሀገራችንን ጠብቀው ያቆዩት በየዘመኑ ባዕዳንና ባንዳዎችን ከትቢያ ጋር በማዋሐድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህ እውነት ነው! እውነትም ይህ ነው! ሌላ እውነት የለም!

ባሁኑ ሰዓት ዳኞች ከአንዲት ጥቁር አውቶሞቢል ወርደዋል። ከችሎት አዳራሽ አጠገብ ደርሰዋል። የመሐል ዳኛው ኢጣሊያዊው ኮንቴ ዴላ ፓርቶ ከፊት ሆኖ ሁለት ለማዳ አገልጋይ ባንዳ ኢትዮጵያውያን ተከትለውታል። ወደ አዳራሽ እየገቡ ነው! አሁን ሶስቱም ዳኞች ገብተዋል። ህዝቡ ለክብራቸው ከመቀመጫው ተነስቷል። አዳራሹ በጆሮ ጠቢዎች ተሞልቷል። ጆሮ ጠቢዎቹ ለማዳ አገልጋይ ወዶ ገባ ሆድ አደር ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ታውቋል። ጥቂት የውስጥ አርበኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በአሳማኝ የቋንቋ ቃና አቡነ ጴጥሮስን እያወገዙ ተሰምተዋል። ከጆሮ ጠቢዎች መካከል ኢጣልያኛ የሚናገሩ ከሁለት እንደማይበልጡ ለማወቅ ተችሏል። በችሎቱ ላይ ከፍተኛ የሐዘን ድባብ ይነበባል። ይነበባል! ይነበባል!

ኢጣሊያዊው የመሓል ዳኛ ፈገግ በማለት ህዝቡ እንዲቀመጥ ለወለሉ ትእዛዝ አወረደ። ወዲያው እሱም ተቀመጠ። ቀጥሎ የግራ ዳኛ ወንበር ይዟል። ነጋድራስ ወዳጆ ዓሊ ይባላል። ነጋድራስ ወዳጆ ዓሊ የክፍሌ ወዳጆ አባት መሆኑ ይመዝገብልን! የቀኝ ዳኛው በቀኝ ተቀምጧል! ብላታ አየለ ገብሬ ይባላል! የመኻል ዳኛውን ስሜት ይከታተላል! ባንዳ በጌታው ሳንባ ይተነፍሳል! ሕሊናውን በሊሬ የሸጠ ምን ሊሆን ይችላል? ነጋድራስ ወዳጆ ዓሊ በተፈጥሮአዊ ሞት ከዚህ ዓለም ተለይቷል። ብላታ አየለ ገብሬን ግን ታህሳስ 7 ቀን 1953 ዓ.ም. ብርጋዲዬር ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ ገድሎታል። እርግጥ ነው! በዕለቱ አርበኞችም ተገድለዋል። ለኀጥያን የመጣ ለጻድቃን ይተርፋል። የነዋይ ወንድማማቾች የግድያ የሒሳብ ስሌት ግን በዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር አይስማማም! የአምስት ዓመት አርበኞች የሃያ ዓመት ቀማኞች እንደ ነበሩ በሰንጠረዥ አስቀምጧል። ገዳዮቹ በግልፅ ናቡቴ መኳንንትን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማውረድ የሀገር ባለውልታ ጀግና አርበኞችን መጻረር እንዳልነበረ ተናግረዋል። ይህ የነዋይ ወንድማማቾች ድምፅ ነው! አንድ! ሁለት! አንድ! ሁለት! ይህ የነዋይ ወንድማማቾች ድምፅ ነው! ከአረንጓዴው ሣሎን!

አቡነ ጴጥሮስ ከወንበዴዎች ጋር በማበር ወንጀል ተከስሰዋል። ፍርዱ ምን ሊሆን ይችላል? አቡኑ ውጭ ተቀምጠዋል። እጆቻቸውን በረጅም ሰንሰለት ታስረዋል። ሁለት ለማዳ አገልጋይ ባንዳዎች በአጠገባቸው ቆመዋል። አንዱ ባንዳ ኢጣሊያንኛ ይናገራል። ሁለተኛው ጆሮውን ቢቆርጡትም አይሰማም። ዳኞቹ ለጥቂት ደቂቃዎች ሲወያዩ ቆይተዋል። የመኻል ዳኛው ሰዓቱን ተመለከተ። በመቀጠል ወደ ተቀመጠው ህዝብ አየ። ብዙም አልቆየም። ከቆሙት ኢጣሊያውያን ወታደሮች አንዱን ጠራው። ወታደሩ ቀረብ በማለት ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ እንዲገቡ እንዲያደርግ ታዘዘ። ወታደሩ በታዛዥነት አቋም ለሁለተኛ ጊዜ ለዳኛው ሰላምታ አበረከተ። ትእዛዙ ለአቡኑ ጠባቂዎች ከመቅፅበት ደርሷል። ጠባቂዎቹ አቡነ ጴጥሮስን ይዘው ተንቀሳቅሰዋል።

ትርጁማኖች ተነስተው ቦታቸውን ይዘዋል። ሁለት ናቸው። አንደኛው ደጃዝማች አርአያ ዋሴ የተባለ ሰው እንደነበር መረጃ ይዘናል። ሁለተኛው ደግሞ ፊታውራሪ ሮዛርዮ ተብሎ ይታወቃል። ሁለቱም ከማስተርጎም የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። አሁን አቡነ ጴጥሮስ ከችሎት አዳራሽ ገብተዋል። ታዳሚው ህዝብ ከንፈሩን ይመጥጣል። የመኻል ዳኛው በኢጣሊያንኛ የተደራጀውን የክስ ዝርዝር በደጃዝማች አርአያ ዋሴ አማካይነት ለአቡኑ ጴጥሮስ አሳውቋል። አቡነ ጴጥሮስ በደንብ ሰምተዋል። አቡኑ ምንም ነገር ቢመጣ በፀጋ ለመቀበል ወስነዋል። ለሀገራቸው ነፃነት፤ አንድነትና ሉዓላዊነት እንደማያቅማሙ ፍርጥም ባለ ቋንቋ መልስ ሰጥተዋል። እሳቸውም በአስተርጓሚ አንፀባርቀዋል። በዚህ የድፍረት መልስ የመኻል ዳኛው ተናድዷል። ወዲያው ሶስቱም ዳኞች አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ በመወሰን መዝገቡን ተመላሽ አድርገዋል። በፈጣን ችሎት አስቸኳይ ውሳኔ ተሰጥቷል። አለቀ!

ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. አቡነ ጴጥሮስ በጥይት ይደበድባሉ። ወሬው በመላው አዲስ አበባ ተሰምቷል። ቁርጥ ቀን ሆኗል። በዚያን ጊዜ ጨው ተራ ተብሎ ይታወቃል። ዛሬ ከማስታወቂያ ሚኒስቴር ሕንፃ ዝቅ ብሎ የሚገኝ ስፍራ መሆኑን እንወቅ! ከጧቱ ሶስት ሰዓት አንስቶ ጨው ተራ በሰው ተጨናንቋል። ጆሮ ጠቢው በበኩሉ ይርመሰመሳል። አራት ሰዓት ሲሆን አቡነ ጴጥሮስ በበርካታ ለማዳ አገልጋይ ባንዳዎችና በጥቂት ኢጣሊያውያን ወታደሮች ታጅበው ከጨው ተራ ደረሱ። ከፊታቸው ድፍረት ይነበባል። ዘለዓለማዊ መንፈሳቸውን ለሟች ስጋ ላለማስገዛት ፀንተዋል። እንደ አብርሃም በግ ተነድተዋል። አሁን ከተመረጠላቸው ነጥብ ስፍራ ደርሰዋል። ጥያቄ አልተነፈጉም። ዓይንዎት በጨርቅ እንዲሸፈን ይፈቅዳሉ? መልስ ለመስጠት አላቅማሙም። ፊታቸው ባይሸፈን ደስተኛ መሆናቸውን አረጋገጡ። ተኳሽ ጓድ ተዘጋጅቷል። አቡነ ጴጥሮስ ፊታቸውን ወደ መርካቶ አቅጣጫ እንዲያዞሩ ተደረጉ። ዓይኖቻቸው እንዳልተሸፈኑ ልብ በሉ! ስምንት ተኳሾች አንድ ላይ አነጣጠሩባቸው። አዛዡ ከጥቂት ጊዜአት በኋላ ትእዛዝ ይሰጣል። አቡነ ጴጥሮስ በልባቸው ፀሎት ላይ ናቸው። ‹‹አምላኬ ሆይ! ግፈኞች እኔን ባርያህን ሊገድሉኝ ተዘጋጅተዋል። ለሀገሬና ለሃይማኖቴ እሞታለሁ። ወዳንተ እመጣለሁ። ነፍሴን ተቀበላት። ሀገራችንን ጠብቃት።››

አዛዡ አሁን ጮኽ ባለ ድምፅ ትእዛዝ ሰጠ። ስምንቱም ነፍሰ ገዳዮች ተኰሱባቸው። አቡነ ጴጥሮስ ወደቁ። የሕክምና ክፍል አዛዥ በወደቁበት ገልብጦ ተመለከታቸው ነፍሳቸው ገና ከስጋቸው እንዳልተለየች አስተዋለ። ወዲያው ሽጉጡን መዝዞ በሶስት ጥይት ራሳቸውን አከታትሎ መታቸው። ሞተዋል።

አርበኛውና ሐዋርያው ብፁዕ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ የኢጣሊያን ገናናነት አምነው እንዲቀበሉ ብዙ ተለምነዋል። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪቃ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት መሆኗን አምነው ከተቀበሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪ እንደሚሆኑ ተነግሯቸዋል። ግን ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበሩም። ባንዳ መነኩሴ! ከመባል በላይ ምን ሞት አለ? የቪክቶሪ አማኑኤልን ንጉስነትና የቤኒቶ ሙሶሎኒን ቻንስለርነት ከዕውቅና እርከን አላሳደጉም። ከሮማ ውድ ዋጋ ያለው ሽልማት እንደሚጠብቃቸው ተገልጾላቸዋል። አቡኑ ግን በንቀት መልስ አልፈዋል። ውብ አውቶሞቢል በትእዛዝ ከኢጣሊያን ሀገር እንደሚመጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል። መልሳቸው ግን የተለመደ እምቢታ ሆነ። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሊሬ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል። አቡነ ጴጥሮስ ግን ምንም ዓይነት ቁሳዊ ሀብት አልለወጣቸውም። በአማላጅ ጋጋታ አልተበገሩም። ይልቁንም ምድሪቱም ጭምር ለጣሊያን እንዳትገዛ አወገዟት። የኢትዮጵያ ነፃነት አይገሠሥም! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐይማኖት አይረክስም! ይህ የአቡነ ጴጥሮስ ድምፅ ነው!! ሰማዕትነትን በድፍረት የተቀበሉት አርበኛውና ሐዋርያው ብፁዕ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ በመስከረም ወር 1868 ዓ.ም. በሰላሌ ዋና ከተማ በፍቼ ተወለዱ። በሕፃንነታቸው በጎሓ ፅዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትምህርት መጀመራቸው ታውቋል። በመቀጠልም በደብረ ሊባኖስ ትምህርታቸውን በስፋት ተከታትለዋል። ከዋሸራ በቅኔ መምህርነት ተመርቀዋል።

አርበኛውና ሐዋርያው አቡነ ጴጥሮስ እስከ 1921 ዓ.ም. ድረስ በየቦታው እየተዘዋወሩ አስተምረዋል። የአድባራት አለቃም ሆነው አገልግለዋል። በ1921 ዓ.ም. ወደ ግብፅ ሔደው ተሹመው መመለሳቸውም በህይወት ታሪካቸው ውስጥ ተወስቷል። ከግብፅ ሲመለሱ የመንዝና ወሎ ጳጳስ ሆነው ሰርተዋል። በ1928 ዓ.ም. ደግሞ ማይጨው ዘምተዋል። የወገን ጦር ወደ ኋላ ሲመለስ እሳቸውም ተመልሰዋል። ነገር ግን ትግላቸውን አላቋረጡም። ይልቁንም በግንደ በረትና በሰላሌ የተጠናከረ የአርበኝነት እንቅስቃሴ ያደርጉ ገቡ። በእርግጥ እሳቸው ራሳቸው ጠብመንጃ ይዘው ጥይት አጉርሰው በፋሽስቶች ላይ የተኩሱበት ወቅት አልነበረም። ነገር ግን ህዝቡን በማረጋጋትና አርበኞችን በማስተባበር በኩል ትልቅ ተግባር አከናውነዋል። መጠባበቂያ ጠብመንጃ ባለበት አካባቢ ደግሞ የመሳሪያ አጠባበቅ አመራር መስጠታቸው ታውቋል። አቡነ ጴጥሮስ የጀግናው የደጃች ባልቻ አባነፍሶ የንስሓ አባት እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

ፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ወቅት አንስቶ በተከታታይ ጳጳሳትን ቀሳውስትንና መነኰሳትን እንደ ገደለ ታሪክ በቂ ማስረጃ ይሰጠናል። በዚህም መሰረት በኢሊባቡር ውስጥ በጎሬ ከተማ አቡነ ሚካኤል ተገድለዋል። እንዲሁም አለቃ መርሻ ወልደማርያም ሶስት ጣሊያኖችን ደምስሰው ራሳቸውም መስዋዕት ሆነዋል። በደብረ ሊባኖስ ውስጥ ደግሞ 229 መነኩሳት ተገድለዋል። እንዲሁም 129 ዲያቆናትና መዘምራን በዚሁ በደብረ ሊባኖስ ውስጥ በግፍ ተረሽነዋል። ጄኔራል ግራዚያኒ ራሱ አረጋግጧል። ታሪክ ይናገራል።

በእውነት ስለእውነት እንናገር! አርበኛውና ሐዋርያው አቡነ ጴጥሮስ ንፁሕ የሐይማኖት አባት ነበሩ። የህይወት ታሪካቸው ይመሰክራል። ተምረውና አገልግለው በታላቅ ሰማዕትነት ወድቀዋል። ወንጀል አልሰሩም። ከባለስልጣናት ተመሳጥረው ጳጳስ ገልብጠው በትእዛዝ ጳጳስ አልተደረጉም። በውጭ ሀገር አልኖሩም። ሀብት ንብረት አልነበራቸውም። ለሆዳቸው ኖረው የሞቱ አድር ባዮችን እየመረጡ ፍትሐተ ፀሎት አላደረጉም። በሐይማኖት ፀንተው ከኖሩ አልተለዩም። አቡነ ጴጥሮስ በሕይወት ዘመናቸው እሳቸውን ወክላ መግለጫ የምትሰጥ የስጋ ዘመዳቸው የሆነች ሴት አላዘጋጁም። ለሟች ተክለ አካል መታሰቢያ በምዕመናን ገንዘብ የተሰራ ሐውልት አልነበራቸውም። ማንም የፈለገውን ሐይማኖት መከተል እንደሚችል በመስበክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ምዕመናንን ሐይማኖታዊ ሞራል አልተፈታተኑም። አቡነ ጴጥሮስ ለሐይማኖታቸው ኖሩ! ለሀገራችን ሰማዕት ሆኑ!

አቡነ ጴጥሮስ ታላቅ ሐዋርያ ነበሩ፡፡ ታላቅ ተግባር ፈፀሙ፡፡ በታላቅ ሰማዕትነት ወደቁ። እውነተኛ የሐይማኖት አባቶች በታላቁ ሐዋርያ በአቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊ ኩራት ይሰማችሁ!

ኢትዮጵያ እናታችንም ትኩራ!

አርበኞች መሞትን ማን አስተማራቸው?
ታላቁ ጴጥሮስ ነው ባርኮ የሰጣቸው::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jul 30, 2012 3:33 am

ሰላም ነገደ-አርበኛ ዘዋርካ :-

የዛሬ 77 ዓመት ሰማዕቱና አርበኛው አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ : በፋሽስት ጣሊያኖች ትዕዛዝ : በወያኔው ሎሌ ሟቹ ክፍሌ ወዳጆ አባት በእነ ደጃዝማች ወዳጆ አሊ ፈራጅነት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሥማቸው በተሠየመው አደባባይ አጠገብ ከኤርትራ ምድር በፈለቁ የጣሊያን ባንዳ ሹምባሾች የእሩምታ ተኩስ የተረሸኑበት ዕለት ነው ::

ምንጭ:- ስንክሳር- የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ : አርብ ሐምሌ 20 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ::

    ......«ሐምሌ 22 ቀን 1928 ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተንጠቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ «ተኩስ» በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቷቸው። ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው። .........
በ1875 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ። ወላጆቻቸው ዕድሜያቸው ገና በወግ ለትምህርት ሳይደርስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ባሕታዊ ተድላ ለተባሉ መምህር አደራ ሰጧቸው። በዚያው ገዳም የንባብ ቤቱንና የዜማውን የትምህርት ደረጃዎች በሚያስገርም ሁኔታ በአጭር ጊዜ አቀላጥፈው በመጨረስ ገና በልጅነት የዕድሜ ደረጃቸው ሦስተኛውን የቅኔ ትምህርት ጀምረው በአጭር ጊዜ ሙሉ ቤት ተቀኙ። ይህንኑ የቅኔ ትምህርት ለማስፋፋት በምዕራብ ጎጃም አገረ ስብከት ወደሚገኘው የቅኔ ትምህርት ማዕከል ዋሸራ ተሻግረው ለመምህርነት የሚያበቃውን ትምህርት ፈጽመው አስመሰከሩ።

ከዚያም ከቅኔው ዐውድማ ጎጃም ወደ ዜማው አዝመራ ጎንደር ተሻገሩ። በዚያም እንደ ቅኔው ሁሉ እስከ ማስመስከር ባይደርሱም የዜማውን ትምህርት በአጥጋቢ ሁኔታ ቀጸሉ። ከጎንደርም በወቅቱ ወሎ ቦሩ ሜዳ ከተባለው ቦታ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጻሕፍትን ምሥጢር በየዓይነቱ ሲመግቡ ወደ ነበሩት ስመ ጥሩው መምህር አካለ ወልድ ዘንድ በመሔድ ዋና ዋናዎቹን የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርቶች ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በብቃት አሔዱ።

ከዚህ በኋላ ልክ በ1900 ዓ.ም. እዚያው ወሎ አማራ ሳይንት በተባለው ቦታ ወደሚገኘው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም በመሔድ ወንበር ዘረጉ። በዚያው ቦታ ለዘጠኝ ዓመታት ያህል ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ።

በዚህ ዓይነት በመማርና በማስተማር ራሳቸውን በእግዚአብሔር ቃል በሚገባ ከጐሰሙ በኋላ በ1909 ዓ.ም. ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመሔድ ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ። ብዙም ሳይቆዩ ማዕረገ ቅስናን ተቀብለው ከወንበሩ አገልግሎት ጋር የቤተ መቅደሱን ተልእኮም ደርበው ያዙ።

በ1910 ዓ.ም. መምህር ኃይለ ማርያም ተብለው በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ተሾሙ። በ1916 ዓ.ም. እንደገና በዝዋይ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በመምህርነት ተሾሙ። በ1919 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አበ ንስሐ ሆኑ።

የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ አገረ ስብከት ተሾሙ።

በ1928 ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ አገራችንን ለመውረር ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት በማለት ውቅያኖስ አቋርጦ በመምጣት ኢትዮጵያን ሲወርና ሕዝቧን፣ ሊቃውንቷን፣ ገዳማቷንና አድባራቷን በግፍ ሲጨፈጭፍ ያዩት ብፁዕነታቸው ወራሪውን ኃይል ከኢትዮጵያውያኑ አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎት ሊዋጉት ቆረጡ። የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከአረመኔው ፋሺስት ጦር ጋር በመፋለም ላይ የነበረውን አርበኛ ለማበረታታት ወደ ማይጨው በሔዱ ጊዜ ብፁዕነታቸው ተከትለው ሔዱ። ከዚያ እንደ ተመለሱም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ተሰባስበው የቤተ ክርስቲያን አምላክ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጣውን ችግር እንዲያስታግሥ በጸሎት እየተጉ ወደነበሩት አባቶችና አርበኞች በመሔድ ለአገርና ለነጻነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ሁሉም እንዲጋደሉ ማሳሰብ እና ማትጋት ጀመሩ። ኋላም የገዳሙ መነኮሳትና የሰላሌ አርበኞች ይባሉ የነበሩት አርበኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተሳታፊ ሆኑ። ከዚያም አርበኞቹ የቻሉትን ሁሉ አድርገው ወደ ሰላሌ ሲመለሱ ብፁዕነታቸው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሳይቆዩ በጠላት እጅ ተያዙ።

ብፁዕነታቸው በተጠቀሰው ቀን በጠላት እጅ ከወደቁበት ቀን ጀምሮ በፋሺስት ኢጣልያ የጥይት እሩምታ በሰማዕትነት እስካለፉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሒደት የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞችና የታሪክ ጸሐፍት እንደሚከተለው ዘግበውታል።

«በኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፤ ተከታዮቼን ግን አትንኩ» የሚለውን ቃለ ምዕዳን ለገዳዮቻቸው ፋሺስቶች ያስተላለፉት ስለ አገር ነጻነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ክብር፣ ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ሲሉ በሰማዕትነት ያረፉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው።

ይህንንም የተናገሩት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ደኅንነት ሕይወቱን ለመስጠት በዚያች በመከራ ሌሊት ሊይዙትና ሊገድሉት ለመጡት ለሮማውያን ጭፍሮች “ማንን ትፈልጋላችሁ? እኔ እንደ ሆንኩ አለሁላችሁ። እነሱን ግን ተዉአቸው ይሒዱ” /ዮሐ. ፲፰፥፰/ ሲል በተከታዮቹ ላይ መከራ እንዳይፈጽሙባቸው የተናገረውን ቃል ለሕይወታቸው መመሪያ በማድረግ፣ መስቀሉንም ተሸክመው በኋላ ለመከተልና ፍኖተ መስቀሉንም ተጉዘው የሰማዕትነት አክሊል ለመቀዳጀት ነበር። ቆመው ሞትን በሚጠባበቁበት ጊዜ የዛሬ 75 ዓመት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. ነበር።

እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገባው ቺሮ ፓጃሊ “ከሪያሬ ዴስራ” የተባለው ጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረ ሲሆን ስለ አቡነ ጴጥሮስ የተሰጠውን ፍርድና የተፈጸመውን ግድያ ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር።

«ሐምሌ 22 ቀን 1928 አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዝያኒ ቀረቡ። በዚህ ጊዜ አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊው ጳጳስ ቀርበው ለእስክንድርያው መንበረ ፓትርያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ አንዳች ነገር ማድረግ አይገባህም ሲሉ ለግራዝያኒ ነገሩት። ምክንያቱም ይላሉ አቡነ ቄርሎስ፤ አቡነ ጴጥሮስ ታላቅ ሰው ናቸው። በመሠረቱ ሊያዙ ባልተገባ ነበር። ከተያዙም ደግሞ ልትገድላቸው ትችላለህ። ነገር ግን በርሳቸው ላይ የምታደርገውን ነገር ሁሉ ለእስክንድርያው መንበረ ፓትርያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ ምንም ማድረግ አይገባህም አሉት።

አቡነ ቄርሎስ ይህን ማለታቸው በዲፕሎማቲክ ደረጃ ለዓለም ለማሰማትና የአቡነ ጴጥሮስን ሕይወት ለማትረፍ አስበው እንደ ነበር ግልጥ ነው። ነገር ግን ግራዝያኒ ይህ የአቡነ ጴጥሮስ የሞት ፍርድ እንኳንስ እስከ ግብፅ ከአዲስ አበባ ውጭ እንኳ ከመሰማቱ በፊት በግማሽ ቀን እንዲፈጸም ትእዛዝ አስተላለፈ።

ጸሐፊው ሲገልጥ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር። በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ። ለፍርድም የተሰየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣልያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው። የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር። የቀረበባቸውም ወንጀል ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል የሚል ነበር። ዳኛውም «ካህናቱም ሆኑ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣልያን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?» ሲል ጠየቃቸው።
አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መለሱ። «አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለአገሬና ስለቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደ ወሰናችሁ ዐውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ» አሉ።

ኢጣልያዊው ጋዜጠኛ ቺሮ ፓጃሊ «እኒህ ጳጳስ ሐቀኛ ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣልያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርጐም በቀር ጳጳሱ የሚናገሩትን ሐቀኛ ንግግር አላስተረጐመም። እኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበባ ለሠላሳ ዓመት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ኃላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቤ ተቀምጦ ስለነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለገለጠልኝ ነው። እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተሰበሰቡት ጣልያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበባ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰሙ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር» ይላል።

ሆኖም አስተርጓሚው በጳጳሱ ላይ ተጽዕኖ ስላሳደረባቸው እውነተኛ ንግግራቸው ሳይገለጥ እንደ ቀረ ይጽፋል። ቀጥሎም ብፁዕነታቸው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለእርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ። ወዲያው የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣልያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር። ታላቅ ፍርሃትም በፊቱ ይታይ ነበር።

«ይሙት በቃ» የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሟቸው ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲቀመጡም ፈቀደላቸው። በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው። ብፁዕነታቸው እስከመቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ የሆነ ፍጹም የክብር ትሕትና ይታይባቸው ነበር።

የአገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተ ክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ ለመገደል ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይጐዳ ግንብ ይፈለግ ጀመር። ሩቅ ባለመሔድ ከመካነ ፍትሑ 10 ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ። ከገዳዮቹም አንዱ «ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?» ሲል ጠየቃቸው። «ይህ የአንተ ሥራ ነው» ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ። ከመግደያውም ቦታ እንደ ደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ።

ከዚያ በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተንጠቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ «ተኩስ» በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቷቸው። ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው።

የብፁዕነታቸው አስከሬን ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአዲስ አበባ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር እንዲቀበር ተደረገ። በዚያች ሌሊት በአዲስ አበባ ውስጥ በየቤቱ ልቅሶና ዋይታ ሆነ» ሲል ጽሑፉን ይደመድማል። ይህም ጠላት የሰጠው ምስክርነት በካቶሊካዊው ፓፓ ቡራኬ አገራችንን የወረረውን የፋሺስት ኢጣልያን ጦር አረመኔነትና በአንጻሩ የታየውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ጀግንነት ሲያረጋግጥ ይኖራል።

በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?» ሲል ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው እርሳቸውም የሚከተለውን ተናግረዋል። «አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም የያዙትን መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ። የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት። ወዲያው ወታደሮች በእሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው። ይህ እንደ ሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።

ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት «በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል» አለኝ። «እንዴት?» ብለው «አላየህም ሲያጨበጭብ?» አለኝ። እኔም «ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል» አልኩት። «እንዴት?» ቢለኝ እጄን እያጨበጨብኩ አሳየሁት። እሱም አሳየኝ። «ከዚህ በኋላ የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቻለሁ» ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ፣ የኪስ ሰዓታቸውን ጭምር አሳየኝ። መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተሰንጥቋል። መስቀሉም ልክ በመሐከሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል። የኪስ ሰዓታቸውንም እንዳየሁት እንደዚሁ ጥይት በስቶታል» ብለው ያዩትን መስክረዋል።» /ትንሣኤ፣ ቁጥር 58፣ 1978 ዓ.ም./

የብፁዕነታቸው አኩሪ ታሪክ ትውልድ ሲያዘክርላቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት ሐውልት ቆሞላቸዋል።

የተጋዳዩና ሰማዕቱ አባታችን በረከት ይደርብን። አሜን።

ምንጭ፦ ሐመር መጽሔት ግንቦት/ሰኔ ፲፱፻፺፮ ዓ.ም.
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Feb 18, 2018 10:30 pm

ተድላ ኃይሉ ባለህበት፦
የካቲት12 የሰማዕታት ቀን በደረሰ ቁጥር የማስታውሰው በዚህ ርእስ ሥር ያቀረብከውን ከአብዛኛው ኢትዮዽያዊ የተለየ አመለካከት ነው።ነገሩን ከተለያየ አቅጣጫ ለማየት ብሞክርም እስካሁን ድረስ አቋሜን ሊያስቀይረኝ አልቻለም።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1221
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re:

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Feb 19, 2018 5:44 am

ተድላ ሀይሉ
ሰላም ባለህበት እያልኩ ከአንተ ሃሳብ ጋር በሚገባ የምስማማበትን አየሁኝ፡፡እነዚህ ሰላማዊ ህዝብ መሃል ገብተው እስከጥርሱ የታጠቀ ጠላት ላይ ቦምብ የወረወሩ ለህዝባችን በበቀል መጨፍጨፍ ምክንያት ናቸው፡፡ገንጣይ ተገንጣዮችም ሰላማዊ ህዝብ መሃል ቤተክርስቲያን ሳይቀር ገብተው በደርግ ጦር ላይ ፈንጂ እየወረወሩ ህዝቡን አስጨፈጨፉ ተከታይ ጀሌ አበራከቱ ህዝባችንን በግፍ እስከዛሬ ገዙ፡፡ከዚህ በተጨማሪ የባንዳ ዘር ባንዳ የአስረስ የልጅልጅ መለስ ዜናዊ ክፉ ባንዳ ለምእራባዊያን ሎሌ ሆኖ ሃገራችንን ህዝባችንን ከፋፍሎ አባልቶ መቀመቅ ነጎደ ወዳጁ ክፍሌ ወዳጆም የባንዳ ልጅ ባንዳ እንዲሁ ወደጥልቁ ገባ ኢትዮጲያ ግን ለዘላለም በቅን ልጆችዋ ትከብራለች!

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-
ይህንን ዕለት ከሕፃንነቴ ጀምሮ የማስታውስበት ምክንያቱ ብዙ ነው :: ከሁሉም ከሁሉም እኔ ተፈጥሬ በሕይወት ኖሬ ዛሬ ከእናንተ ጋር ኃሣቤን የምለዋወጠው ኢትዮጵያዊ ላልፈጠር የምችልበትን አጋጣሚ ሣስበው ይገርመኛል :: ፋሽስት ጣሊያኖች ኢትዮጵያን በወረሩበት ዘመን ዋና ባለሟሎቻቸው የነበሩት የኤርትራና ትግራይ ሹምባሾች : የሊቢያና (ጥሩምቡሌ) የሶማሊያ ባንዶች ነበሩ :: እኒያ የጣሊያን ባንዶች ከጣሊያኖቹ የከፉ ጨካኞች እንደነበሩ አያቶቼ ታሪኩን በሚገባ ልቅም አድርገው አስጠንተውኛል ::

ከሃምሣ ዓመታት በኋላ የፋሽስቶች የመንፈስ ልጆች ሻቢያና ወያኔዎች በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ድጋፍ በኢትዮጵያውያን ላይ ዳግም የእጅ-አዙር ቅኝ አገዛዝ አሥፍነውብናል :: ታዲያ እነርሱም ከጌቶቻቸው ከፋሽስቶች በተማሩት ትምህርት መሠረት ሕዝብን በጅምላ እየጨፈጨፉ 20 ዓመታት አልፎ 21ኛውን ሊደፍኑ የቀሯቸው ከሦሥት ወራት ያነሠ ጊዜ ነው ::

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ለፋሽስቶች የጅምላ ጭፍጨፋ ምክንያት የሆኑት ሁለት የሀማሴን ተወላጆች የዕብደት ሥራ ነው :: አብርሃ ደቦጫና ሞገስ አስገዶም በተለምዶ ጀግኖች ተብለው ይወደሣሉ :: ነገር ግን ለእኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፋሽስት ጣሊያኖችን የጥፋት ዘመቻ ያስጀመሩ ክፉ መልዕክተኞች ናቸው :: የእነርሱ ድርጊት ሠበብ ሆኖ በሦሥት ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከ30,000 የማያንሱ ኢትዮጵያውያን በአሠቃቂ ሁኔታ በመጥረቢያ : በሣንጃና በመዶሻ እንዲሁም በቦንብና በመትረየስ እንዲጨፈጨፉ : ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ቤታቸው በእሣት እየተለኮሰ አብረው ተቃጥለዋል :: በመላ ኢትዮጵያም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል :: ለዚህ ሁሉ ሠበብ የሆኑት እኒያ የክፋት መልዕክተኛ የሆኑ ሁለት ኤርትራውያን ናቸው ::

የሀማሴን ሹምባሾች ተግባር ምን ያህል የዘቀጠ ባንዳነት እንደነበረ ታላቁን ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን በእሥር ላይ እያሉ እንዴት እንደገረፏቸው : በኋላም በአደባባይ እንደረሸኗቸው (ሥፍራውም ከአቡነ ጴጥሮስ ኃውልት አጠገብ በማስታወቂያ ሚኒስቴር አጥር ሥር ነው) ማስታወሱ ይበቃል :: በዚያ የጨለማ የፋሽስት አገዛዝ ዘመን የአክሱም ካህናት ጨፍጫፊውን ጄኔራል ግራዚያኒን በሽብሸባና በወረብ እንዴት እንደተቀበሉት ከሚከተለው የቪዲዮ ፊልም ተከታተሉት ::

ምንጭ:- Uploaded by LibiTigray on Nov 20, 2009. A Martyr of the Millenium ~ The story of Abune Petros.

ተድላ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 20, 2018 10:14 pm

አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶምን እንዲሁም ከእነርሱ ኋላ ሆነው ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያመቻቹላቸው የነበሩት በርካታ ስማቸው ብዙም የማይነሳ ተባባሪዎቻቸውን ቆራጥ የጀግንነት እርምጃ ማጣጣል ከታሪክ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋርም የሚያቃቅር አቋም ነው።በተለይም ያን ጊዜ የተፈጠረውን ከአሁኑ ሥርዓት የደህንነት አባሎች እኩይ ተግባር ጋር ለማመሳሰል መሞከር የሚያሳፍርነው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1221
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Feb 21, 2018 3:08 pm

የየካቲት ሰማእታት ምንጊዜም ሲዘከሩ ይኖራሉ ሆኖም ግን ያላስፈላጊ እልቂት በህዝቦች ላይ የሚያመጡ ጀብደኞችን በየዘመኑ ለተፈጠሩ እልቂቶች ተጠያቂነታቸውን መካድ አይቻልም፡፡ትናንት ጣሊያን በገፍ መሳሪያ ታጥቆ ሃገሪቱን በተቆጣጠረበት ወቅት ግብር ሊበላ የተሰበሰበ ምስኪን ህዝብን ጋሻ በማድረግ ብዙዎችን ያስጨፈጨፉ ከዚያም የደርግ እጅግ የታጠቀ ጦር ባለበት በሰላም የተሰበሰበ ህዝብ መካል ሆኖ ፈንጂ በመወርወር ህዝቦችን ማስጨረስ ዛሬም ወያኔ በሃያላኑ ከሚገባ በላይ ታጥቆ ሳለ ለጋ ወጣቶችን በሰላማዊ ህዝብ መሃል በማሰማራት ድንጋይ ወይም ፈንጂ ማስወርወር የከፋ ቅርስ መሆኑ ሊነገር ይገባል፡፡ከትክክለኛው በነማህተማ ጋንዲ በነማርቲን ሉተር ከተመራው ሰላማዊ ትግል የተለየ ጥፋት አምጭ የትግል ዘዴን ቅን ህሊና ያለው ወገንና ሃገር ወዳድ ሁሉ ከማውገዝ ወደሁውላ አይልም፡፡ተድላ በዚህ ጉዳይ የዘገበው በጣም ተገቢ መካሪ ጽሁፍ ነው፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: የየካቲትን ሰማእታት እንዘክራቸው!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 19, 2019 4:38 pm

ዛሬም እንደ ትላንቱ ተድላ ኃይሉ ዲጎኔና መሰሎቻቸው እንደሚሉት ሳይሆን አብርሃ ሞገስና ስምኦን አሸባሪዎች እንዳልነበሩ እንመሰክራለን።በነገራችን ላይ ፹፪ኛው የሰማዕታቱ ቀን በዛሬው ዕለት ፮ኪሎ በሚገኘው መታሰቢያ ሐውልት በርካታ ዜጎች በተገኙበት ታስቦ ውሏል።የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው በማኅበራዊ ሚድያ በተደረገ ጥሪ ከቀደሙት ዓመታት ቁጥራቸው በዛ ያለ ወጣቶችና ታዳጊዎች መገኘታቸው ነው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1221
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests