በፊደላችን ላይ የተቃጣ ዘመቻ...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Dec 08, 2012 2:23 am

ይኽኛውም በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩረው

http://quatero.net/pdf/amharic_fidelat2.pdf
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1174
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ምረቱ » Sun Dec 09, 2012 12:52 am

የዚህ የፊደል ጉዳይ ግራ የሚያጋባ ነው:: የዋቅጂራም ይሁን የደጋፊዎቹ ሀሳብ ፈጽሞ አሳማኝ እይደለም:: ሀዲስ ዓለማየሁም ቢሆኑ እንደተባለው ለፊደሉ አላስፈላጊነት እንደ ማስረጃ ሊቀርቡ አይችሉም:: አይገባምም::

ፊደሉ ምሉዕ ነው:: ይቀነሱ እየተባሉ ያሉትም ፊደላት በምክንያት በጥናት የመጡ እንጂ እንደሚታሰበው አላስፈላጊ አይደሉም:: በዚሁ አጋጣሚ እንዲህ መጽሀፍ እናጥባለን ብለው የሚነሱ የሀገራችን በሬዎች የሀገሩን ሰርዶ በዘዴ እንዲበሉ የተሰናዱም ሊሆኑ ይችላሉ:: ማን ያውቃል::

ቁም ነገሩ ግን ያስፈልጋልም እያስፈልግምም በሚባል ጉዳይ ላይ እና ጉዳዮን ለማሳካት በሚፈጠር ዘመቻ 'ያውቃሉ" ተብለው የሚታሰቡ ሰዎችን በነሲብ ከመከተል ማስተዋል እና በጥሞና ማስተዋል ያስፈልጋል:: በሆያ ሆየ ትርጉም ያለው ለሀገር የሚጠቅም ስራ ይሰራል ብየ እላምንም::

እውነትም ዶ/ር... ዋቅጅራ ወይ "ካላዋቂ ሳሚ..." የሚመደብ ነው ወይ ደሞ "የእዘማኞች" ፈረስ ሊሆንም ይችላል( በዚህ ጉዳይ ላይ ማለቴ ነው::)

ምረቱ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ፊደል እንደ ገና ወሌ ነጋ

Postby እንሰት » Wed Dec 12, 2012 8:42 pm

የፊደልና የአማርኛ ጠበቃው ቅዥቢ ሁለተኛ = ዳግማዊ ቅዝቢው ይህንን ርእስ ከፍቶ ቁጭቱን ንዴቱን እስከ ርግማን በደረሰ ጽሁፍ አስነብቦናል::

ጠበቃው ያልኩበት ምክንያት አማርኛን ሲዘነጣጥሉ ያገኛቸውን በሙሉ እየተከታተለ ስለሚያነሳ እና ስለሚጥል ነው::

ከነ ዲባቶ በድሉ ዋቅጅራ ፊደል ይቀነስ የሚሉ
ከነ ዲባቶ መስፍን አረጋ አማርኛ ከሁሉም የሀገራችን ቁዋንቁዋዎች እየተዋሰ አማርኛ መባል ያለበት አማ(ኦ)ሮምኛ = ሰገላዊ አማርኛ ከሚሉት (በአቁዋም ደረጃ የዲባቶ መስፍንን ስራ አደንቃለሁ ከስያሜው በስተቀር)::

ባለፈው እንደ ጻፍኩት አይቀነስ ከሚሉት ወገን ነኝ::
ትልቁ የዚህ ዘመን ችግራችን አይቀነስ የምንለው ወገኖች ቀሳውስቱም ካህናቱም ቢሆኑ የፊደሉን ስራት በትክክል አለማስተማራቸው ሲሆን ራሳቸውም ቢሆን የማያውቁበት እንዳሉ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገልጸዋል::

መፍትሄ መፍትሄ መፍትሄ
ወቀሳ ብቻ ሳይሆን ውዳሴ የሚገባ ሰውም አግኝቻለሁ ወሌ ነጋ ይባላል::
የዋዜማ ማስሊያ ፈብራኪ ነው:: አርታኢ ነው:: ፊደል ጠባቂ ነው:: አስተማሪ ነው:: ቸር ነው::

ስራዎቹን እዚህ እዩለት
http://gzamargna.net/
እንደኔ እንደኔ ቡክ ማርክም ማድረግ አለባችሁ!!!

ዳግማዊ ቅዥቢ ስማ ስማ ስማ ላልሰማ አሰማ

አርታኢ ነው ላልኩት ::
ርእስት፤ዐዲስ፡ያማርኛ፡መዝገበ፡ቃላት።

ደራሲ፤ደስታ፡ተክለ፡ወልድ።(አለቃ)

ርእስ፤ዐማርኛ-ዐማርኛ፡መዝገበ፡ቃላት።

ኅትመት፤አርቲስቲክ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥1962፡ዓ.ም.፤1285፡ገጽ።


አርትዖት፤

ፊደል፡ይጠነቅቃል፤
አገባብ፡ይጠነቅቃል፤
ትርጕም፡ይጠነቅቃል።

ዐማርኛ፡መጽሐፍ፡ቅዱስ። (የኢትዮጵያ፡ኦርቶዶክስ፡ተዋሕዶ፡ቤተ፡ክርስቲያን።)

አርእስት፤ዐማርኛ፡መጽሐፍ፡ቅዱስ።

ደራሲ፤የኢትዮጵያ፡ኦርቶዶክስ፡ተዋሕዶ፡ቤተ፡ክርስቲያን።

ርእስ፤ዐማርኛ፡መጽሐፍ፡ቅዱስ።

ኅትመት፤ካይነተኛው፡መጽሐፍ፡ቅዱስ፡በማስሊያ፡ተለቅሞ፡በHTMLና፡በPDF፡አቀጻጽ፡የተዘጋ ጀ።2002፡ዓ.ም.።

አርትዖት፤

ፊደል፡ይጠነቅቃል፤
አገባብ፡ይጠነቅቃል፤
ትርጕም፡ይጠነቅቃል።

የፊደል የስራት ጠበቃ አስተማሪ ለጋሲ ነው ላልኩት
ብዙዎቻችን፡ስላላከበርነው፡እንጂ፥የግእዝና፡ያማርኛ፡አጻጻፍስ፡ጥብቅ፡ሥርዐት፡አለው፤ሥርዐቱም፡
ቅን፣ገር፣ተገቢ፡እንጂ፥አንዳች፡ጠማማ፣ወልጋዳ፥ወይ፡ማስረጃ-አልቦ፣ልብ፡ወለድ፡ነገር፡
የለውም።በዚህ፡ምክንያት፥በላዩ፡ታላቅ፡"ሕንጻ"፡ሊታነጽበት፡ይችላል።የማንኛውም፡ያማርኛ፡ወይ፡የግእዝ፡
ቃል፡ተገቢ፡አጻጻፍ፡ዅል፡ጊዜም፡ቢኾን፡አንድና፡አንድ፡ብቻ፡ነው።ለምሳሌ፥"ሥርዐት"፡የሚለውን፡ሳቢ፡
ዘር፥በስምንት፡ዐይነት፡መንገድ፡መጻፍ፡ይቻላል፦
ሥርዐት  ስርዐት 
ሥርዓት  ስርዓት 
ሥርአት  ስርአት 
ሥርኣት  ስርኣት 
ተገቢው፡ግን፡የመዠመሪያው፡"ሥርዐት"፡ብቻ፡ነው።ዘሩ፡"ሠርዐ"፡ስለ፡ኾነ፥"ሳቱ-ሰ"ና፡"አልፉ-አ"፡
ተገቢነት፡የላቸውም፤ከዚህ፡ወዲያ፥"ዐይኑ-ዐ"ም፡ቢኾን፥ተገቢው፡ግእዙ-ዐ፡እንጂ፡ራብዑ-ዓ፡ስሕተት፡
ነው።ለምሳሌ፥
ዘሩን፡ "ሰመረ"፡ ብሎ፥ ሳቢ፡ዘሩን፡ "ስምረት"፡ እንጂ፡ "ስምራት"፡ አይሉም።
ዘሩን፡ "በለጠ"፡ ብሎ፥ ሳቢ፡ዘሩን፡ "ብልጠት"፡ እንጂ፡ "ብልጣት"፡
አይሉም።
እንደዚሁ፥
ዘሩን፡ "ሠርዐ"፡ ብሎ፥ ሳቢ፡ዘሩን፡ "ሥርዐት"፡ እንጂ፡ "ሥርዓት"፡ አይሉም።
ወዘተ.።ራብዑ፡የሚውለው፡ብዛትን፡ለማመልከት፡(ም.፤ብዙኅ፥ብዙኃን/ብዙኃት)፥ወይም፣እላይ፡(1.7)፡
እንዳየነው፥በሣልስ፡ቅጽል፡(ም.፤ጸሐፈ፥ጸሓፊ፤ገበረ፥ገባሪ)፡ነው።

መደምደሚያውን፥የግእዝንና፡ያማርኛን፡አጻጻፍ፡ሥርዐት፡በመንገዱ፡ቢከተሉት፥ከቀላልነቱ፡
የበለጠ፥ምስጢርን፡መግለጹ፣አእምሮን፡ማነጹ፣ዐሳብን፡ማደርጀቱ፣አስተሳሰብን፡ማስፋቱ፣ነገርን፡
ማገናዘቡ፣ጥቅሙ፡በጠቅላላው፡እጅግ፡ስለ፡ኾነ፥ዅል፡ጊዜም፡በደስታ፡ይመላለሱበታል፤ከዚያም፡ወዲያ፡
የፊደል፡ስሕተት፥እንደ፡ነውር፡ዅሉ፥ያጸ፟ይፋል፣ያሠ፟ቀጥጣል።አለመንገዱ፡ግን፥ዐቀበት፡ነው፤አይዘለቅም።

ወሌ ነጋ አስተማሪነቱም ለጋሲነቱም እንዲህ ይገለጻል::

ዋዜማ፡ሥርዐት፥ለሕዝብ፡አገልግሎት፡ይፋ፡በወጣ፡7ኛ፡ዓመቱ፡(ሐምሌ፡1999፡ዓ.ም.)፥ ማይክሮሶፍት፥በታሪኩ፡ለመዠመሪያ፡ጊዜ፥የኢትዮጵያን፡ፊደሎች፡ያከለ፡'ኒያላ'፡የተሠኘውን፡ቅርጸቱን፡ባዲ ሱ፡በ'ዊንዶውዝ፡ቪስታ'፡ምግባሩ፥በUnicode፡አቀማመር፡ላገልግሎት፡አብቅቷል።
Unicode፥ትንሽ፣ትልቅ፡ሳይል፥በዓለም፡ላይ፡አሉ፡የሚባሉትን፡የጽሕፈት፡ሥርዐቶች፡ወይም፡ጻሕፎች፥(ለምሳሌ፥የሮማይስጥ፣ያረብኛ፣የዕብራይስጥ፣የጽርዕ፣የመስኮብና፡የመኻል፡አውሮፓ፣የቻይና፣የህንድ፣የጃፓ ን፣የሞንጎሊያ፣የኮሪያ፣የታይላንድ፣ወዘተ.)፡በነቂስ፡የቀመረ፡እንደመኾኑ፡መጠን፥በሥራ፡ላይ፡መዋሉ፡ለማስሊያ፡ኪነት፡እድገትና፡መስፋፋት፡እጅግ፡ይ ረዳል፤ለኅርመተ፡ብዙው፡የኢትዮጵያ፡ፊደልም፡ታላቅ፡መፍትሔ፡ይኾናል።የUnicode፡አቀማመር፡አጠቃላይነት፡ ባንድ፡ሰነድና፡ባንድ፡ቅርጸት፡የዓለምን፡ፊደላት፡በሙሉ፡ለማስፈር፡ስላስቻለ፥ይህ፡ለረዥም፡ዘመን፡ሲታለ ም፡የኖረ፡ዐቅም፥እንሆ፥ዛሬ፡እውን፡ኾኖ፥ዋዜማ፡ሥርዐትም፡በዚሁ፡ደገ፟ኛ፡ድርስ፡ደንበኞቹን፡ለመጥቀም፥ የቀድሞውን፡ጠባቡን፡የANSI1፡አቀማመር፡ወደ፡ዃላ፡ትቶ፥ባዲሱ፡የUnicode፡አቀማመር፡ዋዜማ፡ሥርዐት፡ክለ ሳ፡2.2ን፡ይፋ፡በማውጣትና፡በነጻ፡በመናኘት፥ከዘመኑ፡ጋራ፡ወደ፡ፊት፡ተረማምዷል።

ወሌ ነጋ እኛ እንድንጠቀምበት ብሎ 107 ገጽ ያለው መጽሀፍ መመሪያ ውሰዱና ተጠቀሙ ግን በነጻ ያገኛችሁትን ለሌላ አትሽጡ እንዳገኛችሁ ስጡ ይላል::

http://gzamargna.net/sened_Wazema_memeriya.pdf

ኢሜሉን አላገኘሁም
ስልክ አለው +44 2082512492 አመስግኑት::
እኔም አደርጋለሁ::
ሰናይ የስራ ሳምንት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Thu Dec 13, 2012 12:27 am

እንሰት ሆይ ምስጋናዬ ይድረስዎ!
በነገራችን ላይ እኔ ለቋንቋ ጥብቅና 'ሚያበቃ ክህሎት የለኝም::የተሰማኝን እንደወረደ ነው 'ማወርደው::እርግጥ ነው ቃላቶቼ የወረዱ እኔም ወራዳ ቢጤ ነኝ::ቢሆንም...ቢሆንም...የተሰማኝን ከማለት ወደኌላ አልልም::አዩ እንሰት ጨለፍ ያደርገኛል...ጩህ ...ጩህ ይለኛል...እነ መረሳ(መረሳ የትግሬ ስም ነው)እና ረጋሳ አምሐራና አምሐርኛ ላይ የመዘዙትን ሰይፍ ወደ አፎቱ እስካልመለሱ ድረስ ጩኸቴን አላቆምም::
ስሙን ቄስ ይጥራውና መስፍን አረጋን ጠሩብኝ ልበል?ይህ አሰዳቢ...አለ ዘሩ በቀል...ይሀ የሳላይሽ ቦርከናና ግሙሀ ጂኒዎች ትራፊ..ይሄ ቢጩ...ቆይ ብቻ...የመስፍኔ ስራ ሴራ ነው::የሱ ፍልስፍና ቋንቋ አወራራሽ ሳይሆን ጅምላ ጨራሽ ነው::መስፍን ስለ ቋንቋና ባሕል ተወራራሽነት ለመጻፍ የሞራል ብቃት የለውም::ምክኒያቱም ለዓረብኛና ፈረንጅኛ መረን የለቀቀ ጥላቻ አለውና::በዚህ ጉዳይ ላይ በደምብ ቅሜ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ::
ወደ ኦቦ ዋቅጅራ ልጅና መሰሎቹ ልመለስና እንደ ደም ብዛት ሁሉ በፊደል ብዛት ጤናችን ታወከ ላሉ ጤና ቢሶች ይረዳ ዘንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከዓመታት በፊት እንደ ዘበት ጣል ያደረጓትን ይችን አጭር መለእክት ዱቅ አድርጌ ወደ በርጫ ተራ ልሸብለል:-
"...They do not invent more than one symbol for a sound. In other words, there were initially as many symbols as there were linguistic sounds that the inventor observed in the language for which he tailored an alphabet. In the course of time some sounds disappear from the language (leaving their symbols behind) while new ones could appear.This is what happened to Amharic. Invention of new symbols or modification of the existing ones would solve the second problem, as Amharic, indeed, did. But what do people do in the first case? You would say they should discard the symbols of the disappeared sounds. They do not need them if their sounds are not there. Well, that is not as easy as it sounds. For one thing, the books preserve them.The sounds have indeed disappeared, but not the words. So how would a literate person in Ge'ez and Amharic read the books with letters that he has not been taught? Second, there is a sentimental attachment to them. I, for one, will miss them as much as one would miss an aspect of one's culture.
Yes, there is lack of uniformity in spelling Amharic words. I have seen many letters addressed to me with my father's name (ኃይሌ) spelled in endless (and awful) ways. However, the dispute is not because there was no uniformity in the mind of the people who invented them but because of the ignorance of their users today.They confuse them because no one taught them how to use them.Just imagine an English-speaking child taking up writing a composition the day after he mastered his a, b, c! He would not go very far, not anywhere near what a child who mastered his ሀ...ለ...ሐ...መ...would do, which is what we do. As soon as we know the fidel , we write Amharic, without learning how to spell Amharic words. Our problem is how to use these few letters. We need teachers to make us literate before we complain. Our problem is not different from that of the Israelites. Unlike the Arabs, we (and the Israelites) have lost the linguistic sounds that were supposed to be represented by five symbols -- the two of the three "ሀ"s , one of the two "አ"s , the one of the two "ሰ"s , and the one of the two "ጸ"s . And unlike the Israelites -- who preserve them, learning how to use them -- we proposed to discard them because we are not literate in them.The effort should not be how to eradicate letters but illiteracy.
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Sun Dec 16, 2012 5:02 pm

አምሐሮችን 'ንጅ አምሐርኛን መግደል አይቻልም!
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Postby እናመሰግንሃለ » Sun Dec 16, 2012 9:07 pm

ጋሽ በድሉ ሆይ!

ኤርትራዎች አፋሮች ሶማሌዎች ደቡቦች: ግፉአን ጥቁር ዐረቦች: ሕንዶች ቻይናዎች: በርበሮች ደንከሎች ኑብያዎች ምኖችና ምኖች ሁሉ--- ለወደፊት ከተገነጠሉ ደግሞ ትግሬዎችም: ደግሞ ካሪብያኖች:ላቲኖች: ጥቁር አሜሪካኖች ዙሉዎች ..... ብቻ ምን አለፋህ.... የአዳም ዘር በሙሉ: በተለይ "ተበደልን!" "ተጨቆንን!" "ተሰደብን" "ተናቅን" ብለው የሚያስቡ ሁሉ: ከሉላዊነት ጋሻ ጃግሬዎች ከምዕራባውያን ጸረ-ክርስቶሶች ጋር ታግለው በመጨረሻ የሚያሸንፈዉን ኢትዮጵያዊነት ሲያጸኑ: ገና ተናድደው በአማርኛ ፊደል ካልሆነ አንጽፍም የሚሉበት ጊዜ ይመጣል:: አሁንም በግለሰብ ደረጃ የሚወራጩ ከመካከላቸው ብዙዎች አሉ:: እና: ሲመጡ: አሓይ ኡሁይ ዋይ ኻይ ኸራይ ዅዅዅ ሕሕሕኅሀኁኡዋይ ህእህእህ እያሉ ስንትና ስንት ድምጽ ይዘውብን ይመጣሉ:: እናንተ ሊቆቹ ገና ድምጾች ፈጥራችሁ ትጠብቁናላችሁ ብለን ስናስብ: ጭራሽ ያለውን ልታጠፉብን ትቃጣላችሁ? You should be fired :!: :!:
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

የ ዲባቶ አምሳሉ አክሊሉ መፍትሄ ያዋጣ ይሆን

Postby እንሰት » Tue Dec 18, 2012 5:39 am

ኢትዮጵያ የቋንቋና ፊደል ድንጋጌ ባለማውጣቷ በዘፈቀደ እየተጻፈ መሆኑ ተጠቆመ

ኢትዮጵያ የጽሕፈት ጥበብ ባለቤት ከኾነች ሦስት ሺሕ ዓመታት ብታስቆጥርም እንደሌሎች አገሮች እስካሁን ለቋንቋዎቿና ፊደሏ ድንጋጌ ባለማውጣቷ በዘፈቀደ እየተጻፈ መሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ አስታወቁ፡፡

የሥነ ቋንቋ ምሁሩ ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ "የአማርኛን ሞክሼን ሆሄያት ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ የጽሕፈት ጥበብ ባለቤት የሆነችው ከክርስቶስ ልደት ከ1000 ዓመት ገደማ በፊት ቢሆንም፣ ከሷ በኋላ የዚህ ጥበብ ባለቤት የሆኑ ብዙ አገሮች ለቋንቋቸውና ለፊደላቸው የማያወላውል ድንጋጌ ስላወጡለት ያወጡትን ድንጋጌ አክብረው ይሠሩበታል፤ እኛ ግን እስካሁን ድረስ እንዲህ ያለን ሥርዓት ለመደንገግ ሳናስብበት ስለቀረን በዘፈቀደ እንጽፋለን፡፡ ሌሎችም እንደኛው በዘፈቀደ የጻፉትን ቅር ሳይለን እናነባለን፡፡

ከዚህ በፊት ለዚህ ጉዳይ አትኩሮት የሰጠ አካል ባለመኖሩና እንዲሁም መመርያም ስለሌለ ማንም እንዳሻው አድርጎ ቢጽፍ የሚወቅሰውና የሚከሰው የለም ያሉት ዶ/ር አምሳሉ፣ ይህ ሁኔታ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን በግእዝም ቋንቋ እየተለመደ መሔዱን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መርሐ ልሳን [ካዴሚ] በ1973 ዓ.ም. ካወጣው የአጻጻፍ ሥርዓት ውሳኔ በስተቀር ሌላ ወሳኝ ጥናት ባለመደረጉ፣ ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ሊሆን የሚችሉ መምህራንንም ስለዚህ ጉዳይ ሆን ብሎ ያስተማራቸው ሰው ባለመኖሩ እነሱ ራሳቸው በዘፈቀደ ስለሚጽፉ ተማሪዎቻቸውም የነሱን ፈለግ በመከተል በዘፈቀደ ይጽፋሉ፤ የሚሉት ዶ/ር አምሳሉ፣ አንዳንድ ወገኖች ሞክሼ ሆሄያት ከፊደል ገበታው እንዳይወገዱ አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡ ዋናው አቋማቸውም፣ “ከአባቶቻቸን ተያይዞ የመጣልንን ፊደል አክብረን እንደ ታሪካዊ ቅርሳችን በማቆየት ፋንታ ይህን እንጣል፤ ያኛውን እናቆይ፣ ማለት በረጅሙ የሥልጣኔ ታሪካችን ላይ ይቅርታ የማይደረግለት ትልቅ በደል እንደ መሥራት የሚቆጠር ነው” የሚል ነው ብለዋል፡፡

ምሁሩ በመፍትሔነት ባቀረቡት ሐሳብም፣ የሁለቱንም ወገን ፍላጎት ለማመቻቸት የሚከተለውን መንገድ መያዝና አማራጭ የሌለውን መንገድ መከተል እንደሚያስፈልግ፣ ከሞክሼ ሆሄያት ውስጥ በአንዱ ብቻ መጻፍ ያለበት አንድ ቃል በአንድ ዓይነት የአጻጻፍ መንገድ ብቻ መጻፍ አለበት የሚለውንም ጠቅሰዋል፡፡ አያይዘውም፣ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ዕውቀቱ ያላቸው ሰዎች አንድ ቃል በእነዚህ ፊደላት ብቻ መጻፍ አለበት ብለው፤ የቃላት መድበል ሲያዘጋጁልን ያንን ተከትለን መጻፍ እንችላለን፡፡ ከዚያ ውጭ ከጻፍን ግን ስሕተት እንደሠራን ስለሚቆጠርብን ጠንቅቀን እንጽፋለን ማለት ነው በማለት አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡

በሔኖክ ያሬድ
http://www.ethiopianreporter.com/life-art-culture
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 25, 2012 1:13 pm

ሞክሼ የአማርኛ ፊደላት እና የባለሙያዎች ማብራሪያ ክፍል ሁለት
የሄኖክ ስብስብ(henoksitotaw65@gmail.com)
ታህሳስ 2005ዓ.ም

. . . ጥናታዊ ታሪኩ
የግእዝ ቋንቋ ጥናታዊ ወይም ሳይንሳዊ ታሪክን ስንመለከት ቋንቋው ከኢትዮጵያ ሴማውያን ቋንቋዎች ማለትም ከሳባ' ትግረ' ትግርኛ' አማርኛ' ጉራጊኛ' አርጎብኛና ከመሳሰሉት ጋር ተደምሮ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ በሴማዊያን ቋንቋዎች ምድብ አረቢክ' አካዲያንና ከነዐናይትን (ዕብራይስጥ' ፍንቄ) የመሳሰሉት ጥንታዊ ቋንቋዎች ይገኛሉ፡፡
ፊደላተ ግእዝ
አዳም ሞተ ልቦናን ከሞተ በኋላ የጠፋበት የቋንቋና ፊደላት እውቀት (እንደ አንዳንድ ሊቃውንት አገላለጽ) በፀፍፀፈ ሰማይ ለሴት ተገለጸለት፤ ሴትም በአባቱ ምክንያት ሞተ ልቦናን ሞቶ ስለነበር ከጊዜ በኋላ ጠፋበት፡፡
እግዚአብሔር አምላክም በድጋሚ በፀፍፀፈ ሰማይ ለሄኖክ ፊደላትን ገለጸለት፡፡ ሄኖክም እንደ አያቶቹ እንዳይጠፋበት በሸክላ የፊደላቱን ቅርጽ ቀረጸ፡፡ እነዚህ ፊደላት የግእዝ ፊደላት ናቸው ብለው የሚከራከሩ እንዳሉ ሁሉ ከሴማውያን ቋንቋዎች የአንዱ (በተለይም የዕብራይስጥ) ናቸው የሚሉ አሉ፡፡
በቅርጽ ስናያቸው የሴም ቋንቋዎች ፊደላት ተመሳሳይ ቅርጽ አላቸው፡፡ የግእዝ ፊደላት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ' ለ' ሐ' መ' ሠ' ረ' ሰ' ቀ' በ' ተ' ኀ' ነ' አ' ከ' ወ' ዐ' ዘ' የ' ደ' ገ' ጠ' ጰ' ጸ' ፀ' ፈ' ፐ
- ጰ እና ፐ ድምፃቸው የግሪክ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ሞክሼ ፊደላት እና ልዩነታቸው
ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት ሀ' ሐ' ኀ ሠ' ሰ አ' ዐ ጸ' ፀ ናቸው፡፡ እነዚህ ፊደላት የድምፅም'የቅርጽም' የትርጉምም ልዩነት አላቸው፡፡
የድምፅ ልዩነት

ሀ' ሐ' ኀ
ሀ - ላልቶ ይነበባል
ሐ - ጠብቆ ይነበባል
ኀ - በጉሮሮ ይነበባል
ሠ' ሰ
ሠ - እንደ ሸ ይነበብ ነበር
ሰ - በጥርስ ይነበብ ነበር
ለምሳሌ፡- ንጉሥ ብለን ነጋሽ እንላለን፡፡ ይህም ሠ እንደ ሸ ይነበብ እንደ ነበር ያስረዳል፡፡
አ' ዐ
አ - ላልቶ ይነበባል
ዐ - ጠብቆ ይነበባል
ጸ' ፀ
ጸ - የራሱን ድምፅ ይይዛል
ፀ - እንደ ጠ ይነበብ ነበር
ለምሳሌ፡- ፀሐይ የሚለውን ቃል ጠሐይ ብለው የሚጽፉና የሚያነቡ አሉ፡፡. .
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: ፊደል...

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Tue Dec 25, 2012 1:30 pm

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:የድምፅ ልዩነት

ሀ' ሐ' ኀ
ሀ - ላልቶ ይነበባል
ሐ - ጠብቆ ይነበባል
ኀ - በጉሮሮ ይነበባል

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

የአባትህ አምላክ ወገብና ጉሮሮህን አላልቶ ያጥብቀውና እንዴት ብለህ ነው "ሀ" እና "ሐ" በድምፅ እያላላህና እያጠበክ የምትለየው :?: :lol: :lol: :lol: :lol: ከቻልክ አጥብቀህና አያላላህ ድምፅህን ቀድተህ ልዩነቱን አሳየን ቅቅቅቅቅቅቅቅ አጥብቆና አላልቶ ይድፋህ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ለምሳሌ፡- ንጉሥ ብለን ነጋሽ እንላለን፡፡ ይህም ሠ እንደ ሸ ይነበብ እንደ ነበር ያስረዳል፡፡

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ንጉሥ.....ንጉሥ ነው......ነጋሽ ደግሞ ነጋሽ ነው........እንዴት ብሎ ነው ሠ እንደ ሸ ይነበብ ነበር ለሚለው ተረትህ ማስረጃ የሚሆነው :lol: :lol: :lol: :lol: ኧረ እባክህ....እባክህ አረቄህን እየጠገብክ ዋርካ ላይ መትፋትህን አቁም ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አ' ዐ
አ - ላልቶ ይነበባል
ዐ - ጠብቆ ይነበባል


አሁንም በድጋሚ "አ" እና "ዐ" ን አላልተህና አጥብቀህ አንብበህ ልዩነቱን አሳየን :wink: .......የሆንክ ላታም ከብት :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ጸ' ፀ
ጸ - የራሱን ድምፅ ይይዛል
ፀ - እንደ ጠ ይነበብ ነበር
ለምሳሌ፡- ፀሐይ የሚለውን ቃል ጠሐይ ብለው የሚጽፉና የሚያነቡ አሉ፡፡. .


"ፀ" እንደ "ጠ" የሚነበበውና የሚፃፈው መቼ ነበር :?: በድንጋይ ዳቦ ዘመን ነበር ወይንስ አንተ በሰከርክ ቁጥር :?: :lol: :lol: :lol:

የአንተ ችግር እኮ.......ጭንቅላትህ ጠቦ......አፍህ ግን ላላ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 25, 2012 1:59 pm

ከንባታው ከበቶ(ሰርጉ...ቦልጤ-ግማዊ ዋልልኝ)እያወራን ያለነው ስለ ሰው ልጆች ቋንቋ ማለትም ስለ አምሐርኛ ነው::አምሐርኛን ጠንቅቆ ለማወቅ ደግሞ ምሉዕ ሰብዕናው የተሟላ ሰው መሆን ያስፈልጋል::እናም የሰዎቹን ለሰዎቹ ብትተውልን ምን ይመስልሀል?በጧቱ አታስለፍልፈኝ እየቀመቀምኩ ነው...በቅርቡ አንድ ጓዳችን ሒውስተን -ቴክሣሥ ብቅ ብሎ ሰው ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሚገባህ ቋንቋ ያስረዳሀል እስከዚያው ቸር እንሰንብት...
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: ፊደል...

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Tue Dec 25, 2012 2:15 pm

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:ከንባታው ከበቶ(ሰርጉ...ቦልጤ-ግማዊ ዋልልኝ)እያወራን ያለነው ስለ ሰው ልጆች ቋንቋ ማለትም ስለ አምሐርኛ ነው::አምሐርኛን ጠንቅቆ ለማወቅ ደግሞ ምሉዕ ሰብዕናው የተሟላ ሰው መሆን ያስፈልጋል::እናም የሰዎቹን ለሰዎቹ ብትተውልን ምን ይመስልሀል?በጧቱ አታስለፍልፈኝ እየቀመቀምኩ ነው...በቅርቡ አንድ ጓዳችን ሒውስተን -ቴክሣሥ ብቅ ብሎ ሰው ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሚገባህ ቋንቋ ያስረዳሀል እስከዚያው ቸር እንሰንብት...

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ስለአማርኛ ፊደላትና ማብራሪያዎች ጥናታዊ ፅሁፍ እያጣቀስክ ስታወራ የነበርክ ጠቢብ ምነው አሁን አፍህ ተሳሰረ ቅቅቅቅቅቅቅቅ ጭንቅላትህ ጠቦ; አፍህ የላላ ዲየዲየብ :lol: :lol: :lol:

የአምሐርኛ ሊቁ ለስንት ሲጠበቁ በቅምቀማ አለቁ :wink: :lol: :lol: :lol:

አህያው.......ጓደኛህን መንገድ አይምታህ በለው.....በፈለገው ቦታ እና ጊዜ.....በፈለገው መንገድ እናስተናግደዋለን.......ለመንገድ ቀጠሮ አያስፈልግም....የጥሪውን ወረቀት ብቻ ይላክልን :lol: :lol: :lol: :lol: .......እኛ አናብስት ወያኔዎች :!: :!: :!:

በዕውቀት; በልማትና; እንዲሁም ለአሸባሪዎች ደግሞ በመረጡት መንገድ ለሁሉም ምላሽ እንሰጣለን እልሀለሁ ዳግማዊ ዋለልኝ :lol: :lol: :lol: :lol:

ንፍጥ ጭንቅላቱ..ለአሁን ግን ይህን ጥያቄ ብቻ መልስልኝ....እባክህን በአምሐርኛ አምላክ ይዤሀለሁ :lol:

የአባትህ አምላክ ወገብና ጉሮሮህን አላልቶ ያጥብቀውና እንዴት ብለህ ነው "ሀ " እና "ሐ " በድምፅ እያላላህና እያጠበክ የምትለየው :?: :lol: :lol: ከቻልክ አጥብቀህና አያላላህ ድምፅህን ቀድተህ ልዩነቱን አሳየን ቅቅቅቅቅቅቅቅ አጥብቆና አላልቶ ይድፋህ :lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 25, 2012 2:31 pm

መድሐኔዓለም ይገልብጥህና መድሐኔዓለም እና ኃይለ ሥላሴ 'ሚሉትን ስያሜዎች ቴክሳስ ላለ አንድ አምሐራ አንብብልኝ በለውና "ሐ" "ዓ" "ኃ" "ሥ" እና "ሴ"ን በምን ዓይነት ቅላጼ እንድሚያነባቸው ለመስማት ሞክር...
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: ፊደል...

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Tue Dec 25, 2012 2:43 pm

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:መድሐኔዓለም ይገልብጥህና መድሐኔዓለም እና ኃይለ ሥላሴ 'ሚሉትን ስያሜዎች ቴክሳስ ላለ አንድ አምሐራ አንብብልኝ በለውና "ሐ" "ዓ" "ኃ" "ሥ" እና "ሴ"ን በምን ዓይነት ቅላጼ እንድሚያነባቸው ለመስማት ሞክር...

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ

ቴክሳስም አነበብከው; ካሊፎርኒያ እንዲሁም ዱባይ ከፈለክም ቶክዮ........"ሐ" እና "ኃ" ያው ናቸው :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: .......ይህ ነው እንዴ የአምሐርኛ ሊቅነት :?: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ለምን ግን ራስህ በድምፅ ቀድተህ የ"ሐ" እና "ኃ" ልዩነቱን አታሳየንም :?: ራስህ ባመጣኸው "ጥናታዊ ፅሁፍ" አትተማመንም እንዴ :?: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ፋንድያ ሐሬ :lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 3 guests