ያራዳ ልጅና ጀግና አያወራም...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ያራዳ ልጅና ጀግና አያወራም...

Postby ክቡራን » Fri Oct 28, 2016 7:18 pm

ባለፈው ጎንደር ፈርስቶች በፈጠሩት ግርግር አንዳንድ የጎንደርና ያካባቢውን ነዋሪዎችን በማሳሳት ትግራውያን ከጎንደር ክመተማ ና ካንዳድድ አካባቢዎች ንብረታቸው ተዘርፎ የለፉበትና የደከሙበት ሃብታቸው ወድሞ ወደ ቀድሞ የትውልድ ሰፈራቸው ትግራይ ክልል እንደተመለሱ ይታወቃል፡፡አሳዛኝ ክስተት ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ድርቡሽ መጥቶ ወረራትሲባል ያላስቻላቸው ጀግናው ና አንበሳው አጼ ዮሃንስ ዘራፍ ብለው ካክሱም በመነሳት ጎንደር መተማ ላይ ደማቸውን አፍሰዋል፡፡
እጼ ዮሀንስ ሞኝ ናቸው..
ንጉስ ቢልዋቸው በመሀሉ..
ወሰን ጠባቂ ልሁን አሉ... ብላ እንድ የጎንደር አዝማሪ መሸታ ቤት አልቅሳላቸው ነበር ይባላል፡፡
ጎንደሬነትና አዝማሪነት እይተጣጠም ይፈላለጋሉ፡፡ ጀግንነትና ድንበር ላይ መሞት ደሞ ትግራይ ውስጥ አለ ይወራረሳሉ፡፡ አሁን በኛ ዘመን መላኩ ተፈራ የሚባል የምድር ጉድ የጎንደርን ወጣት ሲያርድና መግደል የሰለቸውን ደግሞ በቁማቸ እግርና እጃቸውን እያሰረ ከሊማሊሙ ገደል እየወረወረ ሲጥል ለጎንደር ህዝብ እንደ መልአኩ ሚካኤል ከተራራ የወረደለት ወያነ ነበረች፡፡ አንበሶቹ የትግራይ ወጣቶች ቦምብ እየዘለሉ ወይንም እየተረማመዱ ጎንደርን ከመላኩ አይ ሲ ሲ ዎች አጸድዋት፡፡ ሃሌሉያ፡፡ ይ ሁሉ ሲሆን ዛሬ ጎንደር ፈርስት ጎንደር ሰከንድ እያሉ ለጎንደር ህዝብ ተቆርቃሪ ለመምሰል ላይ ታች የሚዳክሩትና ባንጣሩም በጎንደሬው ስም ረብጣ ዶላር አንዴ እስራኤል ሌላ ጊዜ አውስትራሊያ እየሄዱ የሚቀረጭሙት ዘመነኞች በዛ በክፉ ወቅት እግሬ እውጭኝ ብለው በመተማ አድርገው ወደ ሱዳን የገቡ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደሞ የመላኩ ተፈራ አለቃ ገብረሃና ( አጫዋች ) የነበሩ መሆናቸውን ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ታማኝ በየነና አበበ በለው ህያው ምስክር ስለመሆናቸው አንባቢዎች አትስቱም፡፡ ለጎንደር ህዝብ የነጻነት አየር መተንፈስ ትግራይ ዋጋ ከፍላለች፡፡ ወጣት ልጆችዋን ገብራለች፡፡ ጌታ ኢየሱስ ህይወቱን ለአለም ቤዛ እንዳደረገ ህወሃት ለጎንደርና ለጎንደሬው ህይወትዋን ቤዛ አድርጋለች፡፡ እነሆ አመታት አለፉ... ያ የግፉ ዘመንም ተረሳ እስራኤላውያን ሙሴን ይሄ ከፊታችን የሚሄደው ብርሃን ምን እንደሆነ አናውቀውም ግብጽ እያለን የምንበላው ሽንኩርት ይሻለን ነበር ብለው በእጊዚእብሄር ላይ እንደተነሱ ሁሉ የተሳሳቱ ጎንደሬዎች ለነሱ ቤዛ ህይወታቸውን በከፈሉ ትግራዋዮች ና በትግሬ ዘር ላይ እጃቸውን አነሱ ፡፡ ትግሬዎችም አዝነው ወደ ቀድሞ ቦታቸ ሄዱ ፡፡ ይሄ ያበሳጫቸው የሱማሌ ክልል አስተዳደር የአፋር ክልል እስተዳደር ለተፈናቀሉ ትግራውያን ወደ 20 ሚሊዮን ብር በመስጠት አይዞአችሁ ሌሎች ቢረሱም እኛ ግን ውለታ አንረሳም በማለት ወገናዊነታቸውን አሳዩ፡፡ አላህ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክልን!! ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት፡፡ አሁን ደሞ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ትግራዋዮች የወገኖቻቸው መገፋትና ንብረት መቃጠል ተስፋ ሳያስቆርጣቸውና እንደነ ታማኝ በየነ ያይሮጵላን ክፈሉልን ሳይሉ ወይንም ከአገር አገር ኪነት ይዘው ሳይዞሩ ፋንድ በመክፈት ብቻ በ ኦን ላይን $56160 ድላር ሰብስበው $56060ን ወደ መቀሌ ልከዋል፡፡ ዶከዋል፡፡ $100 ዶላር ትራንስ አክሽን የተካሄደባት ናት፡፡ እነ እንትና ይሀን ያህል ገንዘብ ሰብሰበው ሆቴል እንደከፈቱበት ወይንም አንዳንዶቹም ቸርች እንደክፈቱበት ኡራኤል ይመስክር፡፡ ሎል... ለስራ ማስኬጃም ተብሎ የዚህ ገንዘብ ግማሹ እዚህ እንደሚቀር ያደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ የጀግና እጆች ግን አይሰርቁም ለህዝብ ሁሌም ታማኝ ናቸው፡፡ ከራስ ጥቅም ይልቅ አላማ ይቀድማል ፡፡ ምስጋና ተግባሩት ኮሚቴ ረዴኤት ተመዛብሊት ተጋሩ Displaced Tigrians Fund Coordinating committee እንደተለመደው እቺን ጠቅ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests