በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሞት የተፈረደባት ኢትዮጵያዊት በካሣ ተለቀቀች::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሞት የተፈረደባት ኢትዮጵያዊት በካሣ ተለቀቀች::

Postby ክቡራን » Sun Oct 30, 2016 10:47 pm

500 ኢትዮጵያውያንን ከታንዛኒያ ወህኒ ቤት ለማስፈታት ድርድር እየተደረገ ነው

በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የሠው ነፍስ በማጥፋት ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶባት የነበረች ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ፤ በኢትዮጵያ መንግስት ቆንፅላ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የ100 ሺህ ድርሃም ካሣ ተከፍሎ፣ ከእስር ተለቃ ወደ ሃገሯ መመለሷ ተገለፀ፡፡
በሃገሪቱ ባህል መሠረት ነፍስ ያጠፋ የሞት ፍርድ የሚፈረድበት ሲሆን የተጎጂው ቤተሰቦች በሚያቀርቡት ዋጋ መሠረት የካሣ ክፍያ ከተከፈለ ወንጀለኛው ነፃ የሚሆንበት አሠራር በመኖሩ ለሟች ቤተሰቦች ካሳ መከፈሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቋል፡፡ በዩናየትድ አረብ ኤምሬት በተመሣሣይ ወንጀል ሞት የተፈረደባቸው ሌሎች 3 ኢትዮጵያዊያንን ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑ የገለፀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ 100 ሺ ድርሃም የተሠባሠበው በሃገሪቱ ካሉ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያንና ከመንግስት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል በታንዛኒያ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘው ታስረዋል የተባሉ 500 ኢትዮጵያውያንን ለማስለቀቅ 4 አባላት ያሉት ቡድን ወደ ሃገሪቱ ተልኮ ድርድር እያደረገ መሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አስታውቋል፡፡
ድርድሩ መልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ምናልባት እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ ይችላሉ ብለዋል፡፡ Source https://www.facebook.com/Ethiopian-This ... 98610656//
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests