የሻለቃውና የዶክተሩ የዘጠኝ ወር ምጥ ውጤት ...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የሻለቃውና የዶክተሩ የዘጠኝ ወር ምጥ ውጤት ...

Postby ክቡራን » Tue Nov 01, 2016 3:01 am

እንደው ዝም ከማለት ብዬ እቺን ማስታወሻ ብጤ ልጻፍ ብዬ ተነሳሁ፡፡ መቼም ለማንም ብዬ ሳይሆን የዚች አገራችን ጉዳይና በላይዋ ላይ ያሉ ጉዶች ስለሚያስግርሙኝ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ስማቸውና ማእረጋቸው ገዝፎ ተግባራቸው ግን የሃማል ነው፡፡ ሃማል በድሬድዋ አማርኛ እቃ አውራጅና ጫኚ ማለት ነው፡፡ “ዘጠኝ ወር አምጠን አምጠን እነሆ ተገላገልን “ አሉ ሁለቱ ባል ትልቅ ማእርጎች የዘመኑ ጎበናዎች:: እንደኛው ዳዊት ይሰኛሉ.. ሌላኛው መቅለስለስ የሚያበዙቱ ናቸው፡፡ ወንድ ልጅ ሲቅለሰለስ ቡዙም አይመቸኝም እኚህኛው ( መቅለስለስ የሚያበዙቱ) ጌታቸው ይሰኛሉ ማእረግ ፕሮፊሰር፡፡ የበፊተኛው ወታደር ናቸው፡፡ ማእረግ ሻለቃ፡፡ አሁን ደሞ ባፍሪካ ውስጥ እየተዘዋወርኩ

ችግር ፈቺ ነኝ …

መድሃኒት አለኝ

ሲሉ የሰማሁ መሰለኝ፡፡

ድንቄም ችግር ፈቺ!! Lol.. የቤቱን ችግር በቅጥ ያልፈታ የውጭውን ችግር ይፈታል ብዬ አላምንም ፡፡ አባ መቃኖቹ የድላችን ውጤት ነው ብለው ያስጨበጨቡበትን.. እስጨብጭበው ያስደመሙበትን.. እስደምመው ያተራመሱትን ቴራሚሶ ..በነሱ አገላለጽ ንቅናቄ በብእራችን ኣንዳንድ ( ሃደ ሃደ ) እንለው ዘንድ ፈቀድን፡፡ ከስሙ እንጀምር.. "የኢትዮጵያ አንድነት ንቅናቄ" ከስሙ ስንነሳ ስሙ ቀናነት የለውም፡፡ ተወያይዮቹ ወይንም ተፈራራሚዎቹ በቁጥር አራት ብቻ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ የአራት ብሄረሰቦች ብቻ አገር አይደለችም ፡፡ ሁሉንም የህብተረሰብ ክፍል የማይወክሉ የዶክተሩና የሻለቃው የቅርብ ሸሪኮችና የእድሜ ጉዋደናሞች የተሰባሰቡት ስብስብ ነበር ማለት ይቀላል፡፡ አርበኞች ግንቦት 7 የኦዲ ኤፍ, የሲዳማ ህብረትና የአፋር ህብረት ፡፡ ትግራይን የሚወክል ክፍል የለም አማራን የሚወክል ክፍል የለም ወላይታውን የሚወክል ክፍል የለም:: ውጋዴን አልተወከለም.. ሱማሌ አልተወከለም፡፡ ጋምቤላ የለም፡፡ በፎሪ ወጥትውዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ራሳቸውን የሽግግር መንግስት ፕሬዝዳንት ብለው የሰየሙት አቶ ስለሺ ጥላሁንን እንኩዋን ለሞራላቸው ንግግር ያድርጉ ብለው እንኩዋን አልጋበዝዋቸውም፡፡ lol ፡፡ በዚህ ላይ ህብረቱ ያንድ አገር ሰዎች ሳይመስል የሁለት እገር ህዝቦች የሁለት አገር አድባሮች የተቀመጡበት ፍጥጫ ነበረ የሚመስለው፡፡ የኦሮሞ ተወካዮች ባንዲራቸውን ከፊት ሰቅለዋል ሌሎቹ ፈራ ተባ እያሉ አረንግዋዴና ቢጫ ባንዲራ ይዘዋል፡፡ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳን ለስምምነትና ለመፈራረም የተቀመጡ ይመስላል ፡፡ ዶክተር ዲማ ነገዎ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ንግግራቸውን የሚከፍቱት በኦሮምኛ ሲሆን የሚለጥቁት ደግሞ ባማርኛ ነው፡፡ ፕሮቶኮል መሆኑ ነው ፡፡ እነዚህ ሰዎች ወያነን ዘረኛ ይሉታል እንጂ ክወያነ በላይ ዘረኞች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ወያነ ዘረኛ አይደለም፡፡ ቢሆን ኖሮ ሃይለማርያምን ቤተ መንግስት አስገብቶ እሱ አይወጣም ነበረ፡፡ ሌላው ትልቁ ስህተትና ውሸት ደግሞ ተዋሃዱ የተባሉት ፓርቲዎች ጉዳይ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞን ረብሻውና አመጹ ሲጋጋል እኮ ማንም ሳይላቸው ግንቦት 7 ና ኦዴኤፍ ( ODF) ተዋህደናል ብለው የጋራ አጀንዳ ማጽደቃቸውን ሰምተናል እነሱም ይፋ አድርገዋል፡፡ ቅቅቅ፡፡ አሁን እነሱ ላይ የተጨመሩት አፋርና ሲዳማ ብቻ ናቸው፡፡ ምኑ ነው ታዲያ የኢትዮጵያ አንድነት ንቅናቄ የተባለውና “9 ወር አርግዘን ወለድን” እያሉ ህዝቡን በግድ የሚያስጨበጭቡት??? ከዚህ በፊትም ብዬአለሁ እነዚህ ሰዎች በእድሜም ገፍተዋል ባስተሳሰብም መክነዋል ወይም መካን ሆነዋል፡፡ በዜግነትም ኢትዮጵያዊ እይደሉም፡፡ ሲሞቱ መቀበሪያ እንደሆነ የፈለጉት ያይሮጵላን ከከፈሉ አገራችው ሄደው አንዱ ደብር ሄደው መቀበር ይችላሉ፡፡ መንግስት እንደው ለዚህ ግድ የለውም፡፡ የውጭ ምንዛሪ አገራችን ያስፈልጋታል፡፡ lol ከዚህ በዘለለ የነዚህ ሰዎች ሀገራዊ ፋይዳ ቡዙም አይታየኝም፡፡

ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7962
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests