የመከካለኛ አመራር በጥልቀት እየታደሰ ነው፡፡ አሁን ተራው የ ብ አ ዴን ነው፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የመከካለኛ አመራር በጥልቀት እየታደሰ ነው፡፡ አሁን ተራው የ ብ አ ዴን ነው፡፡

Postby ክቡራን » Mon Nov 07, 2016 3:01 pm

የአማራ ብሔር ተወላጆች በስማቸው ይነግዱ የነበሩትን የፊውዳል እና አምባገነን ስርዓቶችን ከመላ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጋር ሆነው ለመጣል ተሰባስበው የመሰረቱት ብአዴን⁄ኢህአዴግ መካከለኛ አመራሮቹ በባህር ዳር በጎንደር በደብረ ታቦር በደሴ በደብረ ብርሃን በአዲስ አበባ በጥልቀት የመታደስ ሂደት ላይ ይገኛሉ። በጥልቀት የመታደሱ አካሄድ ያስፈለገው ህዝብ ደግሞ ደጋግሞ ያነሳቸው ጥያቄዎችን ለመመለስና ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ስኬቶቹ እየበዙ ለህዝብ ተጠቃሚነት እንዲውል አመራሩ እራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ካልሆነም ስፍራውን በገዝ ፈቃዱ ለቆ ህዝባዊ ወገንተንነት የተላበሰ አመራር መስመሩን እንዲያስቀጥል ለማመቻቸት ነው። የተሀድሶ ውይይቱ በብአዴን⁄ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች እየተመራ ሲሆን ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል ነገር ግን በጥልቀት የመታደሱ እንቅስቃሴ በሁሉም ኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ በሂደት ላይ ነው ያለው።

** የኔ ማስታወሻ **

እኔ ነገረኛ እንዳልባል እንጂ እቺን አገር ገደል የሚከታት ብ አዴን ይመስለኛል ፡፡ የእድሳቱን ፎቶ ስመለከት ዝምታ ወርቅ ነው ያሉ ነው የሚመስለው ሎል፡፡ እነ የወንድወሰንና አንዱ አለምን የመሰሉ እልፍ ጀግኖችን ያፈራ የአማራ ልጆች ያሉበት ድርጅት ባደር ባዮች መታጠሩ ያሳዝናል፡፡ ነባር ታጋዮች ( እነ በረከት፣ አዲሱ፣ ህላዌ ፣ታደሰ ጥንቅሹ.. ) አመራራችሁን በደንብ ፈትሹ እንላለን፡፡
https://www.facebook.com/photo.php?fbid ... =3&theater
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests