የአናሳ ትግሬ ጎሳ ወያኔ ግፍና ለኮንግረስ የቀረበ ቢል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የአናሳ ትግሬ ጎሳ ወያኔ ግፍና ለኮንግረስ የቀረበ ቢል

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Nov 07, 2016 8:16 pm

ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም እንድ ጊዜ ኢህድሪ የሚባለውን መንግስታቸውን ካቋቋሙ በኋላ “ዕውን አሁን ደርግ አለ?” ብለው አገሩን በሳቅ ሊፈጁት ነበር። ይዘቱ ያው የሆነ ነገር በቅርጹ ስለተለየ በውጤቱ የተለየ ይሆናል ብለን እንድናመን ፈልገው ነበር መሰለኝ። አሁን ደግሞ የህወሀት መሪዎች ተራ በተራ ካላንዳች ተከራካሪ በሞኖፖል በያዙት ቴሌቪዝን ላይ እየወጡ “ዕውን አሁን የትግራይና የህወሀት የበላይነት ኢትዮጵያ ውስጥ አለ”? የሚል ተጨፈኑልኝ ላሞኛችሁ ዘፈን መሰል ነገር በኦርኬስትራ መልክ እየተቀባበሉ እየደለቁት ነው። (ከብዙ ጥቂቱን እዚህ ይመልከቱ)። ተከራክረው እንደማይረቱ ሰለሚያውቁ ራሳቸው ጎን ለጎን ተኮልኩለው እየተቀባበሉ ይነጋገራሉ እንጂ ሞጋች አያስቀርቡም። ጥያቄ አቅራቢውም መልስ ሰጭውም እነሱ ናቸው። ዲሞክራሲ ማለት ያንድ አቅጣጫ መንገድ ነው ወያኔዎች ቤት። እነሱ ከተናገሩት ዕውነት ነው። አለቀ። ክርክርና ትችት እንደጦር ሲፈሩ ይገርሙኛል። ተቺ ጠቃሚ አስተካካይ ሳይሆን አሸባሪ ነው። ተቃዋሚ ጠላት ነው ብለው ያምናሉ። ይህ ባህሪያቸው እነሱንም ሃገራችንንም አብሮ እያጠፋና ሊያጠፋ የተቃረበ መሆኑ ፈጽሞ የገባቸው አልመሰለኝም።

የመንግስት ባለስልጣን አይዋሽም አይባልም። ውሸቱ ግን ወይ ለከት ወይ የማስመሰል ቅንብር (nuance) እንዲኖረው ይጠበቃል። ውሸት ብዙ አይነት ነው። አንዳንድ ውሸት ያስቃል። ዕውነት ከመሰለ የሚጠቅም ውሸትም አይጠፋም። አንዳንዱ ውሸት ያሳዝን ይሆናል። ውሸት እየዋሹ ሰው የሚያዝናኑ ሰዎችም አውቃለሁ። እንዳንዱ ውሸት ግን የአድማጩን የመገንዘብ ችሎታ (intelligence) የሚሳደብ ይሆንና ያናድዳል። ሰሞኑን የሰማሁት የአቶ ስዩም መስፍንና የሌሎች ህወሀት ባለስልጣኖች አይነቱ ከኋለኛው አይነት የሚመደብ ነው። አቶ ስዩም መስፍን ከዚህ ቀደም በማግስቱ የተጋለጠ አገር ጉድ ያለው ውሸት ሲዋሹ ያየሁዋቸው ሰው ሰለሆኑ ውሸት ካፋቸው እንዴት ወጣ ብዬ የምሞግታቸው ስው አይደሉም። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የግልግል (arbitration) ውሳኔ ማግስት ባድሜም ሁሉም ነገር ለኛ ተወሰነልን ደስ ይበላችሁ ያሉንንና በማግስቱ ጭልጥ ያለ ውሸት ሆኖ መገኘቱን ያልሰማ ኢትዮጵያዊ አይኖርም። እንደዚያ የቀናት አድሜ የሌለው ውሸት በሚሊዩኖች ፊት ለምን እንደዋሹ እስከዛሬ ይገርመኛል። ያሁኑን የትግራይና የህወሀት የበላይነት በኢትዮጵያ ምድር የለም የሚለውን ሌላ ቆሞ የሚሄድ ውሸት ምን እንደምንለው አላውቅም። ሳይኮሎጂስቶች አንዳንድ ሰዎችን እንዲህ ጸባየ ውሸታም (habitual liar) የሚያደርግ የሚገፋና የሚወተውት በሽታ (Compulsive Obsessive Disorder) የሚባል ህመም አለ የሚሉትን ነገር እንጠርጥር ይሆን?
ደሊል
ይህን በጎሳ ወገናዊነት ላይ የሚሰራ መንግስት ጭቆና ለመፋለም ብዙሃኑን ያካተተ መንግስት ይኖር ዘንድ ኮንግረስ ያቀረበውን ቢል የያለንበት ተጠሪዎች እንዲደግፉ እንጣጣር!
የብዙሃን ጎሳዎች በዚህ መንግስት መገፋት መፈናቀል ሊቆም የሚችለው በሁሉም መንገድ ግፈኛውን መንግስት ስንፋለም ነውና በያለንበት የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ እንበርታ!
S.Res.432 - A resolution supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia.
114th Congress (2015-2016) | Get alerts

RESOLUTIONHide Overview icon-hide
Sponsor: Sen. Cardin, Benjamin L. [D-MD] (Introduced 04/20/2016)
Committees: Senate - Foreign Relations
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: ምሰጢር and 3 guests