ነአምን ዘለቀ የት ገባ ??

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ነአምን ዘለቀ የት ገባ ??

Postby ክቡራን » Sun Nov 13, 2016 7:41 pm

ግልፍተኛነት የሚያጠቃው ከዲፖሎማሲያዊና ከበሰለ የፖሎቲካ ውይይት ይልቅ እንደ ሰፈር ተናካሽ ውሻ ሰው ላይ የሚጮሃው በዚህ ላይ ባለጌው ነአምን ዘለቀ ከግንቦት 7 ቀስ በቀስ እየተሰፈነጠረ ይመስላል፡፡ አርበኞች ግንቦት 7 አሁን ደሞ ( ላስት ዊክ ተወልዶ ዚስ ዊክ እንደሞተ የሚነግርለት የኢት ዮጵያ አንድነት ንቅናቄ ) መስራች ከሆኑት እንዱ ግንቦት 7 ቢሆንም ሰውየው ብርሽ ማንን ወክለው ብራስልስ እንደተገኙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ እንደተለመደው ጋብዥዋ እና ጎሜዝ ናት፡፡ ዶክተር ብርሃኑ አሜሪካ ካለችዋ የልጆቹ እናት በላይ የአና ጎሜዝ የግብዣ ወረቀት እጅግ እንደሚያስፈነድቀው የቅርቦቹ የሚላቸው ሰዎች ሁሉ ያውቁበታል፡፡ አናም አና ጎበዜ ተማሙታ የግብዣውን ወረቀት ሊዜ ፓሴውንም ታመቻቻለች፡፡ በስልክ አነጋግርሪኝ በቀጭንዋ ሽቦ ትዝታሽ እንደሚመጣ ደርቦ ደራርቦ የሚለውን የጥንት የቡዙዬን ሙዚቃ እየስማሁ ነው ይሄን ማስታወሻ የምጥፍላቹ፡፡፡ ቅቅቅቅ፡፡ ይሄ በዚህ እንዳለ ግን አንዳንድ ምንጮች ነአምን ዘለቀ ከቆመ መኪና ው ይንም ግድግዳ ሁሉ ሳይቀር እየፈለገ መጋጨቱን ስላልወደዱለት የግንቦት 7 ሰዎች ገለል እንዲል የወሰኑበት ይመስላል፡፡ ስድ አፍ ያለው ነአምን የውጭ ግኑኝነት ክፍል ተብሎ ሲሾም ቡዙውን ሰው ሳቅ በሳቅ አድርጎበት ነበር፡፡ ለነገሩ ሰውየው ትራምፕም እኮ ፕረዝዳንት ሆነዋል ያን ስናስብ የነአምን ቡዙም ሊያስደንቀን ወይንም ላይገርመን ይችላል፡፡ የሚገርመው ግን ነአምን ወደ ግንቦት 7 የመጣው ጥምረት በሚል እንድ ለናቱ የሆነ ድርጅት መስርቶ ነበር፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና የድርጅትህ አባሎች ማናቸው ሲባል መስራቾቹ እኔና ሻለቃ ወልደ ጊዮርጊስ ነን ብሎ ድርጅቱን ለህዘበ ዲያስፖራው አስተዋውቆ ነበረ፡፡ ሻለቃው ታዲያ በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የማንም የፖሎቲካ ድርጅት አባል እንዳይደሉ ሲገልጹጋዜጠኛው በመሃል ጣልቃ በመግባት እረ ቆይ ሻለቃ ከነእምን ጋር የመሰረታችሁት ድርጅት አለ ስምዎም ሰፍሮእል ብሎ ሲጠይቅ ሻለቃው በጭራሽ የሚያቁት ነገር እንደሌለ ግልጽ አድርገው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሂሳብ ከሄድን ደሞ ድርጅቱ ወይንም የፓርቲው ( CEO) አቶ ነአምን ራሱ ብቻውን ነው ማለት ነው፡፡ ሎል፡፡ የውጭ ፕሎቲከኞቻችን ሲላቸው ኮሜድያንም ናቸው፡፡ ቅቅቅቅ፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና ኢትዮጵያን እንድ እድርጎ ሰላምዋን ና ህብረትዋን ሊጠብቅ የሚያስችል የብረት ማገር የተባለለት በዶክተር ጌታቸውና በሻለቃ ዳዊት የ 9 ወር ምጥ የተወለደው የኢትዮጵያ አንድነት ንቅናቄ የት ገባ ? ሱዳን...? ቡጁምብራ..? ወይስ ዋሽንግተን ዲሲ ቤርሙዳ?? ሎል ፡፡ ሰውየው ብሬም አና በጋበዘቻቸው ግብዣ ላይ የተገኙት (በነገራችን ላይ ብራስልስ ለስብሰባ ብለው ከሄዱ ወራት አልፎቸዋል) ቅቅ ድርጅታቸውን ወክለው እንጂ ኢትዮጵያ አንድነት ንቅናቄ የሚባለውን ስብስብ እንዳልወከሉ ድርጅቱም ሲመሰረት ኤርትራ ሳይሆን ብራስልስ እንደነበሩ ከዚህም በተጨማሪ ሳት ብሎአቸውም እንኩዋን የኢትዮጵያ አንድነት ንቅናቄ ስሙንም እንዳልጠሩ ከንግግራቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ እሁን ደሞ ጥብስ ጥብስ የሆኑ ያንድነት ዜማ የሚያዜሙ ብራንድ ድርጅቶች በቅርብ ቀን ይወጣሉ ተብሎአል፡፡ ፡፡ አንዱ ጋ የምገባ ይመስለኛል፡፡ ሎል፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7962
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests