በረከት ስምዖንና የጎንደር ህዝብ...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በረከት ስምዖንና የጎንደር ህዝብ...

Postby ክቡራን » Sun Dec 04, 2016 12:15 am

ባማራ ክልልና በኦሮሚያ ክልል አመጹ በፋመበት አንድ ወቅት ላይና አንዳንድ አካባቢ ደግሞ ትግሬ ገዳይ እየተባለ በሚፎከርበት ወቅት የስምዖና ልጅ የሚባለው በረከት ካዲሱ ለገሰና ከሌሎች ጋዶቹ ጋር በመሆን ከጎንደር ዙሪያ አካባቢ ከመጡ ያገር ሽማግሌዎችና የደብር አለቆች እዛው ጎንደር ከተማ ውስጥ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ ሁሉም ጉልበቱ የፈረጠመበት ወቅት ስለሆነ ውይይቱ የማለሳለስ መልክ ይታይበት ነበር፡፡ አንድ ትልቅ የጎንደር እዛውንት ወደ አቶ በረከት እያዩ ( በረከት በነገራችን ተወልዶ ያደገው እዛው ጎንደር ፒያሳ ከተማ ነው) "ስማ በረከት ይህ ህዝብ ሊበላችሁ ቀርባዋል.. ሳይመሽባችሁ ተደራደሩ!" ይሉታል፡፡ አዳራሹ በጭብጨባ አስተጋባ፡፡ በረከት ስፒከሩን ተቀበለና ጭብጨባው ጋብ ሲል ንግግር ጀመረ፡፡ " አንደራደርም..!!" ህዝቡ በመገረም መስማት ጀመረ ..." የመደራደር አቅሙ የለንም ከህዝብ ጋር ለመደራደር መጀመሪያ እኩያ መሆንን ይጠይቃል፡፡ እኛ የህዝብ ታዛዦች እንጂ ተደራዳሪዎች አይደለንም " ህዝብ ካልፈለገን ትክክለኛ መስሎ የታየውን የራሱን ውሳኔ መውስድ ይችላል ለሀገር እንጂ ለራሳችን ብለን የሰራነው ምንም ነገር የለም፡፡ " በረከት መነጋገሪያውን ወደ ቦታው ሲመልስ ከመጀመሪያው የበለጠ ጭብጨባ አዳራሹን አናጋው፡፡ በቦታው ከነበረ ይያን ምስክር የተገኘ፡፡
Image
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7940
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests