አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔን ሰራዊት በሁመራ አዲስ አለም ከፍተኛ ውጊያ አደረገ!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔን ሰራዊት በሁመራ አዲስ አለም ከፍተኛ ውጊያ አደረገ!!!

Postby ኳስሜዳ » Thu Dec 08, 2016 7:03 pm

የአርበኞች ግንቦት 7 የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊና የግንባሩ ቃለ አቀባይ የሆኑት አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ በወያኔ አገዛዝ ጋር ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ተናገሩ። እንደ ቃለ አቀባዩ ገለጻ የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በጥልቀት ሰርገው ገብተዋል። የፓለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊውም በማከልም እነዚህ ሰርገው የገቡት ወታደሮች ከወያኔ ጦር ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ አጠናክረው እንደቀጠሉ ይናገራሉ። አቶ መንግስቱ ወልደ ስላሴ በጎንደር ውስጥ የነጻነት ሃይሎች ከወያኔ ወታደሮች ጋር በሚያደርጉዋቸው ትግሎች ውስጥ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰርጎ ገብ ወታደሮች ከነጻነት ሃይሎች ጎን ተሰልፈው እየተዋደቁ እንደሆነም አረጋግጠዋል። ባለፉት ወራት በተለያዩ የአማራው ክፍሎች በተለይም በጎንደር ውስጥ ወያኔን ለመውጋት ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች በጥምረት በመሆን ከገዢው ሰራዊት ጋር እየተፈለሙ እንደሚገኙም ተናግረዋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች በካበታ ሁመራ ዳንሻ አዲስ አለም አብደራፊ እንዲሁም በተለያዩ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች የተሳካ ጥቃት በወያኔ ላይ እንዳደረሰና ድልም እንደቀናው ቃለ አቀባዩ አክለዋል። አቶ መንግስቱ ወልደ ስላሴ ገዢው የህውሃት መንግስት ይህ ሁሉ ጥቃቶች በኤርትራ መንግስት ነው የደረሰብኝ የሚለውን ክስና የማይረባ ፕሮፖጋንዳ በማጣጣል እንደውም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በርግጥም ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ጎን ሆኖ ወያኔን ተናንቆ እየተፋለመ ነው ብለዋል።
https://freedom4ethiopian.wordpress.com ... /08/wer-2/
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2119
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests