የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል።

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል።

Postby ኳስሜዳ » Thu Dec 15, 2016 12:25 pm

እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የመጣው የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል። በአርማጭሆ፣ በቆላማው ወገራ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ በመተማ ቋራ በገበሬወች ላይ ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ሰሞኑን ወደ ስሜን በኩል ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው አዳዲስ ሶስት ግንባሮች ላይ ጦርነት ተከፍቶ ፍልሚያ አለ። የተገፋው ገበሬ እራሱን ለመከላከል እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እያደረገ ነው።…

ግራ የገባው ወያኔ የወረዳ መንገዶችን በኬላ በመዝጋት ፍተሻ እያደረገ ነው። ከጎንደር ሾልከው የወጡ መረጃወች እንደሚያሳየው ወያኔ ከፍተኛ የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰበትን ጦር አንስቶ በአዲስ ለመተካት እንቅስቃሴ እያደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።
ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ ህፃናትን፣ እናቶችንና አረጋዊያንን በመያዦነት አስሮ በግፍ እያንገላታ ነው። ለጊዜው ስማቸውን የማንጠቅሰው የገበሬ ሴት ቤተሰቦች ከ6 አመት ህፃን ጋር ጎንደር ውስጥ በ1ኛ ፖሊስ ጣብያ ታስረው ይገኛሉ። ይህ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት የህዝቡን እልህና ቁጣ እየጨመረው እንደሚገኝ ከቦታው ያናገርናቸው ተናግረዋል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 7 guests