የወያኔ ብዓዴን ጦር ሰሜን ጎንደር አበሳውን እያየ ነው፥

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የወያኔ ብዓዴን ጦር ሰሜን ጎንደር አበሳውን እያየ ነው፥

Postby ኳስሜዳ » Fri Dec 16, 2016 11:09 am

የወያኔ አገዛዝ ጎንደር ላይ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት ለማፈን አቅሙን የሚፈታተኑ ብዙ ተግዳሮቶች እንደገጠሙት እየተሰማ ነው፥

ጦር ጭኖም ሆነ በሽምግልና መልክ መርቶ የወረደ የወያኔ ብዓዴን ጦር ሰሜን ጎንደር አበሳውን እያየ ነው፥ ጎንደር ሆስፒታል በቁስለኛ ሞልቷል፥ ከዓምባጊወርጊስ እስከ አዘዞ የሚታየው የወታደር ቀብር በጥይት ሳይሆን በወረርሽኝ በሽታ ያለቀ ይመስላል አሉ።
የወያኔ ስርዓት ዓንታዘዝም የሚሉ የውስጥ ሃይሎች እንደተነሱበትና በሕዝቡ አልገዛም ባይነት ውጥረት ላይ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየመጡ ነው።

ወደ ጦር ግንባር ትጥቅ ጭናችሁ ውጡ የተባሉ የአማራ ክልል ፖሊስ ባልደረባዎች እምቢተኝነት እያሳዩ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ አልሄድም ያለ አንድ የጎንደር ፖሊስ ምን የምታውቀው ነገር ቢኖር ነው በማለት አስረውት በምርመራ ላይ እንደሚገኝ በውስጥ የመጣ መልክት ያመለክታል፥

የጎንደር ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጸሐፊ እንደታሰሩና፥ ጳጳሱም ከሕዝባዊ ዓመጹ ጋር በተያያዘ ታስረው በሕዝብ ጩኸት መፈታታቸው ታውቋል፥ የዓብያተ ክርስቲያናት አመራሮች መነኮሳትን ጨምሮ በኮማንድ ፖስት ማደኛ ወጥቶባቸው እየተፈለጉ ነው።
የትግራይ ነፃ አውጭው ግንባር የወያኔ አየር ሀይል አብራሪዋችም በገበሬ ጦር ላይ ዓንዘምትም በማለት እንቢታ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2143
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests

cron