ወያነነት ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ወያነነት ነው፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያነነት ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ወያነነት ነው፡፡

Postby ክቡራን » Fri Dec 16, 2016 1:26 pm

አንዱ አውቆ እበድ ( የቀን እብድ ማታ ደሞ እቤቱ ሲገባ ጨዋ ) ሎል..ወያነዎችና ኢትዮጵያውያን እንዴት ናችሁ? የሚል መልክት ጽፎ አነበብኩ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ወያነነት ነው... ወያነነት ኢትዮጵያዊነት ነው ፡፡ ሁለቱን ልትነጣጥላቸው አትችልም፡፡ ይሄን ለማለት ሁለቴ ማሰብ አይጠበቅብህም፡፡ ወይንም አያስፈልግህም (ሽም) ፡፡ ምንድነው ወያነነት? እምቢተኝነት ነው! አለመንበርከክ ነው! ለክፋት ለሀኬት ለጭቆና ና ለበደል እልገዛም ባይነት ነው! ተስፋን ሰንቆ በረሃ መውረድ ነው፡፡ እለመበገር ነው ፡፡ አለመሸነፍ ነው ፡፡ ጢያራዎች ከሰማይ እያፍዋጩ መትረየሶች ከተራራ አናት እየተንደቀደቁ እምበር ተጋዳላይ!! ተጋዳላይ ዲሃ ! መስመሪ ህዝቢና.. መስመሪ ሃይሊና እያሉ እየዘለሉ ወደ ፈንጂ ወረዳ መግባት ነው፡፡ አዎ መግባት ነው፡፡ እነዚህ ባህርያት ( ካራክተርስቲክስ) የጀግና ኢትዮጵያዊ ሊትማስ ፔፐሮች ናቸው፡፡ እጅ የሚሰጠውና ጊዜ አይቶ የሚከዳው በእውነተኛ ኢትዮጵያውያኖች አይን ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ሌሎች የትግል ግዋዶቹ በሞቱለት ሞት እሱ ግን የግል ጥቅሙን የሚያካብት ከሆነ ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ወያነነት ንጹህ ህሊናን ትራሱ ያደረገ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ማነው ኢትዮጵያዊ ? በሚል ርእስ ተከታታይ ጽሁፎች በተከታታይ ይቀርባሉ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests