ኮ/ል ደመቀ የግንቦት ሰባት አባል አይደለም። ግንቦት ሰባት ግን በኮ/ል ደመቀ ላይ የጠለቀውን

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኮ/ል ደመቀ የግንቦት ሰባት አባል አይደለም። ግንቦት ሰባት ግን በኮ/ል ደመቀ ላይ የጠለቀውን

Postby ቢተወደድ1 » Tue Dec 20, 2016 2:19 pm

ለነኴስ ሜዳና መሰል ጅላጅሎች፤ ቁልቁል ተጥፎ ያለውን አንብቡትና ተሞናሞኑበት

ስለ ግንቦት ሰባት ሳስብ ለምን እንደምናደድ ላስረዳ

1ኛ ግንቦት ሰባት ታግሎ ከገደለው በግንቦት ሰባት ስም የተገደለው ህልቆ መሳፍር ነው

2ኛ ግንቦት ሰባት ከቦ ከያዘው በግንቦት ሰባት ስም የተያዘው ( የታሰረው ፥ የተገረፈው ፥ የተሳደደው እና የተዋረደው ) የትየ ለሌ ነው
ኮ/ል ደመቀ

ኮ/ል ደመቀ

3ኛ ግንቦት ሰባት በግንቦት ሰባት ስም ታስረው ለተገደሉት እና ለሚገደሉት ወገኖቻችን አንድም ቀን ሃላፊነት ሲወስድ ተሰምቶ አይታወቅም ! ለምን ?

4ኛ በግንቦት ሰባት እና አማሪካኖቹ አልቃይዳ በሚሉት ነኃከል አንድ መሰራታዊ አንድነት ይታየኛል ። እሱም ምንድ ነው አማሪካኖች ፈርጀው መደብደብ የሚፈልጉትን ሃገር አልቃይዳ እዚህ ታይቷል እያሉ ይደበድቡ እንደነበር ፥ የራሳቸው የአማሪካ የጦር መኮንኖች ሰዳም ሁሴን እንኳን ኑኪሊየር ቦምብ የዳቦ መጋገሪያ ይስት ( እርሾ) እንደሌለው ተናግረዋል ። ሰዳም ሁሴን አንድ ብልቃጥ አንትራክስ ቢኖረው ኖሮ አለምን ያጠፋ ነበር ሲሉም መስክረዋል ፥ ያም ሆኖ ሳዳም እና ሀገሩ በሞርታር እንድትገለባበጥ ተደርጓል ። ወያኔ ትግሬም ይህንኑ ዘዴ በመጠቀም ግንቦት ሰባትን አማራን ለመምቻ እንደ ዱላ ሲጠቀሙበት ነው የሚታየው ። ግንቦት ሰባት የአማራ መጥፊያ ስለመሆኑ ሁነኛ ማሳያው ወያኔ ትግሬ ደምሂት የሚባል የታጠቀ ጦር እያለ ፥ አንድም ቀን ደምክሂትን በአሸባሪነት ሲኮንን እና ሲፈርጅ ታይቶ አይታወቅም ። ምክንያቱም ደምሂትን በአሸባሪነት መፈረጅ ፥የትግራይ ህዝብን በአሸባሪነት መፈረጅ ነውና !

5ኛ ግንቦት ሰባት በጀርመን ለድርጅቱ ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የ ኮ/ል ደመቀ ፎቶን ለጨረታ አቅርቧል ። ኮ/ል ደመቀ የግንቦት ሰባት አባል አይደለም። እንደማውቀው እንደውም ኮ/ል ደመቀ ግንቦት ሰባትን የሚጠየፍ ሰው ነው ። የታገለውም የግንቦት ሰባትን ህልም ለማስፈጠም ሳይሆን የወልቃይትን ህዝብ የአማራነት ጥያቄ ለማስከበር ነው ። ግንቦት ሰባት ግን ይህንን ያለውን ወራዳ ነገር ሲያደርግ በ ኮ/ል ደመቀ ላይ የጠለቀውን ገመድ አጥብቆታል። ስለ ኮ/ል ግን ሃላፊነት ወስደን እንታገላለን ሲል አልተሰማም!!! ይልቁንስ መሪው አርበኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ ባደረገው ንግግር « የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ወያኔ ሲወድቅ ምላሽ ያገኛል » ነበር ያሉት ! ድብን ያለ ማድበስበስ ! ወያኔ ሲወድቅ ምላሽ እንደሚያገኝ ማን ጠፋው ? ጥያቄው የወልቃይትን ህዝብ የማንነት ጥያቄ ትደግፋለህ ወይ ነው እኮ ? እንደ ድርጅት መሪ ምን ይሰማኻል ነበር ያልነው ! አይመልስልህም ! ብርሃኑ ነዋ!

6ኛ የግንቦት ሰባት መሪዎች የአማራ እርበኞችን በገንዘብ እንረዳችዃለን በማለት ፥ በተደጋጋሚ ግንኙነት ከፈጠሩ ወዲህ ጥቂት ብሮችን እያሳዩ ፥ ተጨማሪ ብር እንድንልክላችሁ ከኛ ስር ግቡ እያሉ እንደሚያስገድዷቸው እና ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጓቸው እንደሆነም ስለማውቅ ! ይህንንም የምናውቅ እኛ ፥ የአማራን ህዝብ ለመርዳት የምናደርገውን እንቅስቃሴ የተለያየ እንቅፋት በመፍጠር ፥ እንዳንደርስላቸው ፥ ስም በማጥፋት ፥ አጓጉል መረጃዎችን በመልቀቅ ፥ በመፈረጅ እና መሰል ሴራዎችን በመጎንጎን ተጠምደው ፥ ይህንን ተንኮላቸውን ስናጋልጥ የጎንዮሽ ትግል አታድርጉ እያሉ ዛሬም የአማራን ገበሬ እያሳረዱ እንደሆነ ስለማውቅ ! አዎ በደንብ ስለማውቅ !

7ኛ የአባን ታሪክ ፥ ከግንቦት ሰባት ቃል የተገባላቸው 1ሚሊዮን ብር እና የተሰጣቸው 30ሺ ብር፥ አባን ለማሽመድመድ የተደረገው ሴራ እና ወዘተም ገና እፅፋለሁ !

ግንቦት ሰባት ለወያኔ የአማራ ዱላ ነው ! ዱላነቱን አምኖ ተቀብሎ ቁጭ ስላለ በግንቦት ሰባት ስም ለሚሞቱት አማራሮች ሃላፊነት ወስዶ የበቀል እርምጃ እንደሚፈጥም ሲናገርም ሆነ ሲፈጥም አላየንም ! ግንቦት ሰባት ለአማራው ህዝብ መሳደጃ ፤ ከስራ እና ከህይወት መወገጃ ምክንያት ነው የሆነን ! በራሳችን ለራሳችን እንቁም ! ወያኔ በተባበረ የአማራ ክንድ ይወድቃል ! ያለ ማንም እርዳታ እና ውለታ!

አማራ ንቃ ! አማራ ተነስ !

ኄኖክ የሺጥላ
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 210
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests