በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አልታወቀም!!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አልታወቀም!!!!

Postby ኳስሜዳ » Wed Dec 21, 2016 6:45 pm

በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ስም ተመዝግበው ሰፋፊ የእርሻ መሬትን የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አለመታወቁን ከክልሉ መሬት አሰጣጥ ጋር ተፈጥሯል የተባለን ችግር እንዲያጠና የተቋቋመ ቡድን ይፋ አደረገ። ከአንድ አመት በላይ ጥናቱን ሲያካሄድ የቆየው ይኸው ቡድን በጋምቤላ ክልል ለኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 623 ባለሃብቶች መካከል ለ381 ባለሃብቶች የተሰጠው ከ45ሺ ሄክታር በላይ መሬት ተደራርቦ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል። የተደራረበ መሬት የተረከቡት እነዚሁ 381 ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድር መውሰዳቸውንና ድርጊቱ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱም ታውቋል። ከባለሃብቶች መካከል 29 የሚሆኑት የገቡበት አልታወቀም።ሆኖም ግን ድርጅቶቹ ምን ያህል መሬት ተረክበው እንደነበርና የወሰዱት ብድር መጠን ሳይገለጽ ቀርቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ልዩ ትዕዛዝ ጥናትን እንደሚያካሄድ ተቋቁሞ የነበረው የባለሙያዎች ቡድን በጋምቤላ ክልል ለሰፋፊ እርሻዎች ከተሰጠ 630 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ወደ ልማት የገባው ከ15 በመቶ እንደማይበልጥ ማረጋገጡን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል።

የህንድ ኩባንያዎችን ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች በክልሉ መሬትን ተረክበው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ብድርን ከወሰዱ በኋላ የገቡበት አልታወቀም። ይህንኑ እርምጃ ተከትሎ መንግስት ለኢንቨስትመንት የሚሰጥ የሊዝ መሬትና ብድር እንዲቋረጥ ያደረገ ሲሆን፣ ገንዘብ ይዘው ከሃገሪቱ የተሰወሩ የህንድ ኩባንያዎች ላይ ህጋዊ ዕርምጃ ለመውሰድ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ ልማት ባንክና በብሄራዊ ባንክ ለባለሃብቶቹ ሲሰጥ የነበረ ብድር ለታለመለት አላማ አለመዋሉን ጥናቱን ይፋ ያደረገው ቡድን አክሎ አመልክቷል። ይሁንና ቡድኑ በድርጊቱ ስለደረሰው የገንዘብ ኪሳራ ዝርዝር መረጃን ከመስጠት ተቆጥቧል። ይሁንና፣ 200 የሚሆኑ ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5 ቢሊዮን ብር ብድር ወስደው እንደነበር ታውቋል። በጋምቤላ ክልል የተካሄደውን ይህንን ጥናት ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ አድርጓል፣ እርምጃው ከጥናቱ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው የተገለጸ ነገር የለም። በክልሉ ተሰማርተው የነበሩ ባለሃብቶች 565 ትራክተሮችን ከቀረጥ ነጻ እንዳስገቡ ቢገልጹም በቦታው የተገኙት 312 ትራክተሮች ብቻ መሆኑንም ጥናቱ አመልክቷል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests