የኢትዮጵያ የብድር ዕዳ መጠን በእጥፍ መጨመሩ ተነገረ!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የኢትዮጵያ የብድር ዕዳ መጠን በእጥፍ መጨመሩ ተነገረ!!!

Postby ኳስሜዳ » Wed Dec 21, 2016 7:29 pm

የኢትዮጵያ አጠቃላይ የብድር ዕዳ መጠን ባለፉት ሁለት አመታት በእጥፍ በመጨመር ከ23 በመቶ ወደ 55 በመቶ መድረሱ ተገለጸ። በሃገሪቱ ተመዝግቦ ያለው ይኸው የብድር መጠን ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ሆኖ የተቀመጠ ሲሆን፣ በሰብ-ሰሃራን አፍሪካ ሃገራት የእዳ መጠኑ በአማካኝ ከአመታዊ አጠቃላይ ምርታቸው እስከ 40 በመቶ የሚሸፍን መሆኑን የፋይናንስ ተቋማት መረጃ ያመለክታል። በተያዘው የፈረንጆች አመት ኢትዮጵያ ከተለያዩ አበዳሪ ሃገራትና የፋይናንስ ተቋማት የተበደረችው ገንዘብ ከ36 ቢሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ዕዳው ከሃገሪቱ አጠቃላይ አመታዊ ምርት ውስጥ 55 በመቶ ድርሻ መያዙ ታውቋል።

የአለም ባንክ ሃገሪቱ እየተበደረች ባለው ገንዘብ ላይ የማስተካከያ ዕርምጃን እንድትወስድ በማሳሰብ ላይ ሲሆን፣ መንግስት በበኩሉ ብድሩ የሃገሪቱን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ነው ሲል ምላሽን ሰጥቷል።
ከሁለት አመት በፊት የኢትዮጵያ አጠቃላት የብድር ዕዳ ከአጠቃላይ የሃገሪቱ አመታዊ ምርት ውስጥ 23 በመቶ ብቻ ድርሻ እንደነበረው ለመረዳት ተችሏል።

ይሁንና መንግስት የእድገትና ትራንስፎርርሜሽን እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ ከቻይናና ከተለያዩ አበዳሪ አካላት ከፍተኛ ብድር በመውሰድ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ይሁንና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለው የዕዳ ክምችት በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን እያሳደረ መሆኑን ይገልጻሉ። በተያዘው በጀት አመት መንግስት ወደ ሁለት ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ለብድር ክፍያ መመደቡ ይታወሳል።

ሃገሪቱ እየወሰደች ያለው ብድር ወለድ የሚከፈልበት በመሆኑ የዕዳ ክምችቱ ከአምስትና ከአስር አመታት በኋላ ከፍተኛ ጭማሪን እንደሚያሳይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አስረድተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም መንግስት ከተለያዩ አበዳሪ አካላት ለመበደር የወሰነውን ግማሽ ቢሊዮን ዶላር በፓርላማ እንዲጸድቅ ማቅረቡን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በቅርቡ በፓርላማው ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው 500 ሚሊዮን ዶላር የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለማከናወን ያለመ ነው መባሉን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። መንግስት በከፍተኛ ብድር እያከናወነ ያላቸው የልማት ፕሮጄክቶች በኢኮኖሚው ላይ ጫናን በማሳደር የሃገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ብር ከዶላር ጋር ያለው የመግዛት አቅም እንዲያሽቆለቁል ማድረጉን ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

በቅርቡ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ሪፖርትን አውጥቶ የነበረው የአለም ባንክ መንግስት ብር ከዶላር ጋር ያለውን የመግዛት አቅም አሁን ካለበት መጠን ዝቅ እንዲል ማሳሰቡ ይታወሳል።
ዕርምጃውም በመዳክም ላይ ያለውን የሃገሪቱን የውጭ ንግድ ለማነቃቃት እንደሚረዳ ባንኩ ቢገልጽም፣ የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ዕርምጃው ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል በማለት የማስተካከያ ዕርምጃ እንደማይወስድ ምላሽን ሰጥተዋል።
http://amharic.ethsat.com/
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2146
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests