የአምቦ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ አዲስ ውጥረት ነግሷል።

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የአምቦ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ አዲስ ውጥረት ነግሷል።

Postby ኳስሜዳ » Thu Dec 22, 2016 12:29 pm

ህወሃት እስረኞችን “አሰልጥኜ” አስመረኩ አለ፤ እስረኞቹ “ በፍፁም፣ አይደገምም፣ የቀለም አብዮት፣ ህገ መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የሚሉ ኮርሶች የወሰዱ ናቸው። ህወሃት አምስት ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን “ተመራቂዎች” በሚል መፍታቱን ይፋ ባደረገበት ቀን በተመሳሳይ አምቦ ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ተሰማ።

በአምቦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዶ\ር መረራ ጉዲና አቶ በቀለ ገርባና የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተቃውሞ ትእይንት አደረጉ። በጊንጪ፣ በጉደር ፣በኣወዳይና ሻሸመኔ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃና አሰሳ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳና ሕወሓት ስልጣን እንዲለቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሶስት የመንግስት መኪኖች ጥቃት እንደደረሰባቸው ታውቋል።
Image
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 6 guests