ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ዛሬ አረፈ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ዛሬ አረፈ!

Postby ኳስሜዳ » Fri Dec 23, 2016 7:34 pm

Image
Image
(ዘ-ሐበሻ) በኦሎምፒክ መድረክ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ታሪክ ሲያነሳው የሚኖረው ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ዛሬ ማረፉ ተሰማ::

በካናዳ ህክምናውን ሲከታተል የቆየው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በሕይወት እያለ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሞተ ብሎ ዜና አውጆበት ነበር:: ሆኖም ግን አትሌቱ ከልጁ ጋር በመሆን ከካናዳ በለቀቀው ቭዲዮ በሕይወት መኖሩን መናገሩ ይታወሳል::

ምሩጽ ሜይ 15, 1944 በትግራይ አዲግራት ከተማ እንደተወለደ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል::

ማርሽ ቀያሪው እየተሰኘ የሚወደሰው አትሌት ምሩጽ በሞስኮ ኦሎምፒክ የ5,000 እና የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነው:: ከዚህ የሞስኮው ኦሎምፒክ ድሉ 8 ዓመታት ቀደም ብሎ እ.አ.አ በ1972 የሙኒክ ኦሎምፒክ ወቅት ግን እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ ነበረው፡፡
በ5,000 ሜትር በ10,000 ሜትርና በሌሎችም ውድድሮች 271 የወርቅ ሜዳልያዎች ባለቤትና በአሁኑ ወቅት የ670 ብር ጡረተኛው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በሙኒክ ኦሎምፒክ ወቅት በ5,000 ሜትር ውድድር 3ኛ ወጥቶ (መቼም ለኢትዮጵያውያን ይሄ ሽንፈት ነውና) በ10,000 ሜትር ውድድር ደግሞ አሰልጣኙ ዘግይተውበት ወደ ሜዳ እንዳይገባ ተከልክሎ….እያለቀሰ ቢመለስም ሀገር ቤት ሲመጣ 8 ወራት መታሰሩ ይታወሳል::
ነፍስ ይማር ምሩጽ ይፍጠር! I wish his soul rest in peace!
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 5 guests