የአሜሪካ ኩባንያ ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ጥምረት ፈጠረ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የአሜሪካ ኩባንያ ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ጥምረት ፈጠረ፡፡

Postby ክቡራን » Sat Dec 24, 2016 8:48 pm

ሌጀንደሪ ሜጋ ኮርፕ የተሰኘ የአሜሪካ ኩባንያ ከኢትዮጵያ መከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅትና የመከላከያ የግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ጋር ጥምረት በመፍጠር፣ የአሥር ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለማካሄድ ተስማማ፡፡

ድርጅቶቹ ዓርብ ታኅሳስ 14 ቀን ከቀትር በኋላ በሸራተን አዲስ በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ሌጀንደሪ መከላከያ ምርቶች አክሲዮን ማኅበር የተሰኘ አዲስ ኩባንያ በኅብረት መመሥረታቸውን አስታውቀዋል፡፡ አዲስ የተመሠረተው አክሲዮን ማኅበር 51 በመቶ በአሜሪካውያን ሲያዝ፣ ቀሪው 49 በመቶ በመከላከያ ኮንስትራክሽንና በመከላከያ የግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅቶች የተያዘ ነው፡፡ አዲሱ ኩባንያ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጊዜና ወጪን የሚቆጥቡ የግንባታ ግብዓቶችን እያመረተ፣ ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደሚያቀርብ ኃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡

የሌጀንደሪ ሜጋ ኮርፕ መሥራችና ሊቀመንበር ሄክቶር ሬይስ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ የወሰነው፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለች አገር በመሆኗ ነው ብለዋል፡፡ ኩባንያቸው ባካሄደው ጥናት የመከላከያ ኮንስትራክሽንና የመከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅቶች ትክክለኛ አጋር መሆናቸውን ማረጋገጡን አክለዋል፡፡

አዲስ የተመሠረተው ኩባንያ የሚያቀርባቸው ዘመናዊ የግንባታ ግብዓቶች የፕሮጀክት ወጪን ከ20 እስከ 30 በመቶ፣ የግንባታን ጊዜ ደግሞ በ40 በመቶ እንደሚቀንሱ ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው ምርቶቹን ለመንግሥትና ለግሉ ዘርፍ እንደሚያቀርብ ገልጸው፣ በአዲስ አበባ ለሚካሄዱ የኮንዶሚኒየምና የሌሎች ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄና የመከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻምበል መብራቱ ለምለም፣ ድርጅቶቻቸው ከሌጀንደሪ ሜጋ ኮርፕ ጋር አብረው በመሥራታቸው በቴክኖሎጂና ዕውቀት ሽግግር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

ሌጀንደሪ ሜጋ ኮርፕ በመሠረተ ልማት ዘርፍ የተሰማራ የአሜሪካ ኩባንያ ሲሆን በአፍሪካ በካሜሩን፣ ደቡብ አፍሪካና ጋቦን በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅትና የመከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት እ.ኤ.አ. 2010 በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በ1.3 ቢሊዮን ብር ካፒታል በአዲስ መልክ የተቋቋሙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ 777,634,298 ብር በገንዘብና በዓይነት የተከፈለ ካፒታል ነው፡፡ የሁለቱ ድርጅቶች ዓመታዊ ገቢ ከ2.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን በርካታ የመከላከያ ሕንፃዎችን የሚገነባ ሲሆን፣ እጅግ አስቸጋሪ የተባሉ መንገዶችን በአፋር በረሃ ዳሎል አካባቢ በመገንባት ይታወቃል፡፡ ምንጭ ሪፖርተር፡፡Image
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests