በአዲስ አበባ 2ሺ ሄክታር መሬት የደረሰበት እንደጠፋ ተነገረ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በአዲስ አበባ 2ሺ ሄክታር መሬት የደረሰበት እንደጠፋ ተነገረ

Postby ኳስሜዳ » Tue Jan 17, 2017 12:42 pm

ቅርቡ ይፀድቃል እየተባለ በርከት ላሉ ወራት ሲንከባለል የቆየው የአዲስ አበባ 10ኛው የከተማ ዐብይ ካርታ (ማስተር ፕላን) የአዲስ አበባን የቆዳ ስፋት ድምር ወደ 52ሺ ሄክታር አጥብቦታል፡፡ ኾኖም ከተማዋ ከ1986 ጀምሮ የነበራት የቆዳ ስፋት 54ሺ ሄክታር እንደኾነ ይታወቃል፡፡ 2ሺ ሄክታር መሬት የት ገባ የሚለውን የሚመልስ ባለሥልጣን እስካሁን ማግኘት አልተቻለም፡፡

አዲስ አበባ ከነበራት የቆዳ ስፋት እንዴት ልትጠብ ቻለች የሚለው ጉዳይ በርካታ የመሬት ልማት ባለሞያዎችን ሲያነጋግር የከረመ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት ክፍለ ከተሞች መሪ ፕላኑን በተናጥል እንዲተቹ የተበተነላቸውን ደብዳቤ ተከትሎ በሰጡት ምላሽና ተያያዥ ማብራሪያ የክፍለ ከተሞቻቸው የቆዳ ስፋት ማነስ ጉዳይ በሦስት ክፍለ ከተሞች ዘንድ ተነስቷል፡፡ ከዚህ በኋላም ቢኾን ጉዳዩ በተለያዩ መድረኮች እየተስተጋባ ቆይቷል፡፡

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት በካፒታል ሆቴልና ስፖ በኋላም በጌትፋም ኢንተርናሽናል ሆቴል ከአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የመሬት ባለሞያዎች ባደረጉት ዉይይት ‹‹የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት የቀነሰበት ምክንያት ምንድነው? ይብራራልን›› የሚል ጥያቄ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ተነስቶ የነበረ ሲሆን መሪ ፕላኑን በማዘጋጀቱ ረገድ የመሪነት ሚና የነበራቸውና የማስተር ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩትና በቅርቡ በተዋቀረው በአዲሱ የድሪባ ኩባ ካቢኔ ደግሞ የከተማዋ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ኾነው የተሾሙት አቶ ማቴዎስ አስፋው ጥያቄውን አድባብሰው አልፈውታል፡፡ እንደምታውቁት ልብስም ሲታጠብ መጠኑ እየቀነሰ ነው የሚሄደው፣ አደራ ደግሞ እንደ ኮንዶሚንየሙ መሬቱም ጠፋ እንዳትሉ፣ አንዳንድ የቀሩ ሥራዎች ስላሉ ነው… በማለት … ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ በሁለቱም የዉይይት መድረኮች ጥያቄው ቢነሳም የሆነው ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ የሚሉ ድፍን መልሶች እየተሰጡ ወደ ሌሎች ጥያቄዎች ማለፍ ምናልባት በዉስጥ የፖለቲከኞች ድርድር በኦሮሚያና በፊንፊኔ መካከል መሬትን ሰጥቶ የመቀበል ሂደት እየተካሄደ ይሆን? የሚል መላምት እንዲኖር አስችሏል፡፡
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests