የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት አሁንም ጋምቤላ ገብተው ህጻናትን ጠልፈው ወሰዱ፤ 11 ገደሉ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት አሁንም ጋምቤላ ገብተው ህጻናትን ጠልፈው ወሰዱ፤ 11 ገደሉ

Postby ኳስሜዳ » Tue Jan 17, 2017 11:03 pm

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው 2008 ዓ.ም 200 የሚሆኑ ሕጻናትንና ከብቶችን ከጋምቤላ ዘርፈው የሄዱት የደቡብ ሱዳን የሙሌ ጎሳ አባላት አሁንም በደጋሚ በርካታ ወገኖችን በጋምቤላ በመግደል ተጨማሪ ህጻናትን ጠልፈው መሄዳቸው ተሰማ::

ደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት ከትናንት በስቲያ እሁድ በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ ጥቃት በመፈጸም የገደሏቸው ሰዎች ቁጥር 11 የደረሰ ሲሆን ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው:: እነዚሁ የሙርሌ ጎሳዎች ወደ 20 የሚጠጉ ህጻናትን ጠልፈው መሄዳቸውም ተሰምቷል::

ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ዓመት በሙርሌ ጎሳ አባላት የተዘረፉትን ህጻናት የተወሰኑትን አስመለስኩ ቢል ከ50 በላይ ህጻናት እስካሁን የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ በተደጋጋሚ ዘ-ሐበሻ መዘግቧ አይዘነጋም::

በሙርሌ ጎሳ አባላት ተጥልፈው የተወሰዱት ህጻናት የአኝዋክ ብሔረሰብ ልጆች ናቸው::
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/71328
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2162
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 3 guests