ዛጎሎቹ ( ከአልአሚን ተስፋዬ) ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ዛጎሎቹ ( ከአልአሚን ተስፋዬ) ፡፡

Postby ክቡራን » Wed Jan 18, 2017 3:28 pm

በከፍተኛም ይሁን በዝቅተኛ የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ መጠነ ሰፊም ይሁን መጠነ ጠባብ ታዋቂነት የነበራቸው ግለሰቦች እና የቀድሞም ይሁን የአሁን ፖለቲከኞች ሀገር ውስጥ ሲሰሩ ቆይተው በያዙት አቋም ይሁን ባጠፉት ጥፋት ወይም ምክንያቱ በውል በማይታወቅ ሁኔታ ከመንግስት ጋር ፍቺ ፈፅመው የተሰናበቱ በልዩነት የወጡ የኮበለሉ እና በቦሌ በኩል በኩራት ወጥተው ድምፃቸውን ያጠፉ ሹመኞች ታዋቂ ሰዎች እና ፖለቲከኞች የሚያሳዩትን ተመሳሳይ ባህሪ መዳሰስ ነው የዛሬ ፅሁፌ ዋነኛ አላማ፡፡ተለይም በምንም ምክንያት ይሁን ከሀገር ወጥተው ለረጅም ጊዜ ድምፃቸውን አጥፍተው የሚቆዩ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ የተሟሟቀ ሁካታ፣ አመፅ እና በእነሱ አረዳድ መንግሥት አንድ ሀሙስ ቀረው ብለው ሲያምኑ ልክ እንደቀንድ አውጣ ከተደበቁበት ዛጐል ለአጭር ጊዜ ብቅ ብለው ወደ ዋነኛ መኖሪያቸው ጉድጓድ ተመልሰው የሚሸጐጡት ላይ አተኩራለሁ፡፡
ኢህአዴግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ በአሜሪካ የሚገኘውን የተቃዋሚ ኃይል በማስተባበር ሰልፎችን የመሩ ሴናተሮች መሀል ቁጭ ብለው በሚያስደንቅ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸው “ይህ መንግስት ዕውቅና ሊሰጠው አይገባም እንኳንስ ሀገርን አንድ ቤተሰብ መምራት የማይችል ስብስብ ነው” በሚል ንግግራቸው የሚታወቁት የመጀመያው ቀንድ አውጣ ፖለቲከኛ ኮሎኔል ጐሹ ወልዴ ናቸው፡፡ ጐሹ ከተደበቁበት ወጥተው እንዲያ እንዲያቅራሩ ያደረጋቸው ዋነኛ ምክንያት አዲሱን መንግሥት እጅግ በጣም አሳንሰው ከመመልከታቸው በተጨማሪ በፍጥነት ሰላም እና መረጋጋት አስፍኖ እድሜ ያለው መንግሥት ይሆናል የሚል እምነት ሰላልነበራቸው ነው፡፡ ምን ያደርጋል ተመልሰው ወደ ቀንዳውጣ ዛጐላቸው ለመግባት ያን ያህል ጊዜ አልሰደባቸውም የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሆነው አረፉት፡፡
ከጐሹ ወልዴ ጋር በሚመሳሰል የዘጠና ሰባትን ምርጫ ግርግር ተከትሎ እንደ ቀንድ አውጣ ከዛጐላቸው ለአፍታ ብቅ ብለው የታዩ የተጐማለሉ ቀንድ አውጣ ፖለቲከኞች በርካቶች ቢሆኑም ብርሃነ መዋ፣ ክፍሉ ታደሰ እና ያሬድ ጥበቡ ዋነኞቹ ነበሩ፡፡
መቼም የዚህ ፅሑፍ አላማ ሁሉንም መዘርዘር አይደለምና አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማለፍ ተከትሎ “መንግሥት አበቃለት ከእንግዲህ አንድ ወርም አይቆይም” ሲባል ፈፅሞ ፖለቲካ ውስጥ ገብተው የማያውቁ ዶ/ር ፍሰሐን የመሰሉ ቀንድ አውጣዎች የሽግግር መንግሥት መስረተው ሰሞነኛ መድረኩን ተቆጣጠሩት እንደተለመደው ነገሩ ሲረጋጋ ወደ ዛጐላቸው ገብተው ድምፃቸውን ለማጥፋት ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡
ከመለስ ህልፈት በኋላ ባለፈው አመት የተከሰተው መጠነ ሰፊ ሁከት ተከትሎ ከእንግዲህ ወደ ፖለቲካው አልመለስም እውነትም ሕይወትም ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው ሲሉ የነበሩት ታምራት ላይኔ ከሸሹት እና ከተፀየፉት የፖለቱካ መድረክ በተቃራኒ ከዛጐላቸው መሰስ ብለው የወቅቱ ዋነኛ ቀንድአውጣ በመሆን ሁኔታውን መተንተን እና መፍትሔም መጠቆም ጀመሩ፡፡ ምን ያደርጋል ፈረሰ ያሉት ጨዋታ አለመፍረሱን፤ ተቆረሰ ያሉት ዳቦ አለመቆረሱን፤ ሲመለከቱ ፊታቸውን ወደ ቤተክርስቲያን አዙረው ወደ ዛጐላቸው ጥልቅ አሉ፡፡
ከሥልጣን መውረዳቸውን እና ከሀገር መውጣታቸውን እንጂ የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ሳይታወቅ የቆዩት አቶ ጁነዲን ሳዶ መንግስት አብቅቶለታል አዲስ መንግሥት ሊቋቋም ነው ብለው ባመኑ ሰዐት ከተደበቁበት የቀንድአውጣ ዛጐል ለአንድ አፍታ ብቅ ብለው ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ነኝ፡፡ ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር ሆኜ እክሳለሁ በማለት አዲስ ከሚመሰረተው ሥርዓት ጋር የሥልጣን ተጋሪ ለመሆን ያላቸውን ፍላጐት በሚያሳብቅ ሁኔታ የነገሩ ዋነኛ ተንታኝ እና መፍትሔ ጠቋሚ ሆነው ብቅ አሉ፡፡
መቸም እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው እና ያልጠቀስናቸው ስመጥሮች ነገሩ ሲሰክን እና ሲቀዛቀዝ ተመልሰው ወደ ዛጐላቸው መግባታቸው የጋራ ባህሪያቸው መሆኑን ካየን ዘንዳ ልክ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንደሚባለው ፖለቲካን ግርግር እና ሁከት ሲፈጠር የሚገቡበት ግርግር እና ሁከት ሲጠፋ የሚወጡበት የሌቦች ጨዋታ አይደለምና እንደክረምት ወንዝ ለአጭር ጊዜ ጐርፍ ሆኖ ታይቶ በጋው ላይ ለረጅም ጊዜ ጅረት ሆኖ ከመጉደል ይሰውረን የዕለቱ መልዕክቴ ነው፡፡

ምንጭ
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: ምሰጢር and 5 guests