ቅንጥብ ጣቢ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Jul 18, 2019 12:50 am

ጀቤሳ.........የዘንድሮውን እሬቻ አዱ ገነት ነው የምናከብረው ምንትላለህ?

እስኬቻው.......ማክበር ትችላለህ ኬኛ ማለት አትችልም፤ ጠቅላዩም ወዶ አይደለም ዛፍ የሚተክለው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Jul 19, 2019 12:45 am

"ከፖለቲካው አገር ይበልጣል፡፡ከብሄር ጥቅም በላይ ማዕከላዊ የሆነው "ኢትዮጵያዊነት" ይቀድማል-ይልቃል፡፡"የማንነት" ጥያቄ የሚመለሰው ከአገር ቀጥሎ ነው፤አገርን ጥሎ ማንነትን ማድመቅ፤አገርን አሳንሶ "መንደረተኛነትን"ማግዘፍ ኢ-አመክኖዊ ብቻ ሳይሆን፤ከታላቁ የተፈጥሮ ህግ መጋጨትም ነው(ፀሀይን በምዕራብ እናስወጣታለን እንደ ማለት)"፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Jul 24, 2019 12:24 am

በመከላከያ ሰራዊት የተገደሉ አሉ፤ ሲሉ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ዋና ፀሀፊ ተናገሩ፤ ይቺ ናት ጨዋታ............በፓርላማ ጠቅላዩ የክልል ጥያቄ ህገ መንግስታዊ መብታችሁ ነው በትዕግስት ጠብቁን ብለው በመቶ ሚልዮን ህዝብ ፊት ሲናገሩ፤አጀቶ የሚባል የወጣቶች መንጋ ግን 11-11-2011ለሲዳማ ህዝብ የክልል መሆን ሳይሆን ለዘረፋና ለግድያ የወሰነው ቀን ስለሆነ፤ኢትዮጵያ ሀገሬ ብለው የሚኖሩ ዜጎችን ንብረት በመዝረፍና በማቃጠል ብሎም ህይወትን በማጥፋት፤ አረመናዊ ተግባራቸውን አሳይተዋል፡፡

የሲዳማን ክልል መሆን የምትጥሩ ሰዎች፤ሰውን በማንነቱ በመለየት፤ መግደልና ንብረቱን በመዝረፍ የምታገኙት ጥቅም የለም፤ይልቁንስ በሰላማዊ መንገድ ለሲዳማ ህዝብ አርነት ሲሉ ሎቄ ላይ የተሰውትን ደማቸውን ደመ ከልብ ማድረግ ነው!!!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Jul 24, 2019 1:11 am

"በጎሳ መለያየት የአገርን አንድነት የሚያፈርስ ነው፡፡እኛው እርስ በእርሳችን በጎሳ የምንጯጯህ ሲሆን፤ የበለጠ ሁከት ተፈጥሮ እስከ ደም መፋሰስ ስንደርስ፤ በራሳችን ላይ ጉዳት አድርሰን፤ አገራችንንና ዓላማችንን ለገላጋዮች ሲሳይ ማድረግ ይሆናል"፡፡

ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ(አባባ ጃንሆይ)
Last edited by ዞብል2 on Tue Jul 30, 2019 1:33 am, edited 1 time in total.
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Jul 24, 2019 9:20 pm

በብሄረተኝነት ስሜት ተጠቅመው፤ሌላውን በማሳደድ በዝርፊያና በሌላ መንገድ ፤በርካታ ቤቶችና ሰፋፊ ቦታዎች በመያዝ ፤ከህግ አግባብ ውጪ ሀብት ማካበትና የሚገኝ ጥቅም፤እንደ ቁማርተኛ ገንዘብ ከንቱ ሆኖ ነው የሚቀረው፡፡የኡጋንዳው ኢዲ አሚን ዳዳ የኡጋንዳን ህዝቦችን ሃብታም ለማድረግ ፤ ከሃብታም ህንዶች ላይ ነጥቆ ለህዝቡ ቢሰጥ ፤የኡጋንዳ ህዝቦች ሃብታም አልሆኑም፡፡

አሁንም የኦዴፓ መጤ ካድሬዎች በአዲስ አበባና አካባቢዋ፤ቄሮ በኦሮሚያ፤አጂቶ በደቡብ.........ወዘተ ወገናችሁን ማሳደድና ማፈናቀል አቁሙ፡፡
"አገር ማለት መሬቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ የማህበራዊ ስሪት ጭምር ነውና መጀመሪያ የማንደራደርበት የህግ የበላይነት መከበር አለበት"፡፡ከዚህ ዉጪ ባለው ልንነጋገርና ልንወያይ እንችላለን፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Jul 25, 2019 9:38 pm

በእሬቻ በዓልና በገዳ ስርዓት ሰበብ የአዴፓ/ኦነግ የመስፋፋት አባዜ መግታት አለበት፡፡ከ130ዓመት በሁዋላ በአዲስ አበባ ፤በጉራጌ ዞን ደግሞ ከ158ዓመት በሁዋላ እናከብራለን ይሉናል ለመሆኑ ይህን ሁሉ ዘመን የት ነበሩ?በነዚህ ዘመናት እነባልቻ አባነፍሶና ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ አዳዋ ላይ፤ገርሱ ዱኪና ጃጋማ ኬሎ በጣሊያን ወረራ ሲሳተፉ፤ እሬቻ በዓል ወይም የገዳን ስርዓት አያውቁትም ማለት ነው?ወይስ የዘመኑ ኦሮሞ ሊህቃን የኦሮሞን ታሪክ መፃፍ ሲጀምሩ ምንሊክ ብለው ካልጀመሩ ስለማይሆን ነው? ለማንኛውም እግዚአብሄር ሰላሙን ይስጣችሁ፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Jul 26, 2019 12:49 am

"መኖርም መሞትም የከበደብሽ
የነ ንጠቅ ሀገር ጦቢያ እንዴነሽ"
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat Jul 27, 2019 9:33 pm

የወያኔ አለቃ የነበረው መለሰ ዜናዊ በአንድ ወቅት "ኦነግ የኛ አስተዳደር ደስ ካላለው ወደ መጣበት ማዳጋስካር መሄድ ይችላል"ሲል የኦሮሞ ሊህቃን ምንም አላሉም፤እንዲያውም ጠቅለው አዳማ ከተሙ፤ ጨፌያቸውን እዛው አደረጉ፡፡አሁን ደግሞ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ ኦሮሞ ማዳጋስካር አግኝቻለሁ ብላ እንደ ምሳሌ ብትናገር፤ያወቁ የመሰላቸው ነገር ግን ከዕውቀት ነፃ የወጡ አትርሱን ባዮች እሪ እምቧ እያሉ ነው፡፡ ለማንኛውም ግን ትንሽ የዕውቀት ነፋስ ሽው እንዲልባችሁ፤ ሙሉው ንግግር በዩ ቲዩብ ስለሚገኝ ለግንዛቤ ስለሚረዳችሁ እዩት፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat Jul 27, 2019 9:40 pm

"ዶ/ር አብይ የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ቢነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ"


ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ
Last edited by ዞብል2 on Mon Jul 29, 2019 8:26 pm, edited 1 time in total.
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Mon Jul 29, 2019 8:25 pm

"ኦሮሞና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም"(አሪፍ የመልስ ምት)ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Jul 30, 2019 1:32 am

ተስፍሽ...........ሀገራችንን በችግኝ ተከላ በጊነስ መፅሃፍ ላይ በቀዳሚነት ለማስመዝገብ ደፋ ቀና እያልን ነው

ገብርሽ...........ይልቁንስ በሌላ ነገር እንዳንታወቅ ፍራ

ተስፍሽ..........በምን?

ገብርሽ..........በችግር ተከላ

ከሪፖርተር ደረ ገፅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Jul 31, 2019 12:10 am

የአዱ ልጅ.......ጁዋር ለምን ችግኝ አትተክልም

ጁዋር......ምነው ግድ አለብኝ እንዴ?

የአዱ ልጅ........አይ የለውጡ አራማጅ ስለሆንክ

ጁዋር........ስም አታጥፋ እኔ የለውጥ አራማጅ አይደለሁም

የአዱ ልጅ........አሃ አሁን ነቃሁብህ.......የዛሬ ዓመት ዛፊ ኬኛ ለትል ነው አይደል?

ጁዋር.......ቡዳ በምን አወቅህ?

የአዱ ልጅ..........አንተ ሌላ ምን መፈክር አለህ ከሀገር ውጪ እያለህ ቢትኔሽን ኢትዮጵያ ሀገር ቤት መጥተህ ሁሉም ነገር ኬኛ ኬኛ ነው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Aug 01, 2019 9:17 pm

የአዱ ልጅ............ጃዋር አንተ አራዳ ነህ ፋራ? ወይስ አሪፍ ነህ ቀሽም?

ጃዋር...................እኔ አራዳ አደለሁም ነገር ግን አሪፍ ነኝ

የአዱ ልጅ..........አትኮምክ.........እስቲ ስለ እርፍናህ ንገረኝ?

ጃዋር......... ስለ እኔ እርፍና ትጠራጠራለህ እንዴ?ቄሮና አጀቶ ምስክሬ ናቸው፡፡

የአዱ ልጅ.......ማለት?

ጃዋር............እኔ ሰንበት ት/ቤት የቦክራ ወተት እጠጣ የነበረው ነገር ግን በወተትና በቅቤ ያደጉትን ቄሮና አጀቶ የሚባሉ ወጣቶችን በአንድ ቃል ሳንጋጋቸው ስታይ አሪፍ መሆኔ አይታይህም?

የአዱ ልጅ.......እሺ ሌላስ

ጃዋር..........የኩዬ ፈጨ ኮንዶሚንዬምን ጅራ ጅርቱ በሚል መፈክር ሳስቆም፤የሆሮማያ ዩንቭርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቤ ፊንፊኔ ኬኛ ሳስብል እርፍና አይደለም?

የአዱ ልጅ.......እሺ ቀጥል

ጃዋር...............እኔን ለመቀበል ቦሌ የተገኘው ህዝብ መንግስቱ ሃ/ማሪያም በ17ዓመቱ አይቶት አያውቅም፤መለሰ ዜናዊ እንኳን በህይወቱ ሳይሆን እሬሳውን ለመቀበል የወጣው ሰው ብዙ ነው......እና ይሄ እርፍና አይደለም?

የአዱ ልጅ.........ሰው አንተን ለመቀበል የወጣው በአፍ ስትናገር ሰምቶ እንጂ ድርጊትህን ተመልክቶ አይደለም

ጃዋር...............እኔ የአክሽን ሰው አይደለሁም ማለት ነው?

የአዱ ልጅ.......አዎ አፈ ሌባ ነህ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ጃዋር.........ኢንዴ ነች ኢና ኢ ኢ ኢ ኢ

የአዱ ልጅ......በል ቻው ቂቂቂቂቂቂ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Aug 02, 2019 9:12 pm

ጠቅላዩ 100ሚልዮን ህዝብ የሚመሩት፤ለአገዛዜ ካልተመቸኝ፤ ኢንተርኔትን እስከ ወዲያኛው እዘገዋለሁ አሉ፤ታጥቦ ጭቃ ወይም የከርሞ ጥጃ ማለት አሁን ነው፡፡ ምን አልባት
እኚህ የተማሩ የተመራመሩ፤በየአዳራሹ ዲስኩር ሲያሰሙ ህዝብ በጭጨባና በሆታ የሚቀበላቸው ሰው፤በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን ኢንተርኔት ከሰብዓዊ መበት አንዱ መሆኑን ረስተውት ይሆን? ወይስ እኔ አሸጋግራችኋለሁ እንዳሉት፤ኢንተርኔቱንም በእሳቸው ፈቃድ የሚለቁልን?
የተሸውደነው ያኔ እኔ አሸጋግራለሁ ያሉ ጊዜ ነው፤ኢህአድግ መሆናቸውን እረስተን፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Aug 06, 2019 11:54 pm

"ትላንት ለሃሳብ ነፃነት ሲጮሁ የነበሩ፤ዛሬ የሌሎችን የተለይ ሃሳብ አልሰማም እያሉ ሲወራጩ ማየት አንገት ያስደፋል፡፡በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እያስተማሩ ያሉና የዕውቀት አባት ይሆናሉ ተብለው የሚገመቱ፤ቁልቁል ወርደው የዘረኝነት መርዝ ሲረጩ ያማል፡፡በአጠቃላይ የብልሆችበመርህ መሰብሰቢያ መሆን የሚገባውን ፖለቲካ፤ የመንደር ጨዋታ የሚያደርጉ እየበዙ ናቸው፡፡በመርህ ሳይሆን በስሜት ነው የሚመሩት፡፡የነሱ ሳያንስ የሚያሰልፉት መንጋ ደግሞ ዓይኑን ጨፍኖ ስለ ሚደግፍና ስለ ሚቃወም፤ከሐሳብ ልውውጥ ይልቅ የሚቀናው መገዳደልና ማዉደም ነው፡፡ኢትዮጵያ ካሰበችው ሳትደርስ መንገድ የምትቀረው በእንዲህ አይነቶቹ አጉል ፉክክር ምክንያት ነው"፡፡

ከሪፖርትር ደረ ገፅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2326
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 10 guests