ቅንጥብ ጣቢ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Aug 09, 2019 12:16 am

የአዱ ልጅ...........ሃሎ ሃሎ እንዴነህ ጃዋር

ጃዋር..........ማነህ?

የአዱ ልጅ..........የአዱ ልጅ ነኝ ከአዱ ገነት

ጃዋር.............የምን አዱ ገነት? የፊንፊኔ ልጅ ነኝ በል

የአዱ ልጅ.........ስማ አንተ አንጀበኛ አሁንም ይሄ ትቢትህ አለቀቀህም ሚኒሶታ መጥተህ?

ጃዋር.............አንተ መጤ ሰፋሪ ስድቡን ተውና ለምን ነው የደወልክልኝ?

የአዱ ልጅ........ጀጋው ኬኛ ቅቅቅቅቅቅ አቢሲኒያ እያለህ ምን እንደተሳካልህ ልጠይቅህ ነው?

ጃዋር...............ስማ አንተ ነህ የእኔን ስኬት የምትጠይቀኝ? ወይ ድፍረት?

የአዱ ልጅ........ምነው ጃዋር ገጀራና ዱላ ይዘው ስታሰልፋቸው የነበሩትን ሰዎች አየናቸው እኮ?

ጃዋር...............አይ እነሱ መንደር ውስጥ ማስፈራሪያ የምጠቀምባቸው ናቸው፡፡

የአዱ ልጅ.........ማስፈራሪያ? አክትቪስት ነኝ ስትል አልነበር እንዴ?

ጃዋር................አዎ አሁንም አክትቪስት ነኝ!!!!

የአዱ ልጅ...........በማህል አዲስ አበባ ቄሮ ፤በሃዋሳ አጀቶ የሚባል የጠረባ ቡድን መስርተህ፤ ህዝብ ስታተራምስ የነበርክ፤አክትቪስት ሳትሆን ደንበኛ ጀጋ አናርኪስት ነህ ቂቂቂቂቂቂ

ጃዋር.............አንተ ወመኔ ጆሮህ ላይ እንዲህ ነው የምዘጋው

የአዱ ልጅ.........ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Aug 13, 2019 9:48 pm

"ዛፍ መትከል ተስፋን መትከል ነው"እንዲሉ፤ ነገር ግን 4ቢሊዮን ዛፍ ለመትከል ፤40ቢሊዮን ገንዘብ ማውጣት ግን ጥያቄን ያጭራል?ምክንያቱም ይህ ገንዘብ ለመጪው ትውልድ ዕዳ ነው፡፡40ቢሊዮን ብር እንደ ኢትዮጵያ ላለ ድሃ ሀገር ለችግኝ ማውጣት ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው፡፡ከ4ቢሊዮን ችግኝ ስንቱ እንክብካቤ አግኝቶ እንደ ሚያድግ እግዜር ነው የሚያውቀው፤ምክንያቱም በዘመቻና በሆይ ሆይ የሚደረግ ሁልጊዜም ውጤቱ አመርቂ አይደልም፡፡ለዚህም የዘመቻ ታሪካችን ምስክር ነው፡፡40ቢሊዮን=40ሺ ሚሊዮን ብር ነው፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Aug 14, 2019 12:01 am

"አሮ ሆዴ ተክኖ ሆዴ፤ፍምም አልወረደው
እህል እየበላ፤ ውሃ እያበረደው"
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Aug 20, 2019 1:05 am

"እሪ በከንቱ"

"ያበጀሁትን ሻማ
ጠልፈውት በጭለማ
ቁጭ ብያለሁ ከጥጌ
ቁጭትን እንኳን ተነፍጌ"


ደራሲ ዳንኤል ታረቀኝ "ባይተዋር" ከሚለው ግጥም <<የአዲስ አበባ ጉዳይ አይመለከታችሁም ለተባሉ የአዲስ አበባ ልጆች>>ያበረከተው፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Aug 20, 2019 9:09 pm

ኖረን እኮ አናቅም
ከባህር ጠርዝ ላይ
እንደ ክቡር ድንጋይ
እሬሳ ስንለቅም፡፡
ከሙሴ ተምራን
ባህር መግመስ ሲያምረን
በታንኳ ሄድንና በሳጥን ተመለስን፡፡

ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Aug 23, 2019 12:34 am

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሚኛ አይነገር ያለህ ማነው?ቋንቋ ማወቅ ወንጀል አይደለም፡፡ጃዋር(ሽብሩ) ጫንቃውን እንደ ወፍጮ ቤት ፍየል አሳብጦ በአአአአአ.......በአአአአአ.....በአአአአ እያለ ሀገር የሚያሸብረው በኦሮሚኛ ሳይሆን አማርኛ መናገር በመቻሉ ነው፡፡ኦቦ ሽመልስ አንተ ከቀረው የሃገሪቱ ክልል ባለስልጣናት በአማርኛ እየተግባባህ ሌላውን ህብረተሰብ መናገር አትችሉም ማለት ወንጀል ነው፡፡ጋሽ ሽመልስ ለነገሩ ሲያዩህ የሲቪል ሰራተኛ ሳይሆን ቦዲጋርድ ወይም ደረትህ ላይ ዲንጋይ የምታስፈልጥ የመንደር ጉልቤ ነው የምትመስለው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Aug 23, 2019 9:49 pm

ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ በጊዜ ገደቡ መደረግ አለበት ከሚሉት ቡድኖች ህውሃትና ኦነግ ይገኛሉ፤ህውሃት ማለት የትግራይ ነፃአውጪ፤ኦነግ ደግሞ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ማለት ነው፤እነዚህ ድርጅቶች ነፃ ለመውጣት ከፈለጉ ለምንድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ ምርጫ የሚያካሂዱት? ደግሞስ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይካሄድ ከተባለ እንደ ህውሃት ያለ እስከ አፍንጫው የታጥቀ፤ኦዴፓና አዴፓ በክልልና ልዩ ሃይል በሚል የሚያዙት የታጠቀ ሃይል ያላቸው እያሉ፤ እንዴት ተደርጎ ነው ሰላማዊ ምርጫ የሚደረገው? ምርጫ ቦርድ ማድረግ ያለበት፤በነፃ አውጪና በንቅናቄ ስም የሚጠሩትን የታጠቀ ሃይላቸውን አፍርሰውና ስማቸውን ቀይረው እንዲመዘገቡ፤እንደ ኦዴፓና አዴፓ ያሉ በክልል ስም የታጠቀ ሃይል ያላቸውን፤የእዙን ቁጥጥር ከፓርቲያቸው እንዲያወጡ ማስደረግ፡፡ይህ እስካልተደረገ ድረስ ምርጫው ተአማኒ ሊሆን አይችልም፡፡ይህ ካልሆነ መሳሪያ የያዘው ሲሸነፍ፤እጅ ወደ ላይ ሊል ይችላል፡፡ይህንንም አካሄድ በምርጫ 1997 አይተነዋል፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Aug 27, 2019 9:25 pm

"በመሰረቱ ቋንቋ ካወቅህ ተናጋሪውን ታውቃለህ፡፡ተናጋሪውን ካወቅህ ባህሉን፤ስነ ልቡናውን ታውቃለህ፤አስተሳሰቡን ታውቃለህ፤ችግሩ ችግርህ እንደሆነ ታወቃለህ፡፡የአንድ አገር ልጆች መሆናችሁን ታውቃለህ፡፡አባቶቻችሁ ለሀገራችን ነፃነትና አንድነት በአንድ ጉድጏድ መቀበራቸውን ታዉቃለህ፡፡ይህን ካወቅህ የራስህ ባለቤት ትሆናለህ፡፡የራስህ ባለቤት ከሆንክ አትታዘዝም፤ካልታዘዝክ አይመቻቸውም፡፡ነፃ ከሆንክ እንደ ጃዋር ያሉ ፅንፈኞች ይከስራሉ"፡፡

ሙክታር አደም(የቦረናው) ጃዋርን ስቀሉት(ሃሳቡን) ከሚለው ፅሁፍ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ፤ፅሁፉ ዘሐበሻ ደረ ገፅ ላይ አለ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Aug 29, 2019 12:09 am

በቅርቡ በወጣው የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሰረት፤

1ኛ፡አማርኛ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ይሰጥ ተባለ እንጂ፤ሁሉም የትምህርት ዓይነቶች በአማርኛ ቋንቋ ይሰጥ አልተባለም፡፡

2ኛ፡ የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በብሄራዊ ደረጃ ተዘጋጅቶ በየ ክልሉ ቋንቋ ተተርጉሞ እንዲሰጥ ነው፡፡

በሀገራችን እንግሊዘኛ በሁሉም ክልል እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት በየክፍሉ ይሰጣል፤ምክንያቱም ዩንቭርሳል ቋንቋ ስለሆነና ለከፍተኛ ትምህርት የሚያገለግሉ በቂ ሪሶርስና መፃህፍት በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻልና......ወዘተ፡፡

አማርኛም እንደ እንግሊዝኛ እንደ አንድ ትምህርት ቢሰጥ፤ተማሪው በቀላሉ ከሌሎች የሀገሪቱ ተማሪዎች በቀላሉ ለመግባባት፤ወደፊትም ትምህርቱን ጨርሶ ስራ በሚይዝበት ጊዜ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ቋንቋ ሆኖ ያገለግለዋል፡፡

የስምንተኛ ክፍል ፈተና በትምህርት ሚኒስትር መዘጋጀቱ፤ከ9ኛ እሰከ 12ኛ ያለውን የትምህርት ስርዐት በበላይነት የሚመራው የፌደራሉ ትምህርት ሚ/ር ስለሆነ የሚቀበላቸውን ተማሪዎች የሚመዝነበት ይሆናል ማለት ነው፡፡

በቀላሉ የትምህርቱ የፍኖተ ካርታ ይህን ይመስላል፤ አንድ ኢትዮጵያዊ የዓለም መግባቢያ የሆነው እንግሊዝኛ እየተማረ፤ከወገኖቹ ጋር የሚግባባበት የፌደራሉን የስራ ቋንቋ አትማር ማለት ትርጉም አይሰጥም ደግሞስ ማን ማን ማንዴት ሰጥቶት ነው አይማሩም ብሎ የሚከለክለው?

የሚኒሶታ አራዶች ስለ ኦሮሚያና ኦሮሞ ነጋ ጠባ ያ ወራሉ፤ ሁል ጊዜ ስለ አንድ ነገር ሰለሚያወሩ ደንቁረው ሌላውንም ያደነቁራሉ፡፡ ለዚህም እነ ጃዋር ኦሮሞና ኦሮሚያ እንዲህ ነው ይሉና መፍትሄውን ሳይነግሩህ፤ይህቺ ሀገር የመበተን አደጋ ላይ ነች ወይም ደግሞ ቢቴንሺን ኢትዮጵያ ይሉሃል፡፡ቂቂቂቂቂቂ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Aug 30, 2019 12:14 am

ጃዋር(ሽብሩ) የሚያስበው እንደ መንደር ህፃን ነው፤ አይደለም አገር ሊመራ ቀበሌም ማስተዳደር አይችልም፡፡ቂቂቂቂቂቂቂቂቂ

ጌታቸው ረዳ(ቮድካ) ስለ ጃዋር የተናገረው
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Aug 30, 2019 5:45 pm

የአረና ፓርቲ አባል ንብረት የሆኑ 13 ፍየሎች ትግራይ ክልል ውስጥ መታሰራቸው ተሰማ ቅቅቅቅቅቅ ይቺ ናት ጨዋታ ፤ አቦ እነዚህ ቢቴንሽን ኢትዮጵያ እያሉ ከሚያላዝኑብን የመንደር ጋጠ ወጦች(ጃዋር ጋቢሳ አራርሶ)የወያኔዎች ፍየል ማሰር ጫዋታ ይለብጣልቂቂቂቂቂቂቂ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat Aug 31, 2019 8:04 pm

የአረና ፓርቲ አባል ንብረት የሆኑትና አሁን በእስር ላይ የሚገኙትን ፍየሎች፤ቅጠላቅጠልና ሳር ይዘው ለመጠየቅ የሄዱትን በጎች ለተወሰነ ስዓታት በማገት፤አዛኝ ቅቤ አጏች፤አስመሳይ.....ወዘተ በሚሉ ወያኔያዊ ማስፈራሪያ ቃላቶችና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ተለቀዋል፡፡ቅቅቅቅቅቅቅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue Sep 03, 2019 9:46 pm

ቀሲስ በላይ የሚባለው ሰው ፡የመንፈሳዊ ኮሌጅ ስራ አስኪያጅና፤ከዚያም በኦህዴድ አባልነት ተመርጦ ፓርላማ የገባ ነው፡፡ ቀሲስ በላይ የፓርላማ አባልነት ደመወዙን እና የመንፈሳዊ ኮሌጅ ስራ አስኪያጅ ደመወዙን ሲከፈለው የነበረ ሰው ነው፡፡

"ቁራ ቀሚስ ወደ አንገቱ ያጠልቃል ፤ቁራ የተባለው ቁራ አይደለም የዘመኑ ቄስ እንጂ"
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Sep 04, 2019 12:32 am

ቀሲስ በላይ ዛሬ ጠቅላይ ፅህፈት ቤት ልመስርት ካለ፤ ነገ አራዳ ጊዮርጊስ ኬኛ፤ግቢ ገብርኤል ኬኛ፤ ቁሉቢ ኬኛ፤ደብረ ሊባኖስ ኬኛ፤አሰቦት ገዳም ኬኛ፤..........ወዘተ እንደ ማይሉ ምን ማረጋገጫ አለን?ከሁሉ የሚገርመው በሃይማኖት ስም መግለጫ ለመስጠት መጥተው አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት ስለ ሆነም በኦሮሚኛ መቀደስ አለበት እያሉ ሲደነፉ፤ምን አይነት ፋናቲክና ዝም ብለው ፤የዕውር የድንብር የሚነዱ መሆናቸውን ያስታውቃል፡፡ኦሮሚያ ውስጥ በኦሮሚኛ ለማስቀደስ የሰው ሃይል እጥረት ባለበት፤እንዴት አድርገው ነው 44 ታቦታት ያሉበት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በኦሮሚኛ ማስቀደስ የሚችሉት?ደግሞስ በሃይማኖት ለእግዜር ይሰጣል እንጂ እንዴት እንደ ፖለቲከኛ እርምጃ እንወስዳለን ይባላል?
ቀሲስ በላይ ከዋልድባ ገዳም ትምህርት ውሰዱ ፤አባ ጳውሎስና መለሰ ዜናዊን አከታትሎ የወሰደው ዋልድባ ነው ፡፡
Last edited by ዞብል2 on Thu Sep 05, 2019 12:27 am, edited 1 time in total.
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Sep 05, 2019 12:27 am

"የማነው ብትለው ዘልቀህ ማጀቱን
የእግዜር ነው ይልሀል የገዛ ቤቱን
ዛሬ ኖሬ ሟች ሰው ነገን መች አውቃለሁ
እንኳን አለኝ ያልኩት እኔም የኔ አይደልሁ"

ጊዜ ከተሰኘው የጃኪ ጎሳዬ ዘፈን የተወሰደ ስንኝ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2362
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests