ቅንጥብ ጣቢ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu May 09, 2019 11:34 pm

ያኔ በደጉ ዘመን(የጭቁኖች ልደት የሚባል ቀን ባልነበረበት ዘመን) ጨቅላ ነበርኩኝ ህፃን፤ኑኑዬ ጨቅላዋ፤የሺ ሃረጊቱ፤ያ ጥቁር ግስላ፤ያ ደበሌ ያዳ፤ደቅሰይ ነይረ.........ወዘተ በዘር በማይዘፈንበት ጊዜ፤ሻይ ቤት ሻይ ታዞ ከ4 ብስኩት(ትኩሌ.ፓስቲ.ጮርናቄ ወይም ዳቦ)ይቀርብ ነበር፤ሌላው ቢቀር ቀበሌ ተሰልፈን በ1ብር 10 ዳቦ ገዝተን በፌስታል ይዘን እንሄድ ነበር፤ያኔ የወር ደሞዝ በኪስ ነበር የሚያዘው...........አሁን ግን እንደ ሽንኩርትና ቃሪያ በፊስታል ነው የሚያዘው፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Tue May 21, 2019 10:05 pm

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ማሰብ ራሱ የአባቶቻችንን ስጋና አጥንት ማፍረስና መቀንጠስ ማለት ነው፡፡በጣልያን ቦንብ ተደብድቦ የተበተነውን አካላቸውን እንደ ጅብ መጋጥ ነው፡፡ እርም መብላት ነው፡፡ክህደትም ነው፡፡ኢትዮጵያ የነፃ ስጦታ ሳትሆን በመስዕዋትነት የተሠራች፤የደም ዋጋ ናት፡፡ከድረ ገፅ ላይ የምናወርዳት ፊልምና ታሪክ ሳትሆን፤በፈርሰ የጀግኖች ሥጋና አጥንት፤በውድ የሰው ልጆች ደም የተገኘች ብርቅ ናት፡፡
ኢትዮጵያ የሁላችንም አባቶችና ቅድመ አያቶች መስዕዋት የከፈሉባት "እኔ ልሙትና አንቺ ኑሪ" ተብላ ተከብራ የቆየች ሃገር ፤"አንቺን ገድዬ እኔ ሆዴን ልሙላ"በሚል አሳፋሪ ታሪክ መቀየር የለበትም!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed May 22, 2019 10:55 pm

"ብሄረተኝነት በድህነታችን ላይ የተወጋነው ማደንዘዣ ነው"
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri May 24, 2019 1:23 am

ባለፈው ዓመት በለገጣፎ ህፃናት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ቤታቸው በህገወጥ ግንባታ ስም ፈረሰባቸው፤በዛሬው ዕለት ደግሞ በአራት ኪሎ አካባቢ የትም መሄጃ የሌላቸው ወግኖቻችን በህግ ወጥ ስም የሚኖሩበትን መጠለያ በማፍረስና የቤት ዕቃዎቻቸውን በማቃጠል ባዶ እጃቸውን አባረሯቸው፡፡ከሁሉ የሚያሳዝነውና በጣሙን የሚያመው ላለፉት ቀናት በጣለው ከባድ ዝናብ ሲሰቃዩበት ከነበረው ድካም እፎይ ሳይሉ ነው፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri May 24, 2019 8:51 pm

ወያኔዎች በመልሶ ማልማት ስም ቤት ሲያፈርሱ፤የለገጣፎ መጤ ካድሬዎች ህገ ወጥ ግንባታ ሲሉ፤ታከለ ኡማ ደግሞ በወረራና በወራሪዎች የተገነቡ ሲሉን፤ በእነሱ ትዕዛዝ ስር ያለው የፖሊስ የት ነበር?ወይስ ቤትን የሚያክል በአንድ ጀምበር በቅሎ አደረ ? ጉድ ነው!!!!

ከሰጡት መግለጫ ውስጥ ቤቱ እንዲሰራ ወይም ድጋፍ የሰጡት ሁለት ፓርቲዎችና ባለ ሃብቶች አሉበት አሉን፤ቀጠል አድርገውም በመፍረሱ የሚጎዱት በዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩ ማህበረሰብ ነው አሉን፤ግን መታወቅ ያለበት፤እዚህ ላይ ህግ እያስከበሩ ካሉ፤የእነዚህንም በዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩትንም ሰዎች የመኖር መብት ማስከበር አለባቸው፤ለሁለት ፓርቲዎችና ባለሃብቶች ጥቅም ሲባል የወንጀል ሰለባ ሆነዋል፤በህገ ወጥ ተሰሩ የተባሉት ቤቶችም ከመፍረሳቸው በፊት በፍርድ ቤት በማስረጃነት ቀርበው፤ለነዚህ መጠጊያና መሄጃ ለሌላቸው ዜጎች ካሳ ወይም ምትክ እንዲሰጣቸው ያስፈልጋል፤ይሄ ሲሆን ነው ህግ ሊከበር የሚችለው፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat May 25, 2019 8:38 pm

"አንዳንዱ ሀገሩን-በድስትና ኪሱ-ሰፍሮ ነው የሚያያት
ጨዋታ ነው ታሪክ-ተረት ነው ዝብዘባ-አጥንት፤ደም፤አያት፡፡
ሌላው ሜዳ ፈሶ-በዕውን እንዳልታይየች-የያዕቆብ መሰላል
ባዶ ድስት ታቅፎ-የከበረች-ሀገር በህልሙ ይስላል፡፡

ገጣሚ አበረ አያሌው
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed May 29, 2019 12:21 am

በውጪ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ በቀን ለቡና መጠጫ ከሚያወጣው 1ዶላር በማዋጣት፤ለትምህርት ቤት ማሰሪያ ለግሱን እየተባለ፤የኢትዮጵያ ህዝብ ከዛሬ 130ዓመት በፊት በባዶ እግሩ እየሄደና በሳር ጎጆ ቤት እየ ኖረ፤የሰራውን የሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለማፍረስ መነሳት ምን ማለት ነው????
የሚሰራውስ መንገድ ከዚህ ታሪካዊና የኢትዮጵጵያ ህዝብ ድንቅ መታሰቢያና የዘመናዊነት አሻራ ቢበልጥና ጥቅም ቢኖረው ነው??
ወይስ እንደ ዘመኑ አባባል ትምህርት ቤቱ የዛሬ 130ዓመት ሲሰራ በተወረረ መሬት ላይ ነው??
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu May 30, 2019 11:54 pm

"ዝቅ ካላለበህ ኑሮህ ካልጎደለ
እኔን እንደ ኑሮዬ ብትተወኝ ምንአለ
አልጨምር አልቀንስ እኔ ባንተ ህይወት
መኖሬ ምንድነው የሆነብህ ፍርሃት"
ከወለላዬ

የክረምት ወር(የዝናም ወቅት)እየመጣ ነው፤በፕላስቲክ መጠለያና በትንሽ ዳስ የሚኖረውን ለፍቶ አዳሪ ፋታ ስጡት፡፡
ከሁሉ የሚገርመው በሀገሪቱ ህገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ፤ባለ ስልጣኖች ተሰብስበው ውሳኔ ያስተላለፉት መቀሌ ከተማ ነው ይቺ ናት የአሁኖቹ ኢህአድጎች አዲሱ ጨዋታ በአደባባይ ሌላ(የተጣሉ መምሰል)የመሬትመቀራመት(የሚበላ ሲገኝ እንደ ጅብ መሰባሰብ)ሲሆን በአንድ ጠረጴዛ ላይ ተሰብስቦ ለውሳኔ መቅረብ እስቲ ይሁና መቼስ ማል ጎደኒ!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Mon Jun 03, 2019 11:50 pm

"በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት መንግስት የዜጎችን መብትና ጥቅም የማስጠበቅ እንጂ ፤የማፈናቀልና መጠለያ የማሳጣት እርምጃ የመውሰድ መብት የሌለው መሆኑን ያሳያል"፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat Jun 08, 2019 9:04 pm

".....ህይወቱን እራሱ መርጦ እንደኖራት
ሞትንም እራሱ ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ እንደሚሞታት
እኔም የራሴን ሞት እራሴው ልሙታት...."

ቴዎድሮስ በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Jun 12, 2019 12:40 am

ስማ በአዲስ አበባ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ዕብዶች አሉ ዕውነት ነው?
ስማ ተፋፍረን ነው እንጂ ሁላችንስ ሳናብድ ቀርተን ነው፡፡
እውነት እኮ ነው፤ ለዘመናት ከልጆቻችን አፍ ሳይቀር ነጥቀን ቆጥበን የሰራነውን ኮንዶሚኒየም፤ባህር ማዶ 11ሺ ማይል ርቀት ተቀምጦ በርገሩን ሲገምጥ የኖረ አክትቪስት የመንደር ወጣቶችን ገጀራና ዱላ አሲይዞ ኮንዶሚኒየም ኬኛ ሲለን፤በአዱ ገነት መንገዶች ገጀራና ዱላ የያዙ ቄሮዎች ዝም ተብለው፤በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ የያዙ የአዱ ልጆች ግን ታፍሰው ጦላይ ሲክረቸሙ፤የአዲስ አበባ ህዝብ ራሱ በመረጠው ህዝብ መተዳደር አለበት ለዚህም መሳካት ባላደራስ የሚል ኮሚቴ ቢመሰርቱ፤ ጦርነት እናውጃለን ተባለ፤ ታዲያ እነዚህን ስናይ ዝም ያልነው አብደን ነው ወይስ ፈርተን????
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat Jun 15, 2019 8:59 pm

"መሸ በሩን ልዝጋው ከቀረ ልማዴ
ተከፍቶ ማደሩን አይሻውም ሆዴ"
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Jun 20, 2019 12:34 am

"የኢትዮጵያ ህዝብ ኢሳትን ሲረዳ ከሁዋላው ያሉትን ፖለቲከኞች፤ከዉስጡ ያሉትን ጋዜጠኞች በአስተዋፆቸው ብቻ እየመዘነ እንጂ በትናንት ማንነታቸው አልነበረም፡፡የነገ አካሄዳቸውን የሚመዝነውም የእለት በእለት ስራቸው እንጂ ጭፍን ዋስትና ይዞ አይደለም፡፡
በኢሳት ውስጥ የቀራችሁትም፤ከኢሳት የወጣችሁትም ከአሁን በሁዋላ የምትመዘኑት በስራችሁ እንጂ በገባችሁት ቃል አይደለም፡፡ከሁሉ በላይ የህዝቡን የማመዛዘን ክህሎት የሚፈታተን እራስን ንፁህ ለማድረግ የምታደርጉት ጉዞ ህዝባዊ ድጋፍ ይቀንስባችሁ እንደሆን እንጂ ምንም አይጨምርላችሁም፡፡ስትከባበሩ ህዝብን እንዳከበራችሁ ይቆጠራል፡፡ሌላ ላይ ጭቃ የሚወረዉር መዳፍ ምንግዜም ንፁህ አይሆንም፡፡በህዝቡ ድጋፍ ያገኛችሁትን ተሰሚነትና ከበሬታ ቆሻሻ ላይ አትጣሉት"፡፡

በያላችሁበት ስራችሁን በከበሬታ ከሰራችሁ ህዝቡ ከእናነተ ጋር ነው፡፡ድጋፍ የምታገኙት በድካማችሁ እንጂ ቃላት በማሳመር አይደለም፡፡ ብርታቱን ይስጣችሁ፡፡

ከአንተነህ መርዕድ ፅሁፍ የተወሰደ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Jun 20, 2019 11:54 pm

"ነፃነቴን የሰጠኝ፤የመናገር መብቴን የመለሰልኝ፤ከመሸማቀቅና ማን አየኝ መሳቀቅና መገላመጥ ያወጣኝ፤ቤተ መንግስት ያስገባኝና ፕሮግራም ምራልኝ ያለኝ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነው፡፡ስለዚህም ያደላሁት ወደ መንግስት ሳይሆን ወደ ዶ/ር ዐቢይ ነው፡፡ ለዚህም ደግ አደረኩ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስህተት ሲሰራ ባይ መንገድ ፈልጌ እነግረዋለሁ እንጂ ከጀርባ ሆኜ እላማውም፡፡ምክንያቱም በአንድ ቀን ሁሉን ነገር መስራት እንደማይችልና አንድ ሰው መሆኑን አውቃለሁና፡፡

ጋሼ ደበበ እሸቱ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Jun 21, 2019 9:49 pm

እስክንድር ፊስታሉን ይዞ እስር ቤት ሲገባ፤እነ አዲሱ አረጋ የደደቢት ምሩቆች አገልጋዮች ነበሩ!!
እስክንድር ፊስታሉን ይዞ እስር ቤት ሲገባ፤እነ አዲሱ አረጋ ለወያኔዎች ብቅል ይፈጩ ነበር!!
እስክንድርን ፊስታሉን ይዞ ከእስር የወጣው በራሱ የዓላማ ፅናትና ትግል ነው!!
ከነ አዲሱ አረጋ ዕውቀት አልባ ጭንቅላት፤እስክንድር ከእስር ቤት ይዞት የወጣው ፊስታል ይሻላል!!!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2342
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests