ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ክቡራን » Tue May 09, 2017 10:36 am

ለማ12/12 እብዶች በከተማ ተባብረው የገነቡት ለማ 12 wrote:ክቡ ምን እንደዘባረቅ ባይገባኝም ጮህቴን የተርዳህ መሆንህን ለማወቅ
አክብድም አየ ለዚህም ነበር ቢአንስ ተኛ አልም ያልኩህ ዶላሩን አፈስክ?
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ባለፈው እነዳጎን እንዳሉህ ስጋ የሚአስቆርጥህ ጌታህ ይሆናል አፍሶ የሰጠሕ
ቁቅቅቅቅቅቅ
አሁን የምንቀልድበት ወቅት አይደለም ፈራሁ አስቡበት ያለቀ ጉዳይ ነው ግን ህዝቡን አታጥፉት
እታች ስትባረሩ እኮ ከላይ አይደልም ባድሜን መቀሌን ሊወስድ ነው ማን ያቁመው እላይ ያለው ህዝብ እኮ እታች ክአለው የበለጠ ሆዱ ቆስሎአል አሁን እኮ ኢሳያስ ሳይሆን ቁጥር 2 ወያኔ ነው ህዝቡን እንደከብት እያሰቃዩት ያሉት
የታችኛው ህዝብ ነሳ አውች ይላልግን አይደለም የኢሳስ ዘበኛ ነው፡፡ ይህን ዝግ እየተባለ ህዝቡ እየገባው ነው፡፡
ስለዚህ ታገሱ እባካችሁ
ተረትክን ማንበብ ባልችልም እንግሊዘኛው አይጠጋህም ያልክ መሰለኝ ነው?
ቁቅቅቅቅቅቅቅ
ያ ራየ ቢሱ መሪያችሁ ስብሰባውን በእንግሊዘኛ ነው የምትረብሹ ከሆነ ይል የነበር እኔን ነበር???
ምን ያደርጋል ቀኑ ጨለመ እንጂ

ለሚቾ እኔ የምለው እንደው ዘመድ የለህም? የቅርብ ሰው አጠገብህ የለም? ጻድቃኔ ማርያም ጥሩ ናት ሲባል እሰማለሁ ..አይዞህ እውነተኛ ወዳጅ ነው ችግርህን የሚነገርህ፡፡ ያየሁትን ስለሆነ የምጽፍልህ እስኪ ጻድቃኔ ማርያም ጠበል የት ነው? በልና ሰው አጠያይቅ፡፡ ይነግርሁሃል ያገራችን ሰው በዚህ አይጨክንም፡፡ አንድ ሳምንት በቂ ነው ከዛ በደንብ እንወያያለን..ሎል፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8357
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Wed May 10, 2017 12:42 pm

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ክቡ ሁልጊዜ በእንተ ለምን ልሳቅ በሁሉም ልሞክረው እንጂ?
እሱ አጠገብህ ያለው ኢትቪ( ኢሳት)ነው ያልከው ወሬውን ከየት እያመጡ ነው የሚእንበሸብሿችሁ
እዚህ እያደነቆረኝ ያለው ኢትቪን ምኑ ለየው?
ለማነኛውም የዛሬውንወሬአችሁን (ዜናችሁ) በዚህ መልኩ ጠግኑት በላቸው፡፡
1. በላነህ ክንዴ ባንኩን የቀማው ሚሊዮን እይደሊም ቢሊዮኖች ናቸው
ለግድብ እኮ 25 ሚሊወን ከባንኩ በኔ ስም ይወሰድ ያለ ጎበዝ ነው
2. ትልቅ ሰው ገዳሙ የቀማችውም እንዲሁ ሪፖርተር ላይ የቀባጠርችው እኮ 680 ሚሊዮን አድርሳው ነበር ለንሱ ከፈለችው ሌላውን 300 የሚሉት
3 .ከንግዱ መስመር ያስወጡት ደግሞ አበባው ደስታ የሚባል ልብስ ሰፊ እንጂ መሀሪ እይደለም
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ
አበባው መሀሪ ማለት መኢሀድ የሚባለውን ያፈረሱበት ጎበዝ ነው
ባለፈውም ትንሽ ብዬ ነበር በዚህ ላይ፡
4. መኮነን ገበየሁ አዎ ለራሴም ጥሩ ወዳጄ ነበር ሞተ ብዙ ብድር የወሰደ ነበር ግን ልፍሳሜ ብድር ቢጠይቅ እንኳን ልንሰጥህ ያለፈውንም መልስ ብለው እበሳጩት ልታከም ብሎ ውጭ ሀገር ሄደ ህክምናውን ጨርሶ ሊመለስ ሲታገል አረፈ
እንዲህ ነው በላቸው
2. አቶ አበባው ደስታ ጎበዝ ጮሌ ነበር ግን ከነስየ ጋር ወገንክ ብለው አበለሻሹበት፡፡
እት ምኑየለት አጥናፉ ጥሩ ሹፌር ነበር ጥሩም ሰው ነው አቅባቡት እንጂ
አሁን ይህን ዝቅ ብዬ የማወራው በየትኛውም እቅጣጫ የሚሰጠው ወሬ ህዝብን ያሳስታል ልታስቡበት ይገባል በሚል ነው
ወያኔ ይውደቅ ምንም ይምጣ የሚለው ህዝብን ያፋጃል ተጠንቀቁ፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Wed May 10, 2017 12:49 pm

ባለ 18 ፎቅ ሆቴል በክልል ከተሞች ቀርቶ በአዲስ አበባም አልተለመደም፡፡ ጣና ሐይቅን ከጀርባው አድርጐ የተሠራው ባለ 5 ኮከቡ ሆቴል ለባህርዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት ሆኗታል፡፡ የሆቴሉ ባለቤት ትልቅሰው ገዳሙ ወደ ኮንስትራክሽን ቢዝነስ የገቡት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም የሆቴሉን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ችለዋል - ፈተናዎችን እየተጋፈጡ፡፡ በጐጃም ውስጥ በገጠር አካባቢ የተወለዱት ወ/ሮ ትልቅሰው፤ ከአምስት አመት በላይ በባሌ እና በአዲስ አበባ በአስተማሪነት ከሰሩ በኋላ ነው ወደ ቢዝነስ የገቡት፡፡ ከትንሽ ንግድ ተነስተው፣ አንዱን ቢዝነስ ለሌላ ትልቅ ቢዝነስ መሰላል እያደረጉ ዛሬ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀ ሆቴል ሰርተዋል፡፡ ከወ/ሮ ትልቅሰው ጋር ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለ-ምልልስ እነሆ! የትልቁ ሆቴል ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው… ባህርዳር ከተማ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል “G+18” ፎቅ እየሰራሁ ነው።

በከተማውና በክልሉ ሆቴል ኢንቨስትመንት ትልቁና የመጀመሪያው ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። 150 ክፍሎች፣ አምስት ሬስቶራንት፣ መዋኛ፣ ሳውና፣ ስቲም፣ ጃኩዚ... የባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ደረጃዎችን የሚያሟላ ነው። የፊታችን ሐምሌ ወር ላይ በ“ሶፍት ኦፕኒንግ” ስራ ለማስጀመርና በ2006 ዓ.ም. ለማስመረቅ እቅድ አለኝ። 24 ሰዓት እየተሰራ ነው። ዘጠና ፐርሰንት ተጠናቋል። ሻምፑና ኮንድሽነር፣ ሹካና ማንኪያ ካልሆነ በስተቀር... ሁሉም ነገሮች ገብተዋል።

ማኔጅመንቱ ፍሬንቻይዝድ ነው፤ ነጮች ናቸው የሚያስተዳድሩት። እግዚአብሄር ከፈቀደ ብዙ ነው አላማዬ። ሄሊኮፕተር ገዝቼ እንግዶቼን ለማስጎበኝበት ህልም አለኝ። ለምሳሌ ከአዲስ አበባ እንግዶችን ተቀብለናቸው ደብረ ማርቆስ እናሳርፋቸዋለን። ከዛ ባህርዳር እኛ ሆቴል፤ ከዚያም ላሊበላ ጎንደር እያልን ለማስጎብኘት በቅብብሎሽ መስራት ነው ቅድመ ዝግጅታችን። የሄሊኮፕተር ጊዥውን አጥንተን ጨርሰናል። ሆቴሉ ስራ ሲጀምር አስር ማርቼዲስ፤ አራት ላንድ ክሩዘር፤ ሶስት ጀልባዎች ይኖሩታል። ሶስቱ ጀልባዎች ከጀርመን ታዘው እየመጡ ነው። አንደኛው ጀልባ 45 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችልና የባህር ላይ እራት የሚዘጋጅበት ነው። ሶስት መኝታ ቤቶችና አንድ ሻወር ያለው ጀልባ ነው። ሁለቱ 25 ሰው የሚጭኑ ትናንሽ ጀት ስክኒች ናቸው። ሆቴሉ የሚከፈተው ይሄ ሁሉ ተሟልቶ ነው። የየት ሀገር ባለሞያዎች ናቸው ሆቴሉን የሚስተዳድሩት? ማኔጅመንቱን እኔ መያዝ አልፈልግም። ከአለም አቀፍ የሆቴል ማኔጅመንት ጋር እየተነጋገርን ነው። ገና አልተፈራረምንም። ግን ፍራንቻይዝ ነው የሚሆነው።

ከ400 በላይ ሰራተኞች ይኖሩታል። የሆቴሉ ስም ምን ተባለ-- በፍራንቻይዝ ስለሚሰራ፣ የሆቴሉን አስተዳደር በሚመራው ኩባንያ የሚወሰን ይሆናል። ምናልባት ከእነሱ ጋር ካልተስማማሁ “ግራንድ ባህርዳር” እለዋለሁ። በባህርዳር ላይ እየተሰራ ያለው ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል መጀመሪያ ላይ ባለ 18 ፎቅ እንዲሆን አልታሰበም ነበር ሲባል ሰምቻለሁ። ደግሞም፤ የህንፃ አርኪቴክቶችና ዲዛይነሮችን እየተከታተልሽ ትፈታተኚያቸዋለሽ ይባላል? እውነት ነው። የሆቴሉ ቁመት ወደ ላይ ረጅም እንዲሆን የፈለኩት እኔ ነኝ፡፡ ክልሉ የሰጠኝ ቦታ ቆንጆ ነው። ታወር ነበር፤ ዲዛይን አቀረብኩላቸውና “አስራ አራት አድርጊው” ሲሉኝ “አስራ አራት ከደረስኩ፤ አስራ ስምንት ለምን አይሆንም” ብዬ አስራ ስምንት አድርጌ ሰራሁት። ከዲዛይነሮች ጋር እኩል ነው የምራመደው። እኩል ነው ቻሌንጅ የማደርጋቸው። ኤክስፓዠሩ አለኛ! ዓለም ላይ ብዙ አገር እዞራለሁ።

ሆን ብዬ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ነው የማርፈው። ይህቺ ግድግዳ፣ ጣሪያ ምን ትመስላለች? ፍሪጅዋ ምን ላይ ተቀመጠች? እያልኩ የሚሉትን ነገሮች በደንብ እመለከታለሁ። ካሜራዬ ውስጥ ብታይ የሰው ፎቶ አታይም። የመፀዳጃ ቤት፣ የመታጠቢያ ገንዳ፣ የአልጋ ዓይነት፣ የሆቴሉ ክፍሎች፣ የግድግዳና የጣሪያ ቀለማቸው፣ የሬስቶራንት ዕቃ አቀማመጥ ፎቶ ነው የምታይው። አርክቴክቶች ከእኔ ፈቃድ ውጪ አይሰሩም። እያንዳንዱዋን ነገር እኔ ማየት አለብኝ፤ መተማመን አለብን። ለእኔ ሳያሳዩ ያደረጉት ነገር ካለ፣ ቀስ ብለን እናሳምናታለን ብለው ነው የሚሰሩት፡፡ የሚመቸኝንና የሚሆነውን ነው የማሰራቸው።

ከዱባይ ኤሚሬት ኮንኮርድ፣ ግራንድ አይነት ሬስቶራንት እኔ ጋ እንዲደገም አድርጌዋለሁ። ውስጡ ምን ይመስላል? የሚለው በሙሉ የእኔ ምርጫና ፍላጎት ነው፡፡ አልጋ፣ የአልጋው ቀለም፣ የቤቱ ግድግዳ ቀለም “ይሄ የራሴ ስራ መሆን አለበት” ብያቸው ሙሉ በሙሉ የእኔ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ከሠራተኞቼ ጋር እኩል ቱታ ለብሼ፣ ኮፍያ አድርጌ አንዱን ሳነሳ አንዱን ስጥል ነው የምውለው። በጣም ደስተኛ ነኝ። ኤስያ፣ ቻይና ሌሎች በሆቴልና ቱሪዝም ትልልቅ ስም ያላቸው አገሮችን ጎብኝቻለሁ። አምስት ኮኮብ ሆቴል አርፌ አይቻቸዋለሁ። ብቻዬን ሳይሆን አርክቴክቸሮቼንም ይዤ፣ በዓለም ላይ ያልተጓዝኩበት አገር የለም። እንግሊዝ አገር ብቻ ነው የሚቀረኝ። ሌላ የት የት ከተማ ነው ሆቴሎች የሠራሽው? ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ፈረስ ቤት፣ ደብረ ማርቆስ፣ አሁን ደግሞ ትልቁና ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሉ የባህር ዳሩ ነው። በሆቴል ኢንዱስትሪ ውስጥ ደግሞ ሰፊ ስራ ጀምሪያለሁ።

በተለያዩ ክልሎች ስራዬን ማስፋፋት እፈልጋለሁ። በርግጥ ደክሞኛል.. ግን ባለኝ የተፈጥሮ ባህሪ ከስራ ርቄ መኖር አልችልም። ቱሪዝሙን ተከትዬ የምሰራ ይመስለኛል። በደብረማርቆስ ከተማ በጥሩ መስተንግዶ የሚታወቀው “ትልቅ ሆቴል” የሚባል ባለ ሶስት ኮኮብ ሆቴል አለኝ። 50 የመኝታ ክፍሎች፣ ሳውና፣ ስቲም፣ መጠነኛ የስብሰባ አዳራሽ አለው። አምስት ሺ ካሬ ሜትር ማስፋፊያ ቦታ ሰጥተውኛል። አሁን ደግሞ አስፋፍቼ የተለያዩ ነገሮችን ለመስራት ዲዛይኑ ተሰርቶ ግንባታ ላይ ነው። በማህበረሰባችንም በቤተሰብም ሴት ልጁ በተለያየ ስኬትና ኃላፊነት ለማጨት ያለው ውስንነት ደፍሮ ለመውጣት ፈተናዎችንና ችግሮችን ለመጋፈጥ ያለውን አስተሳሰብ በመስበር ምን ሰራሁ ትያለሽ--- “ሴት” የሚለው ቋንቋ እኔን አይገልፀኝም።

ወንድ ሊያደርግ የሚችለውን ነገር ሁሉ ማድረግ እችላለሁ። መማታት ቢኖርብኝ፤ እማታለሁ(ሳቅ)። ግፍና በደል እንኳን የደረሰብኝ የለም። በእምነት በኩል ያጎደልኩት ነገር የለም። ባንኩም ሰዉም “ትልቅሰው ትሰራለች፣ ተበድራ ትከፍላለች” ይላል እንጂ፣ በጥርጣሬም ሆነ በሌላ ስሜት የሚያየኝ የለም። ስራዎቼን አይተው አድንቀው ከጨረሱ በኋላ፣ “አይገርምም ሴት አኮ ናት” ብለው የሚናገሩ አሉ። ይኼ በጣም የሚያናድደኝ ቋንቋ ነው፡፡ “እና ሴት ብሆንስ ማድረግ አልችልም?” ነው የእኔ ጥያቄ። ወንድ ከእኔ የተሻለ አእምሮ አለው? እሱ ሊያስብ የሚችለውን ያህል እኔም አስባለሁ። እንዲያውም ከወንዱ የተሻለ ዲሲፕሊን የሚታየው በሴቶች ላይ ነው። ለ”ኮሚትመንት” ተገዢ በመሆንም ሴቶች ይበልጣሉ። በቃላችን ለመገኘት እንበረታለን።

ገንዘብ አናባክንም፣ ሴቶች ጥንቁቅ ነን። ዕዳና ብድር ብዙ አንደፍርም። ብዙ መስራትና መሄድ እችል ነበር። ወደ ጠንቃቃነት እናደላለን ብዬ አምናለሁ። ቤተሰብም ላልሽው የሰጡኝ ነገር ሲኖር ገንዘባቸውን እንዳላባክንባቸው ሊሆን ይችላል። እኔ ጥሬ ግሬ ያመጣሁት ገንዘብ ነው። ማንም በእኔ ህይወት ጣልቃ ሊገባ የሚፈልግ የለም። የምፈልገውን እሸጣለሁ፤ የምፈልገውን አጠፋለሁ። ይሄ መንገድ ልክ አይደለም የሚለኝ ሰው የለም። በርግጥ ቤተሰቦቼ የገጠር ሰው ናቸው። አስተማሪነትን ስለቅ በጣም ተሰምቷቸዋል። ኑሮዬን ያበላሸሁ መስሎ ስለታያቸው። ኑሮዬ በየጊዜው እየተቀየረ ሲያዩ ግን በጣም ያደንቁኝ ጀመር።

ካልሽስ፣ አንድ ጊዜ ወደ ባህርዳር በአውሮፕላን እየተጓዝኩ ሳለ ከአንዲት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ጋር እያወራን ነበር፡፡ እኔን አታውቀኝም። ስለ እኔ እያደነቀች ለኔ ታወራለች። “አንድ ሴት ጀግና፤ በጣም ጎበዝ…” እያለች ስታወራልኝ፣ ዝም ብዬ አዳምጣታለሁ። መጨረሻ ላይ፤ እኔ መሆኔን ስነግራት፣ ተነስታ ተጠመጠመችብኝ። በክልሌ እንደብርቅ ነው የሚያዩኝ። በጣም ያከብሩኛል። ህዝቡ የባህርዳሩን አዲሱን ሆቴሌን ወደ ላይ ቆሞ ሲቆጥር፣ ሲያደንቅ፣ መተዋወቅ ሲፈልግ ነው የማየው። የልጅነት ህልምሽ ምን ነበር? ነጋዴ፣ የቢዝነስ ሰው የመሆን ምኞት ነበረሽ? በእንጨት የተሰራ ትንሽ ሳጥን “ባንክ” እያልሽ ሳንቲም ማስቀመጥ… “የእንቁጣጣሽ” ሳንቲም ማጠራቀም… የገጠር ልጆች ነኝ።

ሳንቲም አላውቅም ነበር ንግድ ምን እንደሆነ አላውቅም። የአካባቢዬ ልጆችና ወንድሞቼ እንዳጋጣሚ ወደ ቢዝነስ ገብተው ውጤታማ የሆኑበት ጊዜ ነበር። እነሱን ተከትዬ ነው የገባሁት እንጂ ቢዝነስ ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም ነበር። የት ነው የተወለድሽው፣ ያደግሽው? ጎጃም ቆላ/ደጋ ዳሞት የሚባል አውራጃ ደጋዳሞት ውስጥ አሁን ምዕራብ ጎጃም ፈረስ ቤት ነው የተወለድኩት። ትምህርቴንም ያጠናቀቁት እዛው ፈረስ ቤት ነው። ከዛም መምህራን ማሰልጠኛ ባሌ ገባሁ። ሁለት ዓመት ሰርቻለሁ። አዲስ አበባ አምስት ዓመት ሰርቻለሁ። ከባሌ ወደ አዲስ አበባ ስቀየር ያኔ አዲስ አበባ ክልል አልነበረም። በጊዜው ዝውውር የለም። አዲስ አበባ እየሰራሁ ደሞወዛችንን ክልል ይከፍለን ነበር። ባሌ ክ/ሀገር ማለት ነው።

በኋላ ክልል ሲመደብ “ይሄንን ዓይነት ዝውውር አናስተናግድም” ብሎ አዲስ አበባ ላይ ማስታወቂያ ሲያወጣ፤ ወደ ባሌ ተመለሽ ተባልኩኝ.. ከ5ዓመት በኋላ ማለት ነው። አንድ ጓደኛዬ “አትሄጅም፤ እኛ ጋ ትሰሪያለሽ” አለኝ። ያኔ ነው አሰተማሪነቱን የተውኩት። መጀመሪያ ወደ ንግዱ ስትገቢ ገንዘብ ከየት አመጣሽ? ሰው ብር ሰጥቶኝ በብድር? እረ! ስጦታ ነው። ምን ያህል ገንዘብ--- 18 ሺህ ብር የመጀመሪያው የንግድ ስራሽ ምን ነበር? በጣም ትንሽ የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ነው የከፈትኩት። ትንሽ ዓመት ሰራሁና ወደ ግሮሰሪ አሳደኩት። ከትንሽ ተነስቶ የማደግ ምሳሌ ነኝ። እንደ ጓደኞቼ ማደግ፤ ሰው መርዳት፣ አገሬ ላይ መስራት እፈልግ ነበር። እግዚአብሄር ይመስገን የተመኘሁትን ሁሉ አድርጌያለሁ።

ነገ ደግሞ የተሻለ ሰው እንደምሆን አውቃለሁ። የሸቀጣሸቀጥ ሱቁና ግሮሰሪው አሁንም አሉ? አይ የሉም። ወደያው የውጭ ንግድ ጀመርኩ። ከዛ ደግሞ አድጌ ወደ ትራንስፓርት ንግድ ገባሁ። ትራንስፓርቱ ስራ አሁንም ድረስ አለ። የውጭ ንግድ ስትይ ---? የዛሬ 16 ዓመት ወደ ቻይና፣ ወደ ዱባይ አገር ሄጄ ጨርቃጨርቅና ኮርያ ብርድ ልብስ አመጣ ነበር። በጅምላ ልብስ አከፋፍል ነበር። ስራው ደስ ስላላለኝ ነው እንጂ አድካሚ ነበረ፡፡ ጉምሩክ ላይ ያለው ጣጣ “ኤስ ጂ ኤስ” የሚባል መስሪያ ቤት ነበር። እዚያ ሄዶ መዞሩና መግዛቱ ፈተናውና ድካሙ ከባድ ነው። ብዙ ስላልወደድኩት ወደ ትራንስፖርት ገባሁ። በተፈጥሮዬ አንድ ስራ ላይ ሙጭጭ ብዬ መቆየት አልወድም። የተወሰነ ነገር በተወሰነ ጊዜ ነው በፍቅር የምሰራው።

ከዚያ በኋላ መገልበጥ ወደ ሌላ ነገር መሄድ እፈልጋለሁ። ለሆነ ጊዜ ያህል ከሰራሁ በኋላ ቁጭ ብዬ ገንዘብ መቁጠር አይደለም። ለምሳሌ ሆቴል ሰርቼ ገንዘብ መሰብሰቡ ላይ አይደለም የማተኩረው። ደብረ ማርቆስ ያለውን ንግዴን ትንሽ ወንድሜ ነው የሚሰራበት። ፈረስ ቤት ያለውን ሆቴል፤ ትልቅ ወንድሜ ማኔጅ እንዲያደርገው ሰጥቸዋለሁ። የትራንስፓርት ስራውስ? አገር አቋራጭ ሦስት የህዝብ አውቶብሶች ገዛሁ። ከዛ ደግሞ ሶስት ቦቴዎችን። ስሰራ ቆይቼ፤ እንደገና ሶስት ቦቴዎች ጨመርኩ። ወደ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርትም ገባሁበት፣ 27 የደረቅ ጭነት መኪኖች ነበሩኝ። ከዚያ ደግሞ፤ አርባ ገልባጭ መኪኖችን በአንድ ጊዜ አስገባሁ። ከባድ ስራ ነው፡፡ ሾፌር፣ ረዳት፣ ጥገና... ከባድ ነው። ከጊዜ በኋላ ወደ ግንባታው አዘነበልኩ።

አሁን የተወሰኑት መኪኖች ተሸጥዋል። የተወሰኑት አሉ፤ የትራንስፓርት ድርጅቱ እየሰራ ነው። የትራንስፓርት ድርጅትሽ ስም ምን ይባላል? “ቻኩ ትራንስፓርት” ይባላል። የደረቅ ጭነትና የፈሳሽ ጭነት መኪኖች፣ ገልባጮችና ሌሎች የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን እያሰማራ ሲሰራ ነው የቆየው። ገልባጮቹን ቀስ በቀስ ሸጥኳቸው። አሁን ደረቅ ጭነቱ ይሰራል። ለንግድ ስኬታማነትሽ አይነተኛ ሰው ለአንቺ ማን ነው? ወንድሞቼንና የአካባቢ ልጆቼን አይቼ ነው ወደ ንግድ የገባሁት ብየሽ የለ? በጣም የምወደው ወንድሜና ጓደኛዬ፣ እንደ ራሴ የማየው፣ ‹‹ጥላሁን ደስታ›› ይባላል። ዛሬ ለእኔ ብር ማግኘት ቀላል ነው። 4 እና 5 ሚሊዮን ብር መበደር እችላለሁ። ከሆነ ሰው ሄጄ መቀበል እችላለሁ። ያን ጊዜ ማንም በማያውቀኝ ሰዓት፤ ማንም በማይሰጠኝ ሰዓት ”አበድረኝ” ብዬ አይደለም የምጠይቀው። “ብር እፈልጋለሁ” ብዬ ነው የምጠይቀው። በተለይ የማልረሳው አንድ ጊዜ 425 ሺ ብር ነበር እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የመኖሪያ ቤቴን የገዛሁት። እኔ የነበረኝ 300 ሺ ብር ብቻ ነበር። ቀብድ ከፈልኩና በቀጥታ ደውዬ፣ “125 ሺህ ብር እፈልጋለሁ” አልኩት።

“ቢያንስ ተዘጋጅ እንኳን አትይኝም ወይ?” ሲለኝ፤ “በቃ፤ እፈልጋለሁ፣ እፈልጋለሁ” አልኩት። እንዳለውና እንደሚሰጠኝ አውቃለሁ። እቁብ ብንገባ ቅድሚያ የሚሰጠኝ ለእኔ ነው። ጓደኞቹን ይሰበስብና ተጣጥለው ለእኔ ነው የሚሰጠኝ። ጠንካራ እንድሆን ነው የሚለፋው። ችግር እንኳን ቢኖርብሽ፣ “ሰው አለኝ፤ እገሌ አለኝ” የምትይው አለኝታ ሲኖር፤ ጠንካራና ደፋር ትሆኛለሽ። ለዚህ ሁሉ ስኬት ያበቃኝ፣ ጥላሁን ደስታ ይባላል። እሱ ነው ለእኔ አይነተኛው ሰው። እኔም የወሰድኩትን ያህል ገንዘብ ብወስድ፣ ባልኩት ሰዓትና ጊዜ ሳላዛንፍ ነው የምመልሰው። ከትራንስፓርቱ ቀጥሎ ንግድሽ ወደ ምን አደገ? ኤምባሲ የተከራያቸው ቤቶች አሉኝ። ነዳጅ ማደያ አለኝ። ኧረ ተይኝ፣ መዘርዘሩ ሳይሆን መስራት ደስታን ይሰጠኛል። ዕድሜሽ ስንት ነው? ለቤተሰብሽ ስንተኛ ልጅ ነሽ? መስከረም 21 ቀን 2005 ዓ.ም. 40 አመቴን አክብሬአለሁ፡፡

አምስተኛ ልጅ ነኝ። ከእኔ ላይ አራት፣ ከእኔ ታች አራት አሉ ዘጠኝ ነን። አንድ እህቴ አለች፤ እኔ ነኝ አሳድጌ የዳርኳት፤ ጥሩ ህይወት አላት ባሏም ጎበዝ ነው፡፡ ሌሎችም አሉ ጥሩ የሚያግዙኝ - እግዚአብሄር ይመስገን። አባቴ በህይወት የለም፤ እናቴ አለች። በሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው በስፋት ለመስራት ስትነሳሺ ወደ ፊት እንደ ዕቅድ የያዝሻቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ክልሎች ላይ ለመስራት እፈልጋለሁ። በቅርብ እንኳን የማስበው አዋሳ፣ ላሊበላ፣ ጎንደር መስራት እፈልጋለሁ። በምን ያህል ካፒታል ተገነባ የደብረ ማርቆሱም፣ የባህር ዳሩም? የደብረ ማርቆሱን ስሰራ ሁሉም ነገር ርካሽ ነበር። ምን ያህል እንዳወጣሁ አሁን በትክክል አላስተውሰውም። ምናልባት ከ16 እስከ 20 ሚሊዮን ብር ይሆናል። የባህርዳሩ ግን ተይው። በጣም ሁሉ ነገር ያበደበት ጊዜ ነው። ግን አንድም ቀን ስራውን ለማቆም አልፈለግኩም። አንድም ቀን አንድም ሰዓት ስራው አልቆመም። ከተጀመረ ሦስት ዓመቱ ነው። በ2,540 ካሬ ላይ ነው ያረፈው። 350 ሚሊዬን ብር ድረስ ይጨርሳል ተብሎ ይገመታል። ከባንክ ተበደርሽ? ወይም ዛሬም ጓደኛሽን አስቸገርሽ? ኖኖ ዛሬስ አላስቸገርኩትም። 58 ፐርሰንት ከራሴ 42 ፐርሰንት ከባንክ ተበድሬ ነው።
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ክቡራን » Sat May 13, 2017 2:22 am

ለሚቾ 12 እብዶች ተባብረው የገነቡህ የፍኖተ ሰላም ጠጅ ቤት አጥር ! "ክቡ ጭሁቴን ተረድተህኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" የሚል ነገር መጻህፍህን አሁን አየሁ፡፡ እኔ ጩሀትህ ስለምን እንደሆነ ስለማላውቅ አልተረዳሁትም...እንድረዳውም አልፈልግም ፣ እንዲገባኝም አልመኝም፣ ዛሬም ሆነ ወይፊትም እስከ ወዲያኛውም እንዳይገባኝ ጸሎት አድርጋለሁ፡...አሜን በልልኝ ለሚቾ ... ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8357
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Sun May 14, 2017 9:57 am

ቁቅቅቅቅቅ
ክቡ ከዚህ በላይ መረገም አለ ጆሮህ ከሀያይቱ መቼ ተሻለና ጨምርህ ልትድኖቆር ነው ርግማን የፈለከው?? ከዚህ በላይስ ጭፍን ድንቁርና ይኖራል የሚል ግምት የለኝም የሚሳካልህ ከሆነ ያድርግልእዚህ ላይ ያልኩት ዜናው ልክ አይደለም ይስተካከል ነው ያልኩህ ጮማ ራሱ

1. በላይነህ ክንዴ የሚሉት ከአንተ የማይሻል ጥብጠብ ራስ የወሰደው ገንዘብ ሚሊዮን እይደለም ቢሊዮን ነው
2. ትልቅ ሰው ገዳሙ ወሰደችው ያሉት ሚሊዮን ብቻ አይደለም ቢሊዮን ነው አስተካክሉ በላቸው ነው ያልኩህ
3. አበባው መሀሪ ሳይሆን አበባው ደስታ የሚባል ወሮበላ ነው አገር ያጠፋው ንጂ አበባው መሀሪ መኢሀድ የሚባለውን ማህበር ያፈረሰ ጎበዝ ነው ያልኩት
ይህን አድርግ ባልኩ ለምን አትርሳኝ ትለኛለህ?

በነካ እጄ ሰሞኑን መቀሌ እስፖርት ሜዳ ተከስተ የተባለው እውነት ቢሆንም ወያኔ ያደረገው እንጂ ህዝቡ አላደረገውም ታገሱ ካድርወች ሆነ ብለው የሞከሩት ነው ፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ክቡራን » Sun May 14, 2017 1:26 pm

ለማ12/ሽማኔ የደወረው ድውር wrote:ቁቅቅቅቅቅ
ክቡ ከዚህ በላይ መረገም አለ ጆሮህ ከሀያይቱ መቼ ተሻለና ጨምርህ ልትድኖቆር ነው ርግማን የፈለከው?? ከዚህ በላይስ ጭፍን ድንቁርና ይኖራል የሚል ግምት የለኝም የሚሳካልህ ከሆነ ያድርግልእዚህ ላይ ያልኩት ዜናው ልክ አይደለም ይስተካከል ነው ያልኩህ ጮማ ራሱ

1. በላይነህ ክንዴ የሚሉት ከአንተ የማይሻል ጥብጠብ ራስ የወሰደው ገንዘብ ሚሊዮን እይደለም ቢሊዮን ነው
2. ትልቅ ሰው ገዳሙ ወሰደችው ያሉት ሚሊዮን ብቻ አይደለም ቢሊዮን ነው አስተካክሉ በላቸው ነው ያልኩህ
3. አበባው መሀሪ ሳይሆን አበባው ደስታ የሚባል ወሮበላ ነው አገር ያጠፋው ንጂ አበባው መሀሪ መኢሀድ የሚባለውን ማህበር ያፈረሰ ጎበዝ ነው ያልኩት
ይህን አድርግ ባልኩ ለምን አትርሳኝ ትለኛለህ?

በነካ እጄ ሰሞኑን መቀሌ እስፖርት ሜዳ ተከስተ የተባለው እውነት ቢሆንም ወያኔ ያደረገው እንጂ ህዝቡ አላደረገውም ታገሱ ካድርወች ሆነ ብለው የሞከሩት ነው ፡፡

ለሚቾ በላይነህ ክንዴና ትልቅ ሰው ገዳሙ ሚሊዮን ሳይሆን ቢልዪን መውሰዳቸውን በምን አወክ? ባንኩ ራሱ ቢሊዮን ነበረው እንዴ?? ሎል... አንድ አባባል ግን ትዝ አለኝ ሌቦች ሲካፈሉ እንጂ ሲሰርቁ አይጣሉም ይባላል ..ቅቅቅቅ፡፡ ድርሻህን ከለከሉህ እንዴ ??? ...ለማንኛውም ለጥቆማህ ጌታ ይባርክህ፡፡ አንቺም አብረሽ በስተርጅና ማህተም ተደርጎብሽ ብር ሸለቆ ብትወርጂም!! ቅቅቅቅቅ ..ደጉ እንዳርጋቸውና አለምነህ በተለይ አንተን በሁለት ቢላ በሊታውን አይምሩህም!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8357
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Sun May 14, 2017 3:10 pm

ቁቅቅቅቅ
ክቡ አታስቀኝ እባክህ?
እኔ አባትህ በሳሙና እንደታጠበ ልብስ ንጹህ ነኝ እድሜ ልኬን የስርቆት እድሉ ቢኖረኝም ሳልሞክረው ነው የቀረሁ አሁንም አላደርገውም አባትህ በዚህ መቸም የምለው ነው፡፡
በላይነህ ክንዴ ለምን ብዙ ወሰደ አልክ ላልከው ነግሬህ ነበር ግን እንተ ጨው ራስ ስለሆንክ ካልገባህ ልድገምልህ


በአጠቃላ አሁን እየጨፈረበት ያለውን ንብረት ደምረው
የአዲስ አበባን ግማሽ ይዞ ነው ያለው ይህ ደግሞ ሆቴሉን ብቻ አሁን ባለው ዋጋ ተምነው መደመር ካልቻልክ ጠይቅ

ለግድቡ ማሰሪያ በኔ ስም ከባንኩ ይወሰድ ያለው 25 ሚሊዮን ነበር የት ደረሰ ዘመዶችህን ጠይቅ ዘረፋው እንዲህ ቀላል እይደለም በጣም ሰፊ ነው ሊደበቅ የሚችልም አይደል፡፡
ትልቅ ሰው ገዳሙስ ላልከውም ባለፈው ጠቆ ም አድርጌልህ ነበር ሆቴሌን አስመረኩ ስትል አጎትህ ሪፖርተር እውነት ሰርታው ነው ብሎ በጠየቃት ላይ እኮ 680 ሚሊዮን ብድር አለብኝ ብላ የቀባጠረችውን ፈልገህ አንብ
አይሆንም ካልል እዚህ ላይ የለጠፍኩልህን ቃለመጠይቅ ተብዮ ደምረው፡፡
ባትችልም
ይህ ብቻ አይደለም ውሽማዋ አባይጸሀይየ ያደረገውን ዝውውር እስከ ፎቶው ልለቅልህ እችል ነበር ግን የገጾችን ህግ ላለማለፍ ለጊዜው ይቆይ
አበባው ደስታ የሚባለው ጎበዝ ነበር ሰራተኛ ነበር የሚለውን ላንተና ለአሽቃባጮች ላቆየውና እውነቱ ግን ከስየው ወንድም አሰፋ አብርሀ ነው የምትሉት ጋር ሆኖ ሀገሪቱን ያደማ ነው፡
ለዚህ ሁሉ ጥርት ያሉ መረጃወች አሉ ይህን እንመልሳለን በማለት ነው ህዝቡን ከፍጅት ማዳን የሚቻለው እንጂ
እንደምሰማው ወያኔን አባረን እርቅበራሱ ይመጣል የሚለው አይሰራም
ሊታሰብበት ይገባል ሀገሪቱን ለማጥፋት ብዙ ጉዞ የተጏዛች ቢሆንም ሀገሪቱን ለማዳንም ብዙ እየትራመድን ነው፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ክቡራን » Sun May 14, 2017 5:49 pm

ለማ 12 እብዶች ተሰብሰበው የገነቡት የ ግራርጌ ግንብ ይህን ይላል..
Code: Select all
እኔ አባትህ በሳሙና እንደታጠበ ልብስ ንጹህ ነኝ እድሜ ልኬን የስርቆት እድሉ ቢኖረኝም ሳልሞክረው ነው የቀረሁ አሁንም አላደርገውም አባትህ በዚህ መቸም የምለው ነው፡፡
በላይነህ ክንዴ ለምን ብዙ ወሰደ አልክ ላልከው ነግሬህ ነበር ግን እንተ ጨው ራስ ስለሆንክ ካልገባህ ልድገምልህ


በአጠቃላ አሁን እየጨፈረበት ያለውን ንብረት ደምረው
የአዲስ አበባን ግማሽ ይዞ ነው ያለው ይህ ደግሞ ሆቴሉን ብቻ አሁን ባለው ዋጋ ተምነው መደመር ካልቻልክ ጠይቅ


ለሚቾ ከጩሃዎችና( ከዴዴቦች ..አንተን እንኮአን ዴዴብ የምልህ ሰው ስላልሆንክ እንደዛ አልልህም ቢያንስ አከብርሃለሁ..ሎል ) ግን ዴዜዴራይታ ይህን ይላል " ከጩሃዎችና ከዴዴቦችም ቢሆን አንዳች መልካም ነገር እይጠፋምና በጽሞና አዳምጣቸው " ይላል. እና .ያልከው ነገር ጽቡቅዩ በሃቅዬ!! . ..ታድያ በላይነህ ክንዴ ያዲስ አበባን ህንጻ ግማሹን የያዘው እሱ ከሆነ ለምን የወያነ ጄኔራሎች ህንጻ በህንጻ ሆነዋል እየተባለ ስማቸው ይጠፋል?? ለምን ሃቁ አይነገርም..?? እኔ አሁን ስሙን የማልጠቅስልህ እንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ለምሳሌ የናት አባቱ ልጅ የሆነችው እህቱ በኮንዴሚኒየም ቤት ተከራይታ ስትኖር እሱም መንግስት በሰጠው ቤት ይኖራል...እስኪ ማነው ታዲያ ሌባው እዚህ ጋ?? እስኪ ፈታ ብልህ እውነቱን አውጣው ለንስሃም ለስጋ ወደሙም ይሆንልሃል፡፡ እኔም ፍታት አደርግልሃለሁ፡፡ የቄስ ቤተሰብ ነኝ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8357
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Mon May 15, 2017 10:09 am

ክቡ ወዴት ወዴት የወያኔ ፍየል ጠባቂወች የሉም የሚል አልወጣኝም በነዚህም ዙሪያ እንደ እነ በላይነህን የመሰሉም ደንቆሮ ጅቦች አሉ ነው ያልኩት
እንጂ አንተ መኮነን የምትላቸው ፍየል ጠባቂወችማ ተከድኖ ይብሰል ማስረጃ ፎቶ ሁሉ ነው ያለው
አበበ ተክለ ሀይማኖት አልዘረፈም እንዲያው ህንጻውን ቆሞ አገኘው እሱም በመንግስት ንብረት ነው የሚጨፍረው ብትለኝ ግማሽ እውነት ነው የሚል ነው

እሱም ይህን ያህልም ዝርፎ ከህዝብ ትክሻ ላይ መጨፈሩ እውነት ነው፡
መዝረፉም እውነት ነው የካበው ደንጋይ አይደብቅም
ሳሞራም አይዘርፍ የሚስቱ ነው?
ቁቅቅቅቅቅቅ

አበበ ደግሞ ምንድን ነው የሚቀባጥረው ብሄራዊ መግባባት?
ድንቄም መግባባት
ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቶች ዋናወቹ ናችሁ አሁንም መፍትሄው እናተው ላይ ነው ይህን ሀብት መልሱና ይህ ህዝብ ታገስ ይባል፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Thu May 18, 2017 2:49 pm

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እረ ክቡ ተረጋጉ
ልታብዱ ነው?


ይድረስ ለርዕዮት ዓለሙ
ሀገረ አሜሪካ
ውድ ርዕዮት …
ሰሞኑን ለዓለም የጤና ጉባዔ (World Health Assembly) የጻፍሺውን ግልጽ ደብዳቤ አነበብኩት፡፡ በርግጥ በስርዓቱ በደል እንደደረሰብሽ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን የስርዓቱ በደል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆኖ ከመመረጡ ጋር ምን ግንኙነት፣ ምንስ ዝምድና አለው? ሁለተኛው ነገር አንቺ በሙያሽ መምህር እንጂ ጋዜጠኛ ነሽ እንዴ? በየመጽሔቱና በየጋዜጣው የጻፈ ሁሉ ጋዜጠኛ ነው ማለት ነው? እኔ ላለፉት 31 ዓመታት (ገና የ15 ዓመት ልጅ/ተማሪ) እያለሁ ጀምሮ በጋዜጣ፣ በሬዲዮ፣ በመጽሔት፣… ስጽፍ ነው የኖርኩት፡፡ አሁንም አልፎ አልፎ እጽፋለሁ፡፡ እና እኔ ጋዜጠኛ ነኝ
ማለት ነው?
ታዋቂው ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ እንደሚለው “ጋዜጠኛነት ደምና ላብን የሚጠይቅክቡር ሙያ ነው፡፡” አንቺ ግን ለጋዜጠኛነት ሙያና ክብር የደምም የላብም ዋጋአልከፈልሺም፡፡ ጠመኔ ይዘሽ እያስተማሽ በትርፍ ጊዜሽ አንዳንድ መጣጥፍ ትጽፊ ነበር፡፡በነዚያ ጽሑፎችሽ ኢህአዴግን በመሳደብሽ ኢህአዴግ “ጀግና (Hero) እና ጋዜጠኛ”ያደረገሽ ጸሐፊ ነሽ እንጂ ጋዜጠኛ ለመሆን ብዙ ብዙ ይቀርሻል፡፡ አንዳንድ ጽሑፎችሽ እንዲያውም አለማንበብሽን ስለሚያሳብቁ ለአቅመ-ጋዜጠኛነት የደረስሽ አይመስለኝም፡፡ጋዜጠኛ የሚሆን ሰው ከመጻፉ በፊት ብዙ ብዙ ማንበብ ይጠበቅበታልና አንቺም ከመጻፍሽ በፊት ብታነቢ የበለጠ ተመራጭ ነው፡፡ እነ ጋዜጠኛና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ፣ ማሞ
ውድነህ፣… እንዲያ ነበሩ!!!
ውድ ርዕዮት …
እንዲያው ለነገሩ … እነ በዓሉ ግርማ፣ ወ/ሮ ሮማንወርቅ ካሣሁን፣ ብርሃኑ ዘርይሁን፣ፍቅሩ ኪዳኔ፣ ዓለም መዝገበ፣ ልዑልሰገድ ኩምሣ፣… የሚጠሩበት ስም ያለ አግባብ ተጭኖብሽ “ጋዜጠኛ” ስትባይ ትንሽ አይቀፍሽም?
በመምህርነትሽ እድሜ ልክሽን ስትፈጊ ብትኖሪ አሁን ያለሽበት ምቹ ሁኔታ አያጋጥምሽም ነበር፡፡ እናም ለእስር ያበቃሽን መስዋእትነት የከፈልሺው የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ነበር -ያ ተሳክቶልሻል፡፡ በዚህ ረገድ የነደፍሺው ስትራቴጂ (የኢህአዴግ እንከፍነት ተጨምሮበት) ሰርቷል፡፡
ትግልሽ ለሕዝብ ሰላም፣ ዴሞክራሲና እኩልነት ቢሆን ኖሮ ግን ከእስር እንደተፈታሽ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳ ጓዝሽን ቀርቅበሽ፣ ሻንጣሽን ሸክፈሽ ወደ ሀገረ አሜሪካ አትሄጂም ነበር - እስከ ሕይወትሽ ፍጻሜ ትታገይ ነበር እንጂ!!!
ውድ ርዕዮት …
እኔ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን አላውቀውም፡፡ በዘር፣ በሃይማኖትም ሆነ በጎሳ አንገናኝም፡፡ለሀገሪቱ የሰራውን ስራ ግን አደንቃለሁ፣ አከብራለሁ፡፡ በግልጽ ደብዳቤሽ ላይ
ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰራውን መጥፎ ተግባር መግለጽሺን ልብ አላልኩም፡፡ ቢኖረው ኖሮ አንቺም
ትጠቅሺው ነበር፤ እኔም አወግዘው ነበር፡፡
በሙሰኛና አምባገነን ስርዓት ውስጥም ቢሆን እንደ ቴዎድሮስ ዓይነት ለሀገር የሚሰሩ ሰዎች
የሉም ብሎ መደምደም ደደብነት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ስም ሊሰጠው አይችልም፡፡በደርግም
ጊዜ እነ ሽመልስ አዱኛ እያለቀሱ እየለመኑ የተራበ ሕዝብ እርዳታ እንዲያገኝያደርጉ ነበር፡፡
በብልሹ ስርዓትም ውስጥ ቢሆን በጎ ሰሪ፣ ቅን አሳቢ ግለሰቦች ምንጊዜም ይኖራሉ ማለት
ነው፡፡
እናም… ውድ ርዕዮት ሆይ! ብዕር አንስተሽ ከመለቅለቅሽ በፊት የብእርሽ ቅርሻት
የሚያደርሰውን የጥፋት መጠን ደግመሽ ደጋግመሽ ማሰብ ይኖርብሻል እላለሁ፡፡ ካለበለዚያ
ዛሬ ለያዝሺው የፖለቲካ ግብ ስኬት ይረዳኛል ብለሽ የጻፍሺው ነገር ነገ በታሪክና በሕዝብ
ፊት ተጠያቂ ያደርግሻል፡፡ “ጋዜጠኛ” ወይም ጥሩ ጸሐፊ ማለት ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም
ግምት ውስጥ አስገብቶ ስራውን የሚሰራ ነው! ምንጊዜም አጠገብሽ ባሉ ሰዎች ተገፋፍተሽ
ሳይሆን ራስሽ አስበሽ፣ አውጥተሽና አውርደሽ ስራሺን ብትሰሪ ደግሞ የበለጠ ራስሽን
እንድትሆኚ ያደርግሻል፡፡ ብቃትሽንም ከፍ ያደርገዋል፡፡ ከጸጸትም ያድንሻል፡፡ አድናቆትንም
ያተርፍልሻል እላለሁ፡፡ ምንጊዜም አክባሪሽ
ኩርኩራ ዋፎ
ከለገጣፎ
05-18-17
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Fri May 19, 2017 2:58 pm

ክቡ ቁቅቅቅቅ
እኔማ አውቄው ውሀው ደፍርሶ
ነው ያለችው አክስቴ?
እዚህ ያመጣሁት የሚአንብላችሁ ሰው እንዲኖር ነው አይጋን የሚእይ ኢትዮጵያዊ እኮ እኔና አንተ ብቻ ስለሆን ነው
እዚህ ያሉ ወጣቶች እኮ ዘወር ብለው አያዩትም ምነው ተቆጣህ?
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ
ለመሆኑ ምን ብሎ ነው የከሰሳት ? ቴወድሮስ ደግፊ ነው የሚል?
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ
ባለፈው ሀብታሙ የሚባል ጎረምሳ የገረፉኝ ሑሉም ትግሬወች ናቸው ሢል
የትግራይን ህዝብ ጥላቻ ነው ብሎ ዘባረቀ
ቁቅቅቅቅቅ
አሁን ደግሞ ሌላውን ተረት ጨመረ እረ ታገሱ ህዝቡን ከሜዳ አስወጣችሁት?
ደግሞ ምን አሳቀኝ መሰለህ?
ከለገጣፎ ነው ያለው?
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ወርቅነህ ከመቂ እይሻልም?
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እባካችሁ አትዘባርቁ ይህን ደሀ ወገናችንን ለሳት እትማግዱት
እስኪ ልጠይቃችሁ በቀን ስንት እንጀራ ትበላላችህ?

ለአንድ እንጀራ?
እረ እንደሰው ለማሰብ ሞክሩ ?
የለሁበትም፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Mon May 22, 2017 1:25 pm

ክቡ ቀንድህን ስልህ አረፍክ ብዬ ነበር
ወርቅነህን ከመቂ ስሙ አልከን
መጀመሪያ ምንም ጥርጥር ውዥንብርም የለለበት አባይ ወልዱ የተፋው ነው፡
የትግርይ ህዝብ ርዳታና አሳቢ ይፈልጋል ያለው ምንም የምቀንሰው የለም ግን መጀመሪያ እናተ እንደ ሰው ብታዩትስ?
ይህ ህዝብ አሳሳቢ ችግር ላይ ነው የጣላችሁት እባካችሁ ተመለሱ፡፡

ምንድነው ደግሞ አጎትህ ወርቅነህ ከመቂ የሚለን

ሰላም ማስከበርደረጃ ላይ የደረስነው አሁን ነው
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ
ሰዎች በራሳቸው ውሸት ሲደሰቱ እንደእናተ በመሬት ላይ አላየሁም

ቁቅቅቅቅቅቅታሪካችን እኮ ብዙ የሚለው አለ
ሰወች ኮርያ
ኮንጎ
ሄደው ነበር ይላል ለሽርሽር ነበር?
ቁቅቅቅቅቅቅ
ከሳውዲ ተመለሱና መልሰን እንልካችሁ አለን ነው የሚለው?
ቁቅቅቅቅቅ
እባካችሁ እነዚህን ህጻናት አየር መንግድ ሲደርሱ ጀምሮ እያደረጋችሁባቸው ያለው እንግልት ተውና ይግቡ
ቢቻል ቀረጥ አትጠይቋቸው ካልሆነ ደግሞ የአቅማቸውን አስከፍሉና ተውአቸው፡
እረ ህዝብ ልታባሉ ነው ህጻናቷ እኮ አደለም ትግሬኛ አማረኛም አይችሉም ይህንም ተረዱላቸው እባካችሁ፡፡
ስቃዩ በዛብን እያሉ እየተደዋወሉ ነው እባካችሁ ተውአቸው ይመለሱ አዳጋው መጥፎ ነው ፡፡
አስቡበት
ክቡ እረ አይናችሁን ለግለጻ ሞክሩ
እረ ተወሳሰበ፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Thu Jun 01, 2017 2:50 pm

እረ ተንጫጫን ነው ያሉት?

ክቡ ዝም ያልኩት ከበሮ ድለቃችሁን ጨርሱ ብዬ ነው ለምን?
እዚህላይ የሚከተለውን ሀሳብ ልስጥ ፍቀድልኝ ወደ ዋናው ከመግባቴ በፊት፡፡

1. አቶ ዲአጎን
2.ኳስ ሜዳ
3 አቶ እሰፋ ማሩ
የሚባሉ ሰወችን ሀሳብ ን
ሳላደንቅ አላልፍም
ክቡ አንተን ቢመርህም
ጥሩ ሀሳብ ነው የሚሰጡት ሀሳብ፡ በርቱ ነው የምለው፡፡
መጀመሪያ ቴወድሮስ ተመረጠ ብለው ለጮሁት ይህ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ ሞቱ ቆመ አይደለም የቀኑ ለት ዳሬክተርነቱ ቀርቶ ከተጠያቂነት ማንም አያድነውም ለጊዜው ይፈንጭ ያው እየፈነጩበት አይደለም ወይ በህዝቡ
ከመንግስተ ሰማያት ቢሆን አታመልጠኝም ነበር ያለው ያ ቦሊስ ነኝ ያለው እውነቱን ነው፡፡
እዚ ላይ፡፡የሚገርመው ለምርጫየ የከፈለችው ሀገሪቱ ናት ነው ያለው ቢታወቅም ያሳዝናል፡፡
ማሸነፈን እንደ ሀገራችን ምርጫ ውጤቱን ከውር በፊት አውቀው ነበር ነው ያለው
ቁቅቅቅቅቅ
ታዲያ ይህን ያህል ገንዘብ እየዘራ??
ስለዚህ መናደዱን ተው እላለሁ እላይ የጠቀስኩ አቸውን ሰወችና መሰሎችን፡፡
አለቆቻችን ፈርንጆች ደገፉ የሚለው ታዲያ ምን ይጠበቅ ነበር?
26አመት እያደረጉ ያሉት ምንድን ነው??
አንድ ጥያቄ ላንሳ ?
ኢትዮጵያውን ሱማሌ ገብተው ያለቁ የራሳቸውን ሀገር ለመጠበቅ ነበር? ምናቸው ተነካና
በ1991 አም አሜሪካ የደረሰባቸውን ሽንፈት ክፍሉ በማለት አይደለም?
ታዲያ ይችን ሀገር የሚአጠፋ ግሩፕ ቢደግፉ ምኑ ላይ ነውስጥቱ?ፈረንጆች የሀገራችንን መኖር ይፈልጋል? ከሽንፈታቸው ጀምሮ ቂሙን ረሱ
ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን እነዚህ ፈረንጆች ይረዱናል ለጥቅም የሚለውን ሀሳብ ተው ልክ የተወሰነ የህብረተ ሰቡ ክፍል ዛሬም ሚኒልክ ነው የሚበድለን እንደሚባለው ነው ራሳችሁን አውጡ፡፡
አሁን እያመራን ያለነው ወደ መጥፎ ደረጃ ነው ተው አስቡበት፡፡
ሰሞኑን እየሰማሁት ያለው ህዝቡን እያሳቀ ያለ ነገር እየመጣ ነው
ትግራይ አልተጠቀመችም?
ቁቅቅቅቅቅ
ትግራይ ማለት ምኑን ለማለት ነው?
ህዝቡ
ሀገሩ
ሌቦች?
ደሀው ገበሬ ጠብ ያለለት ብዙም አይደለም በተዘዋዋሪ መንገድ ጥቅሞቹን መዘርዘር ይቻላል የሚል ግምት አለኝግን ጥቅሙና ጉዳቱን በደብ እንየው
ሀገሩ? ይህን ለጫጫታ ካልሆነ በቀር ህዝቡ እንደሚለው ትልማ ግድ የለም የሚለው በጣም መጥፎ ነገር አለው፡ የለሁበትም፡፡
ሌቦቹ ተው ጎበዝ ጎጃም ሰርቆ ትግራይ የተደበቀው ሌባ ለነፍሱ ነው? እረ እነዚህ ነገሮች ከጅ ሊወጡ ነው
የአማራው ማህበር ትግራይ ላይ ትምህርት ቤት ሰርቶ አስረከቡ? ጥሩ
የኦሮሞው ማህበርም እንደዚሁ ሰርቶ አስረከበ ጥሩ
የደቡቡ ማህበርም አስረከበ ጥሩ
ግን የወያኔው ማህበር
ለአማራው
ለኦሮም
ለደቡቡ
ባህር ዳር ላይ
አዳማ ላይ
አዋሳ ላይ

የሰራው ጎጆ ይኖር ይሁን?
እባካችሁ አዲስ ዘፈን ባወጡ ቁጥር አብራችሁ እየዘፈናችሁ የመንገዱን አቅጣጫ አታስቀይሩ
ይህች ሀገር እንደ ሀገር ትቀጥል የምትሉ ዝም ብላችሁ ታገሉ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ለማ12 » Wed Jun 14, 2017 11:08 am

ክቡ ኢተርነቱን ፈተና ብለው ዘግተው ፈተናውንም የባስ አዘበራረቁትእ ኛንም ጨላማውን አብዝተውብን ሰነበቱ እንተ ደግሞ እሁን ንዳየሁት ዋርካን EEN ነው የሚሉት እዲሱ መጨፈርቲያቸው 2 እድርገህው ነው ያየሁት
ቁቅቅቅቅቅቅቅ
ረ ተረጋጉ 9 ሞት መጣ ቢሉት 1ዱን ግባ በለው ነው ያለው እጎቴ) እንዱን ሞት እኮ ነው የምትሞቱት ምን እስቸገራችሁ ተጋዳላይ እይደላችሁ ?
ቁቅቅቅ
ለመሆኑ አንተም ሆንክ አለቆችህ እንደምትሉት ይህን ያህል ደካማ ሰው ከሆነ ብርሃኑን ለምን ፈራችሁት? ለምን ያለሱ እለም የለም ትላላችሁ?
አውቀዋለሁ ግን እንቀራረብም ነበር እሁን ግን አንተንም ሆነ ዘመዶችህን በውናችሁ ብቻ ሳይሆን በህልማችሁም ጭምር ሲያንጫጫችሁ ሳይ ላከብረው ነው ጎበዝ፡፡

ደግሞ ማንና ማን ናቸው ተጋብተው ወለዱ የምትለን
ቁቅቅቅቅ
እረ የምትጨብጡትን አጣችሁ ተጠንቀቁ መላቀቅ የለም
ሰሞኑን እዚሂ በረታችሁን ያቃጠሉትን ለማገኝት ብዙ ታግየ ነበር እኔ ምንም ነገር ባይወድም እመርጣለሁ ግን እንዳሉኝ አማራጭ ጠፍቶ ነው ግፉ በዛ ነው ያሉኝ በቦታው የሚፈጸመው ግፍ በዛ ነው ያሉኝ፡፡
አሁን እኮ ያልገባችሁ ነገሩ ያለቀ መሆኑን ነው
ዘ ጌም ኢዝ ኦበር ነው ያለው አጎትህ
ነው እኮ ለምን እገሩን ሁሉ ታቅባባላችሁ በቃ ለቴወድርሶ ከመጠን ያለፈ ገንዝብ ከፈልንላችሁ በዚህ ከበሮ ምቱ በቃ ለቁንጫ ቆርበት እነሰው ክቡ ይበቃችኋል እኮ
ቁቅቅቅቅቅ
ዘመነ ካሴ የሚባለው ወያኔ ነው አለ ያልከው ጎዝ እላለም ዞሮብህ ነው ጨው ራሱ ድሮ ወያኔ ነበር ነው ያለው እሱ ደግሞ ትክክል ነው ያማራው ያላችሁት የነበረከት ማህበርተኛ ነበር ትቶ እስከጠፋ
እሁን ግን ትግሉን እደግፋለሁም አደንቃለሁም ነው ያለው ስሙት ያልከን ጎበዝ ጥሩ ምክር ነው ሁሉንም ይመለከታል ሁሉም እንዲስብ እኔም እመክራለሁ የሁሉንም አስቡ ነው የሚል እምነት አለኝ
እዚህ ላይ ወዳጅህ ኳስ ሜዳ ያለውን በጥብቅ ልድገም እሱም ለሚሰማው ሁሉ እንዲአስተላልፍ እለምናለሁ፡
በአሁኑ ወቅት ያማራው ብቻ ሳይሆን የህዝብ ጠላት አለ እሱም 1 ነው ወያኔ ሌል ጠላት የለም ሰው ነኝ የሚል ሁሉ እዚህ ላይ ጠጠር ይወርውር አለዚያ አተደናቅፉ በላቸው
1 ኢሳት ያማራ ጠላት ነው የሚለው ሀይል ኢሳት ማነው አማራ የለውም እኔ እኮ በደብ የማውቀው ጥሩ ጎበዝ አምስተር ዳም ያለው ፋሲል የሚሉት ጎብዝ አማራ አይደለም ነው የተለየ አማራ አለ? ከባልሽ ባሌ ይበልጣል የሚለው እይሰራም ያው ወያኔነት ነው አስቡበት እንዲህ የምትሉ ልጆች አስቡበት ረፉ
2 ሞረሽ ወገኔ የሚለው ሀይል ማነው እስክማውቀው አፓሳደር እምሩ መሰረትኩት እንዳሉ ቀምተው የመደር እድር አደረጉት? ሞረሽ ወገኔ ( ተክሌ ይሻው) የሚል እያየሁ ነው እረፉ አንተ ማን ሆነህ ነው እነታማኝ ያማራው ጠላቶች አድረገህ ቁጭ ያልክ?? ተው አተደናግሩ እያሰባችሁ ተራመዱ
ኦሮሞኛው ከማዳግስካር ነው የመጣው ብሎ ሲጽፍ ተክሌን አይቻለሁ ወዳጀ ዳዊት ወልደ ጊወርጊስ ያለውም ይህን መሰለኝ
ሞረሽ ይህን አላለም የሚል መልስ ያየሁ መሰለኝ ?
ምን ማለት ነው?
ቁቅቅቅቅቅ
ሰው ከሆናችሁ ጠላታችሁን እወቁ በጎን ጉንተላችሁን አቁም በልልኝ
ኳስ ሜዳ አደራህ
በተረፈ ግንኙነቱ እያስቸገረኝ ነው እመለሳለሁ ካልዘጉት፡፡
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ወደ መጨራሽው ጥንቃቀ ያስፈልጋል!

Postby ኳስሜዳ » Wed Jun 14, 2017 1:55 pm

እውነት ብለሃል ለማ 12! እዚህ ላይ መስተዋል ያለበት ኢትዮጵያዊ ሁሉ የወያኔ አገዛዝ እንገሽግሾታል!! በቃን አንፈልግም ብሏል በግድ እንግዛህ!!! ወገኖች ከፋሽስት ጣልያን በላይ በወገናችሁ ነኝ ባይ እየተጨፈጨፉ መኖር ይብቃ ብለዋል፡፡ህዝቡ የነ ክቡራን እሽቃባጭነት ቋቅ ብሎታል፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑን የሚጠሉት ለማንኛውም ነገር ወሳኙ የኢትይጵያ ህዝብ መሆኑን ስለሚያምንና ባደባባይ ስሊሚናገር ነው፡፡ ትብብርም ይፈጠር የሚለው ባንድ ኢትዮጵያዊነት ከምያምኑት ጋር ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ወያኔዎቹ ከነጡረተኞቻቸው ነጋ ጠባ የሚበረግጉት በሞኖፖሊ እምየን ኢትዮጵያ እንዝረፍ ስለሚሉ ነው፡፡
ለማ12 wrote:ክቡ ኢተርነቱን ፈተና ብለው ዘግተው ፈተናውንም የባስ አዘበራረቁትእ ኛንም ጨላማውን አብዝተውብን ሰነበቱ እንተ ደግሞ እሁን ንዳየሁት ዋርካን EEN ነው የሚሉት እዲሱ መጨፈርቲያቸው 2 እድርገህው ነው ያየሁት
ቁቅቅቅቅቅቅቅ
ረ ተረጋጉ 9 ሞት መጣ ቢሉት 1ዱን ግባ በለው ነው ያለው እጎቴ) እንዱን ሞት እኮ ነው የምትሞቱት ምን እስቸገራችሁ ተጋዳላይ እይደላችሁ ?
ቁቅቅቅ
ለመሆኑ አንተም ሆንክ አለቆችህ እንደምትሉት ይህን ያህል ደካማ ሰው ከሆነ ብርሃኑን ለምን ፈራችሁት? ለምን ያለሱ እለም የለም ትላላችሁ?
አውቀዋለሁ ግን እንቀራረብም ነበር እሁን ግን አንተንም ሆነ ዘመዶችህን በውናችሁ ብቻ ሳይሆን በህልማችሁም ጭምር ሲያንጫጫችሁ ሳይ ላከብረው ነው ጎበዝ፡፡

ደግሞ ማንና ማን ናቸው ተጋብተው ወለዱ የምትለን
ቁቅቅቅቅ
እረ የምትጨብጡትን አጣችሁ ተጠንቀቁ መላቀቅ የለም
ሰሞኑን እዚሂ በረታችሁን ያቃጠሉትን ለማገኝት ብዙ ታግየ ነበር እኔ ምንም ነገር ባይወድም እመርጣለሁ ግን እንዳሉኝ አማራጭ ጠፍቶ ነው ግፉ በዛ ነው ያሉኝ በቦታው የሚፈጸመው ግፍ በዛ ነው ያሉኝ፡፡
አሁን እኮ ያልገባችሁ ነገሩ ያለቀ መሆኑን ነው
ዘ ጌም ኢዝ ኦበር ነው ያለው አጎትህ
ነው እኮ ለምን እገሩን ሁሉ ታቅባባላችሁ በቃ ለቴወድርሶ ከመጠን ያለፈ ገንዝብ ከፈልንላችሁ በዚህ ከበሮ ምቱ በቃ ለቁንጫ ቆርበት እነሰው ክቡ ይበቃችኋል እኮ
ቁቅቅቅቅቅ
ዘመነ ካሴ የሚባለው ወያኔ ነው አለ ያልከው ጎዝ እላለም ዞሮብህ ነው ጨው ራሱ ድሮ ወያኔ ነበር ነው ያለው እሱ ደግሞ ትክክል ነው ያማራው ያላችሁት የነበረከት ማህበርተኛ ነበር ትቶ እስከጠፋ
እሁን ግን ትግሉን እደግፋለሁም አደንቃለሁም ነው ያለው ስሙት ያልከን ጎበዝ ጥሩ ምክር ነው ሁሉንም ይመለከታል ሁሉም እንዲስብ እኔም እመክራለሁ የሁሉንም አስቡ ነው የሚል እምነት አለኝ
እዚህ ላይ ወዳጅህ ኳስ ሜዳ ያለውን በጥብቅ ልድገም እሱም ለሚሰማው ሁሉ እንዲአስተላልፍ እለምናለሁ፡
በአሁኑ ወቅት ያማራው ብቻ ሳይሆን የህዝብ ጠላት አለ እሱም 1 ነው ወያኔ ሌል ጠላት የለም ሰው ነኝ የሚል ሁሉ እዚህ ላይ ጠጠር ይወርውር አለዚያ አተደናቅፉ በላቸው
1 ኢሳት ያማራ ጠላት ነው የሚለው ሀይል ኢሳት ማነው አማራ የለውም እኔ እኮ በደብ የማውቀው ጥሩ ጎበዝ አምስተር ዳም ያለው ፋሲል የሚሉት ጎብዝ አማራ አይደለም ነው የተለየ አማራ አለ? ከባልሽ ባሌ ይበልጣል የሚለው እይሰራም ያው ወያኔነት ነው አስቡበት እንዲህ የምትሉ ልጆች አስቡበት ረፉ
2 ሞረሽ ወገኔ የሚለው ሀይል ማነው እስክማውቀው አፓሳደር እምሩ መሰረትኩት እንዳሉ ቀምተው የመደር እድር አደረጉት? ሞረሽ ወገኔ ( ተክሌ ይሻው) የሚል እያየሁ ነው እረፉ አንተ ማን ሆነህ ነው እነታማኝ ያማራው ጠላቶች አድረገህ ቁጭ ያልክ?? ተው አተደናግሩ እያሰባችሁ ተራመዱ
ኦሮሞኛው ከማዳግስካር ነው የመጣው ብሎ ሲጽፍ ተክሌን አይቻለሁ ወዳጀ ዳዊት ወልደ ጊወርጊስ ያለውም ይህን መሰለኝ
ሞረሽ ይህን አላለም የሚል መልስ ያየሁ መሰለኝ ?
ምን ማለት ነው?
ቁቅቅቅቅቅ
ሰው ከሆናችሁ ጠላታችሁን እወቁ በጎን ጉንተላችሁን አቁም በልልኝ
ኳስ ሜዳ አደራህ
በተረፈ ግንኙነቱ እያስቸገረኝ ነው እመለሳለሁ ካልዘጉት፡፡
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2410
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], ክቡራን and 6 guests