ሰባተኛ ዓመት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰባተኛ ዓመት

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Mar 29, 2017 6:17 pm

መቼም ከዋርካ ነባር ታዳሚዎች መካከል ሻምበል ሳሙኤል ጥሩነህን የማያስታውስ አለ ብዬ አልገምትም::ዋርካ ላይ ባሳለፋቸው 7ዓመታት ያለማቋረጥ ወርቅሰው1፣ልጁነኝ1፣ላሊበላ4፣ቃኘው፣ታጠቁ በሚሉ ኒኮች በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ሲሳተፍ የነበረ ነው::ታዲያ ዛሬ ሻምበል ጥሩነህ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 7ዓመት ሆነው::ዋርካ ዛሬ የምትገኝበት የውይይት መንፈስ ተስፋ የሚሰጥ ባለመሆኑ ነው ሻምበል ጥሩነህን ለማስታወስ የገፋፋኝ::ከሻምበል ጥሩነህ ጠንካራ ጎኖች መካከል:-
1)ያለመሰልቸት ሳያቋርጥ ረዘም ላለ ጊዜ መሳተፉ
2)ለዋርካ ባለቤቶች የነበረው አክብሮትና በገንዘብ እንዲታገዙ በመደጋገም ማሳሰቡ
3)የታዳሚዎችን(በተለይ አዲስ የገቡ) ጠንካራና ደካማ ጎን በመረዳት ማበረታቱና መምከሩ፣ እንዲሁም ገፍተው ካልመጡበት በቀር ሁሉንም ታዳሚ ማክበሩና ሥነምግባር የተሞላው ውይይት ለማካሄድ መቻሉ::
4)በኢትዮጵያ ፖለቲካና ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ የነበረውን ጠለቅ ያለ ዕውቀት ለታዳሚዎች ለማጋራት የነበረው ጉጉትና ያላሳለሰ ጥረት
5)ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ የነበረውን ቁጭት ዘወትር ማሳወቁ ወ.ዘ.ተ.
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby ክቡራን » Thu Mar 30, 2017 5:59 am

ዘርዐይ ደረስ wrote:
2)ለዋርካ ባለቤቶች የነበረው አክብሮትና በገንዘብ እንዲታገዙ በመደጋገም ማሳሰቡ

ሰላም ዘራይድረስ የወርቅነህን በማስታወስህና በማመስገንህ ምስጋናዬ ይድረስህ፡ መልካም ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ ነፍሱ በሰላም ትረፍ፡፡

እኔ የምለው ግን ከዋርካ አራቱ ዘበኞች አንዱ አንተ ነህ እንዴ?
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8040
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Mar 30, 2017 5:49 pm

ክቡራን wrote:
ዘርዐይ ደረስ wrote:
2)ለዋርካ ባለቤቶች የነበረው አክብሮትና በገንዘብ እንዲታገዙ በመደጋገም ማሳሰቡ

ሰላም ዘራይድረስ የወርቅነህን በማስታወስህና በማመስገንህ ምስጋናዬ ይድረስህ፡ መልካም ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ ነፍሱ በሰላም ትረፍ፡፡

እኔ የምለው ግን ከዋርካ አራቱ ዘበኞች አንዱ አንተ ነህ እንዴ?


አይደለሁም!!
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Mar 30, 2017 10:08 pm

ዘርዐይ ደረስ
ይህን ቤት ለላሊበላ /ልጁነኝ/ ጥሩሰው/ ወርቅሰው ለሻምበል ሳሙኤል ጥሩነህ መታሰቢያ መክፈትህ የሚመስገን ነው፡፡ ይህ ጉድ ያቀረበው ጥያቄ አይሉት ስሞታና ክስ ያስቃል፡፡ሌባ እናት ልጁዋን አታምንም ነው የሚባለው? ዋርካ ላይ ከቢጤዎቹ በስተቀር ያለከፈው ሰው የለም፡፡

`
ዘርዐይ ደረስ wrote: አይደለሁም!![/size]
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby ክቡራን » Wed Apr 12, 2017 12:19 am

እኔ የምለው ግን ከዋርካ አራቱ ዘበኞች አንዱ አንተ ነህ እንዴ? [/quote]

አይደለሁም!!
[/quote]


ዘርአይ ድረስ ያንድ ፎረም አድሚን መሆን አለመሆን ቢግ ዲል እይደለም፡፡ እኔ በምመራቸው የፌስ ቡክ አካውንቶች ዋና እድሚን ነኝ አንዳንዶቹ ጋ ኤዲተር ነኝ፡፡ አድሚን መሆን የድህረገጹን ሚሽንና ቪዥን ማስፈጸም የመቻል ብቃት እንጂ የናሳ ሳይንቲስት መሆንን አይጠይቅም፡፡ ለዚህ ነው ቢግ ዲል አይደለም የምልህ፡፡ ከዚህ በፊት ከዋርካ አራት ዘበኞች አንዱ ነህ ወይ ብዬ ጥያቄ አቅርቤልህ ነበር ፡፡ አይደለሁም አልከኝ፡፡ አይደለሁም ስላልክ አይደለህም ማለት አይደለም፡፡ ነኝም ስላልክ ነህም ማለት እይደለም፡፡ መሬት ላይ ያለው ስብስታንሽያል ፋክት እውነቱን ይነግረናል፡፡ የወርቅ ሰው ጥሩና ሀገሩን የሚወድ ተሳታፊ እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን፡፡ የወርቅ ሰው መልካም ኢትዮጵያዊ ነው እልን እንጂ ሞኝ ነው አላልንም፡፡ ይሄን የምልበት ምክንያት የወርቅ ሰው ያልነገረንን የመጻፊያ ስሞቹን ታጠቅ ፣ ላለበላ 1 ፣ ላሊበላ 2 ፣ ልጁ ነኝ ....እያልክ ቿንተ ቾንቴ ቻቻ ቾቼ እያልክ ዘረገፍከው ፡፡፡ እንዴት ይሄን ሁሉ የወርቅ ሰውን የብእር ስሞች ልታውቅ ቻልክ?? ዘርአይ ድረስ አንተ የዋርካ ዘበኛ እይደለሁም ትላለህ ፕሮፋይልህ ግን ሌላ ዜማ ያዜማል እንዴት ኖ ኢቺ ነገር አለች ቶሎሳ...ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8040
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat May 06, 2017 10:00 pm

ክቡራን:-አንተ ዋርካ ላይ ዘግይተህ ስለገባህ ይሆን ይሆናል እንጂ በርካታ ቀደምት የዋርካ ታዳሚዎች ወርቅሰው በጠቀስኳቸው ኒኮች እንደሚጠቀም ያውቃሉ::ይህንን ለማወቅ አንተ እንደጠረጠርከው የዋርካ ‚ዘበኛ‘ መሆን የግድ አይልም::በተረፈ ሻምበል ሳሙኤል ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ በኋላ እነዚያ ኒኮች ዋርካ ላይ አልተጻፈባቸውም::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby humaidi » Sun May 07, 2017 10:00 am

ዘርዕይ ደረሰ የሻምበል ጥሩነህን ሂወቱን ይማር አንተም አስታውሰህ ይህን ቤት ሰለከፈትክ ትመሰገናለህ ይመሰላኛል ከዚህ በፊት ዋርካ ጀነራል ላይም እንዲሁ ቤት ተክፍቶለት ነበር ግን እርግጠኛ እይደለሁም እዚህም በሚገባ ሰለሱ ገልጸሃል !
humaidi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1741
Joined: Tue Jan 03, 2006 11:50 am

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Mar 29, 2018 10:00 am

ስምንተኛውንም እናስበው
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰባተኛ ዓመት

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Mar 26, 2019 11:16 pm

፱ኛውንም ዓመት አስበን እንዋል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests