ወያኔ በአፋር እያካሄደ ያለው ወረራ ተቃውሞ እያስከተለ መሆኑ እና ሌልች ወቅታዊ ዘገባዎች!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔ በአፋር እያካሄደ ያለው ወረራ ተቃውሞ እያስከተለ መሆኑ እና ሌልች ወቅታዊ ዘገባዎች!

Postby ኳስሜዳ » Mon Jul 03, 2017 6:21 pm

ፍካሬ ዜና #ርዕሰ ዜና #
#በአስገንጋጭ ሁኔታ እየተዛመተ የሚገኘው የተምች ወረርሽኝ ስጋት አሳደረ
#ወያኔ በአፋር እያካሄደ ያለው ወረራ ተቃውሞ እያስከተለ መሆኑ ተሰማ
#ወያኔ ሀገሪቱን የብድር ማጥ ውስጥ መክተቱ አነጋጋሪነቱ እየጨመረ መሆኑ ታወቀ
#ትምህርት ሁኔታ ጥራቱ እየወረደ መሆኑ በይፋ ተነገረ
#የአዲስ አበባን የቆዳ ስፋት ለመለጠጥ በልዩ ጥቅም ስም አዋጅ መዘጋጀቱ አመጽ ቀስቃሽ ሊሆን እንደሚችል ተነገረ
#ወያኔ በኢንዱስትሪ መንደሮች የሚሠሩ ሠራተኞችን እጅግ ዘግናኝ ለሆነ ብዝበዛ እንደዳረጋቸው ተገለጸ


#በአስገንጋጭ ሁኔታ እየተዛመተ የሚገኘው የተምች ወረርሽኝ ስጋት አሳደረ

▪ የተምቹ ወረርሽኝ በአሁኑ ሰዐት ከወያኔ በይፋ የተነገረ ባይሆንም ድፍን ሀገሪቱን ማዳረሱ እንደማያጠራጥር የሰብል እርሻ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ በመስኖና በበልግ ዝናብ ይመረት የነበረውን የበቆሎ ምርት ተምቹ እዛው ማሳው ላይ እንዳ እምሽክ አድርጎ እንዳስቀረው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለወትሮው በዚህ ወቅት በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ የበቆሎ ጥብስና ቅቅል የሚሸጥበት እንደነበር ብዙዎች እያስታወሱ ዘንድሮ ለዐይንም መጥፋቱ የመጪውን ዘመን የእህል እጥረት የሚያመላክት መሆኑን በርካቶች በቁጭት ያስረዳሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ወያኔ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ሲል ብቻ የበቆሎ ምርት ወደ ውጪ እንዲላክ መወሰኑ ወያኔ ከአፍንጫቸው አርቀው ማሰብ የማይችሉ ስብስብ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ብዙዎች ስምምነታቸውን ሲገልጹ ይሰማል፡፡

#ወያኔ በአፋር እያካሄደ ያለው ወረራ ተቃውሞ እያስከተለ መሆኑ ተሰማ

▪ ወያኔ የትግራይን ግዛት ለማስፋፋትና በእርሻና በማእድን እራሷን የቻለች ትግራይ ለማድረግ በግልጽና በስውር የሚያደባው ሴራ ሕዝባዊ ተቃውሞ እያስከተለበትና ህልውናውን እየተፈታተነው መሆኑ እየታወቀ ከአፋር በጨው ማዕድን የበለጸገውን አካባቢ ወደ ትግራይ ውስጥ ውስጡን መጠቅለሉ የአፋር ሕዝብ በቁጣ በወያኔ ላይ እንዲነሳና እንዲያምጽ እያደረገው መሆኑን ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ከአፋር እየተጋዘ የሚወሰደው የጨው አለት መቀሌ ላይ ተቀነባብሮ በመቀሌ የተመረተ መባሉ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የጨዉ ማዕድን ሊቀነባበር የሚገባው እዛው ጨዉ የተገኘበር ምድር ላይ ሊሆን ሲገባው ወደ ትግራይ የጨዉን አለት እያመላለሱ ማቀነባበር ትርጉሙ መሬቱን ወደ ትግራይ ለመጨፍለቅ ከተያዘው ስውር ደባ ጋር የሚዛመድ መሆኑን በርካቶች ያስረዳሉ፡፡

#ወያኔ ሀገሪቱን የብድር ማጥ ውስጥ መክተቱ አነጋጋሪነቱ እየጨመረ መሆኑ ታወቀ

▪ ሰሞኑን ይፋ የተደረገው መረጃ ወያኔ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ለ23 ቢሊዮን ዶላር ባለእዳ እንደዳረገ ያሳያል፡፡ ይህ በየአመቱ የሚከፈለው 400 ሚሊዮን የብድር ወለድ እንደማይጨምር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ የብር እዳ ውስጥ ግማሽ ያህሉ በተለያዩ እረከን በሚገኙ ወያኔዎች ተግጧል፡፡ እስካሁን ወያኔ ብርን በስርዐት ለማተም የሚያስችል ህግ እንዲደነገግ ያላደረገ በመሆኑ እንዳፈተተው እያተመ ገበያ ውስጥ የሚያስገባው የብር መጠን ገበያውን እየረበሸው እንደሆነ ማንም ገበያተኛ እለት እለት ለሚያጋጥመው የመገበያ መበላሸት የብር በብዛት መሰራጨት መሆኑን እያወቀው ከመጣ በርካታ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ወደ ውጪ ከሚላኩ ከቡና፣ ከቆዳና ሌጦ፣ ከቅባት እህሎች፣ ከጥራጥሬ፣ ከወርቅና ከሌሎች ከከበሩ ማዕድናት፣ ወዘተ. ለማግኘት ከተሰላው ሦስት እጅ እጥፍ በታች በመውረዱ እዳ መክፈል ጥያቄ ውስጥ እንደሚወድቅ መረዳት ተችሏል፡፡ የወጪ ንግዱን ያሽመደመደው የዶላር ምንዛሪ አለመጨመር እንደሆነ የገንዘብ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት እየገፉ ያሉት የአንድ ዶላር ዋጋ ሠላሳ ብር እንዲሆን መሆኑ በስፋት የተገለጸ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ወያኔ በየአመቱ ለብድር ክፍያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ እንደሚያስከፍለው የሚታወቅ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በቢሊዮን የሚቆጠር ተጨማሪ የብር ኖቶችን ገበያ ውስጥ ማሰራጨት የግድ የሚል ይሆናል፡፡ ይህ ተጨማሪ ብር የማሳተም ጉዳይ በየአመቱ ከአስራ አምስት ከመቶ በላይ እየናረ በመሄድ ላይ ያለውን የገበያ ዋጋ ክፉኛ ይረብሸዋል፡፡ ይህም በእራሱ ህልፈተ ወያኔን ያጣድፈዋል ተብሏል፡፡ ወያኔም ለዚህ ክፉ ሁኔታ ላለመጋለጥ ቢፍጨረጨርም መጨረሻው ግን የዓለም አበዳሪ ድርጅቶቹን ሀሳብ መቀበል የግድ መሆኑን የመዋዕለ-ንዋይ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡

#የትምህርት ሁኔታ ጥራቱ እየወረደ መሆኑ በይፋ ተነገረ

▪ በቅርቡ በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቭርሲቲዎች የተደረገ ጥናት እንደሚያስረዳው በአሁኑ ወቅት ዩኒቭርሲቲ ውስጥ እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች ወስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጉት የሰባተኛና የስምንተኛ ክፍል የሂሳብና የሳይንስ ፈተናዎችን ማለፍ አለመቻላቸው ትምህርት ሆን ተብሎ እንደተቀበረ የሚያሳይ መረጃ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ እንዲሁም ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ተማሪዎች ማንበብና መጻፍ የማይችሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ ወያኔ ትውልድ ገዳይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ለሚቀርበው ክስ ተጨባጭ ማስረጃ ነው ተብሏል፡፡

#የአዲስ አበባን የቆዳ ስፋት ለመለጠጥ በልዩ ጥቅም ስም አዋጅ መዘጋጀቱ አመጽ ቀስቃሽ ሊሆን እንደሚችል ተነገረ

▪ ወያኔ ስር የሰደደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማምከን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ አጠቃላይ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በወታደራዊ እዝ ስር ቢያስገባም ውስጥ ውስጡን ለወያኔ ህልውና አስጊ በሆነ መልኩ ሕዝባዊ አመጽ ሊከሰት እንደሚችልና በወያኔ ጥቅሞች ላይ አደጋ ሊጣል እንደሚችል ስጋት እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰሞኑን በይፋ እየተነገረ ያለው አዲስ አበባ በኦሮሞ ክልል ስር በመሆኗ ለኦሮሞ ክልል ልዩ ጥቅም መክፈል እንደሚገባት የሚደነግግ ህግ መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡ በዚህ ህግ መሰረት ኦሮምኛ በአዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ መሆን እንዳበትና በአዲስ አበባ ለኦሮሞ ህፃናትና ወጣቶች በቋንቋቸው የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱላቸው፣ የአዲስ አበባ መጠሪያ እንዳለ ሆኖ ፊንፊኔ የሚለው የኦሮሚኛ መጠሪያ ጎን ለጎን ጥቅም ላይ እንዲውል፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ ገበሬዎች ከመሬታቸው ሲፈናቀሉ የተከፈላቸው ክፍያ ማስተካከያ እንዲደረግ ወዘተ. የሚደነግግ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ብዙዎች አስተያየታቸውን ሲሰነዝሩ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ብለውታል፡፡ በድፍን ኢትዮጵያ አምና እንደ ሰደድ እሳት በየአቅጥጫው የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጥያቄው ሌላ ሳይሆን፣ ጥያቄው ሽርፍራፊ ጥቅም ለማግኘት ሳይሆን፣ በአንድ ቃል ወያኔ ይወገድ የሚል ነበርና ሕዝቡ በአመጹ
ይገፋል የወያኔም የመደለያ ህግ ፌዝ ሆኖ ይቀራል ተብሏል፡፡

#ወያኔ በኢንዱስትሪ መንደሮች የሚሠሩ ሠራተኞችን እጅግ ዘግናኝ ለሆነ ብዝበዛ እንደዳረጋቸው ተገለጸ

▪ ወያኔ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እያወጣ መሆኑን ነጋ ጠባ የሚወሻክትባቸው የኢንዱስትሪ መንደሮች የሚባሉት ከቻይና በተገኘ ብድር እየተገነቡ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በመንደሮቹ ውስጥ ከሚገኙት ፋብሪካዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የቻይና በመሆናቸው ብድሩ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ በነፃ ካለምንም ኪራይና ለሌሎች የንግድ ሁኔታዎች ሊከፈል የሚገባውን ሁሉ እንደማይከፍሉ ከውስጥ አወቆች የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ከዚህ ቀደም ወያኔ ሕዝብን ለማደናገር “ግብርና ተኮር” የሚል ጨዋታ ተጫውቶ ገበሬዎችን ከደህነት ወደ ከፋ ድህነት አዘቅት መክተቱ የማይረሳ ነው ተብሏል፡፡ በተመሳሳይም የኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ የሚሠሩ ለጋ ወጣቶች የሚከፈላቸው ጥቅል ደሞዝ በወር ከአንድ ሺ ብር የማይበልጥ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የግብር ክፍያዎች ተቀናንሰው በእጃቸው የሚደርሳቸው ከስድስት መቶ ብር የማይበልጥ መሆኑ ወያኔ የቱን ያህል ሀገር ገዳይ ትውልድ ቀባሪ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡ የኢንዱስትሪ መንደር ጨዋታ እነ ካምቦዲያን የመሳሰሉ ሀገራትን እንደ ቀበራቸው ኢትዮጵያም ለቁራኛ መዳረጉ አይቀርም እየተባለ ነው፡

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=78013
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot], Majestic-12 [Bot] and 7 guests