ቁርጥ ግብር – የህውሓት ገጀራ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ቁርጥ ግብር – የህውሓት ገጀራ!

Postby ኳስሜዳ » Mon Jul 10, 2017 6:34 pm

የሰሞኑ የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ አዲስ አበባ ውስጥ በአነስተኛ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች ላይ የተጣለው ከፍተኛ “ግብር” ነው፤ ይህ ግብር “ቁርጥ ግብር” ወይንም “Presumptive tax” በመባል ይታወቃል፤ “ቁርጥ ግብር” ታማኝ ያልሆኑ ዜጋ የሚቀላበት (የሚወገድበት) ሎሌ የሚተከልበት የህውሓት አንዱ ስውር ገጀራ ነው:: ይህ ገጀራ ከወያኔ የዕዝ ሰንሰለት ውጭ በንግድ ተሰማርተው የተገኙትን ዜጎች ይቀስፋል፤ የወያኔ ዕዝ <<የህብረት ስራ ማህበራት፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝስ ወ.ዘ.ተ>> በሚባሉ ስያሜዎች የሚታወቁት ናቸው፤ የወያኔ ገጀራው ከሰገባው የሚመዘዘው በአመት አንዴ ነው፤ ብዙ ዜጎችን ሙት እና ቁስለኛ ሳያደርግ ወደ ሰገባው አይመለስም፤ የዚህ ገጀራ ሰለባ ከሆኑት መካከል ጋሽ መሐመድ ሐሰን አንዱ ናቸው::

ጋሽ መሐመድ የአካባቢውን ነዋሪ ልብስ በማጥበብ፣ በማሳጠር እና በመጠገን ስምንት ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ታታሪ ዜጋ ናቸው፤ ከልጅነት እስከ እውቀት የማውቃቸው በዚህ ሙያቸው ነው፤ አንድ ክፉ ቀን የህውሓት እጅ የጋሽ መሐመድን ሱቅ በርቅሳ ግድግዳው ላይ <<ማኔን፣ ቴቄል፣ ፋሬስ> ብላ ጻፈች፤ <<መዘንኩህ (በታማኝነት ሚዛን) ቀለህም ተገኝህ፣ ሱቅህም ለታማኝ ሎሌ ተሰጠች>> ስትል ነው፤ ጋሽ ማሜ ሰምተውት እንጂ አየተውት የማያውቁትን ገንዘብ እንዲከፍሉ ተጠየቁ፤ 5 ሺህ ብር! ጋሽ መሐመድን ብዙም አልደነገጡም፤ ባለመረበሻቸው የተገረሙ ወዳጅ እና ዘመዶች ጠጋ ብለው ሲጠይቋቸው ለሁሉም የሚሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነው፤ <<5 መቶ ቢሉኝ ከልጆቼ ጉሮሮ ነጥቄ፣ ተበድሬ ወይም እቁብ ገብቼ ለመክፍል በደከምኩ፤ አላህ ይስጣቸውና 5 ሺህ ብር ብለው ከዚህ ሁሉ ድካም ገላገሉኝ>> ይላሉ:: ጋሽ ማሜ መሰዋት ሆኑ!

ሌላው የህውሓት ቆንጨራ <<የሙያ ብቃት ማረጋገጫ>> በሚባል ይታወቃል፤ እንጀረ በመጋገር የምትተዳደር አቅመ ደካማ እናት ሳትቀር በህውሓት ሰራዊት <<የሙያ ብቃት ማረጋገጫ>> ስለሌለሽ አክንባሎሽን ስቀይ መባሏ የቅርብ ቀን ትዝታ ነው፤ እንግሊዘኛ ተናገር የተባለ ጊዜ ምላሱ ከትናጋው የሚጣበቅበት ካድሬን (ጸጋዬ በርሄን መጥቀስ ይቻላል) ባለ ሙሉ ስልጣን አንባሳደር አድርጋ የምትሾም ህውሓት አንድን እናት የእንጀራ ጋገራ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ካላመጣሽ ምጣድሽን እሰብራለው ማለቷ ግርምታን ያጭራል::

ለቱርክ፣ ለሳውዲ፣ ለህንድ እና ለሎች የውጭ ሃገር <<ባለሃብቶች>> ከሊዝ ነጻ መሬት፣ 70% ብድር እና የአምስት አመት የትርፍ ግብር እፎይታ አዘጋጅታ “ኑ” << ሙሉሄ በኩሉሄ>> የምትለው ወያኔ ምነው ዜጎች ላይ እንዲህ ጨከነች? ጎዳና ላይ አንጥፎ አልያም መስኮት ቀዶ ጉሮሮውን ለመድፈን የሚወተረው ዜጋ ላይ ምነው ልቧ ደነደነ? ብሎ መጠየቅ ተበጊ ነው፤ አጭሩ መልስ <<የኢኮኖሚ ነጻነቱ የተደፈጠጠበት ህዝብ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ እንደሆነ ስለምትረዳ፤ የኢኮኖሚ ነጻነቱ ዲሞክራሲያዊ መብትን እንደሚያስከትል ጠንቅቃ ስለምታውቅ>> የሚል ይሆናል:: በዚሁ ወደ ፍሬ ጉዳያችን (የኢትዮጵያዊያንን የኢኮኖሚ ነጻነት ያለበትን ደረጃ ወደ መዳሰሱ) እንዝለቅ::

የኢኮኖሚ ነጻነት (Economic Freedom) ዜጎች በፖለቲካ አመለካከት፣ በዘር (በጎሳ ወይም ብሄር)፣ በሃይማኖት ወ.ዘ.ተ አድሎ ሳይደረግባቸው በነጻነት፣ በመረጡትና በፈለጉት የኢኮኖሚ መስክ እንዲሰማሩ (እንዲሳተፉ) የሚያስችል የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ነው::

የዜጎች የኢኮኖሚ ነጻነት በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 41 “የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባህላዊ መብቶች” ውስጥ የተካተት ቢሆንም በሃገራችን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ነጻነት እጦት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ:: ይህንን ከሚጠቁሙት መረጃዎች መካከል ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን (Heritage Foundation) እና የዎል ስትሪት ጆርናል (The Wall Street Journal) በተባሉ ተቋማት ከ1995 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ በየአመቱ የሚወጣው የኢኮኖሚ ነጻነት ደረጃ (Economic Freedom index) ሪፖርት ዋነኛው ነው:: ይህ አህዛዊ መለኪያ የሚያመለከተው ዜጎች በሃገራቸው ውስጥ በነጻነት (በምርጫቸው)፣ ያዋጣኛል ባሉት የኢኮኖሚ መስክ ሃብታቸውን እና እውቃታቸውን ተጠቅመው (ሌሎች ዜጎችም ይህንኑ የማድረግ መብታቸውን ሳይጋፉ) የማምርት፣ የመሽጥ እና የመለወጥ መብትን ነው::ከስር ከተመለከተው ከግራፉ ማየት እንደሚቻለው በ2013 እና 2014 (እ.ኤ.አ.) ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጭቆና ካለባቸው ሃገራት ውስጥ ተካታለች::

በቅርቡ ይፋ የሆነው የ2017 (እ.ኤ.አ). ይህ የሃገራት የኢኮኖሚ ነጻነት ደረጃ ሪፖርት ኢትዮጵያን ከዓለም 142ኛ፤ ከሰሃራ በታች ካሉ 46 የአፍሪካ ሃገራት ደግሞ 31ኛ አስቀምጧታል:: በዚህ ሪፖርት ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ነጻነት ከሌለባቸው ሃገራት ውስጥ ተካታለት:: ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ሙስና ሲሆን ሌላው ደግሞ መድሎ እንደሆነ በሪፖርቱ ተጠቅሷል:: ሪፖርቱ የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና ውስጥ የተዘፍቁ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ ብድር፣ የመስሪያ ቦታና የስራ ቅጥር የሚያገኙት የገዥው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች መሆናቸውን አስቀምጧል:: “በመንደር ለማሰባሰብ” (Villagization) እና <<ለልማት>> በሚሉ ሰንካላ ምክንያቶች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ያለፍላጎታቸው ከቀያቸው እንዲነሱ መደረጉ ኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ነጻነት ከሌላባቸው ሃገረት ተርታ ያሳለፍት ሌላኛው ምክንያት እንደሆነ ይሄው ሪፖርት ያትታል:: ሪፖርቱ በመንግስት የተጣለው የግብር አይነትና መጠን የዜጎችን የመስራት፣ የመቆጠብና ኢንቨስት የማድረግ አቅምንና ፍላጎትን በከፍተኛ ደረጃ የሚፍትን መሆኑን በመጥቀስ ይህም ሃገሪቷን የምጣኔ ሃብት ነጻነት ከሌላቸው ሃገራት ግርጌ እንድትሰለፍ ማድረጉን ያብራራል:: ይህ ሪፖርት የግብር ስርዓቱ የዜጎችን የኢኮኖሚ ነጻነት ይጻረራል ሲል የሚጠቅሰው የስራ ቅጥር ግብር ጣሪያ 35% እና የንግድ ስራ ትርፍ ግብር 30% መሆኑን ጠቅሶ ነው:: ይህንን ሪፖርት ያወጡት ተቋማት ሰፋ ያለ ጥናት አድርገው ቢሆን ኑሮ ውጤቱ ከዚህ እጅጉን የከፋ ይሆን እንደነበር አያጠራጥርም:: ለምሳሌ ያክል በቁርጥ ግብር ስርዓት (Presumptive taxation system) በአነስተኝ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች ቆጥረውት አይደለም አይተውት የማያውቁትን የገንዘብ መጠን በግብር መልክ እንዲከፍሉ እንደሚጠየቁ፤ በዚሁም ምክንያት ንግዳቸውን ለመዝጋት እንደሚገደዱ፤ መንገድ ዳር ጫማ በመጥረግ የሚተዳደሩ ዜጎች ጭምር በወር 12 ብር እንደሚከፍሉ (እንደሚቀሙ)በሌላ በኩል ደግሞ እነ ሃጎስ ከቀረጥ ነጻ ወደ ሃገር ቤት ያስገቧቸውን የኮንስትራክሽን ማሽኖች ለመንግስት ፕሮጀክቶች ሳይቀር በሰዓት እስከ 1,000 ብር በነጭ ወረቀት እያከራዩ በግብር መልክ የሚከፍሉት ሰባራ ሳንቲም እንደሌለ ግንዛቤ ውስጥ አልገባም:: ይህቺ ናት ኢትዮጵያ!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/17970/
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2119
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests