በባህርዳር በህወሓት ወታደራዊ ጀነራል ላይ ጥቃት ተሰነዘረ ሲል ከባህርዳር ህቡዕ ቡድን ገለፀ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በባህርዳር በህወሓት ወታደራዊ ጀነራል ላይ ጥቃት ተሰነዘረ ሲል ከባህርዳር ህቡዕ ቡድን ገለፀ

Postby ኳስሜዳ » Wed Jul 12, 2017 1:49 pm

ከባህርዳር ህቡዕ ቡድን
ባለፈው ወር መጨረሻ አካባቢ በቀበሌ 04 ትራፊክ ላይቱ ላይ ባልተፈቀደ መንገድ በሚያሽከረክረው ወታደራዊ ኮንቮይ አንዲት ባጃጂ የገጨው እና በውስጧ የነበሩ 3 ሰወች ላይ የአካል ጉዳት ያደረሰው ወታደራዊ ጀነራል ላይ ጥቃት ተደርጓል። ጀነራሉን ለማጥቃት የተወረወረ ቦንብ በቀበሌ 7 ባህርዳር ዩንቨርስቲ ፔዳ ካምፕስ መስመር ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት ባለ የዳሽን ቢራ ጀንቦ መሸጫ ቤት ከአንድ ባልደረባው ጋር ሲጠጣ ቆይቶ ሲወጣ በቀበሌ 7 ራንዲቦ ካፊ ፊት ለፊት በባጃጂ በሚከታተሉት ወጣቶች ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ሐምሌ 4 /2009 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡30 ነበር። በተወረወረ ቦንብ ጀነራሉ ከጉዳት ሊያመልጥ ችሏል። በጥቃቱ ሌላ በስፍራው የነበረች ባጃጂ ሞተሯ አካባቢ ተቀጣጥሎ ጉዳት ደርሶባታል። ወታደራዊ ጀነራሉ ወዲያውኑ ከስፍራው ሲያመልጥ ከፍተኛ ህዝብ በቦታው ተገኝቶ የተቃጠለውን ባጃጂ ባለቤት ሲያፅናና እና የገንዘብ መዋጮ ሲያደርግ ተስተውሏል።
ከጥቃቱ በኋላ ብዛት ያለው የአድማ በታኝ ልዩ ሃይል እንዲሁም ወታደሮች በቀበሌ 7 ጥቃቱ በደረሰበት ስፍራ አካባቢ ፣ በቀበሌ 12 ፣ በቀበሌ 01 እና 02 ፈሰው ይገኛሉ ። የህዝቡ እንቅስቃሴ ተገድቦ ፍተሻም እየተወረገ እንደሆነ ታውቋል።

http://www.satenaw.com/amharic/archives/35270
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests