በወሊሶ ሕባዊ አመጽ ተዝቀጣጠለ * መኪኖች ተሰባበሩ * ንግድ ቤቶች ተዘጋግተዋል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በወሊሶ ሕባዊ አመጽ ተዝቀጣጠለ * መኪኖች ተሰባበሩ * ንግድ ቤቶች ተዘጋግተዋል

Postby ኳስሜዳ » Tue Jul 18, 2017 2:14 am

ዘ-ሐበሻ) በአምቦ በድጋሚ የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ ወደ ሌሎች ከተሞችም በመዛመት በወሊሶ ከተማ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በህዝባዊ አመጽ ስትናወጥ መዋሏ ተዘገበ::

በወሊሶ ከተማ መንግስት አላግባብ የጣለውን ግብር በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ እንደሚደረግ እንደዚሁም የትራንስፖርት አገግሎት እንደሚቋረጥ በሕዝቡ በተበተነ መረጃ ሕዝቡ ሲነገረው የቆየ ሲሆን ሁሉም ንግድ ቤቶች ሲዘጉ አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ግን ሲያሸከረክሩ በመገኘታቸው ሕዝቡ በመኪና በመውገር እንደሰባበራቸው መረጃዎች ጠቁሟል::

በወሊሶ ሰላማዊ ሰልፍና እንደዚሁም በንብረቶች ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ የሚገልጹት ምንጮቻችን ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተዘጋግታ በአጋዚ ሠራዊት መወረሯንም ገልጸዋል::

እንደምንጮች ገለጻ መንግስት በሕዝቡ ላይ የጣለውን አግባብ ያልሆነ ግብር ካላነሳ ሕዝባዊው አመጽ ይቀጥላል:፡
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=78352
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 5 guests