ኮማንድ ፖስቱ ሃላፊነቱን ለክልሎች አስተላለፈ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኮማንድ ፖስቱ ሃላፊነቱን ለክልሎች አስተላለፈ፡፡

Postby ክቡራን » Tue Jul 18, 2017 2:19 pm

Image

በአገሪቱ ያለው ሰላም እየተሻሻለ በመምጣቱ የፌደራል ኮማንድ ፖስት በክልሎች ያለውን የፀጥታ ስራ ለክልሎች እየሰጠ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ ገለፀ፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ባለፉት 9 ወራት በአገሪቱ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን የተከናወኑ ስራዎችን ገምግሟል፤በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ላይም ተወያይቷል፡፡
የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያትና የኢፌዲሪ መከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 9 ወራት በተከናወኑ ስራዎች የአገሪቱ ሰላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡ ለዚህም ህዝቡና በየደረጃው ያለው አመራር ተቀናጅተው መስራታቸው ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኮማንድ ፖስቱ የፀጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፀጥታ አካላትን በማሰልጠን ፣ በማደራጀት እንዲሁም ችግር ያለባቸውን አካላት በማጥራት ውጤታማ ስራ ማከናወኑን አቶ ሲራጅ ተናግርዋል፡፡
አሁን ላይ በአገሪቱ ያለው ሰላም እየተሻሻለ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የፌደራል ኮማንድ ፖስት አካላት በክልሎች ያለውን የፀጥታ ስራ ለክልሎች የፀጥታ አካላት እየሰጡ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳል ወይ በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ሰላሙ እየተረጋጋ መምጣቱንና አስፈላጊ የፀጥታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ኃላፊው፣ ለጉዳዩ የሚመለከተው አካል ሁኔውን አጢኖ ውሳኔ እንደሚሰጥበት አመልክተዋል፡፡
አቶ ሲራጅ እንዳሉት ባፉት ዘጠኝ ወራት የሰላም ሁኔታው በመሻሻሉ የመሰረተ ልማትና የመንግስት ተቋማትን በመጠቀም ባለሃብቶችና ዜጎች ስራቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያናውኑ ማድረግም ተችሏል፡፡ይሁን እንጂ በአገሪቱ ለተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ዋንኛ ምክንያት የሆኑት የመልካም አስተዳደርና የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ አሁንም በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል፡፡

ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests