በምእራብ ኦሮሚያ ለ3ኛ ቀን የስራ አድማው እንደቀጠለ ነው ከሆሎታ እስከ ወለጋ መንገድ ተዘግቷል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በምእራብ ኦሮሚያ ለ3ኛ ቀን የስራ አድማው እንደቀጠለ ነው ከሆሎታ እስከ ወለጋ መንገድ ተዘግቷል

Postby ኳስሜዳ » Wed Jul 19, 2017 3:25 pm

ዛሬ ረቡእ በምእራብ ኦሮሚያ፣ከሆሎታ እስከ ወለጋ ደምቢ ዶሎ ያለው መንገድ ለትራፊክ ዝግ እንደሆነ የተገለጽ ሲሆን የንግድ ተቋማት፣መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ መ/ቤቶችም ካለምንም ስራ ተዝግተው እንዳሉ ከስፍራው ካሰባሰብነው መረጃዎች መረዳት ተችላል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እኩለ ቀን ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምራል ብለው የሰጡትን መግለጫ ለማጣራት ወደ አምቦ እና ጊንጪ ከተሞች ባደረግነው ጥያቄ ከነዋሪው የተሰጠን መልስ ከአስኮ ጀምሮ ቡራዩ፣ገፈርሳ፣ሆሎታ፣ኦሎንኮሚ፣ጊንጪ፣አምቦ፣ጉደር፣ሸኖ፣ለቀምትና ደምቢ ዶሎ ድረስ አንዳችም የትራንስፖርት አገልግሎት አለመጀመሩን ተናግረው በመንግስት በኩል ግን ህዝቡን አስፈራርቶ ስራ ለማስጀመር ባልሰልጣናቱ ሙከራ ሲያደረጉ ነበር ብለዋል።

በወሊሶ ያለውም የስራ ማቆም አድማ ዛሬ በሶስተኛው ቀንም እንደቀጠለ ነዋሪዎቹ ገልጸው፣ በመንግስት በኩል ታቅዶ የነበረው ስብሰባም ሳይካሄድ ቀርቷል ብለዋል።

በምእራብ ኦሮሚያ ዞን እና በጂማ፣በፍቼ እና በምስራቅ ሀረርጌ ያሉ ነጋዴዎች በመንግስት በኩል የተመደበብን የዚህን ዓመት ግብር ተመን ከእለት ተእለት ገቢና ወጪያችን ጋር የማይጣጣምና እጅግ የተጋነነ ነው በማለት መቃወም መጀመራቸውን ቀደም ብለን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

http://amharic.abbaymedia.com/archives/32468
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2143
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests