ሙሉውን ይከታተሉ፡፡ የዛሬ 6 አመት አካባቢ ስካይ ላይን ከጉዳኞቸ ጋር ስንጠጣ ( ምሽት ነበር) መስፍን ኦልዲስ ( የንጊሊዝኛ ዘፋኙ) ሚኒልክ ሌሎችም ነበሩ ይመስለኛል በጣም ሃሪፍ ምሽት ነበር፡፡ እኔና ዶክተር በላይ ሃብተየሱስ ሌሎችም ሆነን ስንጨፍር ነአምን ካንዲት ወጣት ጋር አብሮ ያብዳል፣ ይጨፍራል፣ ሁላችንም ሞቅታ ላይ ነበርን፡፡ ነእምን እኔን አያውቀኝም እኔና ዶክተር በላይ ግን እናውቃዋለን፡፡ ዶክተር በላይ የሚዲያ ሰው ስለሆነ ( በዚህም ላይ የሮያል ቤተሰብ ) መሆኑን ስለሚናገርም ስለሚታወቅም ቡዙዎች ራሱም ነአምንም ጭምር ያውቀዋል፡፡ በጨዋታ ላይ እንዳለን እንዱ ለምን ከዚህ የወያነ ደጋፊ ጋር አብረህ ትጫወታለህ አለኝ፡፡ ወንደሜ ነው አልኩት እይኔን እፍጥጨ፡፡ መልክቱ ገባው መሰለኝ ገላምጦኝ ሄደ፡፡ ትንሽ እንደተጫወትን ይሄን ካለኝና ክሌሎቹም ጋር ሌላውን ትተን ጨዋታው ደራ፡፡ በዝህ መአል ነአምን ወደ ሽንት ቤት ሲሄድ ባጠገባችን ሲያልፍ ከኔ ጎን የነበረው ጠራውና ነፍሴ! አንበሳው ! አለውና ሰላምታ ሰጠው፡፡ ሰውየው ሞቅ ብሎታል፡፡ እኔንና ዶክተር በላይን ሰላም አላለንም፡፡ ይሄን ታውቀዋለህ አለኝ አዎ ነአምን እይደለም እንዴ? እልኩት፡፡ የኢሳት ባለቤት ዋናው እሱ ነው አለኝ፡፡ ወይ ውስኪ ቡዙ ታናግሪያልሽ ብዬ ሳቄ መጥቶ ዝም ብዬ አልፌው ነበር፡፡ እሁን ግን ይሄ ከሆነ ከቡዙ አመታት በሁዋላ ያ ሰውዬ ይሄን ያለበት ሚስጥር ገባኝ ፡፡ ቪዲዮውን ይከታተሉ፡፡
https://youtu.be/ZJMg-nQM99A