መስፍን ኢንዱስትሪያል በውቅሮ ያቋቋመውን ትራክተር መገጣጠሚያ አስመረቀ::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

መስፍን ኢንዱስትሪያል በውቅሮ ያቋቋመውን ትራክተር መገጣጠሚያ አስመረቀ::

Postby ክቡራን » Mon Jul 24, 2017 11:42 am

Image

የኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍተ ሓዱሽ በወቅቱ እንደገለፁት ፋብሪካው በወር 240 ትራክተሮችን የመገጣጠም አቅም አለው ።
”ሶናሊካ” ከተባለው የህንድ ኩባንያ ጋር በመተባበር በፋብሪካው የሚገጣጠሙ ትራክተሮች ከ20 እስከ 110 የፈረስ ጉልበት ያላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
የትግራይ መልሶ ማቋቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍን በበኩላቸው “በትግራይ መልሶ ማቋቋም ስር የሚገኙ ተቋማት ሀገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት እየደገፉ ናቸው” ብለዋል።
ተቋማቱ ከተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በሚፈጥሩት ትብብር የዲፕሎማሲ ግንኙነቱ ለማጎልበት አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።
በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኪሮስ ቢተው በበኩላቸው በኩባንያው የተቋቋመው የትራክተር መገጣጠሚያ የክልሉ አርሶ አደሮችን የቆየ ዘመናዊ ማረሻ ይቅረብልን ጥያቄን የሚመልስ መሆኑን ጠቁመዋል።
የክልሉ የእርሻ መሬት በትራክተር በጥልቀት ከታረሰ እርጥበት በመጨመር እስከ 30 በመቶ የምርት ጭማሪ ማግኘት እንደሚቻል በጥናት መረጋገጡንም ጠቁመዋል።
በክልሉ በግብርና ስራ የተሰማሩት ባለሃብቶችም ከ40 ዓመታት በፊት የያዙዋቸው ትራከተሮች በመለዋወጫ እጦትና በእርጅና የተፈለገውን አገልግሎት ሳይሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
መገጣጠሚያ ፋብሪካው የዘርፉን ችግር ለመፍታት አስተዋፆ እንደሚኖረው ተናግረዋል ።
በክልሉ በግብርና ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሀብቶች መካከል አቶ ተወልዴ ሃይሉ በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም የእርሻ ትራክተሮች ለመግዛት ከሑመራ ወደ አዲስ አበባና ወደ ሱዳን በመሄድ የጊዜና የገንዘብ ብክነት ያጋጥም እንደነበር አስታውሰዋል።
የትራክተር መገጣጠሚያው በአቅራቢያቸው መቋቋም ብክነቱን በማሰቀረት የእርሻ ስራቸውን በአግባቡ ለማካሄድ አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል። source ( ENA)

ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests