ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Jul 28, 2017 1:37 pm

ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ላለፉት 9 ወራት በመላው ኢትዮጵያ ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳላደርግ አግዶኛል በማለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ::ስለሆነም ከሐምሌ 27 በኋላ ይህ አዋጅ መራዘም እንደሌለበት አሰጠነቀቀ::በተጨማሪም በነሐሴ ወር መጀመርያ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የመጥራት ዕቅድ እንዳለው አሳውቋል::ፍቃዱንም የሚጠይቀው ኮማንድ ፖስቱን ሳይሆን በደንቡ መሠረት የአዲስ አበባን ማዘጋጃ ቤት እንደሆነ ገልጿል::መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያራዝም ከሆነ ግን ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይጠይቅ ሰልፉን መጥራቱ እንደማይቀር አሳስቧል::መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ እና የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊው ናቸው::ሰማያዊ ፓርቲ የጎሳ ፖለቲካን አጥበቀው ከሚቃወሙና በኢትዮጵያውነት ሥም ከሚንቀሳቀሱ ጥቂት ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Aug 04, 2017 2:11 pm

እንግዲህ ዛሬ ይፋ እንደሆነው የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላራዘመውም፡፡ስለዚህም ሰማያዊ ፓርቲ 'ሕግ' መጣስ ሳያስፈልገው ሰልፉን መጥራት ይችላል ማለት ነው፡፡በሚቀጥለው ሳምንት የከተማውን አስተዳደር ፈቃድ ጠይቆ ሰልፉን ማካሄድ ይችል ይሆን?ፈቃድ ካላገኘስ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 05, 2017 7:22 pm

እንደምናስታውሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አልተራዘመም::በዚህም ምክንያት ሰማያዊ ፓርቲ አደርገዋለ ያለውን ሰልፍ ሳያደርግ ቀርቷል::በፓርቲውና በገዢው ግንባር መሐል የነበረው ፍጥጫ ግን ተባብሶ ቀጥሏል::ምክንያቱም ሰማያዊ ፓርቲ መስከረም28 ቀን መስቀል አደባባይ ላይ ለማካሄድ ያቀደው ሰልፍ በሕግ መሠረት ከከተማው አስተዳደር የጠየቀውን ፈቃድ ባለማግ ኘቱ(ስለተከለከለ)ነው::ፓርቲው ክልከላውን ፍርድ ቤት እንደሚያቀርበው አሳውቋል::ፍርድ ቤቱስ አቤቱታውን ካልተቀበለ የፓርቲው ቀጣይ እርምጃ ምን ይሆን?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Oct 06, 2017 10:20 pm

ዘርዐይ ደረስ

የሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊና ተገቢ እርምጃዎች እየወሰደ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ዋናው ነገር የፓርቲዎችን ውህደትና የአንድነት ግንባር በማጠናከር እንደደቡብ አፍሪካው ANC የአፍሪካዊያን ህብረት የወያኔን የግፍ አፓርታይድ አገዛዝ ለመጣል በሚገባ መቀናጀትና ልዩነቶችን በማቻቻል መተባበር በጣም ያስፈልጋል፡፡
ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ላለፉት 9 ወራት በመላው ኢትዮጵያ ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳላደርግ አግዶኛል በማለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ::ስለሆነም ከሐምሌ 27 በኋላ ይህ አዋጅ መራዘም እንደሌለበት አሰጠነቀቀ::በተጨማሪም በነሐሴ ወር መጀመርያ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የመጥራት ዕቅድ እንዳለው አሳውቋል::ፍቃዱንም የሚጠይቀው ኮማንድ ፖስቱን ሳይሆን በደንቡ መሠረት የአዲስ አበባን ማዘጋጃ ቤት እንደሆነ ገልጿል::መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያራዝም ከሆነ ግን ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይጠይቅ ሰልፉን መጥራቱ እንደማይቀር አሳስቧል::መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ እና የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊው ናቸው::ሰማያዊ ፓርቲ የጎሳ ፖለቲካን አጥበቀው ከሚቃወሙና በኢትዮጵያውነት ሥም ከሚንቀሳቀሱ ጥቂት ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል::
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1514
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Oct 17, 2017 9:46 am

ሰላም እሰፋ ማሩ:-
እኔ በበኩሌ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች አንድነት ይመጣል ብዬ ተስፋ አላደርግም::እንዳልከው ደቡብ አፍሪካውያን የተለያዩ ችግሮች ቢኖርባቸውም ቢያንስ ነባር ነዋሪዎቹ አንጻራዊ አንድነት አላቸው::ወደ እኛ አገር ስንመጣ ግን ብዙዎቹን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ የሚያደርጋቸው ገዢውን ኃይል መቃወማቸው ብቻ ነው::ታሪክንም ወደ ኋላ ዞር ብለን ብንቃኝ ተመሳሳይ ነገር ነው የነበረው::ለምሳሌም የኢህአፓና የመኢሶን ታጋዮች የጻፏቸውን ስናነብና በየጊዜውም የሚሰጧቸውን ቃለ መጠይቆች ስናዳምጥ የምንረዳው እውነታ ይህ ነው::ሁለቱም የግራ ኃይሎች(ሶሺያሊስቶች) የሚባሉ ነበሩ::ሁለቱም ንጉሣዊ አገዛዝን ይቃወሙ ነበሩ::ሁለቱም ለጭቁኑ ህዝብ በተለይም ለአርሶ አደሩና ለወዛደሩ(ላብ አደሩ) የቆሙ ነበሩ::ሁለቱም ኢትዮጵያዊነትን አስቀድመው የሚንቀሳቀሱ የነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ህዝባዊ መንግሥት እንዲቋቋም የሚፈልጉ ነበሩ::ስለሆነም ሁለቱም የፖለቲካ ድርጅቶች በበርካታ ጉዳይችተመሳሳይ ዓላማ ቢኖራቸውም ይህን ዓላማ ለማሳካት ምን ማድረግ አለብን በሚለው ጉዳይ ላይ ግን ሳይስማሙ ቀርተው የተፈጠረው እልቂት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቶሎ የማይሽር ጠባሳ ጥሎ አልፏል::
አሁንም የምናየው ተመሳሳይ ነገር ነው::የህወሃት/ኢህአዴግን ሥርዓት የሚቃወሙ በርካታ ድርጅቶች እንዳሉ የታወቀ ቢሆንም አንድ ሆኖ ከመታገል ይልቅ እንዲያውም እርስ በእርስ እየተናከሱ ለሥርዓቱ ፋታ ሲሰጡ ነው የምናየው::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Oct 18, 2017 12:24 am

ዘርዐይ ደረስ
በመሰረታዊ አባባልህ ላይ እስማማለሁ ሆኖም ግን አሁንም ለመስተካከል ጊዜው አልረፈደም፡፡በየከተማው የተቃዋሚዎች ልዩነት በተከታዮቻቸው ሲስተጋባ የማይ ሲሆን አንዳንድ አሰታዋይ ሃገር ወዳዶች ግን በሚዛናዊነት ሁሉንም የተገፉ ወገኖች ወደአንድነት የሚያመጣ ሃሳብ ሲሰነዝሩ ስለማይ በተባበረ የህዝብ ትግል የወያኔ የግፍ አገዛዝ እንደሚሚወገድ በእርግጥ አምናለሁ፡፡እስኪ ሁላችንም መለስተኛ ልዩነቶችን ወደጎን በማስቀመጥ ህዝባችን እንደሌሎቹ ሃገሮች ፍትህና ዲሞክራሲ በሚቀዳጅበት አቅጣጫ እንተባበር፡፡
ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም እሰፋ ማሩ:-
እኔ በበኩሌ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች አንድነት ይመጣል ብዬ ተስፋ አላደርግም::እንዳልከው ደቡብ አፍሪካውያን የተለያዩ ችግሮች ቢኖርባቸውም ቢያንስ ነባር ነዋሪዎቹ አንጻራዊ አንድነት አላቸው::ወደ እኛ አገር ስንመጣ ግን ብዙዎቹን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ የሚያደርጋቸው ገዢውን ኃይል መቃወማቸው ብቻ ነው::ታሪክንም ወደ ኋላ ዞር ብለን ብንቃኝ ተመሳሳይ ነገር ነው የነበረው::ለምሳሌም የኢህአፓና የመኢሶን ታጋዮች የጻፏቸውን ስናነብና በየጊዜውም የሚሰጧቸውን ቃለ መጠይቆች ስናዳምጥ የምንረዳው እውነታ ይህ ነው::ሁለቱም የግራ ኃይሎች(ሶሺያሊስቶች) የሚባሉ ነበሩ::ሁለቱም ንጉሣዊ አገዛዝን ይቃወሙ ነበሩ::ሁለቱም ለጭቁኑ ህዝብ በተለይም ለአርሶ አደሩና ለወዛደሩ(ላብ አደሩ) የቆሙ ነበሩ::ሁለቱም ኢትዮጵያዊነትን አስቀድመው የሚንቀሳቀሱ የነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ህዝባዊ መንግሥት እንዲቋቋም የሚፈልጉ ነበሩ::ስለሆነም ሁለቱም የፖለቲካ ድርጅቶች በበርካታ ጉዳይችተመሳሳይ ዓላማ ቢኖራቸውም ይህን ዓላማ ለማሳካት ምን ማድረግ አለብን በሚለው ጉዳይ ላይ ግን ሳይስማሙ ቀርተው የተፈጠረው እልቂት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቶሎ የማይሽር ጠባሳ ጥሎ አልፏል::
አሁንም የምናየው ተመሳሳይ ነገር ነው::የህወሃት/ኢህአዴግን ሥርዓት የሚቃወሙ በርካታ ድርጅቶች እንዳሉ የታወቀ ቢሆንም አንድ ሆኖ ከመታገል ይልቅ እንዲያውም እርስ በእርስ እየተናከሱ ለሥርዓቱ ፋታ ሲሰጡ ነው የምናየው::
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1514
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 25, 2017 9:29 pm

ሰማያዊ ፓርቲ ስትራቴጂውን በመቀየር ለቀጣዩ እሁድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል::ስብሰባውንም ለማካሔድ የሚያስፈልገውን ፈቃድ ማግኘቱን የድርጅቱ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አበበ አካሉ ገልጸዋል::የስብሰባው ቦታም ሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘው የመብራት ሃይል ክበብ አዳራሽ ከቀኑ 7 ሠዓት ተኩል ጀምሮ መሆኑ ታውቋል::በተጨማሪም ለጥቅምት 26 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውን አቶ አበበ ገልጸዋል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Apr 29, 2018 8:39 pm

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሺዋስ አየለ አቢይ አሕመድ እንደተመረጠ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ‘’ንግግራቸው ተስፋ የሚሰጥ ነው’’ብሎ እንደነበር ይታወሳል።የአዲሱ ካቢኔ አባላት ከታወቁ በኋላ ግን የሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ እየተሸረሸረ መሆኑ እየተሰማ ነው።ከዚህ በተጨማሪ አዲሱ የኦህዴድ/ኢህአዲግ ጠቅላይ ሚኒስትር ከወራት በፊት የተጀመረው ድርድር ላይ አንሳተፍም ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሁን እንዲሳተፉ ማሳሰቡ ቅሬታ መፍጠሩ ታውቋል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰማያዊ ፓርቲ ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jun 16, 2018 2:31 pm

ሰማያዊ ፓርቲ በነገው እለት ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በአምባሳደር ቴያትር የሚያካሂደውን ስብሰባ እንዲታደሙለት አባላቱና የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል ለሚሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ጥሪ አቅርቧል።በስብሰባውም ላይ በቅርቡ ከእስር የተፈታው አንዱዓለም አራጌ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያቀርብ ታውቋል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests