ሰላማት ካዶ ገነት...ዋርካ ያለምንም proxy አዲስ አበባ ውስጥ ትከፈታለች..

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰላማት ካዶ ገነት...ዋርካ ያለምንም proxy አዲስ አበባ ውስጥ ትከፈታለች..

Postby ክቡራን » Tue Aug 01, 2017 12:22 pm

አድሚን በሚል ራሳቸውን የካቡ ዘበኞች አድላዊ ስራ ሲሰሩና ውሸት ነገር ሲጻፍ እያዩ እንዳላዩ በመምሰል ሲያልፉ አንድን ብሄር በተለይ ትግራዋይነት ላይ ስድብና ጥላቻ ሲዘመር እንዳላዩ በመምሰል ዝም ሲሉ ስሜታችንን ቅሬታችንን በይፋ ስንናገርና አንዳንዴም ድህረ ገጻቸውን እንዲያስተካክሉ ስንመክር ዛሬም ኩስ ሜዳን ና አሰፋ ማሩን የመሰሉ ውሸተኞች መረን የለቀቀ የውሸት ዜና ሲለቁ እንዳላየና እንዳልሰማ ለመምሰል ሲሞክሩና እነሱ ጆሮ ዳቦ ልበስ ቢሉና የጥላቻ ከበሮ እያሰደለቁ ብናይም ቅሉ ዋርካን ግን አዶ ገነት ላይ አቦል ቡና እየጠጣን እናነባታለን፡፡ አራት ኪሎ ጆሊ ባር ስር የደራሲው ማስታውሻ መጽሃፍ ይነባባል፡፡ ህይወት ዛሬም በመዝወርዋ ትዞራለች፡፡ ኢትዮጵያን ያሉ ሃቀኛ ኢህአደጋወያን ደሞ ጉበኞችና ሙሰኞችን የሚያድኑባት አዶ ገነት እየተወሰደ ባለው ርምጃ እሷም ሰሞኑን አቦል ቡና እየጠጣች ነው ፡፡ የንግድ ቤቶች በሙሉ ክፍት ናቸው፡፡ የተዘጋ ሱቅ የለም፡፡ የተዘጋው የነኩስ ሜዳ ጉሮሮ ብቻ ነው፡፡ ሎል፡፡ ያም ሆኖ ግን መንግስት ዛሬም የታክስን ጉዳይ ሊያስብባብትና እንደገና ሪቫይዝ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ አብዛኛው ህዝብ በታክስ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለው፡፡ ቅሬታውን ግን አየስራ የቀን ተቀን ህይወቱን እየኖረ የዳቦ መግዣውን ሳንቲም እየያዘ በመግለጽ ላይ ነው፡፡ የተዘጉ ድርጅቶች የሉም፡፡
ክቡራን ነኝ ከቱስሪት ሆቴል አራት ኪሎ፡፡ ከነ ጥላዬ ሰፈር ፡፡ ሎል፡፡
የሰሙኑን የሙሰኝነት ዘመቻ በተመለከተ የኢትዮጵያው ፈርስት ቤን ይህን ይልናል፡፡
"...ብረት ምጣዱ ግሏል ..አሁን ይለያል.."
ያዳምጡ፡፡ ሰላም ያገናኘን፡፡

https://youtu.be/66DWBeXeU_8
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7962
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 9 guests