ደብረጺዮንና ደመቀ መኮንን መደባደባቸው ተነገረ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ደብረጺዮንና ደመቀ መኮንን መደባደባቸው ተነገረ!

Postby ኳስሜዳ » Thu Aug 24, 2017 3:20 pm

በም/ል ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን እና በህወሃቱ ም/ል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ያለው አለመግባባት ወደ ሃይል እርምጃ ማምራቱን የኢሳት ምንጮች ገልጻዋል።

ባለፈው ሰኞ በረከት ስምዖን፣ ሽፈራው ሽጉጤና ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተገኝተው በነበረበት ወቅት፣ “ደብረጺዮን እኔን አያዘኝም ብለህ ለ ሽፈራው ተናግረሃል፣ እንዴት እንዲህ ትላለህ?” ብሎ ደብረጺዮን ጥያቄ ሲያቀርብ፣ ደመቀም፣ “ አዎ ብያለሁ።

እኔ እኮ ም/ል ጠ/ሚኒስትር ነኝ፣ መዋቅሩን አታውቀውም እንዴ? ” በማለት መልስ ሲሰጠው፣ ጭቅጭቁና ንትረኩ እየጨመረ መምጣቱን፣ በመሃሉ ደብረጺዮን በስሜት ሆኖ ከመቀመጫው ተነስቶ በ ደመቀ ላይ እጁን መሰንዘሩን፣ ደመቀም ራሱን ለመከላከልና መልሶ ለማጥቃት ሲሞክር በረከትና ሽፈራው መሃል ላይ በመግባት መገላገላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

በደብረጺዮን ድርጊት የተበሳጨው ደመቀ “ አሁንም፣ ወደፊትም አንተ አዘኸኝ የምሰራው ምንም ስራ የለም፣ አይኖርምም” በማለት ደጋግሞ የተናገረ ሲሆን፣ እነ አቶ በረከት ገላግለው ሁለቱ ባለስልጣናት እንዲለያዩ አድርገዋል።

የህወሃት እና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ግጭት በህወሃትና በብአዴን መካከለኛ አመራሮች መካከል የሚታየው ልዩነት ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እየተሸጋገረ መምጣቱን የሚያመላክት ተደርጎ ተወስዷል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2143
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: ደብረጺዮንና ደመቀ መኮንን መደባደባቸው ተነገረ!

Postby ጌታህ » Fri Aug 25, 2017 11:33 am

ቅቅቅቅቅቅቅቅ.... ዶንኪው እዚያ ሆነሸ ገላጋይ ነበርሸ አሉ !!!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

ኳስሜዳ wrote:በም/ል ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን እና በህወሃቱ ም/ል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ያለው አለመግባባት ወደ ሃይል እርምጃ ማምራቱን የኢሳት ምንጮች ገልጻዋል።

ባለፈው ሰኞ በረከት ስምዖን፣ ሽፈራው ሽጉጤና ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተገኝተው በነበረበት ወቅት፣ “ደብረጺዮን እኔን አያዘኝም ብለህ ለ ሽፈራው ተናግረሃል፣ እንዴት እንዲህ ትላለህ?” ብሎ ደብረጺዮን ጥያቄ ሲያቀርብ፣ ደመቀም፣ “ አዎ ብያለሁ።

እኔ እኮ ም/ል ጠ/ሚኒስትር ነኝ፣ መዋቅሩን አታውቀውም እንዴ? ” በማለት መልስ ሲሰጠው፣ ጭቅጭቁና ንትረኩ እየጨመረ መምጣቱን፣ በመሃሉ ደብረጺዮን በስሜት ሆኖ ከመቀመጫው ተነስቶ በ ደመቀ ላይ እጁን መሰንዘሩን፣ ደመቀም ራሱን ለመከላከልና መልሶ ለማጥቃት ሲሞክር በረከትና ሽፈራው መሃል ላይ በመግባት መገላገላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

በደብረጺዮን ድርጊት የተበሳጨው ደመቀ “ አሁንም፣ ወደፊትም አንተ አዘኸኝ የምሰራው ምንም ስራ የለም፣ አይኖርምም” በማለት ደጋግሞ የተናገረ ሲሆን፣ እነ አቶ በረከት ገላግለው ሁለቱ ባለስልጣናት እንዲለያዩ አድርገዋል።

የህወሃት እና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ግጭት በህወሃትና በብአዴን መካከለኛ አመራሮች መካከል የሚታየው ልዩነት ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እየተሸጋገረ መምጣቱን የሚያመላክት ተደርጎ ተወስዷል።
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests