የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ!

Postby ኳስሜዳ » Sat Aug 26, 2017 6:26 pm

ህወሓት በትግራይ ላይ የራሱን አቋም እንዲወስድ ተመክሯል

በኢትዮጵያ ያለማቋረጥ ሲካሄድ ከቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ አኳያ በህወሓት የደህንነት ክፍል የተሰበሰበው መረጃ፤ አሁን ካለው የተቃውሞ ንቅናቄ የተነሳ የኢህአዴግ የገጠር መዋቀር በኦሮሚያና በከፊል የአማራ ክልሎች ሊፈርስ እንደሚችል አስታወቀ። ከሁኔታው አሳሳቢነት የተነሳ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች ቢኖሩም ህወሓት ትግራይን አስመልክቶ የራሱን አቋም እንዲወስድ ሃሳብ ተሰጥቶታል።

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ተስኖት ይገኛል። በተለይ “ባለራዕዩ መሪውን” ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ካስፈነጠረው ወዲህ ግምባሩ በአንድ መጓዝ፣ በአንድ መስማማት፣ በአንድ ማሰብ አቅቶት በተቃዋሚው መዳከምና በአንጋሾቹ አለሁ ባይነት ብቻ በሥልጣን መንበር ላይ ሲንገታገት ቆቷል። ሕዝብ ፊቱን ካዞረበት ቢቆይም በተለይ ትውልድ ካመጸበት ወዲህ ግን የአገዛዙ ኃይል እንደ ሹራብ ክር መጎልጎል ጀምሯል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራና በኦሮሞ ቦታዎች የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ህወሓት በኢህአዴግ ሥም እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራቸው ብአዴንና ኦህዴድ “ሕዝባቸውን” መምራት የተሳናቸው መሆኑን ያስመሰከረ ሆኗል። የእነዚህ ሁለት ድርጅቶች የበታች አመራሮች መክዳት በስለላና በጥርነፋ ሁሉንም “ልክ አስገባለሁ” እያለ የሚፎክረውን ህወሓት ከራሱ የውስጥ ችግር ጋር ተዳምሮ የማይለቅ ራስ ምታት ሆኖበታል። እንደ አንዳንዶች አገላለጽ ሁለቱን ድርጅቶች አራቱም ጎማው ወልቆ መንገድ ዳር ከቆመ መኪና ጋር ያመሳስሏቸዋል።

የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተጀመረውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሁኔታውን በዘገበበት ወቅት ስለ ኦህዴድ መክዳት ይህንን ብሎ ነበር፤

ሳምንታት ያስቆጠረውና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ምክንያት በማድረግ የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመጠኑም ሆነ በዓይነቱ ልዩ እየሆነ መሄዱ ኦህዴድ ኢህአዴግን የመክዳቱ ማስረጃ ነው ሲሉ በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ ለጎልጉል መረጃ የሚያቀብሉ አመራር አስታውቀዋል።

“በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ፤ ስለላ፤ ሕዝባዊ አደረጃጀት፤ ቁጥጥር፤ … መዋቅሮችን ሁሉ አልፎ ይህንን ያህል ሕዝብ ያለአንዳች ከልካይ መውጣቱ አገዛዙ ሕዝቡን ለመጠርነፍ የተጠቀመበት አሠራር መልሶ ራሱን እየጠረነፈው እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ታማኝ ተብሎ የተቀመጠው ካድሬም ሆነ የጥርነፋው መዋቅር ሕዝቡን ሊያስቆም አለመቻሉ የኦህዴድ እምቢተኛነትና ለአገዛዙ ድጋፍና እገዛ ከማድረግ ይልቅ ከሕዝቡ ጋር ለመቆሙ እንደ ዓይነተኛ ማስረጃ ይጠቀሳል።

http://www.goolgule.com/tplf-eprdf-rura ... integrate/
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ!

Postby ጌታህ » Sun Aug 27, 2017 7:40 am

ቅቅቅቅቅቅቅ...ዶንኪው አንተም አልፈረሰክም !!!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

ኳስሜዳ wrote:ህወሓት በትግራይ ላይ የራሱን አቋም እንዲወስድ ተመክሯል

በኢትዮጵያ ያለማቋረጥ ሲካሄድ ከቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ አኳያ በህወሓት የደህንነት ክፍል የተሰበሰበው መረጃ፤ አሁን ካለው የተቃውሞ ንቅናቄ የተነሳ የኢህአዴግ የገጠር መዋቀር በኦሮሚያና በከፊል የአማራ ክልሎች ሊፈርስ እንደሚችል አስታወቀ። ከሁኔታው አሳሳቢነት የተነሳ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች ቢኖሩም ህወሓት ትግራይን አስመልክቶ የራሱን አቋም እንዲወስድ ሃሳብ ተሰጥቶታል።

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ተስኖት ይገኛል። በተለይ “ባለራዕዩ መሪውን” ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ካስፈነጠረው ወዲህ ግምባሩ በአንድ መጓዝ፣ በአንድ መስማማት፣ በአንድ ማሰብ አቅቶት በተቃዋሚው መዳከምና በአንጋሾቹ አለሁ ባይነት ብቻ በሥልጣን መንበር ላይ ሲንገታገት ቆቷል። ሕዝብ ፊቱን ካዞረበት ቢቆይም በተለይ ትውልድ ካመጸበት ወዲህ ግን የአገዛዙ ኃይል እንደ ሹራብ ክር መጎልጎል ጀምሯል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራና በኦሮሞ ቦታዎች የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ህወሓት በኢህአዴግ ሥም እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራቸው ብአዴንና ኦህዴድ “ሕዝባቸውን” መምራት የተሳናቸው መሆኑን ያስመሰከረ ሆኗል። የእነዚህ ሁለት ድርጅቶች የበታች አመራሮች መክዳት በስለላና በጥርነፋ ሁሉንም “ልክ አስገባለሁ” እያለ የሚፎክረውን ህወሓት ከራሱ የውስጥ ችግር ጋር ተዳምሮ የማይለቅ ራስ ምታት ሆኖበታል። እንደ አንዳንዶች አገላለጽ ሁለቱን ድርጅቶች አራቱም ጎማው ወልቆ መንገድ ዳር ከቆመ መኪና ጋር ያመሳስሏቸዋል።

የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተጀመረውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሁኔታውን በዘገበበት ወቅት ስለ ኦህዴድ መክዳት ይህንን ብሎ ነበር፤

ሳምንታት ያስቆጠረውና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ምክንያት በማድረግ የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመጠኑም ሆነ በዓይነቱ ልዩ እየሆነ መሄዱ ኦህዴድ ኢህአዴግን የመክዳቱ ማስረጃ ነው ሲሉ በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ ለጎልጉል መረጃ የሚያቀብሉ አመራር አስታውቀዋል።

“በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ፤ ስለላ፤ ሕዝባዊ አደረጃጀት፤ ቁጥጥር፤ … መዋቅሮችን ሁሉ አልፎ ይህንን ያህል ሕዝብ ያለአንዳች ከልካይ መውጣቱ አገዛዙ ሕዝቡን ለመጠርነፍ የተጠቀመበት አሠራር መልሶ ራሱን እየጠረነፈው እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ታማኝ ተብሎ የተቀመጠው ካድሬም ሆነ የጥርነፋው መዋቅር ሕዝቡን ሊያስቆም አለመቻሉ የኦህዴድ እምቢተኛነትና ለአገዛዙ ድጋፍና እገዛ ከማድረግ ይልቅ ከሕዝቡ ጋር ለመቆሙ እንደ ዓይነተኛ ማስረጃ ይጠቀሳል።

http://www.goolgule.com/tplf-eprdf-rura ... integrate/
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron