አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ወያኔ ፍርድቤት በኬንያ አይን

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ወያኔ ፍርድቤት በኬንያ አይን

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Aug 29, 2017 4:52 pm

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሂደት በጀርመን ሬድዮ የቀረበ ሲሆን አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ለሆነ የኢትዮጲያ ፍርድ ቤትን የኬንያ ያስንቃል፡፡የኢትዮጲያ ፍርድቤት ዳኛ ወያኔ ምስክሩ ወያኔ አሳሪ ወያኔ ምርጫ ቦርድ ወያኔ የፍርድ ሂደት ወያኔ ነው፡፡በኬንያ ግን በገለልተኛነት ፍትህ ማካሄድዋ ጎረቤት ኢትዮጲያ ከፍተኛ የፍትህ ውድቀት እንዳለባት ያሳያል፡፡
http://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8A%AC ... -11646-xml
--------------===================-----------------------------------------------------
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በራይላ ኦዲንጋ የሚመራው የተቃዋሚዎች ጥምረት ያቀረበውን አቤቱታ ተቀብሏል። ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ የገዢና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች በተገኙበት ምርመራ እንዲካሔድ ፈቃድ ሰጥቷል።
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ኮሚሽኑን የመረጃ ማስቀመጫ ሰንዱቅ እና ለድምፅ ቆጠራ ግልጋሎት ላይ የዋሉ መሳሪያዎች እንዲመለከቱ/እንዲፈትሹ ፈቃድ ሰጥቷል። ውሳኔው የተላለፈው ራይላ ኦዲንጋ የሚመሩት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ነው። በውሳኔው ላይ ማንም አስተያየት መስጠት አይችልም። የምርጫ ኮሚሽኑ ባለሥልጣናት ባለፈው ወር በተካሔደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኬንያታ በ1.4 ሚሊዮን የድምፅ ብልጫ አሸንፈዋል ማለታቸው አይዘነጋም። ውጤቱን አንቀበልም ያሉ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ጠንካራ ይዞታቸውን እንደሆኑ በሚነገርላቸው አካባቢዎች የተበታተነ ተቃውሞ አድርገዋል። ከምርጫ ጋር በተገናኘ ኹከት ቢያንስ 28 ሰዎች ተገድለዋል። አብዛኞቹ የተገደሉት ደግሞ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት እንደሆነ ይነገራል። ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የድኅረ ምርጫ ኹከት ለማያጣት ኬንያ ምን ማለት ይሆን?
ፍቅረ ማርያም መኮንን
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: JohnyPeva and 4 guests