የፀረ ሙስና ዘመቻው ተቋርጧል!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የፀረ ሙስና ዘመቻው ተቋርጧል!

Postby ኳስሜዳ » Wed Aug 30, 2017 7:29 pm

የኢህአዴግ የፀረ-ሙስና ዘመቻ በድንገት ተቋርጧል። በተለይም ዘመቻው ለምን በሙስና የሚጠረጠሩ ትላልቅ ሹማምንትን እንዳላየ ያልፋል? የሚለው የህዝብ ጥያቄ በፓርቲው አካባቢ በስፋት መነሳቱ በደህንነት መስሪያ ቤቱና በጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ መካከል የዝግ ውይይት እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ መረጃ ይዤባቸዋለሁ ያላቸውን የተወሰኑ ባለስልጣናት በስም ጠቅሶ ለአቶ ሀይለማርያም ሹክ ብሏቸዋል።

ተጠርጣሪ ባለስልጣናቱን ይዞ ማሰር ለፓርቲውም ሆነ ለሀገሪቱ የሚያስከትለውን ትርምስ ለማስቀረት ጉዳዩ ከህግ ይልቅ በፖለቲካዊ መንገድ ቢፈታ ይሻላል የሚል ውሳኔ ተደርሶበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተጠርጣሪ ባለስልጣናቱ ጋር ተመካክረው የተወሰደ እርምጃን ለህዝብ ይፋ ቢያደርጉ የተሻለ መሆኑን ተመክረዋል። እስካሁን ጠሚሩ የተባለውን ምክክር ስለማድረጋቸው የታወቀ ነገር የለም። ለሙስና ፖለቲካዊ መፍትሄ ማስፈለጉን ግን ለካቢኔያቸው ተናግረዋል። የሙስና ዘመቻው ባለሀብቶችን ክፉኛ ማስደንገጡና አንዳንዶች ከሀገር እንዲሸሹ ማድረጉ ያሳሰበው ኢህአዴግ ዘመቻውን ጋብ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሎ ማመኑን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ።
Image
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: የፀረ ሙስና ዘመቻው ተቋርጧል!

Postby ጌታህ » Thu Aug 31, 2017 4:05 am

ቅቅቅቅቅቅ...ዶንኪው ቀልዱን ትተሸ የአድማው ውጤት ና ዜና ለምን ቀዘቀዘ....እገረ መንገድሸንም ከጀገናው ባለ ራእዮ የኢትዮጵያ መሪያችን ጋር ፎቶ የተነሳው ማን እንደሆነ ብታጫውተን ፈልገን እንሸልመዋልውን...አካባቢው ሰፈራችን ይመሰላል !!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

ኳስሜዳ wrote:የኢህአዴግ የፀረ-ሙስና ዘመቻ በድንገት ተቋርጧል። በተለይም ዘመቻው ለምን በሙስና የሚጠረጠሩ ትላልቅ ሹማምንትን እንዳላየ ያልፋል? የሚለው የህዝብ ጥያቄ በፓርቲው አካባቢ በስፋት መነሳቱ በደህንነት መስሪያ ቤቱና በጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ መካከል የዝግ ውይይት እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ መረጃ ይዤባቸዋለሁ ያላቸውን የተወሰኑ ባለስልጣናት በስም ጠቅሶ ለአቶ ሀይለማርያም ሹክ ብሏቸዋል።

ተጠርጣሪ ባለስልጣናቱን ይዞ ማሰር ለፓርቲውም ሆነ ለሀገሪቱ የሚያስከትለውን ትርምስ ለማስቀረት ጉዳዩ ከህግ ይልቅ በፖለቲካዊ መንገድ ቢፈታ ይሻላል የሚል ውሳኔ ተደርሶበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተጠርጣሪ ባለስልጣናቱ ጋር ተመካክረው የተወሰደ እርምጃን ለህዝብ ይፋ ቢያደርጉ የተሻለ መሆኑን ተመክረዋል። እስካሁን ጠሚሩ የተባለውን ምክክር ስለማድረጋቸው የታወቀ ነገር የለም። ለሙስና ፖለቲካዊ መፍትሄ ማስፈለጉን ግን ለካቢኔያቸው ተናግረዋል። የሙስና ዘመቻው ባለሀብቶችን ክፉኛ ማስደንገጡና አንዳንዶች ከሀገር እንዲሸሹ ማድረጉ ያሳሰበው ኢህአዴግ ዘመቻውን ጋብ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሎ ማመኑን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ።
Image
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests