ወያኔና ባንዳዎቹ ያጠፉት ጣና በቅኖቹ መንገዱ ቀና

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔና ባንዳዎቹ ያጠፉት ጣና በቅኖቹ መንገዱ ቀና

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Sep 01, 2017 3:08 pm

የወያኔ የአማራ ጥላቻና ግፍ በህዝቡና በተፈጥሮ ሃብቱ ላይ ጭምር ነው፡፡በጣና ሃይቅ የተስፋፋው አረም እንዲወገድ የአካባቢው ተወላጆች ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ለወያኔ ያደረው የክልሉ መንግስት አንዳች እርምጃ ሳይወስድ ችግሩ በመባባስ ላይ ነው፡፡ የአካባቢው የቁርጥቀን ልጆች ችግሩ ከጀመረበት ከ2011 ጀምሮ በዘመቻ እያቀኑት ነው፡፡ የወያኔ ተለጣፊዎች በቅርቡ ለዚህ ችግር በጥቂቱ ጆሮ የሰጡት በአብዛኛው ለፖለቲካ ፍጆታ የዋለውን የህዳሴ ግድቡን እቅድ ጎጂ መሆኑን ሲረዱት ብቻ ነው፡፡ስለዚህ ከማንም በፊት ለችግሩ ቀድመው የደረሱትን ጀግኖች በርቱ ተበራቱ እንበላቸው ከሃዲ ወያኔ ከወራዳ ባንዶቹ ጋር ይቃጠሉ፡፡በሰሜን ሸዋ ከአመታት በፊት የአካባቢ ተወላጆች ብዙዎቹ ከዳያስፖራ የጤናና ልማት ስራዎች በበጎ ፈቃድ ለመጀመር ሲጥሩ ለወያኔ ያደረ የጊዜው የወያኔ እፈጉባኤ ተብዬ ዳዊት ዮሃንስ ብአዴን በሚባል ተለጣፊ ድርጅቱ ስር ካልሆነ በማለት ለህዝቡ የሚጠቅም ፕሮጀክት መከልከሉ ይታወሳል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=OIGdOxGZzFk
http://welkait.com/?p=8510
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ወያኔና ባንዳዎቹ ያጠፉት ጣና በቅኖቹ መንገዱ ቀና

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Sep 07, 2017 4:19 pm

የአማራ ክልል የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ፌደራል መንግስቱ ድጋፍ እያደረገልኝ አይደለም አለ
September 7, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
የአማራ ክልል የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ፌደራል መንግስቱ ድጋፍ እያደረገልኝ አይደለም አለ
BBN – በጣና ኃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ በሚደረገው ርብርብ፣ የፌደራል መንግስቱ ድጋፍ እያደረገለት አለመሆኑን የአማራ ክልል አስታወቀ፡፡ ወንዝ እስከማድረቅ የሚደርሰው አደገኛው የእምቦጭ አረም በጣና ኃይቅ ላይ መታየት የጀመረው ከሶስት ዓመታት በፊት ቢሆንም፣ በወቅቱ እርምጃ ባለመወሰዱ አረሙ አሁን ላይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል፡፡ በዚህም የተነሳ የአካባቢው ማኅበረሰብ በራሱ ተነሳሽነት አረሙን ለማስወገድ ከፍተኛ ትግል እያደረገ ይገኛል፡፡
አረሙን በማስወገድ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት ያለበት በህወሓት የሚመራው የፌደራል መንግስቱ፣ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ድጋፍ አለማድረጉን የአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በላይነህ አየለ ‹‹አሁን በተጨባጭ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ እየታገሉ ያሉት የአካባቢው አርሶ አደሮችና በጣና ሐይቅ ዙሪያ ያሉ ወጣቶች ናቸው፡፡›› ሲሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አክለውም ‹‹በአሁኑ ወቅት በአርሶ አደሮችና በወጣቶች አማካይነት የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት፣ የፌዴራል ተቋማት ለአርሶ አደሮች የእጅ መሣሪያ፣ እንደ ልብ ተንቀሳቅሰው አረሙን ለመከላከልም ምቹ መንገድና ተሽከርካሪ ማመቻቸት ይገባቸው ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡
ጣና በኢትዮጵያ ካሉ ወንዞች በስፋቱ እና በርዝመቱ ትልቅ ኃይቅ ሲሆን፣ በላዩ ላይ የተከሰተው አረም ግን የህልውና አደጋ ፈጥሮበታል፡፡ ይህን ችግር በመወጣት ረገድ በህወሓት የሚመራው መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ የማድረግ ግዴታ ቢኖርበትም፣ ያ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በኃይቁ ላይ የተከሰተውን አረም ለማስወገድ እስካሁን ድረስ እስከ 50 ሺህ የሚሆን የአካባቢው ማኅበረሰብ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ አረሙ የተከሰተው በአምስት ወረዳዎች እና በ18 ቀበሌዎች መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests