የቴዲ አፍሮ አልበም ምርቃት ተከለከለ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የቴዲ አፍሮ አልበም ምርቃት ተከለከለ

Postby ኳስሜዳ » Sun Sep 03, 2017 3:36 pm

ፌደራል ፖሊስ ሂልተን ሆቴል በር ላይ ቆሞ ሳውንድ ሲስተም እንዳይገባ አገደ

ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ምርቃት በፌደራል ፖሊስ ከልካይነት እንዳይካሄድ ተከለከለ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከሂልተን ሆቴል እንደዘገቡት ምርቃቱ እንዲካሄድ ቴዲ አፍሮ ከአንድ ሺ ለማያንሱ ሰዎች ካርድ የበተነ ሲሆን ዝግጅቱ ሊካሄድ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን በመውረር ሳውንድ ሲስተም የተሸከሙ ሰዎችን እንዳያወርዱ አግደዋል:: በኋላም ወደ ፕሮግራሙ አዘጋጆች በመሄድ ፖሊሶቹ ስለዛሬው ዝግጅት ሃላፊነት አንወስድም በማለት ያስፈራሩ ሲሆን በመጨረሻም እንዲሰረዝ ማድረጋቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል::

ፖሊሶቹ ሆን ብለው ወደ ፖሊሶቹ ወደ ሂልተን ሆቴል አስተዳዳሪዎች ጋር በመሄድ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ለሚፈጠረው ማናቸውን ነገሮች ሃላፊነቱን ውሰዱ እንዳሉ የሚጠቅሱት ምንጮቹ ሆቴሉ ሃላፊነቱን አልወስድም በማለቱ ዝግጅቱ ሊሰረዝ መቻሉን ገልጸውልናል::

ትናንት ስለቴዲ አፍሮ አልበም ምርቃት የአዲስ አበባ ኤፍ ኤም ራድዮዎች የሚከተለውን ሲያወሩ ነቨር::

https://www.youtube.com/watch?v=235h1rnxzK0
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: እሰፋ ማሩ and 7 guests