የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት ዱሮ ቀረ !

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት ዱሮ ቀረ !

Postby ኳስሜዳ » Thu Sep 07, 2017 10:31 am

የው ጉ ሚንስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ገብረኪዳን ከ ENN ጋር በቅርቡ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ የመጀመሪያን ክፍል ተከታትዬ ካበቃሁ በኋላ ወደ ሌሎችን የዩትዩብ ትይንቶች ላልፍ ነበር፥ ሆኖም በቃለ ምልልሱ ውስጥ የተሰሙኝ አንዳንድ ነገሮች ስለነበሩ፥ መቼም ክቡር ሚንስትሩ ለሚቀጥሉት ያልታወቁ ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ገጽታ ሆነው እንደሚቆዩ በመገመት፥ በታዘብዃቸው ነገሮች ላይ ሳልከትብ አላልፍም ብዬ መጣጥፍን ዠመርኩት፥ ነው የሚባለው።

በብዙ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እንደ ሁለተኛው የመንግስት ባለሥልጣን ይቆጠራል። በኢትዮጵያም ይህን ሥልጣን ይዘው የነበሩ ሰዎች በዓለም ዓቀፍ መድርክ ከባድ ሚዛን የሚባሉ ነበሩ። ከ1958 ዓ ም ጀምሮ እስከ ደርግ ውድቀት የነበሩትን ብንመለከት ከብርሃኑ ባዬ በስተቀር ሁሉም በለም ዓቀፉ መድረክና በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ታሪክ ላይ የየራሳቸውን አሻራ አስፍረው ያለፉ ናቸው።

1958–1960: ይልማ ደሬሳ
1960–1961: ሐዲስ አለማየሁ
1961–1971: ከተማ ይፍሩ
1971–1974: ሚናሴ ኃይሌ
1974–1977: ክፍሌ ወዳጆ
1977–1983: ፈለቀ ገድለ ጊዮርጊስ
1983–1986: ጎሹ ወልዴ
1986–1989: ብርሃኑ ባዬ
1989–1991: ተስፋዬ ዲንቃ
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አገርን ከውጭ የሚያገናኝ ሰው እንደ መሆኑ ቢያንስ የኢንግሊዝኛ ቋንቋን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል። ዶ/ር ወርቅነህን ከዚህ አንፃር አብረን አንገምግማቸውና እስኪ ብቃታቸውን እንመልከት። አዎ ቃለ ምልልሱ በአማርኛ ሆኖ እንግሊዝኛቸውን እንዴት፥ ትሉ ይሆናል። ጥሩ ጥያቄ ነው። መልሱ ክቡር ሚንስትሩ እንደ ኮሌጅ ጀማሪ በአማርኛ መሃል ኢንግሊዝኛ ይሞጃጅሩ ስለነበር የእንግሊዝኛ ችሎታቸውን እንድመዝን ዕድል ሰጥቶኛል፥ እና ወደ ክቡርነታቸው ቃለ ምልልስ እንሂድ፥

/ አገራችን በአለፉት 15 ዓመት the rising country እየተባለች ትጠራለች. . ./

ባለፉት 15 ዓመታት ዕድገት ያስመዘገበ አገር ከሌለ ክቡርነታቸው ትክክል ይሆናሉ። the የሚለው ብቸኛዋ አገር መሆንዋን የሚያሳይ ስለሆነ፥ ግን ኢትዮጵያ እድገት ያሳየች ብቸኛ አገር ስላልሆነት የዶክተሩ አባባል a rising country በሚል ቢስተካከል ሃሳባቸውን ይገልጽላቸው ነበር።

ሌላ ቦታ ላይ ሶማሊያ ስላለው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲያወሩ

/ሴራዊታችን last longing አይደለም። ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አይደለም/ ይላሉ።

ሊባል የተፈለገው long lasting ነበር። እሱም ቢሆን ረጅም ለማያገለግል ቁሳቁስ እንጂ ሰራዊት ላይ የሚጠቀስ ቃል ኣይደለም።

ዋናው የቋንቋ ችሎታቸውን ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ ዕውቀት ክህሎታቸውን ያጋለጠው ኤርትራን በተመለከተ የሰጡት ምላሽ ነው። (55ተኛው ደቂቃ ) እንዲህ ይላሉ።

/ከጦርነት በኋላ reapproachment መነጋገር ይኖራል።/ ሪአብሮችመንት በማለት ያደምጡታል።

reapproachment የሚባል ኢንግሊዝኛ ቃል ጨርሶ የለም። ዶክተሩ rapprochement የሚባል ቃል ሲባል ሰምተዋል ወይም አንበዋል። በዲፕሎማሲ አደባባይ የሚነገር ቃል ሊሆን ይችላል። ትርጉሙ፥ an agreement reached by opposing groups … ዶክተሩ ቃሉ approach ከሚለው ቃል የሚዛመድ ነው የመሰላቸው። ተሳስተዋል። rapprochement ሲደመጥ ሬፕሮሽሟ ነው።

ወደ መጨረሻ blunder የሚል ቃል ተጠቅመዋል። እሱንም በቦታው የገባ ባለመሁኑ ትርጉሙን የሚያውቁት አይመስለኝም። ባልጠፋ አማርኛ ምን እዚህ ጣጣ ውስጥ አስገባቸው!!!

ይህ በአማርኛ ውስጥ ኢንግሊዝኛ የሞሞዠር አባዜ ብዙ ሰዎች ላይ የሚታይ እንከን ቢሆንም፥ ሳይበዛና ትክክለኛውን ቃል በትክክለኛ የሃሳብ ፍሰትና የውይይት ይዘት ውስጥ እስከገባ ድረስ ችግሩ የጎላ ነው ላይባል ይችላል። በተለይ በከፍተኛ የሥልጣንና የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች የሚጠበቅባቸው የቋንቋ ችሎታ ቢያንስ ከአማካኙ ከፍ ያል ስለሆነ ተገቢውን ሥልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ዛሬ፥ ዓለም በከፍተኛ የሥልጣኔ ደረጃ ላይ በምትገኝበት ወቅት፥ የልዩ ልዩ ነገሮች መለኪያዎቻችን በዚያው መጠን ከፍ ብለዋል። የዛሬው ብርና ከ50 ዓመታት በፊት የነበረው ብር ዋጋ የሚለያየውን ያህል፥ ከ50 ዓመት በፊት የነበረ መንግስት ብቃትና ዛሬ ያለው መንግስት ብቃት ይለያያል። ከ50 ዓመት በፊት መሃይም የምንለው ማንበብና መጻፍ የማይችለውን ነበረ፥ ዛሬ ግን ኢ ሜል፥ ፌስቡክ፥ ዩትዩብ መክፈት የማይችለውን ሰው በመሃይምነት ደረጃ መፈረጅ ተጀምሯል። ዓለም የዱሮዋ አይደለችም፥ አቋቋሟ ብቻ ሳይሆን አነጋገርዋም ተቀይሯል። ስለሆነም አገርን ወክለው ወደ ዓለም የሚወጡ ሰዎች አቋቋማቸውንና አነጋገራቸውን እንደ ዓለሚቱ ማሳመር ይኖርባቸዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም በዓለም ጤና ድርጅት ውድድር ላይ ሶስት ጊዜ እንዲደገምላቸው ያቀረቡት ተማፅኖ በኢንግሊዝኛ ቋንቋ እጥረት እንደነበር አይዘነጋም። እንዲህ ዓይነቱ ተግዳሮት በጽናትና በቆራጥነት የሚወጡት አይደለም። ቦታውን ለሚመጥንና ለሚያውቅበት ሰው መልቀቅ ብቻ ነው የሚያዋጣው።

እነከተማ ይፍሩን፥ ሚናሴ ኃይሌን፥ ጎሹ ወልዴን ሲያስታውሱ፥ ውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት ዱሮ ቀረ አያሰኝም?

ባቢሌ
http://www.satenaw.com/amharic/archives/37384
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት ዱሮ ቀረ !

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Sep 07, 2017 4:30 pm

ኳስሜዳ
ስለሚዛናዊ ዘገባህ ተባረክ፡፡የሊቢያው ተወካይ ሃገራችንን በማዋረድ ላቀረበው የተዘጋጀ ስድብና ክስ ዶ/ር ምናሴ ያለምንም ዝግጅት ወዲያውኑ የሰጡት ድንቅ መልስ አለ፡፡ ዶክተር ጎሹ ኢትዮጲያን በወያኔ ለማፍረስ ለተደረገ የምእራባያን ሴራ የሰጡት መልስም ይገኛል፡፡እነዚህ ድንቅ ዲፕሎማቶች የነበሩበትን ወንበር የደደቢቱ ---- ወርቅነህ ሲያገማ ያስዝናል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=jMvNsSGHOe0
https://www.youtube.com/watch?v=orod3OU3jfM
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1518
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron