ድሬደዋ ተወጥራለች!!! እስካሁን 7 የከተማዋ ነዋሪዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ተባለ!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ድሬደዋ ተወጥራለች!!! እስካሁን 7 የከተማዋ ነዋሪዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ተባለ!!!

Postby ኳስሜዳ » Thu Sep 07, 2017 10:39 am

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
በድሬድዋ ከተማ የኮንትሮባንድ እቃ የጫነ መኪና ነው በሚል ለመያዝ በሚያሳድዱ የፌደራል ፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት አንዲት ሴት መገደሏን ተከትሎ በተቀሰቀ ግጭት እስካሁን ክ7 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች መገደላቸውና ብዙዎች መቁሰላቸው ተሰማ፡፡

ባለፈው አርብ ከፌደራል ፖሊስ በተተኮሰ ጥይት በተገደለችው ሴት ምክንያት በከተማዋ ነዋሪዎችና በፌደራል ፖሊስ መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ከስፍራው የደረሰው የመከላከያ ሰራዊት በህዝብ ላይ በከፈተው የተኩስ እሩመታ ከ7 ሰዎች በላይ ሲገደሉ በረካቶች ቆስለው በድሬደዋ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ እንደሚገኙና ሁለት ፖሊሶች ላይ የመፈንከት አደጋ መድረሱን በአካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚሁ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካታ ወጣቶች እየተያዙ ሲሆን በተለይ የእጅ ስልክ የያዙ ወጣቶች መልእክት እየተላላካችሁ እየተባሉ ለእስር መዳረጋቸውን ጨምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ድሬደዋ ከተማ በውጥረት ላይ እንደምትገኝ ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል፡፡

ካገኘናቸው የአይን እማኞች እንደተረዳነው በድሬደዋ ከተማ በኮንትሮባንድ ሰም ሰዎች ሲገደሉ አዲስ ነገር ባይሆንም የአሁኑ የሚለየው ነዋሪው ተቆጠቶ ከፌደራል ፖሊስ ጋር መጋጨቱ ሲሆን የኮንትሮባንዱም ሰራ ቢሆን በመከላከያ ሰራተኞችና ከፍተኛ መኮንኖች የሚሰራና በይፋም የሚታወቅ መሆኑ ሲሆን በሌላ በኩል አርብ እለት ተቀስቅሶ የሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭትን ተከትሎ ዛሬም ውጥረቱና እስሩ እንደቀጠል መሆኑ ተሰምቷል..
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Steeler [Crawler] and 2 guests